TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
19K photos
296 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
加入频道
የሶልቭ ኢት 2023 ምዝገባ በቅርቡ ይጠናቀቃል፣ በማህበረሰባችን ውስጥ ላሉት ዘርፈ ብዙ ችግሮች መፍትሄ የሚሆን የፈጠራ ሃሳብ ካላችሁ ሶልቭ ኢት ለእናንተ ነው።

አሁኑኑ ተመዝገቡ   👉 solveit-et.com

Join our telegram groups

📍የአዲስ አበባ ቡድን      📍የድሬዳዋ ቡድን

📍የጅማ ቡድን                📍የባህርዳር ቡድን

📍የዎላይታ ሶዶ ቡድን       📍 የደሴ ቡድን

#Ethiopia #SolveIT #SolveITWithTech #InnovationCompetition #Startups #USEmbassy #DashenBank
አዋሽ ኢ-ስኩል ሲስተም
=========
ከጊዜው ጋር እየተሽቀዳደመ ከዘመኑ ጋር አብሮ እየዘመነ የመጣው አዋሽ ባንክ ት/ቤቶች ትውልድን ለመቅረፅ ያለባቸው ትልቅ ሃላፊነት በመረዳትና የትምህርት ጥራትን ለማሳካት በማሰብ የዲጂታል ትምህርት አስተዳደር ሥርዓት ወይም የኢ-ስኩል ሲስተም ቴክኖሎጂን አቀረበልዎ!
አዋሽ ኢ-ስኩል ሲስተም የግዜው ውድ ስጦታ!

Learn More- https://eschool.awashbank.com/
#AwashBank #Awash #ESchool #Management #System #Ethiopia #ኢትዮጵያ

ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👉 https://yangx.top/awash_bank_official
አዋሽ ኢ-ስኩል ሲስተም
=========
ከጊዜው ጋር እየተሽቀዳደመ ከዘመኑ ጋር አብሮ እየዘመነ የመጣው አዋሽ ባንክ ት/ቤቶች ትውልድን ለመቅረፅ ያለባቸው ትልቅ ሃላፊነት በመረዳትና የትምህርት ጥራትን ለማሳካት በማሰብ የዲጂታል ትምህርት አስተዳደር ሥርዓት ወይም የኢ-ስኩል ሲስተም ቴክኖሎጂን አቀረበልዎ!
አዋሽ ኢ-ስኩል ሲስተም የግዜው ውድ ስጦታ!

Learn More- https://eschool.awashbank.com/
#AwashBank #Awash #ESchool #Management #System #Ethiopia #ኢትዮጵያ

ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ 👉 https://yangx.top/awash_bank_official
አዋሽ ብር በሁሉም ቦታ
==========
በአዋሽ ብር ያለጥሬ ገንዘብ በመገበያየት ህይወትዎን ቀላል ያድርጉ!
#AwashBIRR #Banking #EveryWhere #Ethiopia #ኢትዮጵያ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አዋሽ ብር በሁሉም ቦታ!
==============
የአዋሽ ብር መተግበሪያን በመጠቀም ወይም ወኪሎች ጋር በመቅረብ የሂሣብ እንቅስቃሴን መከታተል፣ ገንዘብ ማስተላለፍ፣ ከወኪሎችና ኤቲኤሞች ገንዘብ ወጭ ማድረግ እንዲሁም ያለጥሬ ገንዘብ በመገበያየት ህይወትዎን ቀላል ያድርጉ!
#AwashBIRR #Banking #EveryWhere #Ethiopia #ኢትዮጵያ
የክፍያ ደረሰኝዎን ከአዋሽ ብር መተግበሪያ ላይ ያግኙ!
========
የአዋሽ ብር መተግበሪያን በመጠቀም ያለጥሬ ገንዘብ ሲገበያዩም ሆነ ክፍያ ሲፈፅሙ  የክፋያ ማረጋገጫ ደረሰኝ እንደሚደርስዎ ስናበስሮዎት በታላቅ ደስታ ነው!

#AwashBIRR #Banking #EveryWhere #Ethiopia #ኢትዮጵያ
‘ታታሪዎቹ’/ ቀጠሌዋን በቅርብ ቀን
****************
‘ታታሪዎቹ’/ ቀጠሌዋን የሁለተኛ ዙር የአዋሽ ባንክ የስራ ፈጠራ ውድድር በቅርቡ የሚጀምር ሲሆን የፈጠራ ሀሳብ ያላቸው የውድድሩ ተሳታፊዎች ከጥቅምት 12 እስከ ህዳር 13 ቀን 2016 ዓ.ም በባንኩ በይነ መረብ (ኦን ላይን) ወይንም በሁሉም አዋሽ ባንክ ቅርንጯፎች በአካል በመገኘት ማመልከት ይችላሉ፡፡
Dorgommiin kalaqa hojii marsaa 2ffaa Qaxaleewwan Baankii Awaash yeroo dhihootti kan eegalu yoo ta'u dorgomtoonni yaada kalaqaa qabdan Onkololeessa 12 bara 2016 haga Sadaasa 13 bara 2016 A.L.I tti Marsareetii Baankii Awaashiifi dameelee Baankii Awaash hundatti qaamaan argamuun galmaa'uu ni dandeessu.
https://tatariwochu.awashbank.com
#AwashBank #TATARIWOCHU #Qaxaleewwan #Empowering_The_Visionaries #Coming_Soon #Ethiopia #ኢትዮጵያ
👉አዋሽ ባንክ የዓለም ቁጠባ ቀንን አስመልክቶ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ያገናዘበ መደበኛ እና ሌሎችም የቁጠባ አማራጮችን አቀረበልዎ!
👉እኛ ጋር ይቆጥቡ! አብረውን ይደጉ!
👉Learn More:-
TikTok: https://www.tiktok.com/@awashbank_tiktok
Telegram: https://yangx.top/awash_bank_official
Twitter: https://twitter.com/bankawash
YouTube: https://www.youtube.com/awashbankAb
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/awashban/
Instagram: https://www.instagram.com/awash_bank/
Facebook: https://www.facebook.com/bankawash
#የዓለምቁጠባቀን #GuyyaaQusannooAdunyaa #WorldSavingsDay #SavingsAccount #Ethiopia
#UNICEF #ETHIOPIA

° በኢትዮጵያ 10.8 ሚሊዮን ህጻናት አስቸኳይ ሰብዓዊ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።

° በ2024 በኢትዮጵያ ለ 20 ሚሊዮን ዜጎች ለሚደረግ ሰብአዊ እርዳታ እና የተለያዩ ሰብዓዊ ቀውሶችን ለመከላከል 535 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልገኛል።

የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) በኢትዮጵያ በ2024 በትንሹ 10.8 ሚሊዮን ህጻናትን ጨምሮ 20 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን አዲስ ባወጣው የኢትዮጵያ የሰብአዊ ሁኔታ ሪፖርት አስታውቋል።

ዩኒሴፍ በ2024 በኢትዮጵያ ተጋላጭ ማህበረሰቦች እያጋጠማቸው ያለውን ዘርፈ ብዙ ችግሮች አሳሳቢ መሆናቸውን የገለፀ ሲሆን በሀገሪቱ እጨመሩ ያሉ ፈተናዎችን ለመቅረፍ እና በ2024 ይከሰታሉ ተብሎ የተገመቱትን ችግሮችና የሚያደርሱትን አስከፊ ቀውሶች ለመከላከል 535 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያስፈልግ በሪፖርቱ አመልክቷል።

በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2023 ዓመት ውስጥ ባሉት 12 ወራት በኢትዮጵያ የግጭት፣ ድርቅ፣ የጎርፍ አደጋ እና የበሽታ ወረርሽኝ ወደ 31.4 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ለችግር ዳርጓል ያለው ዩኒሴፍ በተጨማሪም 7.6 ሚሊዮን ህጻናት ከትምህርት ገበታቸው ውጪ እንዲሆኑ እንዳደረጋቸውም ነው የጠቆመው።

ዩኒሴፍ በ2023 በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች ድጋፍ ሊያደርግ ካቀዳቸው ሰዎች ውስጥ 42 በመቶ ለሚሆኑት እርዳታ ያደረሰ መሆኑን ሲገልፅ በ2024 በሀገሪቱ በስድስት ክልሎች አዲስ እና ውስብስብ ችግሮች እየተከሰቱ በመሆኑና ነባር ችግሮችንም የሚያባብስ በመሆኑ በመላ ሀገሪቱ 10.8 ሚሊዮን ሕፃናትን ጨምሮ ቢያንስ 20 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ ሰብዓዊ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል ሲል አሳስቧል።

@TikvahethMagazine
#UNICEF #ETHIOPIA

በኢትዮጵያ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ህጻናት እንዲሁም 350 ሺ ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች ለከፋ የምግብ እጥረት ይጋለጣሉ ሲል ዩኒሴፍ አስጠነቀቀ።

በ2024 በኢትዮጵያ ወደ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ህጻናት እና ወደ 350,000 ነፍሰ ጡር እንዲሁም የሚያጠቡ እናቶች ለከፋ የምግብ እጥረት የሚጋለጡ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) በትላንትናው እለት ባወጣው መግለጫ አስጠንቅቋል።

የዩኒሴፍ ምክትል ስራ አስፈፃሚ ቴድ ቻይባን በኢትዮጵያ ለ5 ቀናት ባደረጉት ጉብኝት በመላ ሀገሪቱ እየደረሰ ያለውን የከፋ ሰብአዊ አደጋ ለመከላከል አለም አቀፉ ማህበረሰብ ለህጻናት እና ቤተሰቦች የሚያደርገውን ድጋፍ በአፋጣኝ እንዲያጠናክር አሳስበዋል።

ቻይባን በድርቅ ከተጠቁት አካባቢዎች ውስጥ የትግራይ ክልልን የጎበኙ ሲሆን በክልሉ የምግብ ዋስትና ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ዜጎች ችግሩን ሊቋቋሙ የሚችሉበት መንገዶች መሟጠጣቸውንና በሀገሪቱ ውስጥ የኮሌራ፣ የኩፍኝ፣ የዴንጊ ትኩሳት እና የወባ ወረርሽኝ መከሰቱ የህብረተሰቡን የጤና ሁኔታ የበለጠ እንዳወሳሰበው ጠቁመዋል።

" ኢትዮጵያ በርካታ ቀውሶች ተጋርጠውባታል ያሉት ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚው " በኤልኒኖ ምክንያት የተከሰተውና በሰሜን፣ በመካከለኛው እና በደቡብ ኢትዮጵያ የተከሰተው ድርቅ በሚሊዮን በሚቆጠሩ ህጻናት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው" ብለዋል።

በዚህም በ 2024 ወደ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ህጻናት በከፍተኛ የምግብ እጥረት እንደሚሰቃዩ እና 350,000 የሚጠጉ ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እንደሚገጥማቸው ዋና ስራ አስፈፃሚው ገልፀው አለም አቀፉ ማህበረሰብ ለህጻናት እና ቤተሰቦች የሚያደርገውን ድጋፍ በአፋጣኝ እንዲያጠናክር አሳስበዋል።

@TikvahethMagazine
" 13 ሚሊዮን የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ የግብርና ግብአት እርዳታ ያስፈልጋቸዋል " - FAO

በኢትዮጵያ 13 ሚሊዮን የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን አስቸኳይ የግብርና ግብአት እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብና እርሻ ድርጅት (FAO) ባወጣው ሪፖርት አስታወቀ።

ድርጅቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ለከፋ የምግብ ዋስትና ችግር እንደተጋለጡ የገለፀ ሲሆን በሀገሪቱ እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው 21 ሚሊዮን ሰዎች ውስጥ 13 ሚሊዮን የሚጠጉት የግብርና ግብአት እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ገልጿል።

ሪፖርቱ ኢትዮጵያ በ40 ዓመታት ውስጥ ከፈረንጆቹ 2020 እስከ 2023 ባለው ጊዜ የከፋ ድርቅ እንደገጠማት ያመለከተ ሲሆን፥ በሀገሪቱ የአየር ንብረት ክስተቶች፣ ግጭቶች እና ሌሎች አደጋዎች ምክንያት የምግብ ዋስትና ችግር መባባሱን ጠቁሟል።

በመሆኑም በነዚህ አደጋዎች የተጠቁ ተጎጂ ማህበረሰቦች እንደ ምርጥ ዘር፣ ማዳበሪያ፣ የእንስሳት መኖ እና የመሳሰሉት የግብርና ግብአቶች አስቸኳይ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው በመግለፅ በ2024 ለነዚህ 5.46 ሚሊዮን ሰዎች ድጋፍ ለማድረግ 175 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ገልጿል።

#Ethiopia #Report #FAO

@TikvahethMagazine
ኢትዮጵያ በ11 ወራት ውስጥ ወደ ውጪ ከተላከ የቡና ምርት 1.2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷ ተነገረ

በበጀት ዓመቱ 11 ወራት ውስጥ ወደ ውጪ ከተላከው አጠቃላይ የቡና ምርት 1 ቢሊየን 208 ሚሊየን 73 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን የቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ።

በባለስልጣኑ መረጃ መሰረት ፦

- በበጀት ዓመቱ 11 ወራት በአጠቃላይ 252,466.98 ቶን የቡና ምርት ወደ ውጪ ተልኳል።

- በግንቦት ወር ብቻ 43,481.02 ቶን በመላክ የእቅዱ 105% ማሳካት ሲቻል በወሩ ብቻ 209.54 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል።

- የግንቦት ወር ውጥል ከ 2013/2014/2015 ዓ/ም በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወራት ከተላከው ምርት ከፍተኛ ውጤት የታየበት እንደሆነ ባለስልጣኑ ገልጿል።

#Coffee #Ethiopia

@tikvahethmagazine
" በኢትዮጵያ ተጠልለው ከሚገኙ 1 ሚሊዮን ስደተኞች 80 በመቶ የሚሆኑት ሴቶችና ህጻናት ናቸው " ሪፖርት

በኢትዮጵያ ተጠልለው ከሚገኙ 1 ሚሊዮን በላይ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች መሃከል 80 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች እና ህጻናት መሆናቸውን የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) ከስደተኞች እና ተመላሾች ጋር በመተባበር ያወጡት ሪፖርት አመለከተ።

በሪፖርቱ ምን ተገለፀ?

- ኢትዮጵያ 1,051,918 ስደተኞችን ስታስተናግድ በአፍሪካ ሁለተኛዋ ትልቅ የስደተኛ ተቀባይ ሀገር ሆናለች።

- በዚህም 423,077 ስደተኞች ከደቡብ ሱዳን ፤  347,103 ከሶማሊያ፤ 179,177 ከኤርትራ፤ 93,329 ከሱዳን፤ 4035 ከኬንያ እንዲሁም 252 ስደተኞችን ከየመን አስተናግዳለች።

- ከአጠቃላይ ስደተኞች 77 በመቶ ወይም 810 ሺ 856 የሚሆኑት በሀገሪቱ የሚገኙ የስደተኛ ካምፖች ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ከፍተኛ ስደተኞች የሚገኝበት የጋምቤላ ክልል ነው። ቁጥራቸውም 387 ሺ 420 ነው።

- በአዲስ አበባ እና መቀሌ ከተሞች ደግሞ 8 ከመቶ ወይም 80ሺ 361 ስደተኞች እንደሚገኙ ተመላክቷል።

- 160 ሺ 856 ወይም 15 በመቶ የሚሆኑ ስደተኞች አለምዋጭ፣ ሚርቃን፣ አውላላ እና ኩመር የስደተኞች ሰፈር እና ጣቢያዎች ውስጥ ይገኛሉ ተብሏል።

#Report
#Ethiopia

@tikvahethmagazine
The Mobile Gender Gap Report Summary.pdf
2.1 MB
በወንዶችና በሴቶች መካከል ያለ የስልክ ተጠቃሚነት/ባለቤትነት ልዩነት በኢትዮጵያ

(የሁለት ዓመት የጂ.ኤስ.ኤም.ኤ ሪፖርት ማጠቃለያ)

በሴቶች እና በወንዶች መካከል ያለው የስልክ እና የኢንተርኔት አጠቃቀም ብዙ ነገሮችን ያመለክታል። ይህ ቁጥር ደግሞ ከሌሎች ሀገራት ጋር ሲነጻጸር የሚያመለክታቸው ነገሮች እንደቀላል አይታዩም።

GSMA የተባለው ተቋም በዚሁ ዙሪያ ያሉ ልዩነቶችን በማጥናት በየዓመቱ ሪፖርት ያወጣል። ኢትዮጵያም ተቋሙ በ2023 እና በ2024 ባወጣው ሪፖርቱ ውስጥ ካሉ 12 ሀገራት መካከል ተካታለች።

ይህንን የ2 ሁለት ዓመት ሪፖርት ማጠቃለያ ከማነጻጸሪያ ቁጥሮች ጋር የቀረበ ሲሆን ከሪፖርቱ ኢትዮጵያን የሚመለከቱ መረጃዎች ቀርበዋል።

አንዳንድ ነጥቦች ከሪፖርቱ (ከ2024 የተወሰደ) ፦

- በኢትዮጵያ 79 በመቶ ወንዶች፤ 57 በመቶ ሴቶች የሞባይል ባለቤት ናቸው። በሁሉቱ ጾታዎች መካከል ያለው ልዩነት ደግሞ 28 በመቶ ነው።

- በኢትዮጵያ ስለ ስልክ ኢንተርኔት ግንዛቤ ያላቸው ወንዶች 64 በመቶ ሲሆኑ ሴቶች በአንጻሩ 52 በመቶ ያህሉ ብቻ ናቸው።

- አዋቂ ከሚባሉት እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ከሆነው አጠቃላይ የህዝብ ቁጥር በኢትዮጵያ የስልክ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ተብለው የተቀመጡት ወንዶች 21 በመቶ ሴቶች በአንጻሩ13 በመቶ መሆናቸውን አስቀምጧል፡፡

- በኢትዮጵያ የስማርት ስልክ ተጠቃሚዎች የሆኑ ከ18 ዓመት በላይ ከሆኑ ወንዶች 20 በመቶው ሴቶች ደግሞ 15 በመቶው ብቻ ናቸው፡፡

🔗 ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያዘጋጀው የማጠቃለያ ሪፖርት ከላይ ተያይዟል፤ ይመልከቱ።

#Ethiopia #GenderGap #TikvahEthiopia

@tikvahethmagazine
አሁንም ብዙዎች የቤት ባለቤት ሊሆኑ ነው!
ሰስተኛው አርኪ የሪል ስቴት ኤክስፖ ተጀመረ!
👉በርካታ የቤት አማራጮች
👉ከባለሙያዎች ምክር የሚያገኙበት
👉ከሪል ስቴት ገንቢዎች እና ኤጀንሲዎች ጋር የፖናል ውይይት የሚያረጉበት
👉ለግንባታዎ የሚያስፈልጉዎትን ቁሳቁሶች በቀጥታ ከአቅራቢዎች የሚያገኙበት 

ታላቅ እድል!
ከነሐሴ 24፣ 25 እና 26 በስካይ ላይት ሆቴል እንጠብቅዎታለን!

ለበለጠ መረጃ ወደ 0994373737 ወይም 0923799133 ይደውሉ!

 🌻 በአዲስ አመት አዲስ ቤት🌻

#realstateagent #Ethiopia #realtors #adissabeba #arki #realstates #expo #ethiopia #realstate #ethiopian #addisababaethiopia #addisababa🇪🇹 #buyhome #realestateinvesting101 #events #realestateagent #realestate
TIKVAH-MAGAZINE
ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከ1ሚሊዮን በላይ ፍልሰተኞችን እያስተናገደች ትገኛለች። ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከ1ሚሊዮን ሰባ አንድ ሺ በላይ ፍልሰተኞችንና ጥገኝነት ጠያቂዎችን እያስተናገደች ያለች መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛው የሥደተኞች ኮሚሽን (UNHCR) ቁጥራዊ መረጃዎች ያሳያሉ። ከዚህ ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች እና ህጻናት መሆናቸው ሲገለጽ 54 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ እድሜያቸው 0-…
#Update

° "ኤርትራውያን ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ለእስርና እንግልት እየተዳረጉ ነው በሚል የሚሰራጨው መረጃ ትክክል አይደለም" - የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛው የሥደተኞች ኮሚሽን (UNHCR) በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ትግራይና አፋር ክልል በኩል ከኤርትራ የሚገቡ ስደተኞች ጥበቃ እና ከለላ ያስፈልጋቸዋል ሲል በሪፖርቱ ጠቅሶ እንደነበር ይታወሳል።

ቢቢሲ በሰራው ዘገባም በአዲስ አበባ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች መጠነ ሰፊ እስራት እየተፈጸመባቸው ፖሊስ የሚወስደው ርምጃ እየተጠናከረ መምጣቱን ዘግቦ ነበር።

ይህን ተከትሎም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት በጉዳዩ ላይ ከደቂቃዎች በፊት መግለጫ አውጥቷል።

አገልግሎቱ በመግለጫው፥ የሚዲያዎቹን ዘገባ ተከትሎ አደረኩት ባለው ማጣራት፣ ሕጋዊ የስደተኝነት ዕውቅና ኖሯቸው ለእስርና እንግልት የተዳረጉ ስደተኞች በሀገሪቱ አለመኖራቸውን አረጋግጫለሁ ብሏል።

በዚህም በሀገሪቱ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ላይ ያነጣጠረ የዘፈቀደ እስርና እንግልት እየተከናወነ ነው በሚል በሀገር ውስጥና በውጭ ሚዲያ አውታሮች የተሰሩ ዘገባዎችን ተቋሙ "መሠረተ ቢስ" ሲል አጣጥሎታል።

አክሎም፥ ስደተኞች የሀገሪቱን ሕግና ሥርዓት ጥሰው ለእስር የተዳረጉበት ሁኔታ የሚኖር ከሆነ፣ አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የሚከታተለው ይሆናል ሲል አክሎ ገልጿል፡፡

በተጨማሪም የስደተኞች ምዝገባ ቆሟል በሚል ሚዲያው የሚያሰራጨው መረጃም ከእውነት የራቀ ነው ያለው አገልግሎቱ፥ "የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የስደተኝነት መስፈርትን ለሚያሟሉ አካላት ምንም ልዩነት ሳያደርግ የምዝገባ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፤ እየሰጠም ይገኛል" ብሏል፡፡

የወሳኝ ኩነት ምዝገባና የምስክር ወረቀት አገልግሎትን ጨምሮ የስደተኝነት መታወቂያ የመስጠት ተግባር ከበፊቱ በተጠናከረና በተደራጀ መልኩ እየተከናወነ መሆኑንም ተቋሙ ገልጿል።

ኢትዮጵያ ከ26 ሀገራት ከለላና ጥበቃ ፈልገው ለመጡ ከ1.1 ሚሊዮን በላይ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ከለላና ጥበቃ እየሰጠች ትገኛለች፡፡ ከነዚህ ውስጥ አብዛኛውን ቁጥር የሚይዙት ከጎረቤት ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ሱዳንና ኤርትራ የሚመጡ ስደተኞች ናቸው፡፡

#Ethiopia
#Eritrea
#Refugees

@TikvahethMagazine
ኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጭ ስደተኞችን የምታስተናግድ ሀገር ናት። ከአንድ ሚሊዮን በላይ የውጭ ስደተኞች በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ተጠልለው ይገኛሉ።

በልዩነትም ሁለት ዓመት ሊሞላው ወራቶች በቀሩት የሱዳን ጦርነት ምክንያት ከ67,775 ሰዎች በላይ ወደ ኢትዮጵያ ተሰደዋል።

ከዚህ ውስጥ ከ16ሺ በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በነበረው ጦርነት ተሰደው የወጡ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛው የሥደተኞች ኮሚሽን (UNHCR) ሪፖርት ያመለክታል።

#Sudan  #Ethiopia   #UNHCR

@tikvahethmagazine