#CHAN2023
ለቻን ውድድር አዘጋጇ ሀገር አልጄርያ ቀድማ የገባችው ሞዛምቢክ የአቋም መፈተሻ ጨዋታዋን በትላንትናው ዕለት ማድረግ ችላለች።
በአልጄርያ ሊግ ተሳታፊ ከሆነው ኤሲ ፓራዱ ክለብ ጋር የተጫወተው የሞዛምቢክ ብሔራዊ ቡድን 4ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።
የሞዛምቢክ ቡድን ከቀናት በፊት ከሊጉ ክለብ አልጀርስ ጋር ጨዋታውን አድርጎ 3ለ1 በሆነ ውጤት #መሸነፉ ይታወቃል።
የሞዛምቢክ ብሔራዊ ቡድን በሰባተኛው የቻን አፍሪካ ዋንጫ በምድብ አንድ ከአልጄርያ ፣ #ኢትዮጵያ እና ሊቢያ ጋር መደልደላቸው ይታወሳል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe

አልጄሪያ ውድድሯን በድል ጀምራለች !
በቻን አፍሪካ ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ አዘጋጅ ሀገሯ አልጄሪያ ሊቢያን 1ለ0 በማሸነፍ ውድድሩን በድል ጀምራለች።
የአልጄሪያን የማሸነፊያ ብቸኛ ግብ አይመን ማህዮስ በፍፁም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፏል።
አልጄሪያ በሜዳዋ ያደረገቻቸውን የመጨረሻዎቹ ስድስት ጨዋታዎች ያለሽንፈት አጠናቃለች።
አልጄሪያ ማሸነፏን ተከትሎ ምድብ አንድን በሶስት ነጥብ ስትመራ በቀጣይ የምድቡ ጨዋታ ከ #ኢትዮጵያ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

ኢትዮጵያ 🇪🇹 በፊፋ ሽልማት ማንን መረጠች ?
በትላንትናው ዕለት በተደረገው የአመቱ ምርጥ የፊፋ ሽልማት ላይ #ኢትዮጵያ በአምበሏ መስዑድ መሀመድ ፣ አሰልጣኟ ውበቱ አባተ እና ጋዜጠኛ #ሁሴን አብድልቀኒ በመወከል ድምጿን ሰጥታለች።
በዚህም መሰረት :-
- አሰልጣኝ ውበቱ አባተ :- ሊዮኔል ሜሲ ፣ ኪሊያን ምባፔ እና ሳድዮ ማኔ
- መስዑድ መሀመድ :- ሊዮኔል ሜሲ ፣ ኔይማር እና ካሪም ቤንዜማ
- ጋዜጠኛ #ሁሴን አብድልቀኒ :- ሊዮኔል ሜሲ ፣ ኪሊያን ምባፔ እና ካሪም ቤንዜማን በቅደም ተከተል መምረጣቸውን ለማወቅ ተችሏል።

TIKVAH-SPORT
ሉሲዎቹ ተጋጣሚያቸውን ቀጣይ ሳምንት ያውቃሉ ! የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለፓሪሱ የኦሎምፒክ ውድድር ተሳታፊ ለመሆን ተጋጣሚውን በቀጣዩ ሳምንት ማክሰኞ በግብፅ ካይሮ በሚኖረው የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ያውቃል። በኦሎምፒኩ ላይ አፍሪካን በመወከል ሁለት ሀገራት ብቻ ተሳታፊ የሚሆን ሲሆን የማጣርያው ውድድር አራት ዙሮች ይኖሩታል። በዚህም መሰረት :- 👉 የመጀመሪያ ዙር :- ሐምሌ 4 - 18/2015…
ሉሲዎቹ የምድብ ተጋጣሚያቸውን መቼ ያውቃሉ ?
የ2024ቱ የሴቶች ኦሎምፒክ ውድድር ማጣሪያ ጨዋታዎች የምድብ ድልድል ነገ ማክሰኞ ይፋ የሚደረግ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ( ሉሲዎቹ ) ቋት አራት ውስጥ ተካተዋል።
የምድብ ድልድሉ ቋት ምን ይመስላል ?
👉 ቋት አንድ :- ማሊ ፣ ጊኒ ፣ ሴራሊዮን እና ጊኒ ቢሳው
👉 ቋት ሁለት :- ቤኒን ፣ ቡርኪናፋሶ ፣ አይቮሪኮስት እና ጋና
👉 ቋት ሶስት :- ቻድ ፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ ፣ ኮንጎ ብራዛቪል እና ሩዋንዳ
👉 ቋት አራት :- #ኢትዮጵያ ፣ ሞዛምቢክ ፣ ናሚቢያ እና ዩጋንዳ ሆነው ተቀምጠዋል።
- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ( ሉሲዎቹ ) ከቋት ሶስት ሀገራት ጋር በምድብ ድልድሉ ይገናኛሉ ተብሎ #ይጠበቃል።
- ደቡብ አፍሪካ ፣ ሞሮኮ ፣ ናይጄሪያ ፣ ዛምቢያ ፣ ካሜሩን ፣ ቱኒዝያ እና ቦትስዋና በመጨረሻው የሴቶች አፍሪካ ዋንጫ ባሳዩት አቋም ምክንያት የመጀመሪያው ዙር ማጣርያ የማይወዳደሩ ይሆናል።

የሴካፋ ውድድር ላይ የሀገር ለውጥ ተደረገ !
በጎረቤት ሀገር ኬንያ አዘጋጅነት ለማድረግ ታቅዶ የነበረው የሴካፋ ሴቶች ከ 18ዓመት በታች ውድድር የቦታ ለውጥ ተደርጎበት ታንዛኒያ ዳሬ ሰላም ከተማ እንደሚደረግ አወዳዳሪው አካል በይፋ አሳውቋል።
ውድድሩ በበጀት መዘግየት ምክንያት ቀድሞ ተቀምጦለት ከነበረው ቀን ወደፊት ተገፍቶ ከ ሐምሌ 18/2015 ዓ.ም እስከ ነሀሴ 1/2015 ዓ.ም ታንዛኒያ ቻማዚ ስታዲየም እንደሚደረግ ተገልጿል።
በውድድሩ #ኢትዮጵያን ጨምሮ ስድስት አባል ሀገራት እንደሚሳተፉ ሲጠበቅ ኬንያ ከተማሪዎች ፈተና እና የትምህርት ቤት ውድድሮች ጋር በተያያዘ በውድድሩ እንደማትሳተፍ ተዘግቧል።
ተሳታፊ ሀገራት እነማን ናቸው ?
👉 #ኢትዮጵያ ፣ ታንዛኒያ ፣ ዩጋንዳ ፣ ቡሩንዲ ፣ ሩዋንዳ እና ዛንዚባር መሆናቸው ተገልጿል።

" ለሀገሬ 🇪🇹 ክብር ስል ሪከርዱን አስመልሳለሁ " አትሌት ለተሰንበት ግደይ
አትሌት ለተሰንበት ግደይ የ 5000ሜትር ሪከርድ በኬንያዊቷ አትሌት ፌዝ ኪፕዬጎን ከሀገራችን ስለተወሰደበት መንገድ ስትናገር ቁጭት ውስጥ ሆና ነው።
የ 1500ሜትር የገንዘቤ ዲባባ ሪከርድ ከዛም በቀናት ልዩነት የራሷ የ 5000ሜ ሪከርድ በፌዝ ኪፕዬጎን ሲሰበር መመልከት " የሀገር ክብር " እንደመነካት ነው ትላለች።
" የሚፈለገው ብር አይደለም ሁለቱ ሪከርድ ከሀገራችን ሲወጣ በጣም ተበሳጭቻለሁ " የምትለው ለተሰንበት ግደይ " ይህን ሪከርድ እንደማስመልስ ቃል እገባለሁ ለራሴ #ሳይሆን ለሀገሬ #ኢትዮጵያ ክብር ስል " ትላለች።
በስተመጨረሻም " ኢትዮጵያ ሀገራችን ሁሌም የወርቅ ሀገር እንድትሆንልኝ እመኛለሁ " ስትል ንግግሯን ትቋጫለች።
የአለም ሻምፒዮናው በነገው ዕለት ሲጀምር በ 10,000ሜትር ፍፃሜ የምትወዳደረው ለተሰንበት ግደይ እንደ ኦሪገን ውድድር ሁሉ ለሀገሯ የመጀመሪያውን ወርቅ ለማምጣት ብርቱ ፉክክር ይጠብቃታል።

#ኢትዮጵያ🇪🇹
ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች የሚሳተፉበት የ3000 ሜትር መሰናክል ወንዶች የማጣሪያ ውድድር መካሄዱን ጀምሯል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ በርቀቱ በአትሌት ለሜቻ ግርማ ፣ አብርሃም ስሜ እና ጌትነት ዋለ ተወክላለች።
🇪🇹🇪🇹 ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹🇪🇹

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች የሚሳተፉበት የ1,500 ሜትር ሴቶች የማጣሪያ ውድድር መካሄዱን ጀምሯል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ በርቀቱ በአትሌት ሂሩት መሸሻ ፣ ብርቄ ኃየሎም እና ድርቤ ወልተጂ ተወክላለች።
በውድድሩ ሁለተኛ ምድብ የምትገኘው ድርቤ ወልተጂ ውድድሯን ማድረግ ጀምራለች።

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች የሚጠበቁበት የሴቶች 10,000 ሜትር ፍፃሜ ውድድር መካሄዱን ጀምሯል።
ሀገራችን ኢትዮጵያ በርቀቱ በአትሌት ለተሰንበት ግደይ ፣ ጉዳፍ ፀጋይ ፣ ለምለም ሀይሉ እና እጅጋየሁ ታዬ ተወክላለች።

አትሌት ጥላሁን ሀይሌ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ !
በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን በ5000ሜ ይወክል የነበረው ጥላሁን ሀይሌ ዛሬ ከሰዓት ወደ ኢትዮጵያ መመለሱ ታውቋል።
አትሌቱ ለወራት ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ጋር ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቶ ወደ ሃንጋሪ ቢያመራም ከቡድኑ መቀነሱ ይታወሳል።
በዚህም ምክንያት አትሌት ጥላሁን ሀይሌ ከአሰልጣኙ ጋር ከተማከረ በኃላ ዛሬ ከሰዓት ወደ #ኢትዮጵያ ማቅናቱ ታውቋል።
አትሌቱ ከዝርዝሩ ወጪ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ በውሳኔው ማዘኑን እና ቅሬታውን በማህበራዊ ሚዲያ ካሰማ በኃላ የተለያዩ አስተያየቶች ሲሰነዘሩ ቆይተዋል።
ይሄም አትሌቱ ዜግነቱን #ይቀይራል የሚል ቢሆንም አትሌቱ ዜግነቱ መቀየር ሀሳቡም #እንደሌለው እና በቀጣይ ጠንክሮ በመስራት ኢትዮጵያን ወክሎ አቅሙን ማሳየት እንደሚፈልግ ለናሽናል ስፖርት ገልጿል።