TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.7K photos
1.48K videos
5 files
3.41K links
加入频道
TIKVAH-SPORT
Photo
ኦሊ ጎነር ሶልሻየር ቀዳሚው አሰልጣኝ ሆኗል !

የቀያይ ሴጣኖቹ ዋና አሰልጣኝ ኦሊ ጎነር ሶልሻየር ማንችስተር ሲቲን በመጀመሪያዎቹ ሶስት #ከሜዳቸው ውጪ ባደረጓቸው ጨዋታዎች በማሸነፍ በክለቡ ታሪክ የመጀመሪያው አሰልጣኝ መሆኑ ይፋ ሆኗል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
አሰልጣኝ ኦሊ ጎነር ሶልሻየር !

የ ቀያይ ሴጣኖቹ አለቃ ኦሊ ጎነር ሶልሻየር በ ዛሬው ዕለት 100ኛ ጨዋታውን በ #ሊጉ ማድረግ ችሏል ።

ከዚህም ውስጥ ከ ግማሽ በላይ በሚሆኑት ሀምሳ ሶስት ጨዋታዎች ድል ሲቀናው አስራ ዘጠኝ ጨዋታዎች ላይ ሽንፈት አስተናግደዋል ።

አሰልጣኝ ኦሊ ጎነር ሶልሻየር በዛሬው ዕለት ማሸነፋቸውን ተከትሎ #ከሜዳቸው ውጪ ሀያ ስምንት ጨዋታዎችን ባለ #መሸነፍ አዲስ ታሪክ ፅፈዋል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የ ፒኤስጂ ደካማ ጉዞ !

የፈረንሳይ ሊግን እየመሩ የሚገኙት ፒኤስጂዎች #ከሜዳቸው ውጪ በተከታታይ ጨዋታዎች ውጤት እየራቃቸው ይገኛሉ ።

ፒኤስጂዎች ባለፉት አራት ከሜዳቸው ውጪ ባደረጓቸው ጨዋታዎች ላይ በሁሉም ሽንፈትን አስተናግደዋል ።

ፒኤስጂ የፈረንሳይ ሊግን ከተከታያቸው ማርሴ በአስራ ሶስት ነጥቦች ርቀው እየመሩ ይገኛሉ ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#Barcelona 🇪🇸

ትላንትና ምሽት ማዮርካን በመርታት የላሊጋውን መሪነት #በጊዜያዊነት የተረከቡት ባርሴሎናዎች ተከታታይ ድላቸውን ማስመዝገብ ችለዋል።

ፖላንዳዊው አጥቂ ሮበርት ሊዋንዶውስኪ በሰባት የላሊጋው ጨዋታዎች ዘጠኝ ግቦችን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የዣቪው ስብስብ አስራ ስምንት ተከታታይ ጨዋታዎችን #ከሜዳቸው ውጪ ባለመሸነፍ አዲስ ሪከርድ ሰብረዋል።

ዣቪ ሀርናንዴዝ ሀላፊነቱን ከቀድሞ አሰልጣኝ ሮናልድ ኩማን ከተረከበ በኋላ ከካምፕ ኑ ውጪ ባደረጋቸው የሊጉ ጨዋታዎች አልተሸነፈም።

ግብ ጠባቂው ማርክ አንድሬ ቴር ስቴገን ላለፉት 534 ደቂቃዎች ግብ አልተቆጠረበትም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኳታር ወይስ ኢኳዶር ?

የኳታሩ የዓለም ዋንጫ በይፋ ዛሬ መካሄዱን ሲጀምር አዘጋጇ ሀገር ኳታር የደቡብ አሜሪካዋን ኢኳዶር የምታስተናግድ ይሆናል።

√ አዘጋጇ ኳታር በዓለም ዋንጫው የመጀመሪያ ተሳትፏዋን የምታደርግ ሲሆን ባለፉት ዓመታት የተሻለ ውጤቶችን በእግር ኳሱ እያስመዘገበች ትገኛለች።

√ ኳታር እ.ኤ.አ በ 2019 የኳታር እስያ ዋንጫ ሲያሸንፉ በ 2021 የአረብ ዋንጫ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችለዋል።

√ ለኢኳዶር ፈታኝ ጨዋታ እንደሚሆን ሲጠበቅ በወንዶች የዓለም ዋንጫ ታሪክ አዘጋጅ ሀገር የመክፈቻ ጨዋታ #ተሸንፎ አያውቅም።

√ ኢኳዶር ከስምንት ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ዓለም ዋንጫው ሲመለሱ ከምድባቸው ማለፍ የቻሉበት የ 2006 የዓለም ዋንጫ በበጎ መልኩ ይነሳላቸዋል።

√ ኢኳዶር በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ላይ ከጋና እና አሜሪካ በመቀጠል #ሶስተኛው ወጣት ስብስብ ያላት ሀገር ነች።

√ ኢኳዶር ለዓለም ዋንጫው ለማለፍ በማጣርያው #ከሜዳቸው_ውጪ ባደረጉት #ዘጠኝ ጨዋታዎች #ስምንት ነጥቦችን ብቻ ሰብስበዋል።

√ ኳታር ተከታታይ አምስት የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎችን ከ ኒካራጉኣ ፣ አልባኒያ ፣ ጓቲማላ ፣ ሁንዱራስ እና ፓናማ አድርጋ ሁሉንም በመርታት ለዛሬው ጨዋታ ተዘጋጅታለች።

√ አምበሉ እና የፊት መስመር ተጫዋቹ ሀሰን አልሀይዱስ እንዲሁም አል ሙአዝ አሊ በኳታር በኩል የሚጠበቁ ተጫዋቾች ናቸው።

√ ኢኳዶር በብራይተኖቹ ኢስቱፒናን እና ሞይሰስ ካይሴዶ ተስፋ በመጣል ቡድኗን አዋቅራለች።

√ ሁለቱ ሀገራት ከአራት ዓመታት በፊት ባደረጉት ጨዋታ ኳታር 4ለ3 በሆነ ውጤት በዘጠኝ ተጫዋቾች ጨዋታውን ለመጨረስ የተገደደችውን ኢኳዶር በሜዳዋ መርታት ችላለች።

√ ጣልያናዊው የመሐል ዳኛ ዳንኤል ኦርሳቶ ይህንን ተጠባቂ ጨዋታ በመሐል ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል።

@tikvahethsport
ቼልሲ ነጥብ ጥሏል !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ከኖቲንግሃም ፎርስት ያደረገውን የሊግ ጨዋታ አንድ ለ አንድ በሆነ አቻ ውጤት በማጠናቀቅ ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል።

- የቼልሲን ግብ ራሂም ስተርሊንግ ሲያስቆጥር የኖቲንግሀም ፎረስትን የአቻነት ግብ ሰርጅ ኦሪየር ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

- ራሂም ስተርሊንግ ከሜዳ ውጭ ያስቆጠራቸውን ግቦች ወደ ሀምሳ ከፍ ማድረግ ችሏል።

- ቼልሲዎች #ከሜዳቸው_ውጪ ባለፉት አራት ጨዋታዎች ማግኘት ከሚገባቸው አስራ ሁለት ነጥብ ያሳኩት #ሁለቱን ብቻ ነው።

- በግርሀም ፖተር የሚሩት ቼልሲዎቹ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ከሊጉ መሪ አርሰናል በአስራ ስምንት ነጥብ ርቀው በሀያ አምስት ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዘዋል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሀ ግብር ቼልሲ ከ ማንችስተር ሲቲ ከባድ ግጥሚያ የሚጠብቃቸው ሲሆን ኖቲንግሃም ፎረስት በበኩላቸው ከ ሳውዛምፕተን የሚገናኙ ይሆናል ።

- በቀጣይ የሊጉ #ተጠባቂ መርሐ ግብር ቼልሲ ከ ማንችስተር ሲቲ እንዲሁም ኖቲንግሀም ፎረስት ከ ሳውዝሀምፕተን የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe