#መቄዶንያ
ልክ መቄዶንያ በር ላይ ስትደርሱ በፈገግታ የሚቀበሏችሁ አዛውንቶች በሰላምታቸው ያጠግቧችኋል ትንሽ ገባ ስትሉ ደግሞ የሰውን ፍቅር የሚፈልጉ አይን አይናችሁን የሚያዩ የአዕምሮ ህመምተኞች ትኩረታችሁን ይስቡታል።
በመቄዶንያ የሚያስደንቅ መልካምነት ገዝፎ ይታያል ሁሉም የአቅሙን ይሰራል በማእከሉ ገብተው ህይወታቸው የተቀየረ ሰዎች ጭምር በቻሉት አቅም ተቋሙን ለማገዝ በትጋት ሲንቀሳቀሱ ትመለከታላችሁ።
ሌላኛው የመቄዶንያ ገጽታ የስዕል ተሰጥኦ ያላቸው እራሳቸውን የሚያበቁበት ስፍራ፤ የቆረቡ እናቶች ብቻ ተሰብስበው የሚኖሩበት፤ ጥጥ የሚፈትሉ የተፈተለውን የሚሸምኑበት ስፍራ፤ ለተለያዩ ፕሮግራሞች ምግብ የሚሰራበት ስፍራ እና ሌሎችም በማዕከሉ ያሉ የሚጠቀሙበት ስፍራ መኖሩ ይበልጥ ማዕከሉን አስውበውታል።
ሜቄዶኒያ ያስጀመረው ባለ 12 ወለል ሕንፃ ከሁለት ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ብር በላይ የሚፈጅ ሲሆን፤ በርና መስኮት ለመግጠም 151 ሚሊየን ብር ያስፈልግ ነበር።
ታዲያ ይህ ማዕከል ለሚያሰራው ህንጻ የሚሆን በር እና መስኮት ለማስገጠም ይረዳው ዘንድ በዶንኪ ትዩብ አማካኝነት እሁድ ከቀኑ 9 ሰዓት ተጀምሮ ማክሰኞ ለሊት 6:35 በተጠናቀቀው የቀጥታ ስርጭት የገቢ ማሰባሰቢያ የታሰበው እቅድ መሳካቱ ተነግሯል።
በመጨረሻም የክብር ዶክተር ቢንያም የተናገረው ንግግር የብዙዎችን ቀልብ ስቧል፦
"ቀኑን ሙሉ ለሚተኛ ሰው ማጨብጨብ አይከብዳችሁም? ለእኔ ማልቀስ ነው ያለባችሁ። ትጋት ከእሸቱ መማር አለብን። ስለራሴ ድክመት ነው ማውራት ያለብኝ። እንደ መቄዶንያ እኛ ዜሮ ነን። ከዜሮ በታች ታውቃላችሁ? የሞት ፍርድ የሚገባው ሰው ማለት እኔ ነኝ።"
ይሁንና የህንጻ ስራውን ለማጠናቀቅ አሁንም ተጨማሪ ገንዘብ ስለሚያስፈልግ ሁሉም የአቅሙን ያክል ጥረት እንዲያደርግና ጎዳና ላየ ያሉ አረጋውያንን እንዲታደግ ጥሪ ቀርቧል።
@tikvahethmagazine

የኢትዮጵያ አየርመንገድ የሴቶች ቀንን በማስመልከት ሙሉ በሙሉ በሴቶች የሚመራ በረራ አደረገ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሴቶች ቀንን በማስመልከት ለ7ኛ ጊዜ ሙሉ በሙሉ በሴቶች የሚመራ በረራ ወደ ዛንዚባር አድርጓል። በረራው የአየርመንገዱ የመጀመሪያ ሴት አብራሪ በሆኑት ካፒቴን አምሳል ጓሉ የተመራ ነው።
አየርመንገዱ ወደ ዛንዚባር የሚያደረገውን በረራ ከዋና አብራሪዋ ጀምሮ ረዳት አብራሪ፣ የበረራ አስተናጋጆች እና ቴክኒሽያኖች ሴቶች ናቸው።
ከዚህም ባለፈ የአየር ትራፊክ፣ የበረራ ደህነነትና የጭነት ቁጥጥር፣ የበረራ መለኪያ እስከ አውሮፕላኑ መነሻ ድረስ ሙሉ በሙሉ በሴቶች የተመራ ነው። (EBC)

ኢትዮ ቴሌኮም በመዲናዋ በፅዳት ስራ ለተሰማሩ 353 ሴቶች ዘመናዊ የስልክ ቀፎ በስጦታ መልክ አበረከተ።
ኢትዮ ቴሌኮም የዘንድሮውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ በአዲስ አበባ ከተማ በጽዳት ሥራ ላይ ለተሰማሩ እና የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ከ122 ወረዳዎች የተውጣጡ 353 ሴት የጽዳት ሠራተኞች ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ዘመናዊ ስልኮችን ለእያንዳንዳቸው በስጦታ አበርክቷል።
ሽልማቱ ሴቶች የዲጂታል ቴክኖሎጂና የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል እንዲሁም የዲጂታል ኢኮኖሚ ተካታችነትንና እኩልነትን ለማረጋገጥ ያለመ ነው ተብሏል፡፡
በተጨማሪም ኩባንያው የ2015 ዓ.ም ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ እስከ 25% ቅናሽ የተደረገበት ለ2 ቀናት የሚቆይ የሴቶች ጥቅል ማዘጋጀቱን ጠቅሶ ጥቅሉን ከተጨማሪ 10% ስጦታ ጋር በቴሌብር እንዲሁም በማይ ኢትዮቴል እና በ*999# ማቅረቡን ገልጿል።

የቅዱስ ጴጥሮስ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለህጻናት የነርቭ ቀዶ ህክምና የሚውል ማሽን ተበርተለት።
የቅዱስ ጴጥሮስ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እስከ መቶ ሺህ ዶላር የሚገመት ለህጻናት የነርቭ ቀዶ ህክምና አገልግሎት የሚውል ኢንዶሰኮፒክ ሰርድ ቨንትሪከሎስቶሚ (ኢቲቪ) ማሽን ከሪች አናዘር ፋውንዴሽን ተበርክቶለታል፡፡
ማሽኑ ለህጻናት የነርቭ ቀዶ ህክምና በተለይም የነርቭ ዘንግ ክፍተት ህመም (ሃይድሮሴፋለስ) ላለባቸው ህጻናት በእጅጉ አጋዥ እንደሆነ የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስፈጻም ዶ/ር መታሰቢያ መስፍን ገልጸዋል።
የሪች አናዘር ፋውንዴሽን ካንትሪ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ያቆብ ሰማን በበኩላቸው ለህፃናት የነርቭ ቀዶ ህክምና አገልግሎት የሚውል ማሽን እንደ ሀገር #በዘውዲቱና #ጎንደር ሆስፒታሎች ብቻ ይገኝ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ደግሞ የቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል በሶስተኝነት ተረክቦ አገልግሎት ለመስጠት በሂደት ላይ ይገኛል ብለወላል፡፡
የሆስፒታሉ የነርቭ ቀዶ ህክምና ክፍል ኃላፊ ዶ/ር አብዲ ኤሪሜሎ ማሽኑ ለህጻናት የነርቭ ቀዶ ህክምና በተለይም የነርቭ ዘንግ ክፍተት ህመም (ሃይድሮሴፋለስ) ላለባቸው ህጻናት በእጅጉ አጋዥ እንደሆነ እና ለህጻናቱ ከጭንቅላት ወደ ሆድ በሚዘረጋ ቱቦ ይደረግ የነበረውን ህክምና በማስቀረት የተሻለ ህክምና እንዲያገኙ የሚያስችል ማሽን መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ኃላፊው አክለውም የህክምና ማሽኑ ለህጻናቱ የተሻለ ህክምና ከመስጠቱ ባሻገር ይህንን ህክምና ለማግኘት የነበረውን ብዙ ወረፋ በማስቀረት እና የአስታማሚ ወላጆችን እንግልት በመቀነስ እንዲሁም በህመሙ ምክንያት ህጻናቱ ላይ የሚደርሱትን ውስብስብ ችግሮችን የሚቀርፍ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ጤናማ አመጋገብ
Tikvah Maga3
#ጤናማ_አመጋገብ
የጤናማ አመጋገብን አስመልክቶ ዶ/ር እሴት ጌታቸው ከእንግዳችን ሀና ሳምሶን በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የስነ ምግብ ጤና ባለሙያ ጋር ቆይታ ማድረጓ ይታወሳል።
በውይይቱም በጤናማ አመጋገብ ዙሪያ ኩላሊታችንን ለመጠበቅ ምን አይነት ምግብ መመገብ ይኖርብናል? እና እንዴት አይነት አኗኗርስ መኖር አለብን? የሚሉት እንዲሁም ስለተጓዳኝ ህመሞችና ሌሎች ጉዳዮችን አብራርተዋል።
በተከታታይ ሳምንታት ከኩላሊት ጤና ጋር የሚደገው ግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት ፕሮግራማችን ዛሬ ምሽት 1:00 ሰዓት ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ይቀጥላል።
ይጠብቁን!

በመዲናዋ ስለታገደው የባጃጅ አገልግሎትና ስለተፈጠሩ ጉዳዮች፦
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከነገ ጀምሮ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት መከልከሉን የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል። ቢሮው ለመከልከሉ በምክንያትነት ያስቀመጠው "የአሰራር ማሻሻያ ስራዎችን በማከናወን ላይ ስለምገኝ" የሚል ነው።
ከዚህ አስቀድሞ በትላንትናው ዕለት በከተማዋ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ጋርመንት አካባቢ በባጃጅ አሽከርካሪዎችና በጸጥታ ኃይሎች መካከል ውጥረት ተፈጥሮ ነበር።
ከአከባቢው በደረሱን መረጃዎች መሰረት ከዚህ ቀደም ለሳምንታት ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪዎች (ባጃጅ) ከሀይሌ ጋርመንት አደባባይ እስከ ናሆም አደባባይ ድረስ ተከልክለው ውስጥ ለውስጥ ሲሰሩ ቆይተዋል። ሆኖም ብዙም ሳይቆይ ወደ መስመር ተመልሰዋል።
በትላንትናው ዕለት የተፈጠረውን ጉዳይ አስመልክቶ ተበድለናል ያሉ የባጃጅ አሽከርካሪዎች ለተለያዩ ሚዲያዎች (ለባላገሩ እና ለአሸም ቴሌቪዥን ጣቢያዎች) ባቀረቡት ቅሬታ "የምንተዳደርበት ባጃጅ በፀጥታ ሐይሎች እየተወሰደብን ነው፤ በላያችን ላይም ሌላ ማኅበር እየተደራጀ ነው" ሲሉ ይገልጻሉ።
ትላንት በተፈጠረው ውጥረት የጸጥታ ኃይሎች ተኩስ ሲተኩሱ እንደነበር ከስፍራው የወጡ የቪዲዮ ማስረጃዎች ያመለክታሉ። የተጎዱ ሰዎች መኖራቸውንም ከቅሬታ አቅራቢዎቹ መስማት ተችሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ዛሬ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ በመዲናዋ ከነገ ጀምሮ ሙሉ ለሙሉ የባጃጅ ትራንስፖርት እንቅስቃሴን አግዷል። ይህ ውሳኔ ላልተወሰነ ጊዜ በሚል የተቀመጠ ሲሆን ለህብረተሰቡ ቀድሞ የተገለጸ ነገር የለም።
በጉዳዩ ላይ የባጃጅ ባለንብረቶች፣ አሽከርካሪዎችና የባጃጅ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ምን ትላላችሁ?
በሀሳብ መስጫው ወይም በ @tikvahmagbot ላይ ይላኩልን

ህብረት ባንክ የሞባይል መተግበሪያውን አሻሻለ
የሞባይል ባንኪንግ ስርዓትን ከ15 ዓመታት በፊት ያስጀመረው ሕብረት ባንክ ይህንኑ መተግበሪያውን እንዳሻሻለ አስታውቋል።
ሁሉንም የባንክ አገልግሎቶች ያካተተው አዲሱ መተግበሪያ ከመደበኛ አገልግሎቶች በተጨማሪ የትምህርት ቤት ክፍያን እና የመብራት እና የውሀ ክፍያዎችን ለመክፈል እንዲሁም ድርጅቶች የሰራተኞቻቸውን ወርሀዊ ክፍያ መፈፀም እንደሚያስችለው ተጠቁሟል።
ይህው መተግበሪያ ሙሉ ለሙሉ በሀገር ውስጥ ባሉ በራሱ ባለሙያዎች ማሰራቱን የገለጸው ባንኩ ይህንን በማድረጉ 150 ሺህ እስከ 250 ሺህ ዶላር የሚደርስ ወጪን ማስቀረት እንደቻለ አስታውቋል።
ሕብረት ባንክ ያሻሻለውን የ*811# USSD Code እና የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ሁለት አንኳር ነገሮችን መያዙ የተገለፀ ሲሆን ሁሉንም አገልግሎቶች መያዙ እና በውስጥ አቅም መሰራቱ ለየት ያደርገዋል ተብሏል።
በአሁኑ ሰዓት 9 መቶ ሺህ ገደማ ደንበኞች የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች መሆናቸውን ያስታወቀው ባንኩ ይህም ከATM ተጠቃሚዎች አንፃር ብልጫ እያሳየ እንደሚገኝ ተነግሯል።

የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ነጭ ስኳር ማምረት ጀመረ
ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ የካቲት በትላንትናው ዕለት ከምሽቱ 1 ስዓት ጀምሮ ነጭ ስኳር ማምረት መጀመሩን አሳውቋል።
ነገር ግን ፋብሪካው በዘላቂነት ስራውን እንዲያከናውን የጣና በለስ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ሳብሰቴን መስመር ስራ ማቆም እንቅፋት ሊሆን ሰለሚችል የሚመለከተው አካል ጉዳዩን በመከታተል አፋጣኝ መልስ ሊሰጠው እንደሚገባ ድርጅቱ ጠቅሟል፡፡

2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር የህዝብና የሀገር ሀብት ለብክነት መዳረጉ ተገለጸ
የብሔራዊና የክልል የጸረ-ሙስና ኮሚቴ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ 759 ጥቆማዎች የደረሱት ሲሆን በ175 ጥቆማዎች ላይ ምርመራ በማድረግ በ81ዱ ላይ የክስ መዝገብ ማደራጀቱን እና የክስ መዝገብ በተደራጀባቸው መዝገቦች ውስጥም 640 ተጠርጣሪዎች መኖራቸውን አሳውቋል።
እስከ አሁን በተደረጉ የማጣራት ሥራዎችም 2 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ግምት ባላቸው የመንግሥትና የሕዝብ ኃብት ላይ ጉዳት መድረሱ የተረጋገጠ ሲሆን በሌላ በኩል 25,885 ካ.ሜ በምርመራ የሙስና ወንጀል ተፈፅሞ መገኘቱን ተጠቁሟል።
ይህ የተባለው የብሔራዊና የክልል የጸረ-ሙስና ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና አባላት የጋራ የአፈጻጸም ግምገማ በሚካሄድበት መድረክ ነው።

የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ በአዲስ አበባ ከተማ ባለ 65 ወለል ህንፃ ሊያስገነባ ነው።
የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ በትላንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ ባለ 65 ወለል ህንፃ ዋና መስሪያ ቤት ለመገንባት ከኳታሩ Engineering Consulting Group(ECG) ጋር ስምምነት ፈፅሟል።
በተጨማሪም ፋይናንሻል ዲስትሪክት የተሰኘ ባለ 47 ፎቅ ህንፃ በአዲስ አበባ ለመገንባትም እንቅስቃሴ መጀመሩንም አስታውሷል።
ባንኩ 18ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በማክበር ላይ ሲሆን 699 ቅርንጫፎችን በመክፈት ከ10.4 ሚሊየን በላይ ደንበኞችን አፍርቷል። የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑ 112 ቢሊየን ብር፤ አጠቃላይ ሀብቱ ደግሞ 137 ቢሊየን ብር መሆኑ ተጠቅሷል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ያስመረቀው ዋና መስሪያቤቱ ባለ 48 ወለል ያለውና 198 ሜትር ርዝመት አለው። አቢሲኒያ ባንክ በቅርቡ ሜክሲኮ አደባባይ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ጎን ላይ ከፍታው 270 ሜትር የሆነ ባለ 60 ወለል ህንጻ ለመንባት ውል መግባቱ ይታወሳል። አሁን ላይ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ለመገንባት ያቀደው ባለ 65 ወለል ህንጻ በመዲናዋ ትልቁ ህንጻ እንዲሆን ያስችለዋል።