TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
19K photos
296 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
加入频道
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በማዕከል ደረጃ ያለውን የሰራተኛ ቁጥር በመቀነስ ከፍተኛ የሥራ ጫና ወደ አለባቸው ወረዳ እና ተቋማት #ስርጭት እንዲደረግ ወስኗል።

ውሳኔው የተወሰነው ዛሬ በተካሄደው የካቢኔው የ3ኛ ዓመት 5ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ሲሆን ውሳኔው ከተማዋ ከምታመነጨው ገቢ እና ለህብረተሰብ ከሚሰጠው አገልግሎት አንፃር የማይመጣጠን በመሆኑ የተወሰነ እንደሆነ ነው የተገለጸው።

ይህንንም ውሳኔ ተቋማት ሙያዊ እና ተፈላጊ ችሎታን ታሳቢ አድርገው  እንዲያስተገብሩ እንዲደረግ ትዕዛዝ ተላልፏል።

በተጨማሪም አሁን በውስጥ አቅም የሚሰሩ ሥራዎችን ለ3ተኛ ወገን በማስተላለፍ (Outsource) መስራትን የሚያስችል ውሳኔም ተላልፏል።

ለሦስተኛ ወገን የሚተላለፉት ሥራዎች ጥሩ እና ተፈላጊውን ውጤት ያመጣሉ ተብለው በጥናት የተለዩ አገልግሎቶች እንደሆኑ ነው የተጠቆመው።

👋  @TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#AddisAbaba

ከልደታ ቆርቆሮ ሰፈርና ከዓድዋ ድል መታሰቢያ ዙሪያ ለልማት ለሚነሱ ነዋሪዎች የሚሰጡ ከ300 በላይ የሚሆኑ የመኖሪያ ቤቶች እየተገነቡ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል።

ከንቲባ አዳነች ዛሬ ማለዳ ልደታ ቤተክርስታያን አካባቢ ለልማት ተነሺዎች የሚተላለፍ ሁለት ባለ 9 ወለል የጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር በመሆን የመሰረት ድንጋይ በማስቀመጥ ግንባታውን በይፋ ማስጀመራቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልፀዋል።

ቀድም ተብሎ ከተጀመሩት ጋር ከ300 በላይ የሚሆኑ የመኖሪያ ቤቶች እየተገነቡ መሆኑን የገለፀት ከንቲባዋ እነዚህ በመገንባት ላይ ያሉ ቤቶች ከልደታ ቆርቆሮ ሰፈርና ከዓድዋ ድል መታሰቢያ ዙሪያ ለልማት ለሚነሱ ነዋሪዎች የሚሰጡ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

@TikvahethMagazine
#AddisAbaba

የ20ሚሊዮን ብር የዋጋ ግምት ያለው በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ የተለያዩ መድሃኒቶች በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ፖሊስ መድሃኒት የማከፋፈል ሆነ የመሸጥ ፍቃድ የለውም ያለው ተጠርጣሪ የህገ-ወጥ መድሃኒቱን አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ዱባይ ተራ ህንፃ የታችኛው ክፍል ደብቆት ነበር ብሏል።

ግለሰቡ፥ የካቲት 10 ቀን 2016 ዓ/ም መድሀኒቱን ወደ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው ታደሰ ብሩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀርባ ወዳለው የግል መኖሪያ ቤት በመውሰድ በዚያ አከማችቶ መያዙን ፖሊስ አስታውቋል።

@TikvahethMagazine
#AddisAbaba

በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሆስፒታል እና በሬቲና ፋርማሲዩቲካልስ በጋራ የሚተገበር አዲስ የዲያግኖስቲክ ማእከል ግንባታ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ ስምምነት ተፈርሟል።

ስምምነቱ፥ በተለይም በሆስፒታሉ የሚሰጠው የላብራቶሪ አገልግሎት መቆራረጥን የሚያስቀር መሆኑም የተገለጸ ሲሆን፤ የአገልግሎት ክፍያውም ቢሆን ከግል ተቋማት ጋር ሲነጻጸር በግማሽ ያህል ቅናሽ እንደሚኖረው በመድረኩ ተገልጿል፡፡

ላብራቶሪው አገልግሎት መስጠት ሲጀምር አሁን ላይ በሆስፒታሉ ከሚሰጡት የላብራቶሪ አገልግሎቶች በተጨማሪ ሌሎች አዳዲስ አገልግሎቶችንም መስጠት የሚያችል በመሆኑ በቀጥታ የሆስፒታሉን ተገልጋዮች ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል፡፡

@TikvahethMagazine
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ቡልቡላና አካባቢው ያሉ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የሚያደርግ የ14 ኪሎ ሜትር የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ ከኮየ-አቦ እስከ ቦሌ ቡልቡላ እየተከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።

172 ሚሊየን ብር ወጪ የሚፈጅው ፕሮጀክቱ፤
ጥር 1 ቀን 2016 ዓ.ም ተጀምሮ አሁን ላይ 14 ኪ.ሜ የሚሸፍን 320 የኮንክሪት ምሰሶ ተከላ ስራ ተከናውኗል። ቀድም ሲል በአካባቢው ተደጋጋሚ የኃይል መቆራረጥ የነበረ ሲሆን፤ የተጀመረው ሥራ ሲጠናቀቅ በቦሌ ቡልቡላና አካባቢው የነበረውን ችግር በከፍተኛ ደረጃ መቅረፍ የሚያስችል ይሆናል ብሏል ተቋሙ።

@TikvahethMagazine
#AddisAbaba

የአንበሳ እና ሸገር ከተማ አውቶቡሶች የመገልገያ ትኬት ከነገ ጀምሮ የሚቀየር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት አስታወቀ።

ትኬቶችን የመቀየር ስራ የመዲናዋ የትራንስፖርት ቢሮ በኪሎ ሜትር ባወጣው የትራንስፖርት ታሪፍ መሰረት ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን አስታውቋል። በመሆኑም አውቶቡሶቹ ከዚህ ቀደም ሲጠቀሙበት የነበረው ትኬት በባለ 5፣ 10፣ 15፣ 20 እና ባለ 25 ብር ይቀይራል ብሏል፡፡

በዚህም መሰረት የካቲት 19 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በሁለቱም ድርጅቶች የተቀየረው አዲስ ቲኬት ሙሉ በሙሉ ሥራ የሚጀምር ሲሆን በአዲስ መልክ ስራ ላይ የሚውለው ትኬት ከነባሩ የተለየ ቀለም፣ ወጥ የሆነ ዋጋ፣ ምስጢራዊ መለያ ያለው መሆኑን የዘገበው ኢዜአ ነው።

@TikvahethMagazine
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ የተማሪዎችን አጠቃላይ መረጃ የሚይዝና ጥራት አመላካች አሃዶችን የሚተነትን ኢ ስኩል ሶፍትዌር በትምህርት ቤቶች ተግባራዊ ሊሆን ነው።

ሥርዓቱ በሁሉም አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተግባራዊ እንደሚሆን ሲጠቆም በትምህርት ቤቶች ከመረጃ አያያዝና ትንተና ጋር የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለመሙላት እንዲሁም ለተማሪዎች ዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት ለማቅረብ እድል ይፈጥራል ተብሏል።

ሥርዓቱን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ግብዓቶች ሙሉ በሙሉ በሁሉም ትምህርት ቤቶች መሟላታቸውን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ ገልፀዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

@TikvahethMagazine
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ በ2016 በጀት ዓመት በአዲስ አበባ እና አከባቢው 523 የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች አጋጥመዋል።

በዚህ ጊዜ ውስጥ፦

- 351 የእሳት አደጋ፤ 172 ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች አጋጥመዋል፡፡

- በእሳት አደጋ ሳቢያ የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል።

- የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችን ጨምሮ በ90 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

- በእሳትና በሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ምክንያት የ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር የንብረት ውድመት አጋጥሟል፡፡

- በአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ርብርብ ከ37 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ከውድመት ማዳን ተችሏል፡፡

Source : ENA

#TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ የተገነቡትን የኮልፌና የለሚኩራ የገበያ ማዕከላትን ለ3ተኛ ወገን ማስተላለፉን (Outsource) አስታውቋል።

የገቢያ ማዕከላቱን እንዲያስተዳድሩ ለሁለት የግል ድርጅቶች የተሰጠ ሲሆን 'ሀብ ቢዝነስ ግሩፕ' የአስተዳደሩን ስራ 'ኢትዮ ጥበቃ' ደግም የጽዳትና የጥበቃ ስራውን እንዲሰሩ የተመረጡ ድርጅቶች ናቸው ተብሏል።

ድርጅቶቹ ከሐምሌ 1 ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ ወደስራ መግባታቸውም ተገልጿል። የግብይት ስርዓቱ በየሳምንቱ ንግድ ቢሮ በሚያወጣው ተመን የሚካሄድ መሆኑም የተገለጸ ሲሆን አጠቃላይ ሂደቱን ቢሮው እንደሚቆጣጠርም ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በውስጥ አቅም የሚሰሩ ሥራዎችን ለ3ተኛ ወገን በማስተላለፍ (Outsource) መስራትን የሚያስችል ውሳኔ በዚህ ዓመት ሕዳር ወር ላይ ማስተላለፉ ይታወሳል።

@tikvahethmagazine
#AddisAbaba

የኢትዮ ቴሌኮም ንብረት የሆነውን ገመድ በመቁረጥ በማዳበሪያ ውስጥ ጠቅልሎ ሲጓዝ በቁጥጥር ሥር የዋለውን ተጠርጣሪ መሰረት አድርጎ ፖሊስ ባደረገው ምርመራ ተጨማሪ 6 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋል ችያለሁ ብሏል።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅትም ፖሊስ ከ1 ሺህ ሜትር በላይ የሚሆን የኢትዮ ቴሌኮምና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት ንብረት የሆነ ገመድን ከነመቁረጫቸው አብሮ መያዙን ገልጿል፡፡

በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 አካባቢ የኢትዮ ቴሌኮምና የኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፊያ ገመድን ከሚቀበሉ ግለሰቦች ቤት ውስጥ 3 ጀነሬተሮች፣ 4 የሃይል ማስነሻ ባትሪ እና ባለሙያዎች ለስራ የሚጠቀሙባቸውን ቀበቶዎች መያዙንም ነው ያስታወቀው፡፡

@tikvahethmagazine
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ በ2016 በጀት ዓመት 38 ሺህ 239 ጋብቻ እና 8 ሺህ 949 ፊቺ መመዝገቡ ተገልጿል።

በዚሁ በጀት ዓመት 765 ሺህ 272 የነዋሪነት መታወቂያ የተሰጠ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 715 ሺህ 138ቱ የዲጂታል መታወቂያ መሆኑም ነው የተገለጸው።

ከልደት ጋር ተያይዞም ከዚህ ቀደም በ40 የጤና ተቋማት ላይ ብቻ ይሰጥ የነበረው ምዝገባ አሁን ላይ በ73 ጤና ተቋማት ተደራሽ ማድረግ ተችሏል ተብሏል፡፡ (AMN)

@tikvahethmagazine
#AddisAbaba

- በአዲስ አበባ በ2016 በጀት ዓመት በትራፊክ አደጋ ብቻ 383 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

- በዚሁ ጊዜ ከሁለት ሺህ በላይ ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት በትራፊክ አደጋ ደርሶባቸዋል።

- በበጀት ዓመቱ አንድ ሺህ 573 ቀላል የአካል ጉዳት አደጋ እንዲሁም 34 ሺህ 047 የንብረት አደጋ አጋጥሟል።

(መረጃውን የአዲስ አበባ ፖሊስ የትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ ለኢፕድ ሰጥቷል)

@tikvahethmagazine
አሁንም ብዙዎች የቤት ባለቤት ሊሆኑ ነው!
ሰስተኛው አርኪ የሪል ስቴት ኤክስፖ ተጀመረ!
👉በርካታ የቤት አማራጮች
👉ከባለሙያዎች ምክር የሚያገኙበት
👉ከሪል ስቴት ገንቢዎች እና ኤጀንሲዎች ጋር የፖናል ውይይት የሚያረጉበት
👉ለግንባታዎ የሚያስፈልጉዎትን ቁሳቁሶች በቀጥታ ከአቅራቢዎች የሚያገኙበት 

ታላቅ እድል!
ከነሐሴ 24፣ 25 እና 26 በስካይ ላይት ሆቴል እንጠብቅዎታለን!

ለበለጠ መረጃ ወደ 0994373737 ወይም 0923799133 ይደውሉ!

 🌻 በአዲስ አመት አዲስ ቤት🌻

#realstateagent #Ethiopia #realtors #adissabeba #arki #realstates #expo #ethiopia #realstate #ethiopian #addisababaethiopia #addisababa🇪🇹 #buyhome #realestateinvesting101 #events #realestateagent #realestate
#AddisAbaba

° "ልጆቻችንን ካስመዘገብን በኋላ መዋጮ ካልከፈላችሁ አይማሩም ተባልን" - ቅሬታ አቅራቢ

° "እችላለሁ የሚል መክፈል ይችላል አልችልም የሚል መንግሥት የሚሰራውን ይጠብቅ" - የጋራ ፉሪ ት/ቤት የወላጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ


በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 የሚገኘው የ ጋራ ፉሪ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ለመጪው የ ትምህርት ዘመን በቅድመ መደበኛ ለማስተማር ከመዘገበ በኋላ ለተማሪዎች መማሪያ ቦታ መስሪያ ከ 3 ሺ ብር በላይ እንድናዋጣ ተጠይቀናል ያሉ ወላጆች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።

ትምህርት ቤቱ የተቋቋመው በ 2016 ዓም ሲሆን በአንደኛ ደረጃ ከ 1-8ኛ ክፍል ተማሪዎችን በመቀበል በማስተማር ላይ ይገኛል።

በቅድመ አንደኛ ደረጃ የመማሪያ ቦታ ሳይኖር "ሊማሩም ላይማሩም ይችላሉ ለማንኛውም አስመዝገቡ እና ለሚመለከተው አካል እናመለክታለን" ተብለን ከ 15 ቀን በፊት ልጆቻችንን አስመዝግበናል ሲሉ ቅሬታ አቅራቢው ገልጸዋል።

አክለውም፥ ባሳለፍነው እሁድ ስብሰባ ጠርተው የሚማሩበትን ክፍል ለመስራት 3,731 ብር #እንዲያዋጡ መጠየቃቸውን ተናግረዋል።

"መንግሥት ከታህሳስ በኋላ በራሱ በጅት ስለሚሰራ እስከዛ የተጠየቀውን ገንዘብ አዋጥታቹ ሰርታቹ አስተምሩ ከታህሳስ በኋላ ተማሪ አንቀበልም ስለማለቱ ከትምህርት ቤተ ተነግሮናል" ብለዋል።

እስከ አርብ ግማሹን እስከ መስከረም 20 ደግሞ ሙሉውን ከፍላችሁ አጠናቁ ተብለናል መባላቸውን የገለጹት ቅሬታ አቅራቢው፥ "አቅም ያለው እየከፈለ ነው የሌለው ዝም ብሏል" ሲሉ አክለዋል።

እኛም ቅሬታቸውን ሰምተን በትምህርት ቤቱ የወላጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑትን ሃጂ አብራር ሁሴንን ጠይቀናል።

እንደ ሰብሳቢው ገለጻ፥ ተማሪዎች የመማሪያ ቦታ ሳይኖር የመዘገብነው በወላጅ ኮሚቴ በኩል ሰርተው ለማስተማር ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

አክለውም፥ የወላጆችን ጥያቄ ይዘን ከሚመለከተው አካል ለትምህርት ቤት መስሪያ ቦታ የሚውል ቦታ እንዲሰጣቸው በማመልከት 2,500 ካሬ ቦታ እንደተሰጠ ተናግረዋል።

ጥያቄውን ያቀረቡት 14 የሚሆኑ የወላጅ ተወካዮች ነበሩ የተባለ ሲሆን ይሄ ውሳኔ ከመወሰኑ በፊት ሁለት ጊዜ ስብሰባ መቀመጣቸውንም አስረድተዋል።

ቦታው እንደተፈቀደ ለወላጆች፥ መንግሥት የመማሪያ ክፍል ለመስራት ጨረታ አውጥቶ እየተንቀሳቀሰ በመሆኑ እንዲታገሱ ወይም አዋጥተን እንሰራለን ብለው ባስመዘገቡት መሰረት ሰርተው እንዲያስተምሩ እንደተነገራቸው ጠቁመዋል።

ከዚያም በተሰጠው ቦታ ላይ ት/ቤት ሰርቶ ለማስረከብ መንግሥት የራሱን እንቅስቃሴ እያደረገ ቢሆንም ሰርቶ እስከሚያስረክብ የአመቱ አጋማሽ ስለሚሆን በዚህ ጊዜ ተማሪን መመዝገብ ስለማይቻል አዋጥተው በመስራት ልጆቻቸውን እንዲያስተምሩ መግባባት ላይ ደረስን ሲሉ አስረድተዋል።

በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ለመከታተል የተመዘገቡት ህጻናት በቁጥር ከ 540 በላይ ይሆናሉ የተባለ ሲሆን 6 ዓመት በላይ የሆናቸው ህጻናትም ይገኙበታል።

በራሳቸው ለመስራት በተስማሙት መሰረት በባለሞያ ግመታ 12 ክፍል የሆነ ስድስት ሜትር በስድስት ሜትር የቆርቆሮ መማሪያ ክፍል ለመስራት 2 ሚሊየን ብር እንደተገመተና ለወላጆች የሚደርስባቸውን በማካፈል እንደተነገራቸው ተናግረዋል።

ወላጆች ክፍያውን ለትምህርት ቤቱ ከከፈሉ በኋላ አስተባብሮ ሰርቶ ያስረክባል ተብሏል።

አሁን የተያዘው እቅድ መስከረም 30 ድረስ አልቆ ጥቅምት አንድ ትምህርት ለማስጀመር ነው ያሉት ሰብሳቢው "እችላለሁ የሚል መክፈል ይችላል አልችልም የሚል መንግሥት የሚሰራውን ይጠብቅ" ሲሉ አክለዋል።

ወላጆች ቅሬታ ያቀረቡት ጉዳዩ አዲስ ሆኖባቸው ሳይሆን መንግስት ይሰራዋል የሚል ተስፋ ስለነበራቸው ነው ያሉት ሃጂ አብራር ሁለትም ሦስትም ልጅ ያላቸው ወላጆች የተተመነው ገንዘብ በልጆቻቸው ብዛት መክፈል እንደከበዳቸው ጠቅሰዋል።

ይህን አስመልክቶም፥ መክፈል ለማይችሉ እንዲሁም አቅሙ ለሌላቸው ወላጆች በመፍትሄው ላይ ለመነጋገር እና ገንዘቡን በሌሎች እንዲሸፈን ለማድረግ ለመስከረም 26/2017 ወላጆችን ት/ቤቱ ስብሰባ መጥራቱ ተነግሯል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethmagazine
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ በሩብ ዓመቱ ከ519 በላይ የሚሆኑ የጤና ተቋማት መለኪያውን ባለሟሟላት፣ ከልማት ጋር ተያይዞ ተቋማቸው በመፍረሱ እንዲሁም ከገበያ በመዉጣታቸዉ ምክንያት የፍቃድ ዕድሳት አለማድረጋቸውን የከተማ አስተዳደሩ ምግብና መድሐኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል። (Ahadu Radio )

@tikvahethmagazine
#NationalID🇪🇹   #AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል።

በኤጀንሲው በሁሉም ወረዳዎች እና ክፍለ-ከተሞች እንዲሁም ዋና መስሪያ ቤት እና ሁለት ቅርንጫፎች የፋይዳ ምዝገባም እንደሚጀመር ተገልጿል።

በዚህም በከተማዋ ነዋሪ የሆኑ እንዲሁም ነዋሪ ያልሆኑ ግለሰቦች በእነዚህ ጣቢያዎች ተገኝተው እንዲመዘገቡ ሁኔታዎች መመቻቸታቸውን ነው የብሔራዊ መታወቂያ ያስታወቀው።

ይህም የስማርት ሲቲ ትግበራው ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር በተሳሰረ መልኩ ለመተግበር ይረዳል ተብሏል።

በቅርቡም ከሁሉም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር የስርዓት ትሥሥር (system integration) ሂደት በጥናት ላይ ተመስርቶ ወደ ትግበራ እንደሚገባ ተነግሯል።

ለአብነት በመሬት አገልግሎት እና በገቢዎች የተጀመረውን የፋይዳ መታወቂያን የማሰናሰል ስርዓትን በእጅጉ በማጠናከር ለስማርት ሲቲ ትግበራ ጉልህ ሚና እንዲጫወት የሚሰራ ይሆናል ተብሏል።

ከተማ አቀፍ የምዝገባ ስራውን ለማሳለጥ ይረዳ ዘንድ ሁለቱ ተቋማት የጋራ ግብረሃይል አቋቁመው፣ የእቅድ ዝግጅት እና የቅድመ-ትግበራ ሥራዎችን አጠናቀዋል ሲል የብሔራዊ መታወቂያ ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል።

@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#AddisAbaba

በመዲናችን የሚገኝ አንድ በርበሬ ከባዕድ ነገር ጋር ተቀላቅሎ የሚመረትበት መጋዘን ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገልጿል።

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 ሚካኤል ቤተክርስቲያን ጀርባ የሚገኘው ይኸው መጋዘን በህገወጥ መልኩ በርበሬን ከባዕድ ነገር ጋር በመቀላቀል ምርት ሲመረት በቁጥጥር ስር መዋሉን ወረዳው አስታውቋል።

@tikvahethmagazine