በአዲስ ከተማ እየተገነባ ያለ የግለሰብ መኖሪያ ቤት ተደርምሶ በደረሰ አደጋ የ 7 ሰዎች ህይወት አለፈ
በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታዉ ጠሮ መስኪድ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ እየተገነባ ያለ የግለሰብ መኖሪያ የግንባታ ግብዓት አፈርና ድንጋይ ተደርምሶ በአቅራቢያው ያለ መኖሪያ ቤት ላይ በመናዱ በቤታቸዉ ተኝተዉ የነበሩ 7 ሰዎች ህይወታቸዉ አለፈ።
አደጋው የደረሰው በዛሬው እለት ሚያዚያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት 11 :00 ሰዓት ላይ ነው። የሟቾቹን አስከሬን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አዉጥተዉ ለፖሊስ ያስረከቡ ሲሆን የአደጋዉን መንስኤ ለማጣራት ፖሊስ ምርመራ እያካሄደ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።
@TikvahethMagazine

በኢትዮጵያ በገዳይነቱ የተመዘገበው የ 'ካላዛር' በሽታን ለማከም የሚውል መድኃኒት በሰዎች ላይ መሞከር ተጀመረ
የካላዛር ሕሙማንን ለማከም ለ17 ቀናት የሚሰጠውን የመርፌና የእንክብል መድኃኒት ሙሉ ለሙሉ በእንክብል ብቻ ለመተካት የሚያስችለው መድኃኒት፣ የዕድሜ ክልላቸው ከ18 እስከ 44 በሚደርሱ 52 ፈቃደኛ ኢትዮጵያውያን ላይ ሙከራው ተጀመረ።
በምርምሩ 15 የጤና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ሲሆን፣ ፈውስ ትኩረት ለተነፈጉ በሽታዎች ኢኒሺዬቲቭ ወይንም ዲ ኤን ዲ የጤና ምርምር የተባለ ተቋም እና አጋሮቹ ለዚህ በሽታ የሚያደርጉት የመድሃኒት ፍለጋ ምእራፍ ሁለት የክሊኒካል ሙከራ ደረጃ መሸጋገሩ ተጠቁሟል።
በአፍሪካ አሁን እየተሰጠ የሚገኘው የካላዛር ህክምና ለ17 ቀናት የሚወሰድ ከፍተኛ ህመም የሚፈጥር ክትባት ሲሆን በኢትዮጵያ በምርምር ላይ የሚገኘው አዲሱ የ “LXE408” በአፍ የሚወሰድ መድሀኒት አሁን ከሚሰጠው ህክምና የበለጠ ፈዋሽና እንደሚሆን ይጠበቃል ተብሏል። በኢትዮጵያ በዓመት ከ2 እስከ 3 ሺ ሰዎች በካላዛር በሽታ ይያዛሉ ሲባል በበሽታው ተይዘው ሕክምና ካላገኙት ውስጥ 95 በመቶ ያህሉ እንደሚሞቱ ተጠቁሟል።
Credit: Sheger, reporter

ኬንያ የፕላስቲክ ብክለትን ለመከላከል የፕላስቲክ ቆሻሻ ማጠራቀሚያን መጠቀም ከለከለች
የኬንያ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከአካባቢ ጥበቃ አንፃር የፕላስቲክ ብክለት እያስከተሉ ነው ያላቸውን ቆሻሻን ለመሰብሰብ እና ለማስወገድ የሚያገለግሉትን ፕላስቲክ ከረጢቶች መጠቀም የተከለከለ መሆኑን አስታወቀ።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እገዳውን በኤፕሪል 8 ያስተላለፈ ሲሆን ኬንያውያን ዜጎች የእገዳ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፕላስቲክ ከረጢቶችን በ90 ቀናት ውስጥ መጠቀም ማቆም አለባቸው ተብሏል።
በመሆኑም ሀገሪቱ የአካባቢ ጥበቃን እና ጤናማ የቆሻሻ አወጋደድን ለማረጋገጥ በባህሪያቸው ሊበሰብሱ የማይችሉትን የፕላስቲክ ከረጢቶችን መጠቀም በማቆም፣ ቆሻሻ አስወጋጅ ድርጅቶች ለደንበኞቻቸው ሙሉ በሙሉ ሊበሰብስ የሚችል ቆሻሻ ማጠራቀሚያ (biodegradable bags) ብቻ እንዲያቀርቡ መመሪያ መሰጠቱ ነው የተገለፀው።

ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ አበባን ጨምሮ በ29 ከተሞች የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን አስጀመረ
ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ አበባን ጨምሮ በ29 ከተሞች በሀገር አቀፍ ደረጃ የብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ ምዝገባን ዛሬ በይፋ አስጀምሯል። ዜጎችም ባሉበት ቦታ ሆነው በቴሌብር ሱፐርአፕ መመዝገብ እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም በሀገር አቀፍ ደረጃ የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን በማስጀመር በወር በአማካይ 1 ሚሊየን ዜጎችን በመመዝገብ እስከ 2018 ዓ.ም ለ90 ሚሊየን ዜጎች አገልግሎቱን ለመስጠት ማቀዱም ነው የተገለፀው።

TIKVAH-MAGAZINE
ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ አበባን ጨምሮ በ29 ከተሞች የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን አስጀመረ ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ አበባን ጨምሮ በ29 ከተሞች በሀገር አቀፍ ደረጃ የብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ ምዝገባን ዛሬ በይፋ አስጀምሯል። ዜጎችም ባሉበት ቦታ ሆነው በቴሌብር ሱፐርአፕ መመዝገብ እንደሚችሉ ተጠቁሟል፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም በሀገር አቀፍ ደረጃ የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን በማስጀመር በወር በአማካይ…
#Update: እድሜያቸው ከ5 ዓመት በላይ የሆናቸው ዜጎች የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ማከናወን እንደሚችሉ ተገለፀ
እድሜያቸው ከ5 ዓመት በላይ የሆናቸው ዜጎች የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ለማከናወን ይፋ በተደረጉት የኢትዮቴሌኮም የአገልግሎት ማዕከላት በአካል በመገኘት፣ ማንነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ እንደ ፦
➡ ቀበሌ መታወቂያ፣
➡ የታደሰ የመንጃ ፈቃድ፣
➡ ፓስፖርት የመሳሰሉ ሰነዶችን በመያዝ ወይም የሰው ምስክር በማቅረብ በነጻ መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።
የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ አገልግሎት የሚሰጥባቸው ማዕከሎቻችን የትኞቹ ናቸው?
በአዲስ አበባ፦ ውሃ ልማት (ሃያ ሁለት)፣ ልደታ፣ ስታዲየም፣ ቦሌ መድኃኔዓለም፣ ገርጂ፣ አያት፣ ስድስት ኪሎ፣ ጉርድ ሾላ፣ ሽሮሜዳ፣ ሳሪስ፣ ቃሊቲ፣ አቃቂ፣ ጀሞ፣ ለቡ፣ ቤተል፣ አራዳ፣ ኮልፌ፣ ቡራዩ እና ቲፒኦ (ጥቁር አንበሳ) ናቸው።
በሪጅኖች ደግሞ ፦ በሐረር፣ ደብረብርሀን፣ ፊቼ፣ ለገጣፎኣ፣ አምቦ፣ ሰበታ፣ ጅግጅጋ፣ ድሬዳዋ፣ ሰመራ፣ ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ጎንደር፣ አዘዞ፣ መቀሌ(ሁለት)፣ ባሕርዳር፣ ዓባይ ማዶ፣ አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ ሐዋሳ(ሁለት)፣ ሻሸመኔ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ሆሳዕና፣ ወልቂጤ ጅማ፣ ቦንጋ፣ ሚዛን፣ ጋምቤላ ነቀምቴ እና አሶሳ ናቸው።
ከከተማ እና የገጠር ነዋሪዎች በተጨማሪ የዩኒቨርስቲ፣ የከፍተኛ እና የብሔራዊ 2ኛ ደረጃ መልቀቂያ ተፈታኞች፣ በተፈናቃዮች ጣቢያ የሚገኙ፣ የሴፍቲኔት ፕሮግራም ተጠቃሚዎች እና በሀገራችን የሚገኙ ሕጋዊ የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ ያላቸው የውጭ ሃገር ዜጎች ምዝገባ ማከናወን ይችላሉም ተብሏል።

#Update በዛሬው ዕለት በሦስት ዙር በተደረገ በረራ 1 ሺህ 71 ዜጎች ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። ዛሬ የተመለሱት ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ ዘጠኙ እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው። መረጃው የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ነው። @TikvahethMagazine
#Update: ከሳውዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን ወደ ሀገር በመመለስ ስራ እስካሁን ከ9ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን መመለሳቸው ተነገረ።
በዛሬው እለት በሶስት ዙር በረራ 1 ሺህ 181 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ሁሉም ወንዶች እንደሆኑና 4 እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙበት የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታውቋል።
@TikvahethMagazine
በዛሬው እለት በሶስት ዙር በረራ 1 ሺህ 181 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ሁሉም ወንዶች እንደሆኑና 4 እድሜያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙበት የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር አስታውቋል።
@TikvahethMagazine
ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌን ይኖሩበት የነበረውን ቤትና የሥራ ስቱዲዮ ለመጠገን የስራ ርክክብ ተደረገ
እጅግ የተከበሩ የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ ይኖሩበት የነበረውን ቤትና የሥራ ስቱዲዮ ለመጠገን የሥራ ርክክብ መደረጉን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡ የጥገና ሥራውን ለማከናወን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን፣ ቢዋይ ኤምቲ ኮንትራክተር እና ዳሎል አማካሪ ድርጅት የስራ ርክክብ አድርገዋል፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው ቅርሱ የነበረውን አሻራና ይዘት በመጠበቅ የቅርስ ጥገና መርሆዎችን ተከትሎ በጥንቃቄ መከናወን እንዳለበት የጠቆሙ ሲሆን የጥገና ሥራውም በተቀመጠለት የአንድ ዓመት ጊዜ እንዲከናወን አሳስበዋል፡፡

ስትጠብቁት የነበረው የ12 ክፍል ማትሪክ ፈተና አጋዥ አፕሊኬሽናትችን አሁን playstore ላይ ይገኛል። ዳውንሎአድ እና Upgrade አድርጎ መጠቀም ብቻ ነው የሚጠበቅባችሁ።
✅በነጻ ለውስን ቀናት
✅አዲሱን ስር አተ ትምህርት ያካተተ
✅አጫጭር ኖቶችና አጋዥ ቪድዮዎች የያዘ
አሁኑኑ ይሞክሩት!!!!!!!!!
@examtimeethiopia
ለማውረድ ይህን ማስፈንጠሪያ መጠቀም ይቻላል ➝ Playstore
በተጨማሪም የተለያዩ ማህበራዊ ገፆቻችን ቤተሰብ ይሁኑ።
Instagam | Telegram | Youtube | Facebook | Tiktok |

#cloudbridge. #traininginstitute
ክላውድ በሪጂ ማሰልጠኛ ተቋም ፤ለስልጠና ፍላጊዎች በሙሉ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽ እውቀት አቅም ግንባታ ነፃ ስልጠና ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቆ እናንተን በጉጉት ይጠብቃል::
ስልጠና ሚሰጥባችው ዘረፎች መካከል፡
1,Web development
2,Interior design
የስልጠና ቦታ
ሲቲ ሞል 6ኛ ፎቅ, መገናኛ ድልድይ,wow burger ያለበት፣Megenagna siti Mall 6th, Addis Ababa, Ethiopia
ለተጨማሪ መረጃ
094-228-0000 092-083-8483
ያሉን ቦታዎች ውስን ናቸው ፈጥነው በአካል መተው ይመዝገቡ።
ለአንድ ቀን ሚቆይ ነፃ ስልጠና!
Register online
https://cloudbridgeacademy.com/registration
Telegram :https://yangx.top/cbmtraininginstitute

የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን መሰብሰብ የነበረበትን ከ850 ሚሊዮን በላይ ብር እንዳልሰበሰበ ተገለፀ
የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን ከ 5 እስከ 10 ዓመት ባለው ጊዜ ዉስጥ ሰብስቦ ወደ መንግስት ካዝና ማስገባት የነበረበትን 850 ሚሊዮን 911 ሺህ 237 ብር እንዳልሰበሰበ ተገለፀ።
ይህ የተገለፀው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የ2014/15 በጀት ዓመት የክዋኔ ኦዲት ግኝት ላይ በተወያየበት ወቅት ነው። የኮርፖሬሽኑ የግብርና ኬሚካሎች፣ የእንስሳት መድኃኒትና የሌሎች ዘርፎች አፈጻጸም ዝቅተኛ እንደሆነም ተጠቁሟል።
የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ክፍሌ ወልደማርያም በኦዲት ሪፖርቱ የተጠቀሱ ግኝቶች ለማስተካከል የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰደ እንደሚገኝ ሲገልፁ ኮርፖሬሽኑ በያዛቸው ቦታዎች ላይ የሚፈለገውን የልማት ስራ እያከናወነ ባለመሆኑም በክልሎች የወሰዳቸውን መሬቶች እስከ መቀማት መድረሱም ተመላክቷል።

በኬንያ በተከሰተው ከባድ ጎርፍ በትንሹ 32 ሰዎች ሞተው ከ40 ሺ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸው ተነገረ
በኬንያ በተከሰተው ከባድ ጎርፍ በትንሹ 32 ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ እና ከ40 ሺህ የሚበልጡት ደግሞ ዝናቡ ባስከተለው ጎርፍ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለመፈናቀል መገደዳቸው ተገልጿል።
በርዕሰ ከተማዋ መንገዶች በውሃ ተጥለቅልቀው የታዩ ሲሆን በዚህ ከባድ ጎርፍ ምክንያት 15 ሰዎች ቆስለው፣ 1ሺ የሚጠጉ እንስሳትን እንደሞቱና በሺዎች ሄክታር ላይ ያረፉ ሰብሎችን መውደማቸው ተገልጿል። በሚቀጥሉት ቀናትም በመላ ሀገሪቱ መጠኑ ከፍ ያለ ዝናብ ይጠበቃልም ነው የተባለው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 2 ዘመናዊ የአውሮፕላን መለዋወጫና ጥገና ማዕከላት ወደ ሥራ ሊያስገባ ነው ተባለ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጨማሪ ሁለት ዘመናዊ የአውሮፕላን መለዋወጫና ጥገና ማዕከላትን ወደ ሥራ ሊያስገባ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰው በአፍሪካ አቪዬሽን የአውሮፕላን መለዋወጫና ጥገና ተቋማት ኮንፍረንስ ላይ ተናግረዋል።
የአውሮፕላን መለዋወጫና ጥገና ማዕከላቱ በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ አገልግሎት ይጀምራሉ የተባለ ሲሆን በዚህም የአየር ፍሬም፣ ሞተርና አካል ጥገናን ጨምሮ የምሕንድስና የቁሳቁስ አገልግሎቶችን ይሰጣል መባሉን የዘገበው ኢፕድ ነው።

ኢትዮጵያ ውስጥ 1ሰው ብቻ በቅጡ የሚናገረው ቋንቋ መኖሩ ተነገረ
ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ሰው ብቻ በትክክል የሚናገረው የብራይሌ ማህበረሰብ የሆነው የ "አንጎታ" ቋንቋ መኖሩ ተነገረ።
የብራይሌ ማህበረሰብ አንጎታ ቋንቋን የሚናገሩ አምስት ሰዎች አሉ ቢባልም ቋንቋውን በቅጡ የሚያውቀው አንድ ሰው ብቻ መሆኑን የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ዲኤታ ወርቅነሽ ብሩ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ገልፀዋል።
ከ 145 አመታት በፊት የብራይሌ ብሔረሰብ ብዛት 8 ሺህ ያህል እንደነበረ ጥናት ያመለከተ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ግን ያሉት የብሄሩ ተወላጆችም ሆነ ቋንቋውን መናገር የሚችሉት አምስት ሰዎች ብቻ መሆናቸው ተነግሯል፡፡
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የመጥፋት አደጋ የተጋረጠባቸው ሁለት ቋንቋዎች ከመጥፋት ለመታደግ ጥናት እና ምርምር እየተሰራ መኖሩ ሲነገር ከብራይሌ በተጨማሪ ከፍተኛ የመጥፋት አደጋ ተጋርጦበታል የተባለው ሌላኛው ቋንቋ የባጫ ብሔረሰብ ቋንቋ የሆነው ባጫ ቋንቋ መሆኑን ሸገር በዘገባው አመልክቷል።

ደስ ይበላችሁ!
ካሉበት ሆነው ለሚወዱት ቤተሰቦ/ወዳጆ ለትንሳዔ እንዲሁም ለዳግመ ትንሳዔ በዓላት ሙሉ #ሥጦታ ከሙሉ #ደስታ ጋር ይላኩ!
ድርጅታችን በ #Platinum , #Golden, #Silver አማራጭ #የበግ ሙክትን ጨምሮ በዓል በዓል የሚሉ ሥጦታዎችን ለሚወዱት ሰው #ባለበት #በተመጣጣኝ ዋጋ ይላኩ። እንደ እናንተው ሆነን እናደርሳለን!
ይደውሉ - 0911359234 (WhatsApp NO.) or 0954882764
ሙሉ ፖኬጁን ይመልከቱ 👉 t.me/bluebellgiftstore
😮 #ለቤተሰቦቻችን_ብቻ: ባለፈው ዓመት ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ስጦታ የላኩ እንዲህ ተደስተዋል 👉https://yangx.top/bluebellgiftstore/627
ካሉበት ሆነው ለሚወዱት ቤተሰቦ/ወዳጆ ለትንሳዔ እንዲሁም ለዳግመ ትንሳዔ በዓላት ሙሉ #ሥጦታ ከሙሉ #ደስታ ጋር ይላኩ!
ድርጅታችን በ #Platinum , #Golden, #Silver አማራጭ #የበግ ሙክትን ጨምሮ በዓል በዓል የሚሉ ሥጦታዎችን ለሚወዱት ሰው #ባለበት #በተመጣጣኝ ዋጋ ይላኩ። እንደ እናንተው ሆነን እናደርሳለን!
ይደውሉ - 0911359234 (WhatsApp NO.) or 0954882764
ሙሉ ፖኬጁን ይመልከቱ 👉 t.me/bluebellgiftstore
😮 #ለቤተሰቦቻችን_ብቻ: ባለፈው ዓመት ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ስጦታ የላኩ እንዲህ ተደስተዋል 👉https://yangx.top/bluebellgiftstore/627
#cloudbridge. #traininginstitute
ክላውድ በሪጂ ማሰልጠኛ ተቋም ፤ለስልጠና ፍላጊዎች በሙሉ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽ እውቀት አቅም ግንባታ ነፃ ስልጠና ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቆ እናንተን በጉጉት ይጠብቃል::
ስልጠና ሚሰጥባችው ዘረፎች መካከል፡
1,Web development
2,Interior design
የስልጠና ቦታ
ሲቲ ሞል 6ኛ ፎቅ, መገናኛ ድልድይ,wow burger ያለበት፣Megenagna siti Mall 6th, Addis Ababa, Ethiopia
ለተጨማሪ መረጃ
094-228-0000 092-083-8483
ያሉን ቦታዎች ውስን ናቸው ፈጥነው በአካል መተው ይመዝገቡ።
ለአንድ ቀን ሚቆይ ነፃ ስልጠና!
Register online
https://cloudbridgeacademy.com/registration
Telegram :https://yangx.top/cbmtraininginstitute
ክላውድ በሪጂ ማሰልጠኛ ተቋም ፤ለስልጠና ፍላጊዎች በሙሉ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽ እውቀት አቅም ግንባታ ነፃ ስልጠና ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቆ እናንተን በጉጉት ይጠብቃል::
ስልጠና ሚሰጥባችው ዘረፎች መካከል፡
1,Web development
2,Interior design
የስልጠና ቦታ
ሲቲ ሞል 6ኛ ፎቅ, መገናኛ ድልድይ,wow burger ያለበት፣Megenagna siti Mall 6th, Addis Ababa, Ethiopia
ለተጨማሪ መረጃ
094-228-0000 092-083-8483
ያሉን ቦታዎች ውስን ናቸው ፈጥነው በአካል መተው ይመዝገቡ።
ለአንድ ቀን ሚቆይ ነፃ ስልጠና!
Register online
https://cloudbridgeacademy.com/registration
Telegram :https://yangx.top/cbmtraininginstitute
TIKVAH-MAGAZINE
በኢትዮጵያ የበርካታ አርሶ አደሮችን ምርት የሚጠብቅ የሰብል ኢንሹራንስ ስራ ጀምሯል። በኢትዮጵያ በ1 ቢሊየን ኢንቨስትመንት ተቋቁሞ የአርሶ አደሩን ምርት ከድርቅ፣ ከጎርፍ፣ ከበረዶ ዝናብ፣ ከተባይ እና ከበሽታ የሚጠብቅ የሰብል ምርት ኢንሹራንስ ስራ መጀመሩን የፑላ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ ዳግማዊ ሃይለ እየሱስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል። "ፑላ" በተሰኘው የግብርና ኢንሹራንስና የቴክኖሎጂ ኩባንያ…
#Update: በአማራ ክልል ጃማ እና ወረኢሉ ሰብላቸው በዋግ ለተጠቃ 51 ሺ አርሶ አደሮች 39 ሚሊዮን ብር ካሳ ተከፈለ
የኦሮሚያ ኢንሹራንስ በሰብል መድህን ፕሮግራም በአማራ ክልል ጃማ እና ወረኢሉ በቢጫ ዋግ ሰብላቸው ለተጠቃ 51 ሺ 132 አነስተኛ አርሶ አደሮች 39.4 ሚሊዮን ብር ካሳ መክፈሉ ተገለፀ።
ክፍያውን በኦሮሚያ ኢንሹራንስ ሲከፈል የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት (ATI)፣ የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) እና ፑላ አድቫይዘርስ (Pula) በጥምረት የሰብል መድህን የካሳ ክፍያ ስነ ስርዓቱን በዛሬው እለት አከናውነዋል።
እነዚህ አርሶ አደሮች በፀደይ ባንክ በኩል በገዙት ማዳበሪያ አማካኝነት የኢንሹራንስ ተጠቃሚ መሆናቸው ሲነገር የኦሮሚያ ኢንሹራንስ የፕሮግራሙን ጨረታ በማሸነፍ ክፍያውን ፈፅሟል። በቀጣይ ሌሎች የሰብል ኢንሹራንስ ኩባንያዎች በዚህ ፕሮግራም ተሳታፊ እንዲሆኑና በ3 ክልሎች 1 ሚሊየን አርሶ አደሮች ተጠቃሚ ለማድረግ እቅድ ተይዟል ተብሏል።

#ጥቆማ
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በመጪው ክረምት የስልጠና መርሃ ግብር የሚሳተፉ ተማሪዎችን ምዝገባ ጀምሯል። በስልጠና መርሃ ግብር የሚሳተፉት የመጀመሪያ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆኑ እና ስልጠናውን በሳምንት ለ4 ቀናት መከታተል የሚችሉ መሆን እንደሚጠበቅባቸው ገልጿል።
በመጪው ክረምት ለተከታታይ ሁለት ወራት ለሚሰጠው ስልጠናም ፍላጎት ያላቸው ታዳጊዎች ከዛሬ ጀምሮ እስከ ግንቦት 07/2016 ባሉት ተከታታይ ቀናት መመዝገብ እንደሚችሉ አስታውቋል። ስልጠናው ከሚያተኩርባቸው መካከል የሰው ሰራሽ አስተውሎት መሰረታውያን፣ ሮቦቲክስ፣ ፕሮግራሚንግ፣ ማሽን ለርኒንግ እና ሌሎችም ይገኙበታል ተብሏል።
በዚህም ስልጠናው መሳለፍ የምትፈልጉ አመልካቾች በሊንክ 1 እንዲሁም በሊንክ 2 ላይ ያሉትን የመመዝገቢያ ቅጾች በመሙላት እንድትመዘገቡ ጥቆማ ቀርቧል።

#እንድታውቁት
የአዲስ አበባ ምግብ መድሃኒት ባለስልጣን በዘርፉ የሚሰጡ የብቃት ማረጋገጥ አገልግሎቶች ከስራ ቀናት በተጨማሪ ቅዳሜ ቀን ለተገልጋዮች አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
በዚህም ዘርፉ የብቃት ማረጋገጥ አገልግሎት ማግኘት የፈለጉ የጤና ባለሙያዎች፣ የምግብና ጤና ነክ ተቋማት ቅዳሜ ጠዋት መጥተው አገልግሎቱን ማግኘት የሚችሉም መሆኑ ተጠቁሟል።