TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.6K photos
1.48K videos
5 files
3.41K links
加入频道
ዛሬ የሚካሄዱ #ተጠባቂ የአውሮፓ ሊግ መርሐ ግብሮች :-

🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿
9:30 ሊድስ ዩናይትድ ከ ቼልሲ
5:00 ፉልሀም ከ ማንችስተር ሲቲ
🇪🇸
12:15 ሪያል ማድሪድ ከ ኤልቼ
5:00 ሄታፌ ከ አትሌቲኮ ማድሪድ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#AddisAbabaCityCup

15ኛው የ አዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የ ምድቡ ሁለት የ መጨረሻ ጨዋታዎች በ ዛሬው ዕለት መካሄዳቸውን ይቀጥላሉ ።

አስቀድሞ ማለፋቸውን ያረጋገጡት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ከ ባህርዳር ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ #ተጠባቂ ነው ።

ወደ ቀጣዪ ዙር #አለማለፋቸውን ያረጋገጡት አዳማ ከተማዎች ለ ማለፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ከሚያስፈልጋቸው ፋሲል ከነማ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ ።

የ ጣና ሞገዶቹ ወደ ቀጣዩ ዙር ለ ማለፍ #አንድ ነጥብ ብቻ በቂያቸው ነው ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ባርሴሎና ነጥብ ጥሏል !

የላሊጋው መሪ ባርሴሎና በካታላን ደርቢ እስፓኞልን ገጥመው አንድ አቻ በሆነ ውጤት መርሐ ግብራቸውን አጠናቀዋል።

- ማርኮስ አሎንሶ ለባርሴሎና እንዲሁም ጆሴሉ ለእስፓኞል ጎሎቹን ማስቆጠር ችለዋል።

- ባርሴሎና በውድድር ዓመቱ በላሊጋው ነጥብ ሲጥሉ ለሶስተኛ ጊዜ ሆኗል።

- ባርሴሎና በላሊጋው ከሪያል ማድሪድ ጋር #እኩል ሰላሳ ስምንት ነጥቦችን ሰብስበው በግብ ክፍያ ላሊጋውን በመምራት ላይ ይገኛሉ።

- በቀጣይ የላሊጋው #ተጠባቂ መርሐ ግብር ባርሴሎና ከ #አትሌቲኮ_ማድሪድ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ቼልሲ ነጥብ ጥሏል !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ከኖቲንግሃም ፎርስት ያደረገውን የሊግ ጨዋታ አንድ ለ አንድ በሆነ አቻ ውጤት በማጠናቀቅ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል።

- የቼልሲን ግብ ራሂም ስተርሊንግ ሲያስቆጥር የኖቲንግሀም ፎረስትን የአቻነት ግብ ሰርጅ ኦሪየር ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

- ራሂም ስተርሊንግ ከሜዳ ውጭ ያስቆጠራቸውን ግቦች ወደ ሀምሳ ከፍ ማድረግ ችሏል።

- ቼልሲዎች #ከሜዳቸው_ውጪ ባለፉት አራት ጨዋታዎች ማግኘት ከሚገባቸው አስራ ሁለት ነጥብ ያሳኩት #ሁለቱን ብቻ ነው።

- በግርሀም ፖተር የሚሩት ቼልሲዎቹ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ከሊጉ መሪ አርሰናል በአስራ ስምንት ነጥብ ርቀው በሀያ አምስት ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዘዋል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሀ ግብር ቼልሲ ከ ማንችስተር ሲቲ ከባድ ግጥሚያ የሚጠብቃቸው ሲሆን ኖቲንግሃም ፎረስት በበኩላቸው ከ ሳውዛምፕተን የሚገናኙ ይሆናል ።

- በቀጣይ የሊጉ #ተጠባቂ መርሐ ግብር ቼልሲ ከ ማንችስተር ሲቲ እንዲሁም ኖቲንግሀም ፎረስት ከ ሳውዝሀምፕተን የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe