#የዛሬ (መስከረም 6/2015)
❗️ "የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተሸጋገረ " እየተባለ በአንዳንድ የማህበራዊ ገፆች ላይ የሚሰራጨው መረጃ ምንጩ የማይታወቅ በትምህርት ሚኒስቴር ሆነ በሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ያልተገለፀ ነው። ተማሪዎች እንዲሁም የተማሪ ወላጆች ጥንቃቄ ልታደርጉ ይገባል።
🚘 ገንዘብ ሚኒስቴር የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ኢንቨስትመንትንና አስመጪዎችን የሚያበረታታ እንዲሁም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ የታክስ ማሻሻያ ተግባራዊ መደረጉን አስታውቋል። ከውጭ የሚገቡ ሆነ ሀገር ውስጥ የሚመረቱ የኤሌክትሪክ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች፣ የቤት አውቶሞቢሎችና የእቃ መጫኛ ተሽከርካሪዎች ላይ ዝቅተኛ የጉምሩክ ታሪፍ የሚጣልባቸው ሲሆን ከተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ከኤክሳይዝ ታክስና ከሱር ታክስ #ነፃ እንደሚደረጉ ታውቋል፡፡
✂️ የግል መገልገያ እቃዎች ወደሀገር የሚገቡበትን ሁኔታ የሚወስነው በስራ ላይ ያለው መመሪያ ለህገወጥ ንግድ በር የከፈተና የአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ተፅዕኖ የፈጠረ በመሆኑ በመመሪያ ቁጥር 923/14 ተተክትቷል ተብሏል። በዚህም ቀድሞ ይፈቀዱ የነበሩ እቃዎች በ84% ዝቅ እንዲሉ ተደርጓል።
🌾 ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐብይ አሕመድ ዛሬ ጠዋት በኦሮሚያ ክልል የዱግዳ እና የቦራ ወረዳዎች የስንዴ ኩታ ገጠም እርሻ የጎበኙ ሲሆን "ስንዴን ለውጪ ሀገር ገበያ ለማቅረብ ወደያዝነው ግብ ቀርበናል" ሲሉም በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።
🇺🇸 አሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛዋ አምባሳደር ማይክ ሀመር ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ፣ ከሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮች፣ ከአፍሪካ ህብረት እና ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር #ውጤታማ ውይይት አድርገዋል ብላለች። "ለኢትዮጵያ #አንድነት ፣ #ሉዓላዊነት እና #የግዛት_አንድነት ቁርጠኛ ነን " ስትል ገልጻለች።
⚽️ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የቅድመ ማጣርያ እየተካፈለ የሚገኘው ፋሲል ከነማ በድምር ውጤት 3ለ1 ቡማሙሩን በመርታት ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈዋል። ፋሲል ከነማ በቀጣዩ ዙር የማጣርያ ደርሶ መልስ ጨዋታ የቱኒዚያውን ሴፋክሲያን የሚገጥሙ ይሆናል።
#TIKVAHETHIOPIA
@tikvahethmagazine