TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
19K photos
293 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
加入频道
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ 12 የሙያ ትምህርቶች ይሰጣሉ ተባለ።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ  በ2017 የትምህርት ዘመን ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሙያ ትምህርት መስጠት እንደሚጀምር ያስታወቀ ሲሆን የሙያ አይነቶቹንም ይፋ አድርጓል።

በዚህም በክልሉ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በተፈጥሮ ሳይንስ #በ7 የሙያ አይነቶች እና በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ #በ5 የሙያ አይነቶች ትምህርቱ ይሰጣል ተብሏል።

#በተፈጥሮ_ሳይንስ

1. የእንጨት ስራ ቴክኖሎጂ
2. ፊኒሺንግ ኮንስትራክሽን ስራ
3. ዌብ ዲዛይን እና ዴቬሎፕመንት
4. ኮምፒውተር ጥገና
5. አኒማል ፕሮዳክሽን
6. ተፈጥሯዊ ሀብት አስተዳደር
7. ማህበረሰብ ጤና

#በማኅበራዊ_ሳይንስ

1. ጆርናሊዝም
2. ስነ ልቦናዊ ክብካቤ
3. አካውንቲንግ እና ፋይናንስ
4. ማርኬቲንግ እና ሽያጭ አስተዳደር
5. ቮካል ፐርፎርማንስ እና ዳንስ መሆናቸው ተገልጿል።

እንደ ሀገር በ40 የሙያ አይነቶች ትምህርቱ የሚሰጥ መሆኑን የጠቀሰው የክልሉ ትምህርት ቢሮ ከ12ቱ የሙያ ትምህርቶች በተጨማሪ ወደፊት ሌሎች የሙያ አይነቶች እንደሚካተቱ ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@TikvahethMagazine