TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.6K photos
1.48K videos
5 files
3.4K links
加入频道
ከሴካፋ ውድድር አንድ ሀገር ራሷን አገለለች !

በቀጣይ ሳምንት በሀገራችን አዘጋጅነት በሚካሄደው የሴካፋ ከ 17ዓመት በታች ውድድር #ሩዋንዳ በውድድሩ #እንደማትሳተፍ ተገልጿል።

የሩዋንዳ ከ 17ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን እስከ አሁን ዝግጅት አለመጀመራቸው ሲገለፅ ለውድድሩ ወደ ኢትዮጵያ #እንደማይመጡ ታውቋል።

ሩዋንሳ በምድብ ሁለት ከዩጋንዳ ፣ ብሩንዲ ፣ ጅቡቲ እና ሱዳን ጋር ተደልድላ እንደነበረ ይታወቃል።

የሴካፋ ውድድር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የሚደረግ ሲሆን ተጨማሪ አንድ ሀገር በውድድሩ የመሳተፏ ነገር #አጣብቂኝ ውስጥ ሲገኝ ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የሚረዳው ውድድር #በስምንት ሀገራት እንደሚደረግ ይጠበቃል።

ለመጨረሻ ጊዜ የተካሄደው ከሴካፋ ከ 17ዓመት በታች ውድድር #ሩዋንዳ ስታዘጋጅ #በስምንት ሀገራት መካከል መደረጉ የሚታወስ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe