TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.6K photos
1.48K videos
5 files
3.4K links
加入频道
#AddisAbabaCityCup

15ኛው የ አዲስ አበባ ሲቲ ካፕ በ መክፈቻ ዝግጅት ታጅቦ ሊጀመር ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ቀርተውታል ።

ጨዋታው የሚደረግበት የ አበበ ቢቂላ ስታዲየም አሁናዊ ገፅታ በ ምስሉ ላይ አጋርተንዎታል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#AddisAbabaCityCup

15ኛው የ አዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ በ ደማቅ የ መክፈቻ ስነ - ስርዓት በመካሄድ ላይ ይገኛል ።

የ መክፈቻ ጨዋታቸውን የሚያካሂዱት አዲስ አበባ ከተማ እና መከላከያ ወደ ሜዳ በመግባት እየሟሟቁ ይገኛሉ ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#AddisAbabaCityCup

15ኛው የ አዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ጨዋታዎች ዛሬም መካሄዳቸውን ሲቀጥሉ የ ምድብ ሁለት ጨዋታዎች ይጠበቃሉ ።

በዚህም መሰረት :-

8:00 ባህር ዳር ከተማ ከ አዳማ ከተማ

10:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ፋሲል ከነማ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#AddisAbabaCityCup

የ አዲስ እበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከ ዳሽን ባንክ ጋር በመተባበር የ15ኛው የ አዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ውድድር የ መግቢያ ትኬት በ ዳሽን አሞሌ አማካኝነት እየተሸጠ ይገኛል::

ሆኖም ትናንትና እና ዛሬ የ ባንክ አገልግሎት ባለ መኖሩ እና ከፍተኛ የ ኔትዎር መጨናነቅ በመፈጠሩ የ ስፖርት ቤተሰቡ የ ስታዲየም የ መግቢያ ትኬት ለ ማግኘት ተቸግረዋል::

የ በዓላት መደራረብም በመኖሩ ዛሬ የሚደረጉ ጨዋታዎች #ብቻ የ መግቢያ ትኬት ሽያጭ በ አበበ ቢቂላ ስታድዬም የ መግቢያ በሮች ላይ ይከናወናል::

የ እጅ በ እጅ የ ትኬት ሽያጭ የምትፈልጉ #አስቀድማችሁ #በመገኘት እና አካላዊ ርቀታችሁን በ መጠበቅ ተጠባቂዎቹን መርሃ ግብሮች እንድትታደሙ እናሳስባለን ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#AddisAbabaCityCup

15ኛው የ አዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የ ምድብ አንድ ሁለተኛ ጨዋታዎች በ ዛሬው ዕለት መካሄዳቸውን ይቀጥላሉ ።

በመጀመሪያው የ ምድቡ ጨዋታ መከላከያ እና ጅማ አባ ጅፋር ሶስት ነጥቦችን ማግኘታቸው የሚታወስ ነው ።

ኢትዮጵያ ቡና ከ ምድቡ ለ ማለፍ የ ዛሬውን ጨዋታ #ግዴታ ማሸነፍ ይኖርበታል ።

* የ መግቢያ ትኬቶች በ ዳሽን ባንክ እንዲሁም በ ስታዲም እንደሚሸጥ ተገልጿል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#AddisAbabaCityCup

15ኛው የ አዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ዋንጫ የ ምድብ ሁለት ሁለተኛ ጨዋታዎች ዛሬ ቀጥለው የሚካሄዱ ይሆናል ።

ባህር ዳር ከተማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል የሚቀናቸው ከሆነ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን ያረጋግጣሉ ።

8:00 ባህር ዳር ከተማ ከ ፋሲል ከነማ

10:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ አዳማ ከተማ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#AddisAbabaCityCup

በ ትላንትናው ዕለት ከተካሄዱ የ አዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ጨዋታዎች የተወሰዱ ምስሎችን ይመልከቱ ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#AddisAbabaCityCup

15ኛው የ አዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የ ምድቡ ሁለት የ መጨረሻ ጨዋታዎች በ ዛሬው ዕለት መካሄዳቸውን ይቀጥላሉ ።

አስቀድሞ ማለፋቸውን ያረጋገጡት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ከ ባህርዳር ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ #ተጠባቂ ነው ።

ወደ ቀጣዪ ዙር #አለማለፋቸውን ያረጋገጡት አዳማ ከተማዎች ለ ማለፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ከሚያስፈልጋቸው ፋሲል ከነማ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ ።

የ ጣና ሞገዶቹ ወደ ቀጣዩ ዙር ለ ማለፍ #አንድ ነጥብ ብቻ በቂያቸው ነው ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#AddisAbabaCityCup

በነገው ዕለት የሚደረገው የ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ላይ የሰዓት ማሻሻያ መደረጉን አዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሳውቋል ።

የ አበበ ቢቂላ ስታዲየም በ ምሽት ጨዋታዎችን ማስተናገድ የማይችል በ መሆኑ እና የ ጥሎ ማለፉ ጨዋታዎች በ አቻ ውጤት የሚጠናቀቁ ከሆነ ተጨማሪ ደቂቃዎችን ስለሚወስዱ ጨዋታዎቹ ቀደም ብለው እንዲጀመሩ ተውስኗል ።

በዚህም መሰረት :-

7:00 ጅማ አባጅፋር ከ ባህርዳር

9:00 ቅዱስ ጊዬርጊስ ከ መከላከያ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#AddisAbabaCityCup

ከ ነገ ጀምሮ የ ግማሽ ፍፃሜ ውድድሮች መካሄዳቸውን ሲጀምሩ የ ስታዲየም መግቢያ ዋጋ ማሻሽያ መደረጉን ለ ማወቅ ተችሏል ።

በዚህም መሰረት :-

ክብር ትሪቡን - 300 ብር

ጥላ ፎቅ :- 200 ብር

የተቀሩት የ መግቢያ በሮች ሁሉም 100 ብር መሆናቸው ታውቋል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#AddisAbabaCityCup

የ መጨረሻ ተፋላሚዎቹን ለመለየት ከ ጫፍ የደረሰው የ ዘንድሮው የ ሲቲ ካፕ ውድድር ለ አሸናፊው የሚሰጠው ልዩ ዋንጫ ይፋ ሆኗል ።

አንድ ሜትር ከ አስር ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው ይህ ዋንጫ ዛሬ ከ ጀርመን ሀገር የ ውድድሩ አዘጋጅ በሆነው ሲሳይ አድርሴ ፕሮሞሽን ጋር ድርሷል ።

የ 15ኛው የ አዲስ አበባ ከተማ የ ዋንጫ ባለቤት ከሚሆነው በተጨማሪም ለ #ደረጃ ተፋላሚ እና ለ ፀባይ ዋንጫ አሸናፊ ተጨማሪ ሽልማት ይኖራል ።

የ ወርቅ ፣ብር እና ነሀስ ሜዳሊያዎችም ዛሬ ከ ጀርመን ሀገር ሲገባ ተሳታፊ ቡድኖች እንደ ደረጃቸው የ ገንዘብ ሽልማታቸውም እንደተጠበቀ ነው ።

የዚህ ልዩ ዋንጫ ባለቤት ማን ይሆናል ?

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#AddisAbabaCityCup

የ አዲስ አበባ ሲቲ ካፕ በ ዛሬው ዕለት የሚካሄዱ የ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች በ ጉጉት ይጠበቃሉ ።

7:00 ባህር ዳር ከተማ ከ ጅማ አባ ጅፋር

9:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መከላከያ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#AddisAbabaCityCup

15ኛው የ አዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ፍፃሜውን በ ባህር ዳር ላይ በዛሬው ዕለት ያደርጋል ።

በዚህም መሰረት :-

8:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ጅማ አባ ጅፋር ( ለ ሶስተኛ ደረጃ )

10:00 ባህር ዳር ከተማ ከ መከላከያ ( ለ ዋንጫ )

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#AddisAbabaCityCup

ሻምፒዮኖቹ የ ጣና ሞገደኞቹ የ አዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ አሸናፊ መሆናቸውን ተከትሎ ከ መርሐ ግብር የተወሰዱ ምስሎችን ይመልከቱ ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#AddisAbabaCityCup

የ 15ኛው አዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የ ፀባይ አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ሆኗል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#AddisAbabaCitycup

አስራ ስድስተኛ የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ከመጪው መስከረም 7/2015 ዓ.ም ጀምሮ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እንደሚደረግ ተገልጿል።

የአስራ ስድስተኛው አዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ውድድር ሁሉም ጨዋታዎች በአዲስ ቴሌቪዥን የቀጥታ ሽፋን #የሚያገኝ ይሆናል።

ውድድሩ በስድሰት ክለቦች መካከል ሲካሄድ ኢትዮጵያ ቡና ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ መቻል ፣ ኢትዮጵያ መድህን ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና በተጋባዥነት ለገጣፎ ለገዳዲ ተሳታፊ መሆናቸው ተነግሯል።

የምድብ ድልድሉ ምን ይመስላል?

ምድብ አንድ :- ኢትዮጵያ ቡና ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ለገጣፎ ለገዳዲ

ምድብ ሁለት :- ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ መቻል ፣ ኢትዮጵያ መድህን

የስታዲየም መግቢያ ዋጋ ምን ያህል ነው ?

√ ሚስማር ተራ እና ዳፍትራክ :- 20 ብር

√ ካታንጋ :- 30 ብር

√ ከማን አንሼ :- 50 ብር

√ ጥላ ፎቅ :- 100 ብር

√ ክቡር ትሪቡን :- 200 ብር መሆናቸው በጋዜጣዊ መግለጫው ተነግሯል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#AddisAbabaCitycup

አስራ ስድስተኛ የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ከዛሬ ጀምሮ በአዲስ አበባ ቢቂላ ስታዲየም በስድስት ክለቦች መካከል መደረጉን ይጀምራል።

በዛሬው ዕለት ከቀኑ 8:00ሰዓት ኢትዮጵያ ቡና ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እንዲሁም 10:00ሰዓት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መቻል ጋር ጨዋታቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል።

ተመልካቾች ከቀኑ 6:00 ጀምሮ በስፍራው በመገኘት የስታዲየም መግቢያ ትኬቶችን መግዛት እንደሚችሉ ተገልጿል።

ውድድሩ በአዲስ ሚድያ ኔትዎርክ በማህበራዊ ገፆቹ ፣ በራዲዮ እና ቴሌቪዥን የቀጥታ ሽፋን የሚያገኝ ይሆናል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#AddisAbabaCitycup

አስራ ስድስተኛው የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች ከዛሬ ጀምሮ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም መካሄዳቸውን ይቀጥላሉ።

በዚህም መሰረት :-

8:00 መቻል ከ ኢትዮጵያ መድህን

10:00 ኢትዮጵያ ቡና ከ ለገጣፎ ለገዳዲ ጋር ጨዋታቸውን የሚያከናውኑ ይሆናል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#AddisAbabaCitycup

አስራ ስድስተኛው ሳምንት የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ የምድብ ጨዋታዎች ቀጥሎ ሲካሄዱ ለገጣፎ ለገዳዲ የምድብ አንድ የባለይ የሆነበትን ውጤት አስመዝግቧል።

√ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 3 ለ 1 ያሸነፉት ለገጣፎ ለገዳዲዎች በግብ ክፍያ የምድብ አንድ የበላይ መሆን ችለዋል።

√ ኪሩቤል ወንድሙ የለጋጣፎን ሁለት ግቦች ሲያስቆጥር ቀሪዋን አንድ ግብ ኦና አጎና ከመረብ አሳርፏል።

√ ፀጋ ደርቤ የኢትዮ ኤሌክትሪክን ብቸኛ ግብ ማስቆጠር ችሎ ነበር።

√ ለገጣፎ ለገዳዲ ለፍፃሜ ለማለፍ በሚደረገው መርሐ ግብር የምድብ ሁለት #ሁለተኛን የሚገጥሙ ይሆናል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#AddisAbabaCitycup

አስራ ስድስተኛው የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ውድድር በዛሬው ዕለት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በሚደረጉ መርሐ ግብሮች ፍፃሜውን የሚያገኝ ይሆናል።

በአሰልጣኝ ሳምሶን ሙሉጌታ እየተመሩ ወጣት ቡድኑን በውድድሩ ይዘው የቀረቡት #ፈረሰኞቹ ለዋንጫው ከ #መቻል ጋር ከቀኑ 10:00 ጀምሮ ይፋለማሉ።

ለሶስተኛ ደረጃ በሚደረግ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከ ለገጣፎ ለገዳዲ ጋር ከቀኑ 7:00 ላይ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe