TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
18.9K photos
292 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
加入频道
አንድ ወር ያስቆጠረውና መጨረሻው ያለየለት የUSAID እግድ

የትራምፕ አስተዳደር ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ ካሳለፋቸው ውሳኔዎች መካከል የUSAID እንቅስቃሴ ላይ የ90 ቀን እቅድ መጣል ሲሆን ይህ እግድ ከተጣለ 35 ቀናት አልፈዋል።

ኢትዮጵያ ከአሜሪካ በUSAID በኩል የምታገኘው ድጋፍ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገሮች ውስጥ ትልቁ ነው። በድርቅና በርስ በርስ ግጭት ውጥ ላሉ ዜጎች የአሜሪካ መንግስት በ2023 1.77 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ አድርጓል።

USAID በኢትዮጵያ ከምግብ እርዳታ ቀጥሎ ሁለተኛው ትልቁ ቅድሚያ የሚሰጠው ዘርፍ ጤና ሲሆን በዓመት 200 ሚሊዮን ዶላር ፈሰስ ይደረግበታል።

USAID በዓመት 200 ሚሊዮን ዶላር ለጤናው ዘርፍ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኩል ፈሰስ ያያደርጋል። ጤና ሚኒስቴር ይህንን ለክልሎች የማከፋፈሉን ሥራ ይሰራል። በተጨማሪም ተላላፊ በሽታዎችና የተመጣጠነ ምግብ ላይ የሚሰሩ ፕሮጀክቶችንም ይደግፋል። ይህ አሁን ላይ ቆሟል።

በኢትዮጵያ በግጭት፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና የገንዘብ እጥረት ምክንያት የወባ ተጠቂዎች በ2019 ከነበረው 900 ሺ በ2024 ወደ 7.3 ሚሊዮን ተጠቂዎች ከፍ ብሏል። የኩፍኝ በሽታም ከ2021 ከ 1,941 ተጠቂዎች ወደ በ2024 ወደ 28,129 ከፍ ብሏል።

ሌላው ትልቁ ጉዳይ ደግሞ የኤችአይቪ ኤድስ የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራዎች ላይ ያለው ድርሻ ነው። ለዚህ ተግባር በ2023 ብቻ 3 ቢሊዮን ዶላር ከአሜሪካ መንግስት ፈሰስ ተደርጓል።

በተጨማሪም በUSAID የሚደገፉ ፕሮግራሞች ለኤች አይ ቪ፣ ለሳንባ ነቀርሳ እና ለወባ መድኃኒቶችን ወደ ገጠር ክሊኒኮች ማድረስም ቆመዋል።

የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር በአሜሪካ እርዳታ የተቀጠሩ ከ 5,000 በላይ ሰራተኞችን ለማባረር ሊገደድ እንደሚችልም መገለጹ ይታወሳል።

በሰብዓዊ እርዳታው በኩልም በተመሳሳይ አሁን ባለው ተጨባጭ ኹኔታ፣ የዓለም ምግብ ፕሮግራም የምግብ አቅርቦቶቹን ከጨረሰ፣ ተጨማሪ የዕርዳታ ምግብ መግዛት እንደማይችል ገልጿል።

ዘጋርዲያን ይዞት በወጣው ዘገባ ማሽላና የምግብ ዘይትን ጨምሮ 2 ነጥብ 1 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎችን ለአንድ ወር መመገብ የሚችል 34 ሺሕ 800 ሜትሪክ ቶን እህል፣ ወደ አገር ውስጥ ለሚያስገቡ አካላት የሚከፈል ገንዘብ ባለመኖሩ ጅቡቲ ወደብ ላይ መቆሙን ገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያ ከፍተኛውን የስደተኞች ቁጥር የምታስተናግድ ሀገር እንደመሆኗ ነገሮችን ከባድ ያደርጉታል።

USAID ለኢትዮጵያ በ2023 የ1.8 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ሲያደርግ በዚሁ ጊዜ ኢትዮጵያ 1.4 ቢሊዮን ዶላር የእዳ ክፍያ ፈጽማለች። የUSAID ድጋፍ መቆም ኢትዮጵያ በጀመረችሁ ኢኮኖሚክ ሪፎርም ላይ የሚኖረው ተጽዕኖም ቀላል አይደለም።

በኢትዮጵያ ከ5 ሺ በላይ የሲቪክ ማኅበራት በUSAID ድጋፍ የጀመሯቸው ፕሮጀክቶች ጭምር በመቆማቸው በእነዚህ ተቋማት እና በየፕሮጀክቱ የሚሰሩ ሰራተኞች ላይ ከፍተኛ ጫናም የፈጠረ ነው።

ሀገራት ለአሜሪካ ድንገተኛ ውሳኔ አማራጭ እቅዶችን መንደፍ ግድ ይላቸዋል። ኢትዮጵያም ከዲፕሎማሲያዊ እስከ ሀገር ውስጥ ገቢን እስከማሳደግ እንዲሁም ወጪ ቅነሳ እና የበጀት ዝውውር እቅዶችን እንደ አማራጭ ልትመለከት ትችላለች።

እውን ይህ ክስተት እንደ የዛምቢያው ፕሬዝዳንት ሃካይንዴ ሂቺሌማ አገላለጽ "የማንቂያ ደውል" ይሆን ?

የትራምፕ አስተዳደር የ90 ቀኑን እግድ ሲጠናቀቅ የመጨረሻ ውሳኔው ምን ይሆን ? የኢትዮጵያ መንግስትስ መፍትሔ?


@tikvahethmagazine
" ከፍተኛ የመድኃኒት፣ የሳሙና እና የተለያዩ ግብአቶች እጥረት ገጥሞኛል " ተስፋ አዲስ የካንሰር ህሙማን ህፃናት ማዕከል

ከተቋቋመ 11 ዓመታት ያለፉት ተስፋ አዲስ የካንሰር ህሙማን ህፃናት ማዕከል ሥራውን የጀመረው
በ2005 ዓ.ም ነበር።

ተቋሙ አሁን ላይ ከአዲስአበባ ውጭ በተለያዩ የክልል ከተሞች በጅማ፣ ጎንደር እና በትግራይ  እየተንቀሳቀሰ ይሰራል።

ዋና ዓላማውም አቅም የሌላቸው በካንሰር በሽታ የተያዙ ህፃናትን ሙሉ ወጫቸውን እስከ አስታማሚ ቤተሰቦቻቸው በመሸፈን ማገዝ ሲሆን ላለፉት ዓመታትም ለብዙ ህጻናት እንደደረሰ ይገልጻል።

አሁን ላይ ወደ ማዕከሉ የሚመጡ ህፃናት ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ከፍተኛ የሆነ የመድኃኒት እጥረት መከሰቱን የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሳራ ኢብራሂም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ድርጅቱ ከተመሠረተበት ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ሦስት ሺሕ ገደማ የሚሆኑ የካንሰር ታካሚ ሕፃናትን ታድጓል ሲሉ ዋና ሥራ አስኪያጇ ገልጸዋል።

አሁን ላይ ደግሞ ባሉት የአዲስ አበባ፤ የጅማ፤ ጎንደር እና መቐሌ ማዕከላት ለ260 ህፃናት እና ቤተሰቦች ሙሉ ወጫቸውን በመሸፈን አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

በተጨማሪም በተመላላሽ እና በቋሚ የህክምና አገልግሎት ደግሞ ከ1140 በላይ ለሚሆኑ ማዕከሉ እየሰጠ መሆኑን ሥራ አስኪያጇ ገልፀዋል።

አያይዘውም ህፃናት ሕክምናቸውን እንዳያቋርጡ  ከማደሪያ እስከ ምግብና መድኃኒት፣ የሥነ ልቦና ትምህርት እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጠን ነው ሲሉ ሥራ አስኪያጇ ተናግረዋል።

እስካሁን ለማዕከላቱ ድጋፍ የሚያደርጉ ድርጆቶች ድጋፋቸውን ባያቋርጡም ድጋፉ ግን በቂ ባለመሆኑ በማዕከሉ ከፍተኛ የሆነ የመድሀኒት እና የሳሙና እጥረት መከሰቱን ወ/ሮ ሳራ ጠቁመዋል።

የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ሳሙና፣ ዱቄት ወተት፣ ስኳር፣ ዘይት እና የመሳሰሉ ድጋፎችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን በመግለጽ አሁን ላይ ግን ድጋፉ መቀዛቀዙን አክለዋል።

የካንሰር በሽታ ረጅም ጊዜ የህክምና ክትትል ስለሚወስድ ማዕከሉ ለታካሚዎች እና ላስታማሚዎች ሲሰጥ የነበረውን አገልግሎት ለመቀጠል የግብአት አቅርቦት እጥረት በመከሰቱ ማኅበረሰቡ በአይነትም ሆነ በገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

ማዕከሉን ማግኘት እና ድጋፍ ማድረግ ለምትፈልጉ

📌አዲስአበባ :- ወ/ሮ ሳራ ኢብራሂም
ስልክ:- 0911725455
📌ጅማ :- ወ/ሮ ብርቱካን
ስልክ:- 0935071136
📌ጎንደር:- አቶ ወንድሙ
ስልክ:- 0928503970
📌መቀሌ:- ወ/ሮ ጺዮን
ስልክ:- 0904231532

እንዲሁም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ Tesfa Addis Parents Childhood Cancer Organization (TAPCCO) 1000036686492

#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በጂንካ ከተማ አንዲት እናት 4 ልጆችን በአንድ ጊዜ ተገላገለች።

° ''ልጆቹን እማሳድግበት የገቢ ምንጭ ባይኖረኝም ፤እግዚአብሔር ግን 4 ልጆች ስለሰጠኝ በጣም ደስተኛ ነኝ'' ወላጅ አባት


በጂንካ ከተማ  በትላንትናው ዕለት የካቲት 18 አንዲት እናት በአንድ ጊዜ አራት ልጆችን በሰላም መገላገሏን የጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል አስታውቆ ነበር።

እናት ሁለት ወንድና ሁለት ሴት ልጆችን በሆስፒታሉ መውለዷን የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ሚስጥሩ ሀምዴክ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።


ህጻናቱ አሁን በምን ጤንነት ላይ ይገኛሉ ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄም ከአራቱ አንዷ ጨቅላ ትንሽ ኪሎዋ አነስ ስላል በአይ.ሲ ክፍል ውስጥ ክትትል እየተደረገላት ከመሆኑ ወጭ ሌሎች ህፃናት በጥሩ ጤንነት ላይ ናቸው ሲሉ ነግረውናል።

ዶ/ር ሚሥጢሩ አክለውም፥ እናትም በጥሩ ጤንነት ላይ ናት እንደምትገኝ እና ልጆቿን በኦፕራሲዮን በመወልዷ በትንሹ እስከ 3 ቀን በሆስፒታሉ ክትትል እየተደረገላት እንደምትቆይ አስረድተዋል።

ሆስፒታሉ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ እንዲህ አይነት ነገር ሲያጋጥም የመጀመሪያ መሆኑንም የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

የልጆቹ ወላጅ አባት ምን አሉ?

የእነዚህ አራት ልጆች አባት አቶ አንጁሎ አዲስ ይባላል። ባለቤቱ 4 ልጆች ስለተገላገለችበት፤ እሱም የአራት ልጆች አባት ስለሆነበት አጋጣሚ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ባለቤቱ አራት ልጆች እንዳረገዘች እስክትወልድ ድረስ የሚያውቁት ነገር እንዳልነበረና አራት ልጅ መሆኑን ሆስፒታል ከደረሱ በኋላ መስማታቸውን ነው የነገረን። ይህንን ሲያቅም ደስታ እና ድንጋጤ የተቀላቀለበት ስሜት ተሰማኝ ብሏል።

ከጂንካ ራቅ ብሎ በሚገኝ በቦታ እንደሚኖሩ የገለጸው አቶ አንጁሎ፤
ወደ ጂንካ የመጡትም ለህክምና ክትትል እንደሆነ ነው የገለጸው።

በትዳራቸው እነዚህ አራት ልጆች የመጀመሪያ እንዳልዎኑ የሚናገረው አባት ከዚህ በፊት አንድ ልጅ መውለዳቸውንና እድሜውም አሁን ላይ የ4 ዓመት እንደሆነው ጠቅሷል።

"ልጆቹ ትንሽ ሰውነታቸው ቀጫጫ ከመሆኑ ውጭ ደህና ናቸው። እናታቸው ማርታ ታከለም ጡቷ ወተት እንደፈለገ አሁን ላይ አይወጣትም እንጂ እሷም ጥሩ ሁኔታ ላይ ትገኛለች" ሲል አሁን ስላሉበት ሁኔታ አስረድቶናል።

"እኔ አሁን ልጆቹን እማሳድግበት የገቢ ምንጭ ባይኖረኝም፤ እግዚአብሔር ግን 4 ልጆች ስለሰጠኝ በጣም ደስተኛ ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን" ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

በተፈጥሮ በአንድ ጊዜ አራት ህጻናትን መጸነስ የሚከሰተው ከ700ሺ እርግዝናዎች በአንዱ ላይ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine
በአዲስ አበባ አገልጋዮች ሞባይል ስልክ ይዘው ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ ተከለከሉ።

በኢኦተቤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አገልጋዮች በቅዳሴና ለሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎት ሰዓት ሞባይል ስልክ ይዘው ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ መከልከሉን አስታውቋል።

ሀገረ ስብከቱ ለሁሉም ገዳማትና አድባራት በላከው የመመሪያ ደብዳቤ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚከናወኑ  የጸሎተ ቅዳሴና ሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎቶች የእጅ ሞባይል ስልክ ይዞ መግባት በጥብቅ መከልከሉን ይገልጻል።

የገዳማትና አድባራት አስደዳሪዎችና ሰበካ ጉባኤያት ጥብቅ ክትትል በማድረግ መመሪያውን እንዲያስፈጽሙ ታዘዋል።

መረጃው ከሀገረ ስብከቱ ሚዲያ ክፍል የተገኘ ነው።

@tikvahethmagazine
ዛሬ የካቲት 19 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9:33 ሰዓት ላይ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 2 ካራ ቆሬ በተለምዶ ቢቂላ መናፈሻ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ ለፍራሽ መስሪያ የሚሆኑ ግብአቶች በተከማቹበት መጋዘን ላይ የእሳት አደጋ ተከስቷል።

የእሳት አደጋዉን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችና የጸጥታ አካላት እንዲሁም የአካባቢዉ ህብረተሰብ በአደረጉት ርብርብ እሳቱ በአቅራቢያዉ ወዳለዉ መስጂድ እና ሌሎች መኖሪያና ንግድ ቤቶች እንዳይዛመት ማድረግ መቻሉን የእሳትና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አሳውቋል።

በእሳት አደጋዉ በሰዉ ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።

@tikvahethmagazine
አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል በተለያዩ ክፍት የስራ መደቦች የህክምና ባለሙያዎችን እና ስፔሻሊስቶችን አወዳድሮ ለመቀጠር ማስታወቂያ አውጥቶ ነበር።

ምዝገባ በተጀመረ 3 ቀናቶች ውስጥ 31 አመልካቾች በሁሉም የስራ መደቦች መመዝገባቸውን ለማወቅ ችለናል።

ሆስፒታሉ ካወጣቸው የሙያ አይነቶች ውስጥ የቆዳ ሐኪም ስፔሻሊስት ፣ ከአንገት በላይ ህክምና ስፔሻሊስት ፣ ራዲዬሎጅ ህክምና ስፔሻሊስት ፣የአጥንት ቀዶ ጥገና ህክምና ስፔሻሊስት ፣ አንስቴዣሎጂስት እና ክሊኒካል ፋርማሲ ስፔሻሊስት እነዲሁም ፋርማሲስት ይገኙበታል።

በማስታወቂያው ላይ

- ለአንድ የህክምና ስፔሻሊስት ወርሃዊ ደመወዙ 12,765 ብር  ፣

-
ለአንድ ክሊኒካል ፋርማሲ ስፔሻሊስት 10,600 ብር እና

- ለአንድ ፋርማሲስት ደግሞ 9047 ብር መሆኑን ተጠቅሷል።

የአይደሬ ሆስፒታል ያወጣው ክፍት የስራ ማስታወቂያ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethmagazine
ተሳፋሪዋ ረስተው የወረዱትን ከ82 ሺ በላይ ብር በታማኝነት የመለሰው ወጣት

በሰቆጣ ከተማ አንዲት ግለሰብ ከባጃጅ ላይ ረስተውት የሄዱትን 82ሺ 265 ብር የባጅጅ አሽከርካሪው በታማኝነት ለባለቤቱ መልሷል።

ገንዘብን የመለሰው  የባጅጅ  አሽከርካሪ ወጣት ሰለሞን ቢምረው ግለሰቧን አፈላልጎ በማግኘት በፖሊስ አማካኝነት ንብረቷን  በታማኝነት ማስረከቡን ገልጿል።

የገንዘቡ  ባለቤት የሆነችው ግለሰብ በሰጡት ቃል ገንዘቡን ጥለው መውረዳቸውን ካወቁ በኃላ በከፍተኛ ድንጋጤ ተውጠው ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ ማመልከታቸውን ገልጸዋል።

ከፖሊስ ጋር በመሆንም ባጃጁንም በማፈላለግ ላይ ሳሉ አሽከርካሪው አይቷቸው ወደ እነርሱ በመምጣት የጣሉትን የአደራ ብር እንዳስረከባቸው ተናግረዋል። በዚህም የተሰማቸው ደስታ ወደር እንደሌለው ነው የገለጹት።

ይህ ወጣት ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው ለሄዱ ለስልክ ባለቤቶች በታማኝነት ስልኩን ማስረከቡን ፖሊስ ተናግሯል።

መረጃው የሰቆጣ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ነው።

@tikvahethmagazine
በሀገር አቀፍ ደረጃ የዲጂታል የጤና ክፍያን ለመጀመር የሚያስችል ስምምነት ተደረገ።

የጤና አገልግሎት ክፍያዎችን ሙሉ በሙሉ ዲጂታል ለማድረግ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ጤና ሚኒስቴር ከፋይናንሺያል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር ተፈራርሟል።

ትግበራውም በአዲስ አበባ እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች በተመረጡ የጤና አገልግሎት ማዕከላት የሚጀመር እና ለጤና አገልግሎት ሰጪዎች እና ለተጠቃሚዎች የፋይናንሻል እውቀት ማሻሻያ ስልጠናንም የሚያካትት ነው ተብሏል። 

ይህ ትግበራም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ በገንዘብ ሚኒስቴር፣ በጤና መድኅን አገልግሎት እንዲሁም በዩኤንዲፒ ቤተር ካሽ አላያንስ በጋራ የሚደገፍ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahethmagazine
ዲጅታል የትራፊክ አደጋ መረጃ መሰብሰቢያ ሥርዓት ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑ ተገለፀ።

የመንገድ ደኅንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት ከፌድራል ፖሊስ ጋር ያለሙት ዲጅታል የመንገድ ትራፊክ አደጋ መረጃ መመዝገቢያ ስርዓት የሙከራ ትግበራ ተጠናቆ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሊተገበር መሆኑ ተገልጿል።

ይህንን አስመልክቶ የአገልግሎቱ የተቋም ሪፎርም ሥራ አስፈፃሚና የትራፊክ መቆጣጠር ማዕከል ኃላፊ አቶ ባዩ ሙሉጌታን ተጨማሪ ማብራሪያ ጠይቀናል።

እንደ ኃላፊው ገለጻ የመረጃ ሥርዓቱ ቀልጣፍ፣ ውጤታማ እና ታማኝነት ያለው የትራፊክ አደጋ መረጃ ለመሰብሰብ ታሳቢ በማድረግ የተጀመረ ነው።

ይኽም የዓለም ጤና ድርጅትን ጨምሮ በዓለም አቀፍ ተቋማት የትራፊክ አደጋ መረጃዎች ላይ ይነሱ የነበሩ ቅሬታዎችንም ይቀርፍል ብለዋል።

አቶ ባዩ አክለውም፥ ትራፊክ አደጋው የት ደረሰ፣ በምን ምክንያት፣ ማን አደረሰው፣ ምን ያህል ሰው ጉዳት ደረሰበትና ሌሎች መሰል የትራፊክ አደጋ መረጃዎችን በዲጂታል መልኩ ለመመዝገብ ያግዛል ብለዋል።

በዚህም ተጎጂ አካላት ከካሳ ክፍያ፣ ከህክምና ጋር በተያያዘ መረጃ ለማግኘት ያለውን  መጉላላት በመቅረፍ በቀላሉ እስከ ፍርድ ቤት ላሉ ጉዳዮች ጭምር ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል።

በተጨማሪም አደጋ በተደጋጋሚ እሚደርስባቸውን ቦታዎች በመለየት አደጋን ለመቀነስ፣ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ላይ ያሉ ጉድለቶችን በመለየት እርምጃ ለመውሰድ እንደሚጠቀምም ተናግረዋል።

አሁን ላይ የመረጃ ሥርዓቱ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ወደስራ እንድንገባ የሚያስችል እውቅና ማግኘቱን ገልጸው በሙከራ ትግበራውንም ተጠናቋል ብለዋል።

ኃላፊው የሙከራ ትግበራው በአዲስ አበባ ተደጋጋሚ የትራፊክ አደጋ በሚደርስባቸው 3 ክፍለ ከተሞች ቦሌ፣ አቃቂ ቃሊቲ እና የካ እንዲሁም በድሬዳዋ፤ ባህርዳር፤ ጅማን ጨምሮ በኦላይን እንዲሁም በኦፍላይን እንደሚሰራ መሞከሩን አስረድተዋል።

በሙከራ ትግበራውም ጥሩ ውጤት በመገኘቱ ሲስተሙን ወደ ሥራ ለማስገባት በአሁኑ ሰዓት ከታች ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና በየክልሉ እየሰጠን ነው ሲሉ አቶ ባዩ ሙሉጌታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ሲስተሙም ሙሉ በሙሉ ወደስራ ሲገባ በቅርቡ ለማህበረሰቡ የማሳወቅ ስራ እንደሚሰራም አክለዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine
ለጥያቄያችሁ ምላሽ

ስለ ፈይዳ የዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በተሰበሰቡ ጥያቄዎች ላይ የብሔራዊ መታወቂያ አገልግሎት የበላይ አመራሮች ምላሽ ሰጥተዋል።

#ክፍል_አንድ

🎞 የፋይዳ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮዳሄ አርአያሥላሴ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡትን ምላሾች ይመልከቱ https://youtu.be/b_X_LnM4cTA?feature=shared

#ክፍል_ሁለት

🎞 የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ምክትል አስተባባሪ ራሄል አብርሃም ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡትን ምላሾች ይመልከቱ https://youtu.be/7cYEVy3sDd8

@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🏫ከስቱድዮ እስከ ባለ 4 መኝታ ከተጨማሪ የሰራተኛ፣ ላውንደሪ ክፍል እና የዕቃ ክፍል ያካተቱ ቤቶች

💎 ባለ 1 መኝታ በ 215 ሺ ብር
💎ባለ 2 መኝታ በ 308 ሺ ብር
💎ባለ 3 መኝታ በ 368 ሺ ብር ቅድመ ክፍያ

🛍️🛒ሱቆች ከ 20 ካሬ ጀምሮ

🏦60% የባንክ ብድር የተመቻቸላቸው (እየኖሩበት ወይም አከራይተውት እስከ 20 አመት ቀስ ብለው የሚከፍሉት)

-በ 8% ቅድመ ክፍያ

- እስከ መጋቢት 6 ለሚመጡ ደንበኞች እስከ 30% በሚደርስ ቅናሽ ዋጋ (ለውስን ቤቶች) በመጠቀም
የዘመናዊ መንደራችን አካል ይሁኑ

📌ከዚህ በፊት በዲያስፖራ ቁጥር 1 የፈለጋችሁት ካሬ ወይንም ዝቅተኛ ፍሎር ፈልጋችሁ ላጣችሁ ደንበኞቻችን እነሆ ዲያስፖራ ብሎክ ቁጥር 2 ተለቀቀሎ

ለተጨማሪ መረጃ እንዲሁም ለጉብኝት

☎️ 09 00 02 50 97
@SamuelDMCRealtor (telegram) #WhatsApp
በህፃን ልጀ እገታ ወንጀል የተከሰሱ 2 ግለሰቦች በ21 ዓመት እና 19 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጡ።

በህፃን ልጅ አግተው ከወላጆቹ 7መቶ ሽህ ብር እሰከ 1ሚሊዮን ብር በመጠዬቅ ሲደራደሩ የነበሩ ወንጀለኞች በ21 ዓመት እና በ19 ዓመት ፁኑ እሰራት ተቀጥተዋል።

ሁለቱ ተከሳሾች ህጻኑን መስከረም 11 ከለሊቱ 7:00 ሰዓት ላይ ደሴ ከተማ ጢጣ አዲሱ ሰፈር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከተኛበት በመውሰድ ነው ከቤተሰቦቹ ጋር መደራደር የጀመሩት።

የህፃኑ ወላጇችም ተደናግጠው ወዲያውኑ  ለፖሊስ በማሳወቃቸው በተደረገ ክትትል ህጻኑን ሲያዘዋውሩ መስከረም 12 ቀን በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የክስ መዝገቡ ከደሴ ከተማ አስተዳደር ፖሊሰ መምሪያ የ4ኛ ዋና  ፖሊሰ ጣቢያ የደረሰው የደቡብ ወሎ ዞን ክፍተኛ ፍ/ቤት የካቲት 27/2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሁለቱ ተከሳሾች ላይ የቅጣት ውሳኔውን አስተላልፏል።

@tikvahethmagazine
#AskAAU

በሀገሪቱ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ 75ኛው የአልማዝ እዩቤልዩ በዓሉን ለማክበር ዝግጅት ላይ ይገኛል።

አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ራስ ገዝ መሆኑን ተከትሎ የተለያዩ ተቋማዊ ሪፎርሞችን በማካሄድ ላይ ነው።

ታዲያ ይህ ልምምድ በሀገራችን የመጀመሪያው ከመሆኑም አንጻር እንዲሁም ተቋማዊ የአሰራር ለውጥ በሚኖርበት ወቅት ብዙ ግልጽ መደረግ ያለባቸው ጉዳዮች መኖራቸው እሙን ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ከዚህ ቀደም ከቤተሰቦቹ ሲቀርቡ በነበሩ ጥያቄዎች መነሻ በማድረግ ዩኒቨርስቲው በእስካሁኑ የራስ ገዝነት ጉዞው ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ምላሽ ለመሰጠት ፈቃደኝነቱን ገልጾልናል።

በመሆኑም የዩኒቨርስቲው ማኅበረሰብ ሰራተኞች፣ መምህራንና ተማሪዎች እንዲሁም በዚህ ሂደት ላይ ጥያቄና ማብራሪያ የምትፈልጉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በሙሉ ጥያቄዎቻችሁን እንድታቀርቡ እንጠይቃለን።

ጥያቄዎቻችሁ ተሰብስበው ለዩኒቨርስቲው የበላይ አመራሮች የሚቀርቡና ምላሽ የሚሰጥባቸው ይሆናል።

ጥያቄዎችን ለማቅረብ @tikvahmagbot ይጠቀሙ።

#TikvahFamily🩵

@tikvahethmagazine