TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
19K photos
293 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
加入频道
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች  ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ እና  በዕቃዎቻችን ጥራት ላይ  ደንበኞቻችን ምስክሮቻችን ናቸው። ዛሬም ብዛትንም ጥራትንም ሳንቀንስ እያስተናገድን እንገኛለን።

ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች ፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች  ወ.ዘ.ተ

አቅምን ካገናዘቡ እስከ ቅንጡ ላፕቶፖች ይህ ቀረ ሳይሉ የሚያገኙበትን ሱቃችንን ይጎብኙ። የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ ባሉበት ሆነው ይዘዙን እናደርሳለን።

የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።

@sww2844
0928442662
0940141114

https:/t.me/samcomptech
TIKVAH-MAGAZINE
ኬንያ ከዚህ ወር ጀምሮ በሀገር ዘመናዊ ስልኮችን ርካሽ በተባለ ዋጋ ለዜጎቿ ልታቀርብ ነው። ጎረቤት ሀገር ኬንያ አገልግሎቶችን በበይነ መረብ ለማቀላጠፍ በሚል በሀገር ውስጥ የተገጣጠሙ ዘመናዊ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን በርካሽ ዋጋ የማድረስ የያዘችውን እቅድ በዚህ ወር እንደምትጀምር ገልጻለች። የኬንያ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ዊልያም ሩቶ እና መንግስታቸው ይህንን እቅድ ባለፈው ዓመት ይፋ ሲያደርጉ፥ እቅዱ የማይመስል…
#Update: የኬንያ ዜጎች በ6 ወራት በሀገር ውስጥ የተገጣጠሙ ከ260 ሺ በላይ ስማርት ስልኮችን መግዛታቸው ተነገረ

በኬንያ በ2023 ኦክቶበር ወር መጨረሻ ላይ የኢኤዳክ ኩባንያ በሀገር ውስጥ የሞባይል ስልኮችን መገጣጠም ከጀመረ በኋላ የኬንያ ዜጎች 268,000 ስማርት የሞባይል ስልኮችን መግዛታቸው ተገለፀ።

ስልኮቹን የተገጣጠሙት በሀገሪቱ ሀገር በቀል የቴክኖሎጂ ድርጅቶችና የቴሌኮም ኩባንያዎች ጥምረት በተመሰረተው ኢኤዳክ ኩባንያ ሲሆን ይህ የሞባይል ስልኮች መገጣጠሚያ ፋብሪካ እስካሁን ወደ 330,000 ስልኮችን መገጣጠሙ ተነግሯል። ከተገጣጠሙት ስልኮች 80 በመቶ የሚሆኑት መሸጣቸውም ተገልጿል።

@TikvahethMagazine
"96 በመቶ ያህሉ #የድህረ_ክፍያ ደንበኞቼ ክፍያቸውን የፈጸሙት በዘመናዊ የክፍያ አማራጮች ነው።" የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

በበጀት ዓመቱ 9 ወራት 96 በመቶ ያህሉ #የድህረ_ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች ተቋሙ በዘረጋቸው ዘመናዊ የክፍያ አማራጮችን ተጠቅመው ወርሃዊ የአሌክትሪክ የፍጆታ ሂሳባቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።

ከዚህም ውስጥ፦

- 15 በመቶ በቴሌ ብር፣

- 24 በመቶ በሞባይል ባንኪንግ፣

- 24 በመቶ በሲቢኢ ብር፣

- 20 በአዋሽ ብር ፕሮ

- 13 በመቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባሉ ቅርንጫፎች በአካል በመሄድ ክፍያቸውን የሚፈጸሙ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

ቀሪ 4 በመቶ ያህሉ ደግሞ በማዕከል በመሄድ መክፈላቸውን ተቋሙ አስታውቋል።

@TikvahethMagazine
ኢትዮጵያ ባህርተኞችን አሰልጥና በመላክ በየዓመቱ 50 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እንደምታገኝ ተገለጸ።

ኢትዮጵያ ባህርተኞችን አሰልጥና  ወደ ተለያዩ አገራት በመላክ በየዓመቱ በአማካይ 50 ሚሊዮን ዶላር ገቢ እያገኘች መሆኑን የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን አስታውቋል።

የዓለም አቀፉ የማሪታይም ድርጅት አባል አገር የሆነችው ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በማሰልጠን ለዓለም ገበያ አቅርባ የውጭ ምንዛሬ ገቢ እንድታገኝ እያደረጋት መሆኑ ነው የተገለጸው።

የውጭ ምንዛሬው ባህርተኞች ከደሞዛቸው ላይ ወደ አገር ቤት ከሚልኩት ገንዘብ የሚገኝ መሆኑን የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልበር ሸምሱ አመልክተዋል።

በ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት ስምንት ወራት ከ36 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱንም ነው ዋና ዳይሬክተሩ ለኢዜአ ተናግረዋል።

በዘርፉ ገና ያልተነካ የኢኮኖሚ አቅም መኖሩን ያነሱት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ሕጋዊ እውቅና ያላቸው 7 ሺህ 500 ባህርተኞች እንዳሏት እና በ5 ዓመት ይህንን አሃዝ 40 ሺህ ከፍ ለማድርግ ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ልምድ እያላቸው ነገር ግን ሕጋዊ እውቅናና ተገቢው ክህሎት የሌላቸው ኢትዮጵያውያን በአነስተኛ ክፍያ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በተለይም በአረቡ ዓለም መርከበኛ ሆነው እየሰሩ መሆኑን አንስተዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ፥ ባህርተኞቹ ወደ ሕጋዊ አካሄዱ ቢመጡ በሕጋዊ መንገድ የመቀበልና ክፍያቸውን በየጊዜው የማሳደግ እድል እንደሚያገኙና ሕጋዊ የስራ ዋስትና እንደሚሰጣቸውም አመልክተዋል።

ባህርተኞች በቢሾፍቱና ባህር ዳር ከተሞች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ስልጠና እየወሰዱ እንደሚገኝና የማሰልጠኛዎችን ቁጥር ለማሳደግ እየተሰራም ነው ተብሏል።

@TikvahethMagazine
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ 12 የሙያ ትምህርቶች ይሰጣሉ ተባለ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ  በ2017 የትምህርት ዘመን ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሙያ ትምህርት መስጠት እንደሚጀምር ያስታወቀ ሲሆን የሙያ አይነቶቹንም ይፋ አድርጓል።

በዚህም በክልሉ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በተፈጥሮ ሳይንስ #በ7 የሙያ አይነቶች እና በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ #በ5 የሙያ አይነቶች ትምህርቱ ይሰጣል ተብሏል።

#በተፈጥሮ_ሳይንስ

1. የእንጨት ስራ ቴክኖሎጂ
2. ፊኒሺንግ ኮንስትራክሽን ስራ
3. ዌብ ዲዛይን እና ዴቬሎፕመንት
4. ኮምፒውተር ጥገና
5. አኒማል ፕሮዳክሽን
6. ተፈጥሯዊ ሀብት አስተዳደር
7. ማህበረሰብ ጤና

#በማኅበራዊ_ሳይንስ

1. ጆርናሊዝም
2. ስነ ልቦናዊ ክብካቤ
3. አካውንቲንግ እና ፋይናንስ
4. ማርኬቲንግ እና ሽያጭ አስተዳደር
5. ቮካል ፐርፎርማንስ እና ዳንስ መሆናቸው ተገልጿል።

እንደ ሀገር በ40 የሙያ አይነቶች ትምህርቱ የሚሰጥ መሆኑን የጠቀሰው የክልሉ ትምህርት ቢሮ ከ12ቱ የሙያ ትምህርቶች በተጨማሪ ወደፊት ሌሎች የሙያ አይነቶች እንደሚካተቱ ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@TikvahethMagazine
በፎቶው የምንመለከታት እህታችን ውቤ (ውባለም በለጠ) ትባላለች።

ከቤት እንደወጣች አልተመለሰችም።

የመኖሪያ አድራሻዋ የረር ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ ነው።

ቤተሰቦቿ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 09  ጎሮ ፖሊስ ጣቢያ መጥፋቷን አስመልክቶ ለፖሊስ አመልክተዋል።

ቤተሰብ በሙሉ ፍለጋ ላይ ናቸው።
ሽማግሌ ወላጆች የሚጭበጡትን አጥተዋል።

+251-900-100-765 -/ወንድም
+251-901944453 -/ ወንድም
+251-921941774 -  /እናት
+251-91 052 4661 -/አባት

ይህንን መልዕክት ሼር በማድረግ አፋልጓቸው፤ ከጭንቀት ገላግሏቸዉ።

@tikvahethmagazine
#ለጥንቃቄ

" ትላንት ማታ ሚያዚያ 13 ከምሽቱ 2:30 አካባቢ እኔና ባለቤቴ ዘመድ ጥየቃ ቆይተን ጉዞአችንን ከቄራ ወደ ወሎ ሰፈር አድርገን ስንሄድ ድንገት ጎተራ ማሳለጫ መንገድ ላይ አስደንጋጭ ክስተት ተመለከትን።

ጎተራ ማሳለጫ በላይኛው መስመር አንድ ሰው ከሶስት ሰዎች ጋ ሲታገል ተመለከትን። ቦታው እና ሁኔታው እጅግ አደገኛ ነው።

እግረኛ የማይጓዝበት እና መኪኖች በፍጥነት የሚያልፉበት መንገድ ከመሆኑ የተነሳ ለኛ በዚህ ሁኔታ መቆም እጅግ ፈተኝ ነበር።

ነገር ግን ቢያንስ የተጎጂው ሰው ሕይወት ለማትረፍ በቦታው ቀድመን የደረስን እኛ ብቻ መስሎ ስለታየን እና መኪና አስቁሞ በዚህ ልክ ይዘርፋሉ ብለን ስላልገመትን 7 ሜትር በሚሆን ርቀት ላይ ቆምን።

ይህን ሰው አንዱ መሬት ላይ አስተኝቶ አንቆታል ፤ ሌላኛው በተደጋጋሚ ይደበድበዋ አንደኛው በእጁ በያዘው ስለት ያለው መሳርያ ደጋግሞ ሲወጋው ተመለከትን።

ሰውዬው በዚህ መሀል ከፍ ባለ ድምፅ የሰቀቀን ጩኸት ያሰማ ነበር።

ከመኪናችን መውረድ ስለማንችል ያለን አማራጭ ሀዛርድ አብርተን ያለማቋረጥ ክላክስ ማድረግ ብቻ ነበር። ከኋላ ሌሎች መኪኖች ደረሱብን እነሱም ሁኔታው በግልፅ ስለሚታይ ከመኪናቸው ሳይወርዱ ያለማቋረጥ ክላክ ማድረግ ጀመሩ።

ያኔ ነው ከሌቤቹ/ነብሰ በላዎቹ አንዱ ወደ እኛ መቶ ጮኸብን በእግሩ መኪናውን ደበደበ ፊቱ በደንብ ይታያል። ሌሎች 2ቱ ሰውዬውን ይታገሉታል።

ሪስክ ወስጄ መኪናዬን በጣም ሳቀርብባቸው ሰውዬውን ለቀውት ሶስቱም መንገድ ዳር ያስቀመጡትን ድንጋይ አንስተው ሲያስፈራሩኝ መኪናዬ እንዳይጎዳብኝ ፈጣሪን እየተማፀንኩ በፍጥነት አለፍኩ። ነገር ግን በቀላሉ መስታወቱ ላይ ጉዳት ማድረስ ይችሉ ነበር።

ሰውዬውም ከወደቀበት ተነስቶ በተቃራኒ መስመር እየተንገዳገደ ለመሸሽ ሲሞክር በስፖኪዬ ተመለከትኩት።

ክስተቱን መረጃ ለመስጠት ለፌዴራል ፖሊስ ስንደውል አዲስ አበባ ፖሊስ ጋር መረጃ ስጡ ባሉን መሰረት በ +251111110111 ደውለን አሳወቅን። ቤት ደርሰን ሁኔታው በጣም ስለረበሸን በድጋሚ ስንደውል ፖሊሶች ተልከው " በአከባቢው ምንም የተፈጠረ ነገር የለም " ተባልን።

ይህን ከሰማን በኋላ ሁለት ሀሳብ መጣብን ፤
° ምናልባት ተበዳዩ ሰውዬ የነሱ ተባባሪ እና ግርግር ፈጥረው ከመኪና የወረደ አሽከርካሪ ላይ ጉዳት ለማድረስ እና መኪና እና ሌሎች ንብረቶችን ለመስረቅ ታቅዶ የተሰራ ይሆን ?
° ምናልባት ያለምህረት ሲደበድቡት ሱወጉት እውነትም ተበዳይ ይሆን ?

የሚመለከተው የፀጥታ አካል ትኩረት ሰጥቶ ቢሰራበት እንለለን። የደህንነት ካሜራዎችም የህብረተሰቡን ስጋት መከታተል አለባቸው።

ጎተራ አከባቢ እና ሌሎች ተጋላጭ ቦታዎች ላይ በምሽት የምታሽከረክሩት ጥንቃቄ አይለያችሁ!

(አንተነህ ክ.)

@tikvahethiopia @tikvahethmagazine
ታላቅ ቅናሽ 📣📣📣📣📣

💵 ድርጅታችን ድሪም ቢዉልደርስ በካሬ 90,000 ሲሸጥ የነበረውን ውደ 79,900 ብር ቅናሽ  አድርጓል።

🕧በ10% ቅድመ ክፍያ፣ በ9 ዙር፣ በ2 አመት ከ6 ወር ከፍለዉ የሚጨርሱት።

📍 በ CMC የተሟላ የመኖርያ መንደር ከ ለሚ ኩራ ፓርክ ፊትለፊት

⛰️በ ተንጣለለ 23,000 ካሬ ላይ ያረፉ አፓርትመንቶች፣ ከተሟላ መገልገያዎች ጋር

🛏️ባለ 1 መኝታ  79.92ካሬ  91.56ካሬ 
🛏️ባለ 2 መኝታ 125.4ካሬ   127.44ካሬ 
🛏️ባለ 3 መኝታ  169.92ካሬ

☎️ ለበለጠ መረጃ ይደዉሉልን 0974388888
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በአገልግሎት አሰጣጣችንና በዕቃዎቻችን ጥራት ላይ ደንበኞቻችን ምስክሮች ናቸው።
ዛሬም ብዛት እንዲሁም ጥራት ሳንቀንስ እያስተናገድን እንገኛለ!

ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች፣ ወ.ዘ.ተ.

አቅምን ካገናዘቡ እስከ ቅንጡ ላፕቶፖች ይህ ቀረ ሳይሉ የሚያገኙበትን ሱቃችንን ይጎብኙ! የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ ባሉበት ሆነው ይዘዙን እናደርሳለን።

የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።

@sww2844
0928442662
0940141114

https://yangx.top/samcomptech
ኬንያ ከኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ የገዛችው የኤሌክትሪክ ሀይል ከባለፈው አመት በ41 በመቶ ማደጉ ተገለፀ

ኬንያ ከፈረንጆቹ አዲስ አመት 2024 ጀምሮ ባሉት 3 ወራት ከኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ የገዛችው የኤሌክትሪክ ሀይል ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በ41 በመቶ ማደጉን ተገለፀ።

ኬንያ በተጠቀሰው ጊዜ ከኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ 408.78 Gigawatt-hour (GWh) የገዛች ሲሆን ይህም ባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ከተገዛው የ 288.3 GWh የኤሌክትሪክ ሀይል ግዢ በ41.7 የበለጠ መሆኑ ተጠቁሟል።

ለሀይል ግዢው ኬንያ ወደ 4.23 ቢሊየን የኬንያ ሽልንግ ያወጣች ሲሆን የሃይል አቅርቦቱ ርካሽ እንደሆነና ሀገሪቱ ጥገኛ የሆነችበትን የሙቀት ሀይል ማመንጫ ወጪን እየቀነስ መሆኑን ቢዝነስ ዴይሊ አስነብቧል።

@tikvahethmagazine
የኤሌክትሪክ ኃይልን ባሉበት በመሆን መሙላት የሚያስችለው ቴክኖሎጂ በዚህ ዓመት ይጠናቀቃል ተባለ

ከ900 ሺህ በላይ የቅድመ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ሙሉ በሙሉ በካርድ ብቻ ባሉበት ሆነዉ የኤሌትሪክ ኃይል መሙላት የሚያችላቸዉ ቴክኖሎጂ በተያዘው ዓመት እንደሚጠናቀቅ ተገለፀ።

ቴክኖሎጂው ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ የቅድመ ክፍያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ሙሉ በሙሉ በኦላይን ወይም የካርድ ቁጥርን ከዲጅታል የክፍያ አማራጮች በመጠቀምና ግዢ በመፈፀም ወደ አገልግሎት መስጪያ ማዕከሉ መሄድ ሳይጠበቅባቸዉ ኃይል መሙላት የሚያስችላቸው መሆኑን የዘገበው ካፒታል ነው።

@tikvahethmagazine
የመንግስትን እና የሀይማኖት ተቋማትን ግንኙነት በግልጽ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

መንግሥትና ሃይማኖት አንዱ በአንዳቸው ተግባርና እንቅስቃሴ ውስጥ ጣልቃ አይገቡም የሚለውን ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ መሠረት በማድረግ፣ መንግሥት ከሃይማኖት ተቋማት ጋር ያለውን ግንኙነት በግልጽ የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱ ተገለጸ፡፡

በሕገ መንግሥቱ ውስጥ ያለው ድንጋጌ ሃይማኖትና መንግሥት አይደራረሱም ማለት እንዳልሆነ ሲገለጽ በጋራ የሚሠሩባቸው ጉዳዮች መኖራቸውንና ሆኖም በሕገ መንግሥቱ ያለው ድንጋጌ ጥቅል መርሆዎችን የያዘ በመሆኑ፣ ይህን ለማብራራት ሕግ በማስፈለጉ ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱን ተጠቁሟል፡፡

በዚህም ባለድርሻ አካላት የተሳተፉባቸው ሦስት ጥናቶች ተካሂደው ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ከተወሰኑ ቤተ እምነቶች ጋር ውይይት የተጀመረ መሆኑን በሰላም ሚኒስቴር የሃይማኖት ጉዳዮች ዴስክ ተጠባባቂ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሀለፎም ዓባይነህ፣ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

@tikvahethmagazine
የመስተንግዶ ባለሙያዎች የአለባበስ ኮድ መመሪያ እንዲፀድቅ ለከንቲባ ጽሕፈት ቤት መላኩ ተነገረ

በሆቴሎች የሚሠሩ ሴት የመስተንግዶ ባለሙያዎች ከሀገሪቱ ባሕል ውጪ የሆነውን አለባበሳቸውን ለማስተካከል የሚያስችል የአለባበስ ኮድ መመሪያ ዝግጅቱ ተጠናቅቆ ለከንቲባ ጽሕፈት ቤት መላኩ የአዲስ አበባ ባሕል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ።

አሁን ላይ የመስተንግዶ ባለሙያዎች በተለይም ሴቶች በአንዳንድ ሆቴሎች አማካኝነት ሥነ-ሥርዓቱን ያልጠበቀ አለባበስ እንዲለብሱ ይገደዳሉ የተባለ ሲሆን መመሪያው ፀድቆ ሥራ ላይ ሲውል በሆቴሎች የሚሠሩ የመስተንግዶ ባለሙያዎች ወጥ የሆነ ዓለማቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የአለባበስ ኮድ እንዲከተሉ ይደረጋል ተብሏል።

መመሪያው በከተማዋ ካቢኔ በቅርቡ ፀድቆ ተግባራዊ እንደሚደረግ ሲገለፅ ሕጉ ከፍተኛ የገንዘብ ቅጣትም ጭምር ያለው በመሆኑ መመሪያውን በሚተላለፉ ላይ ቅጣት እንደሚጣል የአዲስ አበባ ባሕል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሣው (ዶ/ር) መግለፃቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

@tikvahethmagazine
በወር 15,000 ብር 💸💵💰💰 ማግኘት ይፈልጋሉ?

እንግዲያውስ
🚴‍♀️ ብስክሌት
🏍 ሞተር
🛵 E-bike ካልዎት ምን ይጠብቃሉ ከ ቢዩ ዴሊቨሪይ ጋር መስራት ይችላሉ።

💰ቢዩ ዴሊቨሪይ የምግብ አድራሽ ድርጅት ሲሆን ብስክሌት ፥ ሞተረ እና E-bike ካለው ግለሰብ ጋር አብሮ መስራት ይፈልጋል።

የስራ አድራሻ ፥ አዲስ አበባ

ለመመዝገብ:-


ከታች ባለው ( Telegram Bot ) በመጠቀም የቀረባልችሁን ጥያቄ በመሙላት

✴️https://yangx.top/DriversRegistration_bot

ወይም

☎️ 9533 ላይ በመደወል መመዝገብ ይችላሉ።
TIKVAH-MAGAZINE
በኢትዮጵያ 68% የሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች እና 51% የሶስተኛ ክፍል ተማሪዎች ማንበብ እንደማይችሉ ተነገረ በኢትዮጲያ በተለያዩ የአንደኛ ደረጃ 168 ትምህርትቤቶች በሚገኙ በ 9,000 ተማሪዎች በተጠናዉ ጥናት መሰረት 2ኛ ክፍል ተማሪዎች 68% እና 3ኛ ክፍል ተማሪዎች 51% ያህሉ ማንበብና መጻፍ እንደማይችሉ ተገልጿል። የተማሪዎችን የትምህርት ዉጤት ለማሻሻል የትምህርት ስርአቱ የተናበበ እና የተቀናጀ…
በኢትዮጵያ የ2ኛ እና 3ተኛ ክፍል ተማሪዎች ከግማሽ በላዩ ማንበብ እንደማይችሉ ጥናት አመለከተ።

የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ንባብን መሠረት አድርጎ ባካሄደው ጥናት በኢትዮጵያ የሚገኙ የ2ኛ እና 3ኛ ክፍል ተማሪች #56_በመቶዎቹ ምንም ዓይነት ቃል ማንበብ እንደማይችሉ አመልክቷል።

👩‍🎓  በጥናቱ ምን ያህል ተማሪዎች ተሳተፉ?

በዚህ ንባብን መሠረት ባደረገ ጥናት ከ9 ክልሎች የተወጣጡ ከ16 ሺህ በላይ ተማሪዎች በዘፈቀደ (Random sampling ) ተመልምለው ተሳትፈዋል። ተማሪዎቹ ከ401 የመንግሥት ትምህርት ቤቶች የተመረጡ ናቸው።

🔍  ጥናቱ እንዴት ተካሄደ?

በጥናቱ የተመለመሉት ተማሪዎቹ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የተጻፉ 50 ቃላት ቀርበውላቸው ቃላቱን ያነቡ እንደሆነ ተጠይቀዋል።

በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ፣ በአፋርኛ፣ በሶማሊኛ፣ በሀዲይኛ፣ በወላይትኛ፣ በሲዳምኛ እና ቤንሻንጉል ውስጥ በሚነገረው በርታ ቋንቋ የሚማሩ ተማሪዎች በዚህ ጥናት ተሳትፈዋል።

ከጥናቱ የሚጠበቀውም ፊደልን የመለየት፣ ቃላት ወይም አጭር አንቀጽ የማንበብ እና የማድመጥ እና የመረዳት ችሎታቸውን መመዘን ነው።

📕 የጥናቱ ውጤት ምን ያመለክታል?

- በጥናቱ ከተሳተፉት የ2ኛ እና 3ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል 56 በመቶ የሚሆኑት አንድም ቃል ማንበብ አይችሉም።

- በጥናቱ ከተሳተፉ የሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል ቢያንስ አንድ ቃል ማንበብ የሚችሉት 37 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው። የተቀሩት 63 በመቶዎቹ አንድም ቃል ማንብብ የማይችሉ (Zero renderers) ናቸው።

- የ3ኛ ክፍል ተማሪዎች ደግሞ 55 በመቶ የሚሆኑት ከየትኛውም ፊደል ጋር እንደማይተዋወቁ ጥናቱ ጠቁሟል።

- ጥናቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች እንዲስፋፉ፤ በተለምዶ ታዳጊ የሚባሉ ክልሎች ላይ ትኩረት እንዲደረግ ምክረ ኃሳብ አስቀምጧል።

🌍 በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመሳሳይ ጥናቶች ምን ያመለክታሉ?

- በዓለም አቀፍ ደረጃ አንድ የሁለተኛ ክፍል ተማሪ በደቂቃ ቢያንስ 60፤ የ3ኛ ክፍል ተማሪ ደግሞ 90 ቃላትን እንዲያነብ ይጠበቃል።

- ከላይ በተነሳው ነጥብ መሠረት በኢትዮጵያ ቋንቋዎች የሚማሩት የ2ኛ ክፍል ተማሪዎች ቢያንስ በደቂቃ 43 እንዲሁም የ3ኛ ክፍል ተማሪዎች 53 ቃላትን እንዲያነቡ ይጠበቅ ነበር።

መረጃው የተወሰደው ከቢቢሲ አማርኛ ነው።

@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ዩናይትድ ኪንግደም ከ150 አመታት በፊት ከአሻንቲ የተዘረፉ 32 የወርቅ እና የብር ቅርሶችን ለጋና በውሰት መለሰች

ዩናይትድ ኪንግደም ከ150 ዓመታት በፊት በብሪቲሽ እና ታዋቂ በነበሩት የአሻንቲ ህዝቦች መካከል በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ ከአሻንቲ ንጉስ ፍርድ ቤት ተዘርፈው የተወሰዱ 32 የወርቅ እና የብር ቅርሶችን ለስድስት አመታት ውል በውሰት ለጋና መስጠቷ ተገለፀ።

ቅርሶቹ ሊመለሱ የቻሉት የወቅቱን የአሳንቲ ንጉስ የሆኑት "ኦቱምፉኦ ኦሴይ ቱቱ 2ኛ" የብር ኢዮቤልዩ በዓልን ምክንያት በማድረግ በሚቀጥለው ወር በአሻንቲ ክልል ርዕሰ መዲና በሚገኘው በማኒሺያ ቤተ መንግስት ሙዚየም ለእይታ እንዲቀርቡ ታልሞ መሆኑ ተጠቁሟል።

ዩናይትድ ኪንግደም እነዚህ ቅርሶች የመለሰችው የአውሮፓና የአሜሪካ ሙዚየሞችና ተቋማት እንደ ብሪታንያ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን እና ቤልጂየም ባሉ ኃያላን አገሮች በቅኝ ግዛት ዘመን የዘርፏቸውን የአፍሪካ ቅርሶች እንዲመለሱ ግፊት እየተደረገባቸው ባለበት ወቅት መሆኑም ነው የተገለፀው።

@tikvahethmagazine
TIKVAH-MAGAZINE
Photo
#Update: በዲላ ከተማ ሚያዝያ 5 በጣለው ንፋስ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ ምክንያት በከተማው ሙሉ ለሙሉ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ተቋርጦ የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም መመለሱ ተገልጿል።

@tikvahethmagazine
በወር 15,000 ብር 💸💵💰💰 ማግኘት ይፈልጋሉ?

እንግዲያውስ
🚴‍♀️ ብስክሌት
🏍 ሞተር
🛵 E-bike ካልዎት ምን ይጠብቃሉ ከ ቢዩ ዴሊቨሪይ ጋር መስራት ይችላሉ።

💰ቢዩ ዴሊቨሪይ የምግብ አድራሽ ድርጅት ሲሆን ብስክሌት ፥ ሞተረ እና E-bike ካለው ግለሰብ ጋር አብሮ መስራት ይፈልጋል።

የስራ አድራሻ ፥ አዲስ አበባ

ለመመዝገብ:-


ከታች ባለው ( Telegram Bot ) በመጠቀም የቀረባልችሁን ጥያቄ በመሙላት

✴️https://yangx.top/DriversRegistration_bot

ወይም

☎️ 9533 ላይ በመደወል መመዝገብ ይችላሉ።
ታላቅ ቅናሽ 📣📣📣📣📣

💵 ድርጅታችን ድሪም ቢዉልደርስ በካሬ 90,000 ሲሸጥ የነበረውን ውደ 79,900 ብር ቅናሽ  አድርጓል።

🕧በ10% ቅድመ ክፍያ፣ በ9 ዙር፣ በ2 አመት ከ6 ወር ከፍለዉ የሚጨርሱት።

📍 በ CMC የተሟላ የመኖርያ መንደር ከ ለሚ ኩራ ፓርክ ፊትለፊት

⛰️በ ተንጣለለ 23,000 ካሬ ላይ ያረፉ አፓርትመንቶች፣ ከተሟላ መገልገያዎች ጋር

🛏️ባለ 1 መኝታ  79.92ካሬ  91.56ካሬ 
🛏️ባለ 2 መኝታ 125.4ካሬ   127.44ካሬ 
🛏️ባለ 3 መኝታ  169.92ካሬ

☎️ ለበለጠ መረጃ ይደዉሉልን 0974388888