#Cybersecurity
"በ2016 ዓ.ም 8 ሺሕ 854 የሳይበር ጥቃቶች ተሰንዝረዋል" - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር
ባሳለፍነው የ2016 ዓ.ም በተለያዩ የሀገሪቱ ተቋማት ላይ 8 ሺሕ 854 የሳይበር ጥቃቶች መሰንዘራቸውን የኢንሳ ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ የሚደርሰው የሳይበር ጥቃት ከዓመት ዓመት እየጨመረ መምጣቱን ዋና ዳይሬክተሯ በ5ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የመክፈቻ ስነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር አስታውቀዋል።
የፋይናስ ተቋማት፣ የመከላከያ፣ የጤናና የኢትዮ ቴሌኮምን ጨምሮ በርካታ የመሰረተ ልማት ተቋማት የጥቃቱ ኢላማ መሆናቸውን ነው የገለጹት።
በ2015 ዓ/ም በቀረበው ሪፖርት የተፈጸሙት የሳይበር ጥቃቶች 6,959 የነበሩ ሲሆን ዘንድሮ በ1,895 ጭማሪ አሳይቷል።
በቅርቡ በተደረገ ዳሰሳ ኢትዮጵያ ለሳይበር ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ የተጋለጠች አፍሪካዊት ሀገር መሆኗን መሆኗን ይገልጻል።
የአለም አቀፍ የሳይበር ደኅንነት መረጃ ጠቋሚ የ2024 ሪፖርት ሀገራት ለሳይበር ጥቃት ካላቸው ዝግጁነት አንጻር በተለያዩ ደረጃዎች ይቀመጣሉ።
በዚህም ሀገራት በአምስት እርምጃዎች ይገመገማሉ። እነሱም ህጋዊ እርምጃዎች፣ ቴክኒካል እርምጃዎች፣ ተቋማዊ እርምጃዎችና የአቅም ግንባታ እና ትብብር ሲሆኑ ባሳዩት አፈጻጸም በመሰረት 5 እርከን ተከፍለዋል።
የአፍሪካ ሀገራት በGCI ምድብ መሰረት ያላቸው ደረጃ፦
🟢 ደረጃ 1/ (Tier 1) ፡ አርዐያ የሆኑ ተብለው የተመደቡ ሞሪሸስ፤ ታንዛኒያ፣ ጋና እና ኬንያ ይገኛሉ።
🟢 ደረጃ 2/ (Tier 2) ፡ በጣም እየተሻሻሉ ያሉ (Advancing) የሚባሉት ሞሮኮ፣ ግብጽ፣ ደቡብ አፍሪካ ናቸው።
🟢 ደረጃ 3/ (Tier 3) : መሰረታዊ የሳይበር ደህንነት ማዕቀፎችን እያቋቋሙ ያሉ ሀገራት ሥር ናይጄሪያ፣ ሩዋንዳ፣ ካሜሩን እና ሴኔጋል ይገኙበታል።
🟢 ደረጃ 4 / (Tier 4) : ብዙ ክፍተቶችን ያሉባቸው ግን የመሰረተ ልማት ግንባታ የጀመሩ ሃገራት ውስጥ #ኢትዮጵያ፣ ኡጋንዳ፣ ዛምቢያ እና አንጎላ ይገኙበታል።
🟢 ደረጃ 5 / (Tier 5 ): የሳይበር ደህንነት ማዕቀፎቻቸውን በማቋቋም ጅማሮ ላይ ያሉ ተብለው ከተጠቀሱት ውስጥ ደግሞ ሶማሊያ፣ ቻድ ይጠቀሳሉ።
በሚያስተናግዱት የጥቃት መጠን ሲታዩ ፦
ደቡብ አፍሪካ እና ናይጄሪያ እንዲሁ በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ሲሆኑ በቅደም ተከተል 59 ኛ እና 57 ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
በሰኔ ወር የወጣ ጥናት እንደሚያሳየው ኬንያ፣ናይጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት ካጋጠማቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል ሲሆኑ፣ ደቡብ አፍሪካ በየሳምንቱ በአማካይ 1450 ጥቃቶች እያስተናገደች መሆኗን ገልጿል።
በኬንያ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ላይ ያነጣጠረ የሳይበር ጥቃት በ16.5 በመቶ ከፍ ስለማለቱ ተነግሯል።
በምሥራቅ አፍሪካ የሚሰነዘረው ቁልፍ መሰረተ ልማቶችን መሰረት ያደረገ የሳይበር ጥቃት በ 115 በመቶ እንዳደገ መረጃዎች ያመላክታሉ።
@tikvahethmagazine
"በ2016 ዓ.ም 8 ሺሕ 854 የሳይበር ጥቃቶች ተሰንዝረዋል" - የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር
ባሳለፍነው የ2016 ዓ.ም በተለያዩ የሀገሪቱ ተቋማት ላይ 8 ሺሕ 854 የሳይበር ጥቃቶች መሰንዘራቸውን የኢንሳ ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሀሚድ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ የሚደርሰው የሳይበር ጥቃት ከዓመት ዓመት እየጨመረ መምጣቱን ዋና ዳይሬክተሯ በ5ኛው ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የመክፈቻ ስነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር አስታውቀዋል።
የፋይናስ ተቋማት፣ የመከላከያ፣ የጤናና የኢትዮ ቴሌኮምን ጨምሮ በርካታ የመሰረተ ልማት ተቋማት የጥቃቱ ኢላማ መሆናቸውን ነው የገለጹት።
በ2015 ዓ/ም በቀረበው ሪፖርት የተፈጸሙት የሳይበር ጥቃቶች 6,959 የነበሩ ሲሆን ዘንድሮ በ1,895 ጭማሪ አሳይቷል።
በቅርቡ በተደረገ ዳሰሳ ኢትዮጵያ ለሳይበር ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ የተጋለጠች አፍሪካዊት ሀገር መሆኗን መሆኗን ይገልጻል።
የአለም አቀፍ የሳይበር ደኅንነት መረጃ ጠቋሚ የ2024 ሪፖርት ሀገራት ለሳይበር ጥቃት ካላቸው ዝግጁነት አንጻር በተለያዩ ደረጃዎች ይቀመጣሉ።
በዚህም ሀገራት በአምስት እርምጃዎች ይገመገማሉ። እነሱም ህጋዊ እርምጃዎች፣ ቴክኒካል እርምጃዎች፣ ተቋማዊ እርምጃዎችና የአቅም ግንባታ እና ትብብር ሲሆኑ ባሳዩት አፈጻጸም በመሰረት 5 እርከን ተከፍለዋል።
የአፍሪካ ሀገራት በGCI ምድብ መሰረት ያላቸው ደረጃ፦
በሚያስተናግዱት የጥቃት መጠን ሲታዩ ፦
ደቡብ አፍሪካ እና ናይጄሪያ እንዲሁ በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ሲሆኑ በቅደም ተከተል 59 ኛ እና 57 ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
በሰኔ ወር የወጣ ጥናት እንደሚያሳየው ኬንያ፣ናይጄሪያ እና ደቡብ አፍሪካ ከፍተኛ የሳይበር ጥቃት ካጋጠማቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል ሲሆኑ፣ ደቡብ አፍሪካ በየሳምንቱ በአማካይ 1450 ጥቃቶች እያስተናገደች መሆኗን ገልጿል።
በኬንያ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ላይ ያነጣጠረ የሳይበር ጥቃት በ16.5 በመቶ ከፍ ስለማለቱ ተነግሯል።
በምሥራቅ አፍሪካ የሚሰነዘረው ቁልፍ መሰረተ ልማቶችን መሰረት ያደረገ የሳይበር ጥቃት በ 115 በመቶ እንዳደገ መረጃዎች ያመላክታሉ።
@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM