TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.6K photos
1.48K videos
5 files
3.4K links
加入频道
TIKVAH-SPORT
የዋልያዎቹ ተጋጣሚ ማን ይሆናል ? በአልጄሪያ አዘጋጅነት ለሚካሄደው በሀገር ውስጥ ብቻ የሚጫወቱ ተጫዋቾች የሚሳተፉበት የቻን የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የሚደረግ የእጣ ድልድል ከሰዓታት በኋላ ይፋ ይደረጋል ። በመጀመሪያው ቋት ውስጥ ሩዋንዳ ፣ ዩጋንዳ እና ሱዳን የተካተቱ ሲሆን በሁለተኛው ዙር ላይ የሚሳተፉ መሆናቸው ይፋ ተደርጓል ። በሁለተኛው ቋት ውስጥ ታንዛኒያ ፣ ኢትዮጵያ ፣ ብሩንዲ ፣ ደቡብ ሱዳን…
ዋልያዎቹ ተጋጣሚያቸውን አውቀዋል !

በአልጄሪያ አዘጋጅነት በሚካሄደው በሀገር ውስጥ #ብቻ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ተሳትፎን የሚያደርጉበት የቻን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የእጣ ድልድል ከደቂቃዎች በፊት በግብፅ ርዕሰ መዲና ካይሮ ይፋ ተደርጓል ።

ዋልያዎቹ በመጀመሪያው ዙር ጨዋታቸውን ከ #ደቡብ_ሱዳን ብሄራዊ ቡድን ጋር የሚያከናውኑ ይሆናል ።

ዋልያዎቹ በደርሶ መልስ ደቡብ ሱዳንን ማሸነፍ ከቻሉ ከ #ሩዋንዳ አቻቸው ጋር የመጨረሻ የቻን የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታቸውን የሚያከናውኑ ሲሆን አሸናፊው ብሄራዊ ቡድን በቀጥታ የቻን የአፍሪካ ዋንጫ ተሳታፊ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ ።

የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ከወራቶች በኋላ ከ ሐምሌ 15 እስከ 17 ድረስ እንደሚካሄድ ካፍ አሳውቋል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ዋልያዎቹ ወደ መጨረሻው ማጣርያ ተቀላቅለዋል !

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድናችን የደቡብ ሱዳን አቻውን 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት በመርታት የመጨረሻውን ዙር ማጣርያ ተቀላቅሏል ።

የዋልያዎቹን ግብ ረመዳን የሱፍ ፣ አማኑኤል ገ/ሚካኤል ፣ መስኡድ መሀመድ ፣ ይገዙ ቦጋለ እና የደቡብ ሱዳን ተጫዋች በራሱ ላይ ባገባው ጎል ድል ተቀዳጅተናል ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በቀጣይ ከ #ሩዋንዳ አቻቸው ጋር የደርሶ መልስ ጨዋታቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል ።

ብሄራዊ ቡድናችን ከፊቱ ያለውን 180 ደቂቃ በድል ከተወጣ ለአልጄርያው የቻን አፍሪካ ዋንጫ ማለፉን ያረጋግጣል ።

የቻን የአፍሪካ ዋንጫ በሰሜን አፍሪካዋ ሀገር አልጄሪያ ከታህሳስ 30 እስከ ጥር 23 ድረስ 2015 ድረስ እንደሚካሄድ ተዘግቧል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ከሴካፋ ውድድር አንድ ሀገር ራሷን አገለለች !

በቀጣይ ሳምንት በሀገራችን አዘጋጅነት በሚካሄደው የሴካፋ ከ 17ዓመት በታች ውድድር #ሩዋንዳ በውድድሩ #እንደማትሳተፍ ተገልጿል።

የሩዋንዳ ከ 17ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን እስከ አሁን ዝግጅት አለመጀመራቸው ሲገለፅ ለውድድሩ ወደ ኢትዮጵያ #እንደማይመጡ ታውቋል።

ሩዋንሳ በምድብ ሁለት ከዩጋንዳ ፣ ብሩንዲ ፣ ጅቡቲ እና ሱዳን ጋር ተደልድላ እንደነበረ ይታወቃል።

የሴካፋ ውድድር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የሚደረግ ሲሆን ተጨማሪ አንድ ሀገር በውድድሩ የመሳተፏ ነገር #አጣብቂኝ ውስጥ ሲገኝ ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የሚረዳው ውድድር #በስምንት ሀገራት እንደሚደረግ ይጠበቃል።

ለመጨረሻ ጊዜ የተካሄደው ከሴካፋ ከ 17ዓመት በታች ውድድር #ሩዋንዳ ስታዘጋጅ #በስምንት ሀገራት መካከል መደረጉ የሚታወስ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe