TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
18.9K photos
292 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
加入频道
#የዛሬ

- በኦሮሚያ እና ሶማሌ ክልሎች በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ከ377 በላይ ትምህርት ቤቶች ሙሉ ለሙሉ ተዘግተዋል።

- የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የትምህርት ስርዓቱን መልሶ የመገንባት ሥራ እየተከናወነ ነውየትምህርት ሚ/ር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አስታውቀዋል። በሚቀጥሉት 5 ዓመታት በትምህርት ጥራት ላይ እንደሚሰራም ነው የጠቀሱት።

- ዛሬ ሀሙስ በቤላሩስ በተካሄደው 2ኛ ዙር ውይይት ሩስያ እና ዩክሬን በጊዜያዊ የተኩስ አቁም የሰብአዊነት ኮሪደሮችን በጋራ ማቋቋም ላይ መግባባት ላይ ደርሰዋል። እነዚህንም ኮሪደሮችን ለማደራጀት ሩሲያ እና ዩክሬን በቅርቡ የግንኙነት እና የትብብር መንገዶችን ይፈጥራሉ ነው የተባለው።

- በዓመት ከ 2,000 ኪ.ግ በላይ ወርቅ በማምረት ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ ያስገኛል የተባለው የአኮቦ ወርቅ ማምረቻ የዝግጅትና ፍለጋ ስራ አጠናቆ ወደ ተግባር መግባቱን የማዕድንና ነዳጅ ሚንስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገልጸዋል።

- የትራፊክ ደንብ ቅጣት ክፍያን በቴሌብር መክፈል የሚያስችል አሰራር ተግባራዊ ተደርጓል። ለዚህም በኢትዮ-ቴሎኮም በተዘጋጀው 6050 አጭር ቁጥር በመጠቀም ይችላሉ መክፈል ይችላሉ ተብሏል።

- የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ዩክሬን ውስጥ የተፈጠረውን ቀውስ በተመለከተ ዛሬ ባስተላለፉት መልዕክት በዩክሬን ቀውስ ውስጥ ሁሉም ወገኖች ግጭትን ከሚያባብሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ ጠይቀዋል።

- ካፍ በአፍሪካ ውስጥ የሚገኙ 23 ስታዲየሞችን ኢንተርናሽናል ጨዋታዎችን እንዳያስተናገዱ አግዷል። ከነዚህም መካከል #ኢትዮጵያ ስትገኝበት ባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም በቂ መስፈርቶችን ባለሟሟላቱ አለም አቀፍ ውድድሮችን ማካሄድ እንደማይችል ካፍ በድጋሚ አሳውቋል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ
የካቲት 24/2014

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
#የዛሬ (ግንቦት 16/2014)

👨‍⚕ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የዓለማችንን ትልቁን የጤና ተቋም የዓለም የጤና ድርጅትን ለሁለተኛ ዙር እንዲመሩ ዳግም ተመረጡ። የዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ብቸኛ ዕጩ ሆነው ዳግም መመረጣቸው የተረጋገጠው በጄኔቫ ላይ እየተካሄደ በሚገኘው 75ኛው የዓለም ጤና ድርጅት ጠቅላላ ጉብዔ ላይ ነው።

🧑‍⚖ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) አመራር የሆነት ኮነሌል ገመቹ አያና ከስር እንዲለቀቁ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 3ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት ወሰነ።

📝 በ2014 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ማጠቃለያ ላይ ተማሪዎች ማጠቃለያ ፈተናዎችን ለመውስድ እየተዘጋጁ ይገኛሉ። ነገር ግን ማህበራዊ ኃላፊነት በጎደላቸው አካላት ሆን ተብሎ ተማሪዎችን ለማዘናጋት በዘንድሮ ዓመት ከክፍል ወደ ክፍል መዘዋወር የለም ተብሎ በማህበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች የሚናፈሰው ወሬ ፍፁም ከእውነት የራቀ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

📣 "ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመኪና ስርቆት እየጨመረ በመምጣቱ ህብረተሰቡ አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዳይለየው " - የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት

🏆 የኳታሩ ዓለም ዋንጫ ሊጀምር የወራቶች እድሜ ብቻ ሲቀሩት የዓለም ዋንጫው በዛሬው ዕለት አስቀድሞ በተያዘለት ቀን #ኢትዮጵያ 🇪🇹 ደርሷል። የአለም ዋንጫው በሀገራችን የሁለት ቀናት ቆይታ ሲኖረው በነገው ዕለት ከ ረፋዱ 4:30 ጀምሮ በመስቀል አደባባይ በመገኘት የስፖርት አፍቃሪው አብሮ ፎቶ መንሳት እንደሚችል ተገልጿል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
#የዛሬ (ሰኔ 2/2014)

🇪🇹 በኮትዲቫር አዘጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በምድብ አራት ላይ በቢንጉ ብሄራዊ ስታዲየም በተካሄደ ጨዋታ #የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከ ግብፅ ጋር ያደረገውን ጨዋታ ከጨዋታ ብልጫ ጋር 2 - 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። የዋልያዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ዳዋ ሁቴሳ እና አምበሉ ሽመልስ በቀለ አስቆጥረዋል። ዋልያዎቹ ከ እ.ኤ.አ 1989 በኋላ በኋላ የግብፅ ብሄራዊ ቡድንን ማሸነፍ ችሏል።

1⃣ የዛሬው ውጤት ተከትሎ ሀገራችን 🇪🇹 በሶስት ነጥብ አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ሀገራችን #ኢትዮጵያ 🇪🇹 ከግብፅ ጋር ያደረገችውን ፍልሚያ በማሸነፏ፤ ማላዊ ደግሞ በጊኒ በመሸነፏ ምድቧን #በአንደኛነት መምራት ጀምራለች።

📖 በሀገራችን የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የቁርዓን እና የአዛን ውድድር የፊታችን እሁድ ይካሄዳል። ሰኔ 5/2014 በአዲስ አበባ ስቲዲዮም ለሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቁርዓን እና የአዛን ውድድርም በርካታ እንግዶች እየገቡ ይገኛሉ። ሀገራችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያስጠራው ይህ ውድድር ከ56 በላይ ሀገራት የሚወዳደሩበት ሲሆን ለውድድሩ ከፍተኛ ዝግጅት ሲካሄድ ቆይቷል ተብሏል።

🇸🇴🇪🇹 ዛሬ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከልዑካቸው ጋር ለአዲሱ የሶማሊያ ፕሬዜዳንት በዓለ ሲመት ለመታደም ሞቃዲሾ ተገኝተዋል። በበዓለ ሲመቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) #ኢትዮጵያ ለአዲሱ የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ያላትን ድጋፍ አረጋግጠዋል። በሶማሊያ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በማየታቸውም ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

🛂 የፓስፖርት አገልግሎት ክፍያዎችን በ " ቴሌ ብር " አማካኝነት መፈፀም እንዲቻል በኢትዮ ቴሌኮም እና በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መካከል ዛሬ ስምምነት ተፈፅሟል።

🌽 ድንበር የለሽ ዶክተሮች (MSF) በአፋር ክልል እየጨመረ የመጣው የምግብ እጥረት ቀውስ ስጋት እንዳጫረበት ገልጿል። ድርጅቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች መሠረታዊ የሚባሉ የጤና ማዕከላትን እንዲሁም ንጹህ የመጠጥ ውሃ በማያገኙበት ሁኔታ ነው የሚኖሩት ብሏል። በተጨማሪም በርካታ ሕፃናት በከፋ የምግብ እጥረት ሕይወታቸውን አጥተዋል ሲል አመልክቷል።

🎤 የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ ሰለሞን ሹምዬ እና መዓዛ መሐመድ በስር ፍርድ ቤት የተፈቀደላቸውን የ10 ሺህ ብር ዋስትና ሽሯል። ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን የሻረው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በዋስትና ትዕዛዙ ላይ ይግባኝ ካቀረበ በኋላ ነው። የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 2 ቀን 2014 ከሰዓት በጽህፈት ቤት በኩል በሰጠው ትዕዛዝ ለመርማሪ ፖሊስ የ8 ቀናት የምርመራ ጊዜን ፈቅዷል።

👮‍♂ የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ዛሬ ሰኔ 2 ቀን 2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት የብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞን ጉዳይ ተመልክቷል። በዚህም፥ የጊዜ ቀጠሮውን ጉዳይ መርማሪ ፖሊስ ምርመራየን ጨርሸ የምርመራ መዝገቡን ለዐቃቢ ህግ ለመላክ በዝግጅት ላይ ነኝ ያለ ሲሆን የክልል ዐቃቤ ህግ በችሎት ቀርቦ አዎ ምርመራው አልቋል የክስ መመስረቻ ጊዜ 15 ቀናት ይሰጠኝ ሲል ጠይቋል። የዋስትና ጥያቄውም ላይ ብይን ለመስጠት ለነገ ለሰኔ 3/2014 ዓ/ም ቀጠሮ ሰጥቷል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
እንኳን አደረሰን ፤ አደረሳችሁ !

ሀገራችን #ኢትዮጵያ በራሷ አቆጣጠር ዛሬ ያለፈውን 2014 ዓ/ም ሸኝታ አዲሱን 2015 ዓ/ም ተቀብላለች።

መላው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦቻችን እንኳን ይህችን ቀን ለማየት አበቃን ፤ እንኳን አደረሰን ፤ አደረሳችሁ !!

2014 ዓ/ም ሸኝተን 2015 ዓ/ምን ስንቀበል ደስታችን ሙሉ ሆኖ አይደለም፤ ልክ 2013 ዓ/ምን ሸኝተን 2014 ዓ/ምን እንደተቀበልነው ጊዜ ሁሉ ዛሬም ከጦርነት እና ከግጭት ቀጠና ያልወጡ ብዙ ወገኖቻችን አሉ።

በ2014 ዓ/ም ብዙ ወገኖቻችን በሀገራችን የተለያዩ ክፍሎች በነበሩ ግጭቶች እንዲሁም ጦርነት አጥተናል ፤ ብዙዎች ተጎድተውብናል፣ በርካታ ወገኖቻችን በደረሰባቸው ችግር ሰው ጠባቂ ሆነዋል። በተፈጥሮም አደጋ ያጣናቸው ወገኖቻችን ብዙ ናቸው።

በዓመቱ ችግር የደረሰባችሁ፣ የምትወዷቸውን ከአጠገባችሁ ያጣችሁ፣ ልጆቻችሁን የተነጠቃችሁ ወላጆች፣ ወላጆቻችሁን እና ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ ሁሉ ፈጣሪ መፅናናት እና ብርታትን ይሰጥልን ዘንድ እንማፀናለን። የተጎዱ ወገኖቻችንም ፈጥነው እንዲያገግሙ እንማፀናለን።

ዛሬ የተቀበልነው 2015 አዲስ ዓመት ከምንም ነገር በላይ ወገኖቻችንን ችግር የማንሰማበት ፣ የሰላም ፣ የደስታ ፣ መልካም መልካሙን ምንሰማበት ፣ ከችግሮቻችን ሁሉ ተቃላቀን ደስ የምንሰኝበት ይሆን ዘንድ እንመኛለን።

የአዲስ ዓመት በዓልን ስናከበር በችግር ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን በማሰብ፣ የታመሙትን በመጠየቅ፣ ፈጣሪ ለሀገራችን አስተማማኝ የሆነ ሰላምን እንዲሰጠን በመማፀን ይሆን ዘንድ አደራ እንላለን።

ፈጣሪ ሀገራችንን #ኢትዮጵያን ይጠብቅልን!
Tikvah Family ❤️

@tikvahethiopia
የቀጠለ......

#ኢትዮጵያ🇪🇹 ኡጋንዳን በጎረቤቶቿ ደቡብ ሱዳን እንዲሁም በኬንያ አማካኝነት ትዋሰናለች። በደቡብ ክልል፣ የደቡብ ኦሞ ዞን ጤና መምሪያ ለወረዳ ጤና ጽ/ቤቶች በጻፈው ደብዳቤ በዞኑ አጎራባች ወረዳዎች የሰዎች ዝውውር መኖሩን ጠቅሶ ስጋት መኖሩን አንስቷል።

"በዞናችን በሚገኙ አጎራባች የደቡብ ሱዳን እና ኬንያ ድንበር ላሉት የዳሰነች እና የኛንጋቶም ወረዳ በእነዚህ አካባቢ ከደቡብ ሱዳን እና ከኬኒያ ብዙ ሰው መግባት እና መውጣት ስላለ አሳሳቢነቱ ከፍተኛ ነው" ሲል ነው የገለጸው።

አክሎም በሁሉም መዋቅር የአሰሳና የቅኝት ሥራ እንዲሰራና የበሽታው ምልክት የሚያሳዩ ሰዎችንም ቶሎ መለየትና ለሚመለከተው አካል ሪፖርት እንዲደረግ አዛል።

በዳሰነች ወረዳ በቡአ እና በኛንጋቶም ወረዳ በካኩታ የልየታ ቦታም የተጠናከረ የልየታ ሥራን በመስራት ከሚመለከተው ግብረ ሃይል ጋር በጋራ በመሆን ሥራዎች በተጠነከረ መንገድ እንዲሰሩም አሳስቧል።

ምስል: የደቡብ ኦሞ ዞን ጤና መምሪያ

@tikvahethmagazine
#የዛሬ (መስከረም 23/2015)

📝 የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተናን አስመልክቶ መግለጫ ተሰጥቷል።

በዚህም፦

- ከ900,000 በላይ ተማሪዎች የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተናን የሚወስዱ ይሆናል።

- በሁለት ዙር በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በሚሰጠው በዚህ ፈተና የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ከመስከረም 26-28 ወደሚፈተኑባቸው ዩንቨርሲቲዎች የሚያቀኑ ሲሆን የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከጥቅምት 5 አስከ ጥቅምት 6 ወደ ዩንቨርሲቲዎች ይጓዛሉ።

- ተፈታኞች ተንቀሳቃሽ ስልኮችን እና ሌሎችም ስጋት ሊፈጥሩ የሚችሉ ቁሶችን መያዝ እንደማይችሉ ተጠቅሷል።

- በተጨማሪም ከሰላምና ፀጥታ ጋር ተያይዞ መፈተን የማይችሉና ከሀገር የወጡ የኮሚኒቲ ተማሪዎች በአጠቃላይ 56,000 ተማሪዎች ሲሆኑ በቀጣይ #ሁለተኛ ዙር ፈተና እንደሚዘጋጅላቸው ሚኒስቴሩ ጠቁሟል።

🇺🇸 አምባሳደር ማይክ ሐመር ከዛሬ ሰኞ ጀምሮ ወደ ኬንያ ፣ ደቡብ አፍሪካ እና #ኢትዮጵያ ጉዞ ያደርጋሉ።

- የአሜሪካ አፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር ከጥቅምት 3 እስከ ጥቅምት 18 ቀን 2022 ወደ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ኢትዮጵያ እንዘሚጓዙ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ዛሬ አሳውቋል።

- ሐመር ወደ ቀጠናው የሚመለሱት በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት በአፋጣኝ እንዲቆምና በአፍሪካ ህብረት የሚመራ የሰላም ድርድር እንዲጀመር ለመደገፍ ነው ተብሏል።

📱 ኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ኢንሹራንስ ሊጀምር ነው

- የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ እንደተናገሩት አገልግሎቱ ደንበኞች ከኩባንያው ጋር በሚገቡት ውል መሰረት የእጅ ስልካቸው በሚጠፋበት እና በሚበላሽበት ጊዜ የሚስተናገዱበት አሰራር ነው፡፡

- ኩባንያው ከዚህም በተጨማሪ ኢ-ሲም ፤ ቴሌ ድራይቭ ፤ ኮል ሲግኒቸር እና ሌሎች በርካታ ምርት እና አገልግሎቶችን ኩባንያው ለደንበኞቹ በበጀት አመቱ እንደሚያቀርብ አስረድተዋል፡፡

⚽️ ስፖርት

- የሴካፋ ከ 17ዓመት በታች ውድድር መካሄዱን ሲጀምር ዩጋንዳ በሰፊ የጎል ልዪነት ቡሩንዲን 4ለ0 በመርታት ከወዲሁ ምድቧን መምራት ጀምራለች። የኢትዮጵያ ከ 17ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከ ሶማሊያ አቻው ጋር ባደረገው ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

- የ2013ዓ.ም የሊጉ አሸናፊ ፋሲል ከነማ የውድድር ዘመኑን አዳማ ከተማን 2ለ1 በመርታት በድል ጀምረዋል። መቻልና ሀዲያ ሆሳዕና ያደረጉት ጨዋታ ደግሞ በመቻል 1 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine
#የዛሬ (መስከረም 25/2015)

🕊 የአፍሪካ ኅብረት #የሰላም_ንግግሩን የሚመሩ አካላትን፤ ቀንና ስፍራን አሳውቆ የሰላም ውይይቱ እንዲጀመር ኦፊሴላዊ ጥሪ አቅርቧል። ይህንን አስመልክቶ የፌዴራል መንግስት በደቡብ አፍሪካ ከጥቅምት 18 ጀምሮ የተጠራውን የሰላም ድርድር መቀበሉን በይፋ ሲያሳውቅ ህወሓትም በዚሁ ድርድር ላይ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑን ዛሬ ምሽት አሳውቋል። ህውሓት ተጨማሪ ተዋናዮች ዝርዝር፣ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሚና እንዲሁም የሎጅስቲክስ ፤ የጉዞ እና የደህንነት ዝግጅቶችን በተመለከተ ማብራሪያ እኝዲሰጠው ጠይቋል።

💬 "ወላጆች የልጆቻችሁን ጉዳይ በሚመለከት በቀጥታ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር፤ የምንነግራችሁ ቁጥሮች አሉ፣ የምንልካቸው የአካባቢው ትምህርት ተወካዮች አሉ በዛ በኩል መገናኘት ያስፈልጋል። አንድ ነገር ቢፈጠር #በእርግጠኝነት የምንነግራችሁ ፤ ከእኛ ውሸት አትጠብቁ የሆነውን ነገር ይሄ ነው የሆነው ብለን እንነግራችኃለን። ምንም የምንደብቅበት ምክንያት የለም።" ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ (የትምህርት ሚኒስትር) ለብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ከተናገሩት የተወሰደ

🇰🇪 የኬንያ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ የመጀመሪያ የአፍሪካ ሀገር ጉዟቸውን ወደ #ኢትዮጵያ ያደርጋሉ። ፕረዚደንቱ ነገ በአዲስ አበባ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የቴሌኮም አገልግሎት ማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ እንደሚታደሙ የተነገረ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ይመክራሉ ተብሏል።

💐 በአዲስ አበባ ትናንት ምሽት ከሌሊቱ 10:00 አካባቢ ባልታወቀ ምክንያት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ልዩ ቦታው ወንጌላዊት አካባቢ በተፈጠረ የመሬት መደርመስ በደረሰ የመሬት መደርመስ የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በሌሎች ሁለት ሰዎች ላይ መጠነኛ ጉዳት በመድረሱ በህክምና እየተረዱ ይገኛሉ ተብሏል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine
#ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ በተሰበሰበ መረጃ በሀገራችን ባለፈው ዓመት 1.5 ሚሊየን ዜጎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ ይህም ከታሰበው እና ከተገመተው በ 3 ዕጥፍ ከፍ ያለ ሲሆን፣ ባለፈው አመት የተገመተው ወደ 5 መቶ ሰው በቫይረሱ ሊያዝ እንደሚችል ቢሆንም ግን በ3 ዕጥፍ ጭማሪ ማሳየቱ ተገልጿል።

ከዚህ በፊት ከነበረው አሁን ላይ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር "በሚያሰጋ ደረጃ እየጨመረ ነው " የተባለ ሲሆን በተደረገ ጥናት ይፋ በሆነ መረጃ እድሜያቸው ከ15-29 ባሉ ሴቶች ቫይረሱ " አስደንጋጭ " በሆነ መልኩ እየተስፋፋ መሆኑን ገልጸዋል።

በየአመቱ እድሜያቸው ከ15-24 ባሉ የማህበረሰብ ክፍልም አዲስ በቫይረሱ ከሚያዙት መካከል ሴቶች 69 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ እንደሚወስዱ ተገልጿል፡፡

በሀገራችን በልጃገረድ እና ወጣት ሴቶች የኤችአይቪ ስርጭት መጠን 0.4 በመቶ እንደሆነ መረጃዎች ቢገልፁም በ2021 እድሜያቸው ከ15-29 ዓመት ያሉ ወጣት ሴቶች በአጠቃላይ አዲስ በቫይረሱ ከተያዙ መካከል 34 በመቶውን ይይዛሉ ነው የተባለው።

ዕድሜያቸው ከ15-24 ባሉ ወጣቶች በወንዶች 39 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ስለ ቫይረሱ መተላለፊያ እና መከላከያ መንገዶች የተሟላ እውቀት ሲኖራቸው በሴቶች ደግሞ 24 በመቶ ብቻ የሚሆኑት ስለ በሽታው ዕውቀት አላቸው።

ይህ ቁጥር ይፋ የሆነው የጤና ሚኒስቴር ከአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ እና  ከኤ.ኤች.ኤፍ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የአለም ኤድስ ቀን ፕሮግራም ላይ ነው።

መረጃው የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ነው

@tikvahethmagazine
#ኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ በ2014 ዓ.ም በመንገድ ትራፊክ አደጋ 3 ሺሕ 971 ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን 10 ሺሕ 325 ሰዎች ደግሞ ለከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መዳረጋቸውን የመንገድ ደህንነትና መድህን ፈንድ አገልግሎት አስታውቋል።

በተደረገ ጥናትም በ2014 ዓ.ም በትራፊክ አደጋ 13 ቢሊየን ብር የሚደርስ የንብረት ውድመት እንደደረሰ ተነግሯል። (ዋልታ)

@tikvahethmagazine
#ባለፈውሳምንት

- ታህሳስ 18 ቀን በሀረር ከተማ ራስ ሆቴል የትራፊክ መብራት አካባቢ በፊስታል ተጠቅልሎ ከመሬት ላይ ወድቆ የተገኘ 55 ሺ ብር ሁለት ሴት የትራፊክ ፖሊስ አባሎች ለፖሊስ አስረክበው ፖሊስም ባለፈው ሳምንት የገንዘቡ ባለቤት ነኝ ላሉ ግለሰብ አስረክቧል። ትራፊኮቹ ለመልካም ተግባራቸው የእውቅና ሰርተፊኬት የተበረከተ ሲሆን በቀጣይ ስራቸውን የሚመጥን ጥቅማጥቅም ይከበርላቸዋል ተብሏል።

- ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ  ቅርንጫፍ ፅ/ቤት  ከ 4 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ የምንዛሬ ተመን ያላቸው  የሰባት ሃገራት የተለያዩ ገንዘቦች በሻንጣ  እጄታ ብረት እና  ቦርድ ውስጥ ተደብቀው ሊወጡ ሲሉ  በቁጥጥር ስር ውለዋል። ህገ ወጥ ገንዘቦቹን ሲያዘዋውር የነበረ ተጠርጣሪንም መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታውቋል።

- ኢትዮጵያን ጨምሮ አፍሪካውያን በዱባይ የአገራቸውን መገበያያ ገንዘብ በመጠቀም የሕክምና አገልግሎት የሚያገኙበት ‘ሄልዝ ላየቭ’ የተሰኘ አማራጭ ይፋ ሆኗል። አማራጩ አፍሪካውያን ውጭ አገር ሄደው ለመታከም የሚያወጡትን የውጭ ምንዛሬ ለማስቀረት ወሳኝ ሚና እንዳለው ተገልጿል። አማራጩ ታካሚዎች በቋንቋቸው በመታገዝ  ሕክምናውን ማግኘት እንደሚችሉም ነው የተገለጸው።

- ኢትዮጵያ በዘንድሮው ዓመት የሀገር ውስጥ ፍጆታዋን ሸፍና 32 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ለውጭ ገበያ የማቅረብ አቅም እንዳላት ብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚና የኤክስፖርት ኮሚቴ ማረጋገጡ ተነግሯል። ሀገሪቱ ካለፈው ዓመት ጀምሮ ስንዴ ከውጭ ማስገባት ማቆሟን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪና የኤክስፖርት ኮሚቴው አስተባባሪ አምባሳደር ግርማ ብሩ አስታውሰዋል። ኢትዮጵያ ስንዴን ወደ ውጭ የመላክ ተግባርን በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን በይፋ አስጀምራለች።

ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይመልከቱ
https://yangx.top/tikvahethiopia

የፈተና እንዲሁም የዩኒቨርስቲ መረጃዎችን ከቲክቫህ ዩኒቨርስቲ ቻናላችን ይከታተሉ https://yangx.top/TikvahUniversity
አዋሽ ኢ-ስኩል ሲስተም
=========
ከጊዜው ጋር እየተሽቀዳደመ ከዘመኑ ጋር አብሮ እየዘመነ የመጣው አዋሽ ባንክ ት/ቤቶች ትውልድን ለመቅረፅ ያለባቸው ትልቅ ሃላፊነት በመረዳትና የትምህርት ጥራትን ለማሳካት በማሰብ የዲጂታል ትምህርት አስተዳደር ሥርዓት ወይም የኢ-ስኩል ሲስተም ቴክኖሎጂን አቀረበልዎ!
አዋሽ ኢ-ስኩል ሲስተም የግዜው ውድ ስጦታ!

Learn More- https://eschool.awashbank.com/
#AwashBank #Awash #ESchool #Management #System #Ethiopia #ኢትዮጵያ

ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👉 https://yangx.top/awash_bank_official
አዋሽ ኢ-ስኩል ሲስተም
=========
ከጊዜው ጋር እየተሽቀዳደመ ከዘመኑ ጋር አብሮ እየዘመነ የመጣው አዋሽ ባንክ ት/ቤቶች ትውልድን ለመቅረፅ ያለባቸው ትልቅ ሃላፊነት በመረዳትና የትምህርት ጥራትን ለማሳካት በማሰብ የዲጂታል ትምህርት አስተዳደር ሥርዓት ወይም የኢ-ስኩል ሲስተም ቴክኖሎጂን አቀረበልዎ!
አዋሽ ኢ-ስኩል ሲስተም የግዜው ውድ ስጦታ!

Learn More- https://eschool.awashbank.com/
#AwashBank #Awash #ESchool #Management #System #Ethiopia #ኢትዮጵያ

ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👉 https://yangx.top/awash_bank_official
አዋሽ ብር በሁሉም ቦታ
==========
በአዋሽ ብር ያለጥሬ ገንዘብ በመገበያየት ህይወትዎን ቀላል ያድርጉ!
#AwashBIRR #Banking #EveryWhere #Ethiopia #ኢትዮጵያ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አዋሽ ብር በሁሉም ቦታ!
==============
የአዋሽ ብር መተግበሪያን በመጠቀም ወይም ወኪሎች ጋር በመቅረብ የሂሣብ እንቅስቃሴን መከታተል፣ ገንዘብ ማስተላለፍ፣ ከወኪሎችና ኤቲኤሞች ገንዘብ ወጭ ማድረግ እንዲሁም ያለጥሬ ገንዘብ በመገበያየት ህይወትዎን ቀላል ያድርጉ!
#AwashBIRR #Banking #EveryWhere #Ethiopia #ኢትዮጵያ
Use our POS Terminals for your shopping in this weekend!
#AwashBank #POS #Saturday #Weekend #Ethiopian #ኢትዮጵያ
የክፍያ ደረሰኝዎን ከአዋሽ ብር መተግበሪያ ላይ ያግኙ!
========
የአዋሽ ብር መተግበሪያን በመጠቀም ያለጥሬ ገንዘብ ሲገበያዩም ሆነ ክፍያ ሲፈፅሙ  የክፋያ ማረጋገጫ ደረሰኝ እንደሚደርስዎ ስናበስሮዎት በታላቅ ደስታ ነው!

#AwashBIRR #Banking #EveryWhere #Ethiopia #ኢትዮጵያ
‘ታታሪዎቹ’/ ቀጠሌዋን በቅርብ ቀን
****************
‘ታታሪዎቹ’/ ቀጠሌዋን የሁለተኛ ዙር የአዋሽ ባንክ የስራ ፈጠራ ውድድር በቅርቡ የሚጀምር ሲሆን የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው የውድድሩ ተሳታፊዎች ከጥቅምት 12 እስከ ህዳር 13 ቀን 2016 ዓ.ም በባንኩ በይነ መረብ (ኦን ላይን) ወይንም በሁሉም አዋሽ ባንክ ቅርንጯፎች በአካል በመገኘት ማመልከት ይችላሉ፡፡
Dorgommiin kalaqa hojii marsaa 2ffaa Qaxaleewwan Baankii Awaash yeroo dhihootti kan eegalu yoo ta'u dorgomtoonni yaada kalaqaa qabdan Onkololeessa 12 bara 2016 haga Sadaasa 13 bara 2016 A.L.I tti Marsareetii Baankii Awaashiifi dameelee Baankii Awaash hundatti qaamaan argamuun galmaa'uu ni dandeessu.
https://tatariwochu.awashbank.com
#AwashBank #TATARIWOCHU #Qaxaleewwan #Empowering_The_Visionaries #Coming_Soon #Ethiopia #ኢትዮጵያ
በ2023 አምስት ምርጥ እንግሊዝኛ ተናጋሪ የአፍሪካ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?

"ኢዱኬሽን ፈርስት" የተባለ ዓለማቀፍ የትምህርት ተቋም እድሜአቸው ከ 18 - 20 የሆኑ 2.1 ሚሊዮን ወጣቶችን ከ113 ሀገራት የእንጊሊዘኛ ቋንቋ ችሎታቸውን በመገምገም የሀገራትን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪ ብቃት ደረጃ አውጥቷል።

ተቋሙ የቋንቋውን ተናጋሪዎች ብቃት በጣም የላቀ፣ ከፍተኛ፣ መካከለኛ፣ ዝቅተኛ እና በጣም ዝቅተኛ በሚሉ አምስት የብቃት ደረጃዎች በመክፈል ነው ሪፖርቱን ይፋ ያደረገው።

በሪፖርቱ መሰረትም ከ1ኛ እስከ 5ኛ የተቀመጡ የአፍሪካ ሀገራት በቅደም ተከተል፦

🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ
🇰🇪 ኬንያ
🇳🇬 ናይጄሪያ
🇬🇭 ጋና
🇺🇬 ኡዳንዳ መሆን ችለዋል።

ከአፍሪካ በቋንቋ ተናጋሪነት ብቃት የመጀመሪያ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ደቡብ አፍሪካ  "#በጣም_የላቀ" በተባለው ከፍተኛ የእንግሊዘኛ ብቃት ያላችው ሀገራት ምድብ ውስጥ ተካትታለች።

2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ኬንያ እንዲሁም 3ኛዋ ናይጄሪያ "#ከፍተኛ" በተባለው እንዲሁም  ዩጋንዳ እና ጋና "#መካከለኛ" በተባለው የቋንቋ ተናጋሪነት ምድብ ተመድበዋል።

ሀገራችን #ኢትዮጵያ🇪🇹 #ዝቅተኛ የእንጊሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪነት ምድብ ውስጥ ከታንዛኒያ፣ ሞሮኮ፣ አልጄሪያ፣ ማዳጋስካር፣ ማላዊ፣ ግብፅ ጋር መመደቧ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

ኔዘርላንድስ፣ ሲንጋፖር፣ ኦስትሪያ፣ ዴንማርክ እና ኖርዌይ ከአለም ከ1 እስከ 5 ያለውን የኢንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪነት ብቃት ደረጃ መያዝ ችለዋል።

@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የዘመን መለወጫ በዓላት በ #ኢትዮጵያ 🇪🇹

🎆 ጊፋታ (የዎላይታ ብሔር ዘመን መለወጫ)

🎆 ማሽቃሮ (የካፊቾ የዘመን መለወጫ በዓል)

🎆 ያሆዴ (የሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል)

🎆 መሳላ (የከምባታ ብሄር ዘመን መለወጫ በዓል)

🎆 የጎፋ ''ጋዜ'' ማስቃላ እና የኦይዳ ''#ዮኦ'' ማስቃላ በዓል

🎆 ሄቦ (የየም ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል)

🎆 ዮ__ማስቃላ (የጋሞ ብሔር ዘመን መለወጫ)

🎆 ጋሪ ዎሮ (በቦሮ-ሺናሻ ብሄረሰብ ዘመን መለወጫ በዓል)

እንኳን አደረሳችሁ!

#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#Cybersecurity

"በ2016 ዓ.ም 8 ሺሕ 854 የሳይበር ጥቃቶች ተሰንዝረዋል" - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር

ባሳለፍነው የ2016 ዓ.ም በተለያዩ የሀገሪቱ ተቋማት ላይ 8 ሺሕ 854 የሳይበር ጥቃቶች መሰንዘራቸውን የኢንሳ ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የሚደርሰው የሳይበር ጥቃት ከዓመት ዓመት እየጨመረ መምጣቱን ዋና ዳይሬክተሯ በ5ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የመክፈቻ ስነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር  አስታውቀዋል።

የፋይናስ ተቋማት፣ የመከላከያ፣ የጤናና የኢትዮ ቴሌኮምን ጨምሮ በርካታ የመሰረተ ልማት ተቋማት የጥቃቱ ኢላማ መሆናቸውን ነው የገለጹት።

በ2015 ዓ/ም በቀረበው ሪፖርት የተፈጸሙት የሳይበር ጥቃቶች 6,959 የነበሩ ሲሆን ዘንድሮ በ1,895 ጭማሪ አሳይቷል።

በቅርቡ በተደረገ ዳሰሳ ኢትዮጵያ ለሳይበር ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ የተጋለጠች አፍሪካዊት ሀገር መሆኗን መሆኗን ይገልጻል።

የአለም አቀፍ የሳይበር ደኅንነት መረጃ ጠቋሚ የ2024 ሪፖርት ሀገራት ለሳይበር ጥቃት ካላቸው ዝግጁነት አንጻር በተለያዩ ደረጃዎች ይቀመጣሉ።

በዚህም ሀገራት በአምስት እርምጃዎች ይገመገማሉ። እነሱም ህጋዊ እርምጃዎች፣ ቴክኒካል እርምጃዎች፣ ተቋማዊ እርምጃዎችና የአቅም ግንባታ እና ትብብር ሲሆኑ ባሳዩት አፈጻጸም በመሰረት 5 እርከን ተከፍለዋል።

የአፍሪካ ሀገራት በGCI ምድብ መሰረት ያላቸው ደረጃ፦

🟢ደረጃ 1/ (Tier 1) ፡ አርዐያ የሆኑ ተብለው የተመደቡ ሞሪሸስ፤ ታንዛኒያ፣ ጋና እና ኬንያ ይገኛሉ።

🟢ደረጃ 2/ (Tier 2) ፡ በጣም እየተሻሻሉ ያሉ (Advancing) የሚባሉት ሞሮኮ፣ ግብጽ፣ ደቡብ አፍሪካ ናቸው።

🟢ደረጃ 3/ (Tier 3) : መሰረታዊ የሳይበር ደህንነት ማዕቀፎችን እያቋቋሙ ያሉ ሀገራት ሥር ናይጄሪያ፣ ሩዋንዳ፣ ካሜሩን እና ሴኔጋል ይገኙበታል።

🟢ደረጃ 4 / (Tier 4) : ብዙ ክፍተቶችን ያሉባቸው ግን የመሰረተ ልማት ግንባታ የጀመሩ ሃገራት ውስጥ #ኢትዮጵያ፣ ኡጋንዳ፣ ዛምቢያ እና አንጎላ ይገኙበታል።

🟢ደረጃ 5 / (Tier 5 ): የሳይበር ደህንነት ማዕቀፎቻቸውን በማቋቋም ጅማሮ ላይ ያሉ ተብለው ከተጠቀሱት ውስጥ ደግሞ ሶማሊያ፣ ቻድ ይጠቀሳሉ።

በሚያስተናግዱት የጥቃት መጠን ሲታዩ ፦

ደቡብ አፍሪካ እና ናይጄሪያ እንዲሁ በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ሲሆኑ በቅደም ተከተል 59 ኛ እና 57 ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

በሰኔ ወር የወጣ ጥናት እንደሚያሳየው ኬንያ፣ናይጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት ካጋጠማቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል ሲሆኑ፣ ደቡብ አፍሪካ በየሳምንቱ በአማካይ 1450 ጥቃቶች እያስተናገደች መሆኗን ገልጿል።

በኬንያ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ላይ ያነጣጠረ የሳይበር ጥቃት በ16.5 በመቶ ከፍ ስለማለቱ ተነግሯል።

በምሥራቅ አፍሪካ የሚሰነዘረው ቁልፍ መሰረተ ልማቶችን መሰረት ያደረገ የሳይበር ጥቃት በ 115 በመቶ እንዳደገ መረጃዎች ያመላክታሉ።

@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM