TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
18.9K photos
292 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
加入频道
#ባለፈውሳምንት

- ታህሳስ 18 ቀን በሀረር ከተማ ራስ ሆቴል የትራፊክ መብራት አካባቢ በፊስታል ተጠቅልሎ ከመሬት ላይ ወድቆ የተገኘ 55 ሺ ብር ሁለት ሴት የትራፊክ ፖሊስ አባሎች ለፖሊስ አስረክበው ፖሊስም ባለፈው ሳምንት የገንዘቡ ባለቤት ነኝ ላሉ ግለሰብ አስረክቧል። ትራፊኮቹ ለመልካም ተግባራቸው የእውቅና ሰርተፊኬት የተበረከተ ሲሆን በቀጣይ ስራቸውን የሚመጥን ጥቅማጥቅም ይከበርላቸዋል ተብሏል።

- ባለፈው ሳምንት በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ  ቅርንጫፍ ፅ/ቤት  ከ 4 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ የምንዛሬ ተመን ያላቸው  የሰባት ሃገራት የተለያዩ ገንዘቦች በሻንጣ  እጄታ ብረት እና  ቦርድ ውስጥ ተደብቀው ሊወጡ ሲሉ  በቁጥጥር ስር ውለዋል። ህገ ወጥ ገንዘቦቹን ሲያዘዋውር የነበረ ተጠርጣሪንም መያዙን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታውቋል።

- ኢትዮጵያን ጨምሮ አፍሪካውያን በዱባይ የአገራቸውን መገበያያ ገንዘብ በመጠቀም የሕክምና አገልግሎት የሚያገኙበት ‘ሄልዝ ላየቭ’ የተሰኘ አማራጭ ይፋ ሆኗል። አማራጩ አፍሪካውያን ውጭ አገር ሄደው ለመታከም የሚያወጡትን የውጭ ምንዛሬ ለማስቀረት ወሳኝ ሚና እንዳለው ተገልጿል። አማራጩ ታካሚዎች በቋንቋቸው በመታገዝ  ሕክምናውን ማግኘት እንደሚችሉም ነው የተገለጸው።

- ኢትዮጵያ በዘንድሮው ዓመት የሀገር ውስጥ ፍጆታዋን ሸፍና 32 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ለውጭ ገበያ የማቅረብ አቅም እንዳላት ብሔራዊ የማክሮ ኢኮኖሚና የኤክስፖርት ኮሚቴ ማረጋገጡ ተነግሯል። ሀገሪቱ ካለፈው ዓመት ጀምሮ ስንዴ ከውጭ ማስገባት ማቆሟን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪና የኤክስፖርት ኮሚቴው አስተባባሪ አምባሳደር ግርማ ብሩ አስታውሰዋል። ኢትዮጵያ ስንዴን ወደ ውጭ የመላክ ተግባርን በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን በይፋ አስጀምራለች።

ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይመልከቱ
https://yangx.top/tikvahethiopia

የፈተና እንዲሁም የዩኒቨርስቲ መረጃዎችን ከቲክቫህ ዩኒቨርስቲ ቻናላችን ይከታተሉ https://yangx.top/TikvahUniversity