TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.7K photos
1.48K videos
5 files
3.41K links
加入频道
ሜሲ በዓለም ዋንጫው ምን ሪከርድ ይሰብራል ?

የሰባት ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊው ሊዮኔል ሜሲ በነገው ዕለት በሚጀምረው የኳታሩ የዓለም ዋንጫ የተለያዩ ሪከርዶችን የግሉ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

ከእነዚህም መካከል በዋነኝነት :-

√ በአስራ ዘጠኝ ጨዋታዎች በአለም ዋንጫው ሀገሩን የወከለው ሜሲ በርካታ ጨዋታዎችን #ለአርጀንቲና በውድድሩ ከተጫዋተው ዲያጎ ማራዶና #በሁለት ጨዋታዎች ብቻ #አንሶ ይገኛል።

√ ሊዮኔል ሜሲ በዓለም ዋንጫ ላይ ስድሰት ጎሎችን ሲያስቆጥር አስር ጎሎችን ካስቆጠረው ባቲስቱታ ይህን ክብር ለመጋራት #በአራት ጎሎች እርቆ ይገኛል።

1. ባቲስቱታ :- አስር ጎሎች
2. ስታቢሌ እና ማራዶና :- ስምንት ጎሎች
3. ሊዮኔል ሜሲ :- ስድስት ጎሎች

√ በአለም ዋንጫው አምስት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ያቀበለው ሊዮኔል ሜሲ ሪከርድን የግሉ ለማድረግ በውድድሩ በሶስት ጎሎች ላይ ተሳትፎን ማድረግ ይጠበቅበታል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe