TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
18.9K photos
292 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
加入频道
5 ደቂቃ . . .
#ምልከታ

ብዙውን ጊዜ "5 ዲቂቃ" የሚለውን ለመጨረሻዎቹ የባከኑ ደቂቃዎች [ 5 ደቂቃ ብቻ ታገሰኝ እንደምንለው] የምንጠቀመው እንጂ ስለመጀመሪያዎቹ 5 ደቂቃዎች ብዙ ግድ አንልም።

የፊተኛው 5 ደቂቃ መዘጋጃ እንጂ ድል ማስቆጠሪያ ወሳኝ ሰዓት ተደርጎም አይወሰድም። ለዚህም የመጀመሪያው 5 ደቂቃዎች ብዙውን ጊዜ በመዘናጋት አንዳንዴም ድልን ቀድሞ በማክበር ይታለፋል።

ብዙ ጊዜ የመጀመሪያ ዕድል በመጀመሪያዎቹ 5 ደቂቃዎች ውስጥ የሚገኝ ነው። ሰዎችን ማሳመን፣ ሀሳባችንን መሸጥ፣ በንግግር ለውጥ መፍጠር ከምንችልባቸው ወሳኝ መንገዶች መካከል የመጀመሪያውን 5 ደቂቃ የተጠቀምንበት ሁኔታ ነው።

አዕምሯችን ላይ የሚመላለሰውን ተደጋጋሚ ሀሳብ በ5 ደቂቃ አስረዱ ብንባል፥ ምን ያህል ፍሬ ነገሩን አስቀምጠን ማስረዳት እንችል ይሆን? ይኽ ነገርን የማሳጠር ጉዳይ ሳይሆን፥ ምን ያህል ሀሳባችንን በግልጽ ማስረዳት እንደምንችል እንዲሁም በጉዳዩ ላይ ያለንን መረዳት የሚያመለክት ነው።

ለምሳሌ፥ ለምታስቡት ሥራ ገንዘብ የሚሰጣችሁ ሰው ድንገት ብታገኙ ሀሳባችሁን በግልጽና በአጭሩ ፍሬ ነገሩን አስረድታችሁ ማሳመን ትችላላችሁን? ወይም ደሞ ይህ ነገር ገብቶኛል ብላችሁ ስለምታስቡት ጉዳይ ለሌላ ሰው በ5 ደቂቃ ውስጥ በግልጽ ቋንቋ የማስረዳት ክህሎት እንዳላችሁ ታምናላችሁ?

በእርግጥ ጉዳዩ ከደቂቃ ጋር ሳይሆን ምን ያህል ተረድቻለው፤ ምን ያህል ዝግጁ ነኝ የሚለውን እንድንፈትን የቀረበ ነው። የተረዳነውን ነገር ሌሎች ሊረዱት በሚችሉበት መንገድ ማቅረብ ትልቅ ችሎታ እንደሆነ ይታመናል። ከዚህም በላይ ራስን፣ አከባቢን ግላዊ/ቡድናዊ አቋምን ለመግለጽ ይረዳል።

በ5 ደቂቃ ስለምን ሊያስረዱ ይችላሉ? https://yangx.top/tikvahforum ላይ ይሞክሩ

@tikvahethmagazine