TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
18.9K photos
292 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
加入频道
TIKVAH-MAGAZINE
#ጥቆማ የኢትዮጵያ ኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያ የቢዝነስ ማስፋፊያ ዕቅድ ውድድርን ይፋ አድርጓል። በዚህ ሂደት የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች እስከ 500,000 የሚደርስ ሽልማት የሚያገኙ ሲሆን የስልጠናና የማማከር አገልግሎትም ያገኛሉ ተብሏል። ለማመልከት http://bit.ly/3TzEl1E @tikvahethmagazine
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ኢንተርፐርነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያ የቢዝነስ ማስፋፊያ ዕቅድ ውድድርን መመዝገቢያ ጊዜ ተራዝሟል።

ኢንስቲትዩቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መረጃ መሰረት የ2015ዓ.ም የኢትዮ -ስፐር የቢዝነስ ማስፋፊያ ዕቅድ ውድድር የመጨረሻ ማመልከቻ ቀን ሚያዝያ 22 ቀን 2015ዓ.ም መሆኑን ገልጿል።

በዚህ ሂደት የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች እስከ 500,000 የሚደርስ ሽልማት የሚያገኙ ሲሆን የስልጠናና የማማከር አገልግሎትም ያገኛሉ ተብሏል።

ለማመልከት http://bit.ly/3TzEl1E

@tikvahethmagazine
በሀረሪ ክልል በትራፊክ አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

በሀረሪ ክልል ሶፊ ወረዳ ሐረዌ ቀበሌ በተለምዶው ገንደ ቃሉ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የካቲት 25 / 2015 ዕለት ከለሊቱ 10፡00 ሰዓት አካባቢ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን የክልሉ ፖሊስ ገልጿል።

ከድሬደዋ ወደ ጅግጅጋ ሲጓዝ የነበረው ኮድ 3 የሰሌዳ ቁጥር 30280 ኢቲ የጭነት መኪና በሶፊ ወረዳ ገንደ ቃሉ በሚባል አካባቢ ከሀረር ከተማ መውጫ ላይ ከሚገኝ የፍተሻ ጣቢያ መንገድ ዳር የሚገኙ ከሶስት በላይ የሚሆኑ ትንንሽ ቤቶችን ገጭቶ ባደረሰው አደጋ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የከፍተኛ አደጋ መርማሪ ዋና ሳጂን ረስተም መዚር ገልፀዋል፡፡

ህይወታቸውን ካጡት ዘጠኝ ሠዎች በተጨማሪ  2 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱንም ጠቅሰዋል፡፡ ፖሊስ የአደጋውን መንስኤ  በማጣራት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

መረጃው የሀረሪ ክልል መገናኛ ብዙሃን ነው።

@tikvahethmagazine
5 ደቂቃ . . .
#ምልከታ

ብዙውን ጊዜ "5 ዲቂቃ" የሚለውን ለመጨረሻዎቹ የባከኑ ደቂቃዎች [ 5 ደቂቃ ብቻ ታገሰኝ እንደምንለው] የምንጠቀመው እንጂ ስለመጀመሪያዎቹ 5 ደቂቃዎች ብዙ ግድ አንልም።

የፊተኛው 5 ደቂቃ መዘጋጃ እንጂ ድል ማስቆጠሪያ ወሳኝ ሰዓት ተደርጎም አይወሰድም። ለዚህም የመጀመሪያው 5 ደቂቃዎች ብዙውን ጊዜ በመዘናጋት አንዳንዴም ድልን ቀድሞ በማክበር ይታለፋል።

ብዙ ጊዜ የመጀመሪያ ዕድል በመጀመሪያዎቹ 5 ደቂቃዎች ውስጥ የሚገኝ ነው። ሰዎችን ማሳመን፣ ሀሳባችንን መሸጥ፣ በንግግር ለውጥ መፍጠር ከምንችልባቸው ወሳኝ መንገዶች መካከል የመጀመሪያውን 5 ደቂቃ የተጠቀምንበት ሁኔታ ነው።

አዕምሯችን ላይ የሚመላለሰውን ተደጋጋሚ ሀሳብ በ5 ደቂቃ አስረዱ ብንባል፥ ምን ያህል ፍሬ ነገሩን አስቀምጠን ማስረዳት እንችል ይሆን? ይኽ ነገርን የማሳጠር ጉዳይ ሳይሆን፥ ምን ያህል ሀሳባችንን በግልጽ ማስረዳት እንደምንችል እንዲሁም በጉዳዩ ላይ ያለንን መረዳት የሚያመለክት ነው።

ለምሳሌ፥ ለምታስቡት ሥራ ገንዘብ የሚሰጣችሁ ሰው ድንገት ብታገኙ ሀሳባችሁን በግልጽና በአጭሩ ፍሬ ነገሩን አስረድታችሁ ማሳመን ትችላላችሁን? ወይም ደሞ ይህ ነገር ገብቶኛል ብላችሁ ስለምታስቡት ጉዳይ ለሌላ ሰው በ5 ደቂቃ ውስጥ በግልጽ ቋንቋ የማስረዳት ክህሎት እንዳላችሁ ታምናላችሁ?

በእርግጥ ጉዳዩ ከደቂቃ ጋር ሳይሆን ምን ያህል ተረድቻለው፤ ምን ያህል ዝግጁ ነኝ የሚለውን እንድንፈትን የቀረበ ነው። የተረዳነውን ነገር ሌሎች ሊረዱት በሚችሉበት መንገድ ማቅረብ ትልቅ ችሎታ እንደሆነ ይታመናል። ከዚህም በላይ ራስን፣ አከባቢን ግላዊ/ቡድናዊ አቋምን ለመግለጽ ይረዳል።

በ5 ደቂቃ ስለምን ሊያስረዱ ይችላሉ? https://yangx.top/tikvahforum ላይ ይሞክሩ

@tikvahethmagazine
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈድና ቁጥጥር ባለሥልጣን በጅምር የቀሩ ሕንፃዎችን ጨምሮ፣ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ሕንፃዎችን ቆጠራ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን የግንባታ ፈቃድ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዳዊት ሁንዴሳ (ኢንጂነር) ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

° ተጀምረው ስለቆሙ ሕንፃዎች ምን አሉ?

- ከሁለት ዓመታት በፊት ተጀምረው የቆሙ ሕንፃዎችን መረጃ ሰብስቦ የመያዝ ሥራ የተሰራ ቢሆንም፣ የመረጃ አሰባበሰቡ ላይ ቅሬታዎች በመቅረባቸው የአሁኑ ቆጠራ ተጀምሯል።

- ከG+0 ጀምሮ ሁሉም ዓይነት የሕንፃ ዓይነቶች የጥናቱ አካል ናቸው።

- የመረጃ መሰብሰብ ሥራው በሁሉም ክፍላተ ከተሞች እየተደረገ ይገኛል።

- የመረጃው ትክክለኛነት ሲጣራ፤ ግንባታዎቹ የቆሙት ምክንያት ተለይቶ የመፍትሔ አቅጣጫ ይሰጥበታል፡፡

- ሕንፃው ባለቤት የሌለው ከሆነ በከተማ አስተዳደሩ የበላይ አካል የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጥበት ይሆናል፡፡

- የሕንፃዎችን መረጃ የማጥራቱ ሥራ በ2 ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል።

° በከተማው ውስጥ ያሉ ጠቅላላ ሕንፃዎችን የመመዝገብ ሥራን በተመለከተ ምን አሉ?

- በከተማው ውስጥ ያሉ ጠቅላላ ሕንፃዎችን የመመዝገብ ሥራ በተናጠል መሥራት ተጀምሯል።

- በመጀመሪያው ዙር ባለ 1 ወለልና ከዚያ በላይ ያሉ ሕንፃዎች መረጃ የሚሰበሰብ ሲሆን፣ ይህ ሥራ እንደተጠናቀቀ የG+0 ሕንፃዎችና የመኖሪያ ቤቶች ቆጠራ ይከናወናል፡፡

- ሕንፃዎችን የመመዝገቡ ሥራ ከተጀመረ 2 ሳምንታት የሆነው ሲሆን በጊዜዊነት ጥናቱ በሦስት ወራት ይጠናቀቀል የሚል ዕቅድ መያዙን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

Source : Reporter

@tikvahethmagazine
ዜጎችን በህጋዊ መንገድ ለስራ ወደ ሳውዲ አረቢያ ለማሰማራት የሚሰጠው ስልጠና ዳግም ሊጀምር ነው።

የኢትዮጵያ መንግሥት ከሳውዲ አረቢያ መንግሥት ጋር ባአደረገዉ ስምምነት መሠረት ዜጎችን ወደስራ ሲያሰማረ የቆየ ቢሆንም ሥራው በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ ቆይቷል።

ይህንን የስራ ስምሪት ስምምነት ዳግም በማስቀጠል በሳውዲ አረቢያ ዜጎችን በቤት ሰራተኝነት ሙያ ለማስቀጠር ስልጠና ለመስጠት የአዲስ አበባ ከተማ የስራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ከወረዳ እስከ ማእከል ኮሚቴ በማዋቀር ወደስራ መግባቱን ገልጿል።

ስልጠናዉን ለማከናወንም በሁሉም ክፍለ ከተሞች 10 የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች እንደተዘጋጁ  ምሩቃንን እና ሰልጥነው የተቀመጡትን የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆኑ ዜጎች ቅድሚያ በመስጠት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚሰራ መሆኑን ይህን አስመልክቶ በነበረ ውይይት ላይ ተገልጿል።

ስልጠናው በሳውድ አረቢያ ፍላጎት መሰረት በቤት አያያዝ እና መሰረታዊ ክህሎቶች ቋንቋ፣ ባህል፣ አኗኗር ዘይቤ፣ የስራ ሥነ-ምግባር፣ የህይወት ክህሎት፣ የቅድመ ጉዞ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ እና ስልጠናው #ከመጋቢት_01 ቀን ጀምሮ እንደሚሰጥም ነው የተነገረው።

@tikvahethmagazine
በጂንካ የነጃሺ ኢስላማዊ ማዕከል መሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ

በየደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ የነጃሺ ኢስላማዊ ማዕከል ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሀጂ ኢብራሒም ቱፋ፣ በም/ፕሬዝዳንት ማዕረግ  የደቡብ ክልል ሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ሀላፊ፣ የዞኑ መስተዳድርና የከተማው ከንቲባ በተገኙበት ተቀምጧል።

ተቋሙን ገንብቶ ለመጨረስ 273 ሚሊየን ብር የሚያስፈልግ ሲሆን ማዕከሉ ተገንብቶ ሲያበቃ አጠቃለይ የዲን ት/ቶችን ያስተምራል ተብሎ ይጠበቃል። ነጃሺ ዒስላማዊ ማዕከል በደቡብ ክልል የመጀመሪያው ዒስላማዊ ማዕከል እንደሚሆንም ተሠምቷል። (Bilal Media)

@tikvahethmagazine
#AddisAbeba💧

በአዲስ አበባ ከተማ በቀን ከሚያስፈልገው አንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ውሃ አሁን ላይ እየተመረተ ያለው 725ሺህ ሜትር ኪዩብ ብቻ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታውቋል።

በውሃ አቅርቦት ዙሪያ የሚነሱ ቅሬታዎች መንስኤ የአቅርቦትና ፍላጎት አለመጣጣም ሲሆን፤ የከተማዋ እድገትና መስፋፋት፣ የሪል ስቴቶችና ሆቴሎች መበራከት፣ ውሃን እንደ ግብዓት የሚጠቀሙ ፋብሪካዎች መብዛት በውሃ ስርጭቱ ላይ ትልቅ ተጽዕኖ ፈጥሯል።

በዚህ ምክንያት ውሃ በፈረቃ እንዲሆን መደረጉ የተጠቆመ ሲሆን፤ በፈረቃ ፕሮግራም ከተጀመረ ወዲህም ብዙ ጊዜ ሰዎች ቅሬታ የሚያቀርቡት የፈረቃ ውሃ ሳይደርሳቸው ሲቀር እንደሆነና ይህ በዋናነት በኤሌክትሪክ መቆራረጥና የመስመር ስብራት ሲኖር የሚያጋጥም እንደሆነ ተጠቅሷል።

ችግሩን ለማቃለል የከተማ አስተዳደሩ በዚህ ዓመት በ570 ሚሊዮን ብር በመበጀት 75ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ ለማልማት እየተሠራ እንደሆነ ተገልጿል፤ ይህንን በሚመለከት እስካሁን በተደረጉ ሥራዎች 20 የውሃ ጉድጓዶች መቆፈራቸውን እና ከዚህ ውስጥም አንዱ ሙሉ ለሙሉ ወደ ሥርጭት መግባቱ ተብራርቷል።

ሌሎች ሰባት የሚደርሱ ጉድጓዶች ቁፋሮ ላይ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን፤ እስከ ሰኔ 30 ድረስ በማጠናቀቅ በውሃ እጥረት ምክንያት የሚመጣው ችግር ለመቅረፍ እንደሚሰራ ኢፕድ ዘግቧል።

@tikvahethmagazine
#ኦሮሚያ

በኦሮሚያ ክልል ከየካቲት20 እስከ የካቲት 27 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናቶች በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች፦

- የ10ሰዎች ህይወት አልፏል

- በ19ሰዎች ላይ ከባድ እና በ20 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል

- በንብረት ላይ የደረሰዉ ዉድመት በገንዘብ ሲተመን ከ1ሚሊየን 760ሺ ብር በላይ እንደሚገመት የኦሮሚያ ፖሊስ አሳውቋል።

የአደጋዎቹ ሁኔታ ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር የቀነሰ ሲሆን ፤ ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት፣ ከፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር ፣ምልክቶችን አለማክበር እና የጥንቃቄ ጉድለት እና ሌሎችም የአደጋዎቹ መንስኤ መሆኑን ብስራት ሬዲዮ ዘግቧል፡፡

@tikvahethmagazine
TIKVAH-MAGAZINE
ዜጎችን በህጋዊ መንገድ ለስራ ወደ ሳውዲ አረቢያ ለማሰማራት የሚሰጠው ስልጠና ዳግም ሊጀምር ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ከሳውዲ አረቢያ መንግሥት ጋር ባአደረገዉ ስምምነት መሠረት ዜጎችን ወደስራ ሲያሰማረ የቆየ ቢሆንም ሥራው በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ ቆይቷል። ይህንን የስራ ስምሪት ስምምነት ዳግም በማስቀጠል በሳውዲ አረቢያ ዜጎችን በቤት ሰራተኝነት ሙያ ለማስቀጠር ስልጠና ለመስጠት የአዲስ…
#Update: ኢትዮጵያ 500 ሺህ ሴቶችን ወደ አረብ ሀገር ልትልክ ነው

በኢትዮጵያ በተያዘው ዓመት 500 ሺሕ ሴቶችን ወደ አረብ አገራት በተለይም ወደ ሳውዲ አረቢያ ለሥራ ለመላክ በመንግሥት እቅድ መያዙ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህን ተከትሎም በአማራ ክልል ሁሉም ዞኖች ሰሞኑን ወደ አረብ አገር ሄደው መስራት ለሚፈልጉ ወጣት ሴቶች ስልጠና ሊሰጥ መሆኑ አስትታውቀዋል።

ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑ ሴቶች የቤት አያያዝና ሌሎች አስፈላጊ የሥራ ስልጠናዎች እንደሚሰጡና ስልጠናውም ለ20 ቀን በመንግሥት በነጻ የሚሰጥ መሆኑን ተገልጿል።

ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሴቶች በዩንቨርሲቲም ሆነ በኮሌጅ የተመረቁ፣ ቀደም ሲል ሰልጥነው ያልተሰማሩ እና የመሄድ ፍላጎት ያላቸው፣ የስደት ተመላሽ ሆነው ለመሄድ የሚፈልጉና የወንጀል መዝገብ የሌለባቸው እንዲሁም ስልጠና ወስደው የመሄድ ፍላጎት ላላቸው ነው ተብሏል፡፡

ፍላጎት ላላቸው ሴቶች በኮሌጆች ቅድመ ስልጠና በመስጠት 50 በመቶ ያህሉ መጋቢት 26/2015 በሚጀመረው ጉዞ እንዲሄዱ ከተደረገ በኋላም፤ ቀሪዎቹ ከዚያ ቀጥሎ የሚሄዱ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ሳውዲ አረቢያ ከአፍሪካ የቤት ሠራተኞችን መቅጠር ካቆመች ከሦስት ዓመታት በኋላ በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞችን መቅጠር ልትጀምር መሆኑን መግለጿ ይታወሳል፡፡(አዲስ ማለዳ)

@tikvahethmagazine
ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት በመንገድ ላይ የዘረፋ ወንጀል ተጠርጥረዉ በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በደቡብ ክልል በደራሼ ልዩ ወረዳ ሆልቴ ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ ከፌደራል ፖሊስ  በክህደት ተቋሙን ለቀዋል የተባሉ ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት ተሽከርካሪ በኃይል በማስቆም ፈፅመውታል በተባለ ዘረፋና፤ የዘረፋ ወንጀል ሙከራ ተጠርጥረዉ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን ፖሊስ አስታዉቋል።

ከአርባምንጭ ወደ ኮንሶ የሚወስደዉ አዉራጎዳና ድንጋይ ደርድረዉ በመዝጋት ተሽከርካሪ በማስቆም በተደጋጋሚ በተፈፀሙ ዘረፋዎችና የዘረፋ ሙከራ ወንጀል ሁለቱ የፖሊስ አባላት እጃቸዉ እንዳለበት ከህብረተሰቡ ለልዩ ወረዳዉ ፖሊስ በተሰጠ ጥቆማ መነሻ ተጠርጣሪዎች የካቲት 21 ቀን 2015 ዓ.ም በፖሊስ መያዛቸዉ ነዉ የተነገረዉ።

ፖሊስ በአካባቢያዊ ማስረጃ ተመርኩዞ የያዛቸዉ ሁለቱ የቀድሞ ፖሊስ አባላት ላይ በአፋጣኝ ምርመራ አጣርቶ ለህግ በማቅረብ የቅጣት ዉሳኔ ሊያሰጥ የሚችል ፖሊሳዊ ስራ አየሰራ መሆኑን ከደቡብ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@tikvahethmagazine
50 የሚጠጉ መኪናዎች የተጋጩበት አደጋ . . .

በደቡብ አፍሪካ ኩዋዙሉ-ናታል ግዛት ውስጥ በምትገኘው ኡምህላንጋ ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ አውራ ጎዳና ላይ 50 የሚደርሱ ተሽከርካሪዎች አውራ ጎዳና ላይ ተጋጭተው በሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።

ኤም 41 በሚባለው አውራ ጎዳና ላይ አንድ ባለተሳቢ የጭነት ተሽከርካሪ ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ የቤት መኪናዎች እና የጭነት ተሽከርካሪዎች እየገጨ አልፎ መገልበጡን ነው የዐይን እማኞች የተናገሩት፡፡

እስካሁን በአደጋው ወዲያውኑ የሞተ ሰው ሪፖርቶ አልተደረገም። ሆኖም በርካታ ሰዎች ላይ ከቀላል እሰከ ከባድ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል፡፡ ሰዎችም ወደ ሀኪም ቤት መወሰዳቸውን ታውቋል። (ሮይተርስ፣ ቪኦኤ)

@tikvahethmagazine
TIKVAH-MAGAZINE
Photo
#Update

ለመቄዶኒያ የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል የሚደረገው የገንዘብ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር በመካሔድ ላይ ይገኛል።

መቄዶንያ የአረጋውያን እና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል በኮሜዲያን እሸቱ መለሰ አስተባባሪነት የካቲት 26 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ የ1 ሚሊየን ዶላር የማሰባሰብ መርሐ ግብር  ዛሬም በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

የገቢ ማሰባሰቢያው ዋና ዓላማ ማዕከሉ በመገንባት ላይ ለሚገኘው ባለ 12 ወለል ሕንጻ የ1ሚሊየን ዶላር መሰብሰብና በርና መስኮቱ መግጠም እንዲሁም ሕንጻው እስኪጠናቀቅ ድረስ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ታስቦ የተዘጋጀ መርሐ ግብር መሆኑ ተነግሯል፡፡

የአንድ መስኮት ዋጋ 80 ሺ ብር እንዲሁም የአንድ በር ዋጋ 106 ሺ ብር ሲሆን በአጠቃላይ 749 መስኮቶች እና 898 በሮች የሚያስፈልጉ መሆኑን ተገልጿል፡፡ ሕንጻው ከ2.3 ቢሊየን ብር በላይ የሚፈጅ  ዘመናዊ ሆስፒታልና የአረጋውያን መኖሪያ ሕንጻ ሲሆን ከተጀመረ 4 ዓመት ባልሞላው ጊዜ ውስጥ ግንባታው 70% ተጠናቋል።

በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አገልግሎቱን ለመደገፍ የሚከተሉትን አድራሻዎች በመጠቀም እርዳታ ማድረግ እንደሚችሉ ከአዘጋጆቹ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት:- 7979
•  ጎ ፈንድ ሚ (GoFundMe) - Mekedonia Charity Homes:  https://www.gofundme.com/f/Mekedonia-Charity-help-build-home-for-the-homeless
•  Cash App: 240-840-6256
•  Zelle: 240-840-6256
•  WEGEN FUND : https://www.wegenfund.com/causes/

መቄዶንያ በማዕከሉ ላሉ ሰዎች ሁሉንም መሰረታዊ አገልግሎቶች ማለትም ምግብ፣ አልባሳት፣ መጠለያ፣ ንፅህና መጠበቂያ፣ ህክምና፣ ትምህርት እና ሌሎች መሰል አገልግሎቶችን በመስጠት የአረጋዊያንን እና የአእምሮ እክል ያለባቸውን ህይወት በመርዳት ላይ ያተኮረ ድርጅት እንደሆነ ይታወቃል።

@tikvahethmagazine
#ነፃ_የትምህርት_ዕድል

LG-KOICA Hope የቴክኒክና ሞያ ኮሌጅ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በግል ከፍለው መማር ለሚቸገሩና የመግቢያ መስፈርቱን ለሚያሟሉ ተማሪዎች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ተማሪዎችን በነጻ ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።

ኮሌጁ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በላከው መልዕክት በዚህ ዙር እስከ 150 ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር መዘጋጀቱን ገልጾ የሀገር ዉስጥና የዉጭ ሀገር የሥራ ዕድል አማራጮችም እንዳሉት ጠቅሷል።

ከዚህም በተጨማሪ መስፈርቱን አሟልተው ለሚመረጡ ተማሪዎች በነጻ ማስተማር ብቻ ሳይሆን የምግብ፣ የትራንስፖርት እና ሌሎች ወጪዎችን እንደሚሸፍን ገልጿል።

ለማመልከት የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፦

1. መንግስት ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ያስቀመጠዉን የቴክኒክና ሙያ የመግቢያ መስፈርት የሚያሟሉ፤

2. የኮሌጁን መግቢያ ፈተና  ማለፍ የሚችሉ፤

3. ከፍለው ለመማር  የማይችሉ ይኽንን የሚገልጽ ማስረጃ ከሚኖሩበት ቀበሌ ካመጡ ቅድሚያ ያገኛሉ።

የትምህርት መስኮች፦

#Electronics: Electrical Electronics equipment servicing management[ Level III & IV]

#IT : Hardware and network servicing [Level III & IV]

#የማመልከቻ_ጊዜ፡ ከየካቲት 24 - መጋቢት 22 ባሉት 21 ተከታታይ የስራ ቀናት

#አድራሻ: ሰሚት ኮንዶሚኒየም 3ኛ በር ከጠዋቱ 2፡00 - 1፡00 ሰአት

#ስልክ:  011-6-67-75-64 / 011-6-66-18-29

@tikvahethmagazine
ኢንስታግራም ያስተዋወቀውና የቴሌግራም ቻናልን የሚመስለው አዲሱ አገልግሎት።

ኢንስታግራም፣ ፌስቡክን እና ዋትስአፕን የሚያስተዳድረው ሜታ ቴሌግራም ላይ የሚገኘውን የቻናል አገልግሎት የሚመስል ቅርጽ ያለው አገልግሎት በኢንስታግራም መተግበሪያው ሊጀምር መሆኑን አስታውቋል።

ሜታ በኢንስታግራም መተግሪያው ያስተዋወቀው ይህ አዲስ አገልግሎት በአብዛኛው የቴሌግራም ቻናልን የሚመስል ሲሆን አሁን ላይ በሙከራ ደረጃ እየተሰራበት ይገኛል። ይህንን መሰሉን አገልግሎት በቀጣይ ሜታ በሚሴንጀርና በፌስቡክ መተግበሪያውም ለመሞከር ማቀዱ ተገልጿል።

ኢንስታግራም በይበልጥ ፎቶና ቪዲዮ ለማሰራጨት የምንጠቀምበት የማኅበራዊ ትስስር መድረክ ሲሆን በዓለም ደረጃ 1.2 ቢሊየን ወራዊ ንቁ ተሳታፊዎች (monthly active users) አሉት። በኢትዮጵያም ወደ 700 ሺ የሚጠጉ ተጠቃሚዎች እንዳሉት የተቋሙ መረጃዎች ያሳያሉ።

@tikvahethmagazine
አንጋፋው የሥነ ጽሑፍ መምህርና ሐያሲ ተባባሪ ፕሮፌሰር ዘሪሁን አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ተባባሪ ፕሮፌሰር ዘሪሁን÷ ‹‹የሥነ ጽሑፍ መሰረታውያን›› እና ‹‹ከበዓሉ ግርማ እስከ አዳም ረታ›› የሚሉትን ለሥነ ጽሑፍ ትምህርት አጋዥ መጻሕፍት ጨምሮ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎችን አሳትመዋል፡፡

ምሁሩ ሕይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ ድረስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሥነ ጽሑፍ መምህርነት እና አማካሪነት እያገለገሉ እንደነበር የሙያ ባልደረቦቻቸው ተናግረዋል፡፡

በቅርቡም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከሰውመሆን ፊልሞች ጋር በመተባበር ለሚሰራው "ፍቅር እስከ መቃብር " ባለ 48 ክፍል የቴሌቪዥን ድራማ ሙያዊ ሀሳባቸውን አካፍለው ነበር። (FBC)

@tikvahethmagazine
#Bonga 🛬

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቦንጋ ከተማ ለሚገነባው ቀላል የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ቀዳማዊት እመቤተ ዝናሽ ታያቸው እና የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በተገኙበት የመሰረት ድንጋይ በዛሬው ዕለት ተቀምጧል።

@tikvahethmagazine