TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.6K photos
1.48K videos
5 files
3.41K links
加入频道
#AddisAbabaCityCup

15ኛው የ አዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የ ምድቡ ሁለት የ መጨረሻ ጨዋታዎች በ ዛሬው ዕለት መካሄዳቸውን ይቀጥላሉ ።

አስቀድሞ ማለፋቸውን ያረጋገጡት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ከ ባህርዳር ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ #ተጠባቂ ነው ።

ወደ ቀጣዪ ዙር #አለማለፋቸውን ያረጋገጡት አዳማ ከተማዎች ለ ማለፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ከሚያስፈልጋቸው ፋሲል ከነማ ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ ።

የ ጣና ሞገዶቹ ወደ ቀጣዩ ዙር ለ ማለፍ #አንድ ነጥብ ብቻ በቂያቸው ነው ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ !

የ አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የምድብ ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ሲካሄድ ክለቦች ወደ አስራ ስድስት ውስጥ ለመግባት ትልቅ ፉክክር ይጠብቃቸዋል ።

ክለቦች ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ ምን ይጠበቅባቸዋል ?

• ሪያል ማድሪድ :- ዛሬ ሼሪፍ ክለብን ማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ሲያሳልፋቸው በቀጣይ ቀሪ ጨዋታቸውን አቻ መውጣት ሌላኛ የማለፍ አማራጫቸው ነው ።

• ኢንተር ሚላን :- የ ጣሊያኑ ክለብ ዛሬ ሻካታርን አሸንፎ ሼሪፍ ሽንፈትን ካስተናገደ ወይም ከ ቀጣዮቹ ሁለት ጨዋታዎች አራት ነጥብ ማግኘት ወደ ቀጣዩ ዙር ያሸጋግረዋል ።

• ሼሪፍ :- ከ ሪያል ማድሪድ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ላይ ሽንፈትን አስተናግዶ ኢንተር ሚላን ሻካታርን ካሸነፈ ወደ ቀጣዩ ዙር #አለማለፋቸውን ያረጋግጣሉ።

• ሻካታር :- ቀጣዩን ዙር ለመቀላቀል ወይም ወደ ዩሮፖ ሊግ ማጣሪያ ለማለፍ ሁለቱን ቀሪ ጨዋታዎች ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል።

• አያክስ :- አስቀድሞ ማለፋቸውን ያረጋገጡት አያክሶች ከቀሪዎቹ ሁለት ጨዋታዎች አንድ ነጥብ ካገኙ የምድባቸው የበላይ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ ።

• ቦርሲያ ዶርትሙንድ :- ከ ስፖርቲንግ ሊስበን ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ላይ ማሸነፍ ከቻሉ ቀጣዩን ዙር መቀላቀል ያስችላቸዋል ።

• ስፖርቲንግ ሊስበን :- ቦርሲያ ዶርትሙንድን ከ ሁለት በላይ የግብ ልዩነት ማሸነፍ ከቻሉ ወደ ቀጣዩ ማለፋቸውን ያረጋግጣሉ ።

• ቤሽኪታሽ :- ከ አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የምድብ ማጣሪያ የተሰናበተ ሲሆን ዩሮፖ ሊግን ለመቀላቀል #አያክስን ማሸነፍ ይጠበቅበታል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe