#Ethiopian_PremierLeague
የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የአዳማ ቆይታውን ሲያገባድድ ፈረሰኞቹ በውድድር ዓመቱ #ያለመሸነፍ ግስጋሴያቸውን አሰቀጥለዋል ።
√ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊጉን ከአምናው ሻምፒዮን ፋሲል ከነማ #በአስር ነጥቦች ርቀው እየመሩ ይገኛሉ ።
√ ሁለተኛ ደረጃን እና በ ካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ለመሳተፍ በሚደረገው ፉክክር ፋሲል ከነማ ፣ ሲዳማ ቡና ፣ ወላይታ ድቻ እና ሀዋሳ ከተማ ተፋጠው ይገኛሉ ።
√ ሲዳማ ቡና ፣ ወላይታ ድቻ እና ሀዋሳ ከተማ በሶስት ነጥብ ብቻ ከሁለተኛው ደረጃ ርቀው ይገኛሉ ።
√ ከስድስተኛ እስከ አስራ ሶስተኛ ደረጃ የሚገኙ ክለቦች #በአራት ነጥብ ብቻ ተራርቀው ይገኛሉ ።
√ ላለመውረድ በሚደረገው ትግል አዲስ አበባ ከተማ ፣ ጅማ አባ ጅፋር እና ሰበታ ከተማ በሊጉ ለመቆየት ከባድ ፉክክር ያደርጋሉ ።
√ ቀጣይ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ በ ባህር ዳር አለም አቀፍ ስታዲየም የሚካሄዱ ይሆናል ።
#Wanaw
#Betika
@tikvahethsport @kidusyoftahe

የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች እንዴት አለፉ ?
የአውሮፓ ታላላቅ ሊጎች ከሳምንቱ መጨረሻ ጀምሮ ሲካሄዱ አዳዲስ ክሰተቶችን እና ውጤቶች ተመዝግበዋል አልፈዋል።
1. ላሊጋ
√ ሪያል ማድሪድ መሪነታቸውን ሲያጠናክሩ በሊጉ ባደረጓቸው 5 ጨዋታዎች ሁሉንም ማሸነፍ ችለዋል።
√ ሮበርት ሊዋንዶውስኪ በ 6 ጎሎች የላሊጋውን ከፍተኛ ግብ አግቢነት እየመራ ይገኛል።
√ በመጪው ሳምንት አትሌቲኮ ማድሪድ ከ ሪያል ማድሪድ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
2. ቡንደስሊጋ
√ የጀርመን ቡንደስሊ በዚህ ሳምንት የተካሄዱ መርሐ ግብሮችን ተከትሎ አዲስ የሊጉ መሪ በታሪኩ አግኝቷል።
√ ዩኒየር በርሊን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ቡንደስሊጋውን መምራት ችለዋል።
√ ባየር ሌቨርኩሰን በወራጅ ቀጠናው ሲገኙ ይህም በሊጉ አግራሞትን ፈጥሯል።
√ ባየር ሙኒክ ( 3ኛ ) ቦርስያ ዶርትመንድ ( 5ኛ ) ከመሪው በ 2 ነጥብ አንሰው ይገኛሉ።
√ በቀጣይ የሪቨር ደርቢ ሻልክ ከ ቦርስያ ዶርትመንድ የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል።
3.ሴርያ
√ የጣልያን ሴርያ በአጓጊነቱ ሲቀጥል ከመሪው ናፖሊ እስከ ዘጠነኛ ላይ የሚገኘው ቶሪኖ #በአራት ነጥቦች ብቻ ተራርቀው ይገኛሉ።
√ ናፖሊ ፣ አታላንታ እና ኤሲ ሚላን በእኩል 14 ነጥቦች ከአንደኛ እሰከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።
√ በሳምንቱ መጨረሻ እሁድ መሪዎቹን ኤሲ ሚላን እና ናፖሊ እንዲሁም አታላንታ ከ ሮማ የሚያገናኙት መርሐ ግብሮች ይጠበቃሉ።
4. ፈረንሳይ ሊግ
√ ፒኤስጂ እና ማርሴይን እያፋጠጠ የሚገኘው የፈረንሳይ ሊግ በእኩል 19 ነጥቦች የደረጃው አናት ላይ አስቀምጧቸዋል።
√ ኔይማር በ 8 ጎሎች የሊጉ ከፍተኛ አግቢነትን ሲመራ ምባፔ በ 7 ጎሎች በ 2ኛነት ይከተለዋል።
√ በሳምንቱ መጨረሻ ፒኤስጂ ከ ሊዮን የሚያደርጉት መርሐ ግብር ተጠባቂው ነው።
@tikvahethsport

ሜሲ በዓለም ዋንጫው ምን ሪከርድ ይሰብራል ?
የሰባት ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊው ሊዮኔል ሜሲ በነገው ዕለት በሚጀምረው የኳታሩ የዓለም ዋንጫ የተለያዩ ሪከርዶችን የግሉ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
ከእነዚህም መካከል በዋነኝነት :-
√ በአስራ ዘጠኝ ጨዋታዎች በአለም ዋንጫው ሀገሩን የወከለው ሜሲ በርካታ ጨዋታዎችን #ለአርጀንቲና በውድድሩ ከተጫዋተው ዲያጎ ማራዶና #በሁለት ጨዋታዎች ብቻ #አንሶ ይገኛል።
√ ሊዮኔል ሜሲ በዓለም ዋንጫ ላይ ስድሰት ጎሎችን ሲያስቆጥር አስር ጎሎችን ካስቆጠረው ባቲስቱታ ይህን ክብር ለመጋራት #በአራት ጎሎች እርቆ ይገኛል።
1. ባቲስቱታ :- አስር ጎሎች
2. ስታቢሌ እና ማራዶና :- ስምንት ጎሎች
3. ሊዮኔል ሜሲ :- ስድስት ጎሎች
√ በአለም ዋንጫው አምስት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ያቀበለው ሊዮኔል ሜሲ ሪከርድን የግሉ ለማድረግ በውድድሩ በሶስት ጎሎች ላይ ተሳትፎን ማድረግ ይጠበቅበታል።

TIKVAH-SPORT
ሜሲ በዓለም ዋንጫው ምን ሪከርድ ይሰብራል ? የሰባት ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊው ሊዮኔል ሜሲ በነገው ዕለት በሚጀምረው የኳታሩ የዓለም ዋንጫ የተለያዩ ሪከርዶችን የግሉ እንደሚያደርግ ይጠበቃል። ከእነዚህም መካከል በዋነኝነት :- √ በአስራ ዘጠኝ ጨዋታዎች በአለም ዋንጫው ሀገሩን የወከለው ሜሲ በርካታ ጨዋታዎችን #ለአርጀንቲና በውድድሩ ከተጫዋተው ዲያጎ ማራዶና #በሁለት ጨዋታዎች ብቻ #አንሶ ይገኛል።…
ክርስቲያኖ ሮናልዶ በዓለም ዋንጫው ምን ሪከርድ ይሰብራል ?
ፖርቹጋላዊው የፊት መስመር ተጫዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በነገው ዕለት በሚጀምረው የኳታሩ የዓለም ዋንጫ የተለያዩ ሪከርዶችን የግሉ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
ከእነዚህም መካከል በዋነኝነት :-
√ 191 ጨዋታዎችን በአለም አቀፍ ደረጃ ያደረገው ሮናልዶ ሪከርዱን የግሉ ለማድረግ #አምስት ጨዋታዎች ብቻ ይቀሩታል።
1. አል ሙታዋ ( ኩዌት ) :- 196 ጨዋታዎች
2. ሶህ ቺን አን ( ማሌዢያ ) :- 195 ጨዋታዎች
3. ሮናልዶ ( ፖርቹጋል ) :- 191 ጨዋታዎች
√ የአምስት ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ግብ ካስቆጠረ በአምስት የተለያዩ ዓለም ዋንጫዎች ላይ ግብ ያስቆጠረ #የመጀመሪያው ተጫዋች ይሆናል።
√ ክርስቲያኖ ሮናልዶን ጨምሮ ፔሌ ፣ ሴለር እና ሚሮስላቭ ክሎዝ #በአራት የዓለም ዋንጫዎች ላይ ግብ ማስቆጠሩ የቻሉ ተጫዋቾች ናቸው።
√ ሰባት ጎሎችን በዓለም ዋንጫ ለሀገሩ ያስቆጠረው ክርስቲያኖ ሮናልዶ #ሁለት ጎሎችን የሚያስቆጥር ከሆነ የሀገሩን ልጅ ኢሴቢዮን በመብለጥ #በውድድሩ የፖርቹጋል ከፍተኛ አስቆጣሪ ይሆናል።

የሊቨርፑል የተከላካይ ክፍል ?
የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል በዘንድሮው የውድድር ዓመት ካደረጓቸው አስራ ሰባት ጨዋታዎች ምንም ግብ ሳይቆጠርባቸው መውጣት የቻሉት #በአራት ጨዋታዎች ብቻ ነው።
በዚህ ዓመት በሊጉ ደካማ እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኘው የየርገን ክሎፑ ሊቨርፑል ባለፈው ዓመት ሰላሳ ስምንት ጨዋታዎች አድርጎ ሀያ አንድ ጨዋታዎች ላይ ግብ ሳይቆጠርባቸው መውጣታቸው ይታወሳል ።
ሊቨርፑል በዘንድሮው የውድድር ዓመት በሊጉ ሀያ ሁለት ግቦች ተቆጥረውበት በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ በ ሀያ ስምንት ነጥብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ።

የኤሲ ሚላን ደካማ ጉዞ !
የጣልያን ሴሪያው ክለብ ኤስ ሚላን ከኳታሩ ዓለም ዋንጫ ውድድር መልስ በሊጉ ደካማ የሚባል ጊዜን በማሳለፍ ላይ ይገኛሉ።
ኤስ ሚላን ከዓለም ዋንጫ መልስ ካደረጓቸው ሰባት ጨዋታዎች ውስጥ ማሸነፍ የቻሉት #አንዱን ብቻ ሲሆን #በአራት ጨዋታዎች ተሸንፈው #በሁለቱ አቻ ተለያይተዋል።

ዋልያዎቹ ሽንፈት አስተናግደዋል !
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከግብፅ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።
የግብፅ ብሔራዊ ቡድንን የማሸነፊያ ግብ ሙስጣፋ ፋቲ ያስቆጠረ ሲሆን ፈርኦኖቹ ምድቡን በበላይነት ያጠናቀቁበትን ውጤትም ማስመዝገብ ችለዋል።
ዋልያዎቹ የማጣሪያ ውድድራቸውን በአራቱ #ተሸንፈው ፣ አንድ #አቻ ወጥተው እና አንድ #አሸንፈው #በአራት ነጥብ የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።