TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.8K photos
1.48K videos
5 files
3.42K links
加入频道
ቪንሰስ የዘረኝነት ጥቃት ከደረሰባቸው ሜዳውን እንደሚለቁ ገለጸ !

የሪያል ማድሪዱ የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር የዘረኝነት ጥቃቶች የሚደርሱባቸው ከሆነ ከቡድን አጋሮቹ ጋር ሜዳውን ለቀው ለመውጣት ማሰባቸውን ገልጿል።

ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር ባለፈው አመት በተቃራኒ ቡድን ደጋፊዎች ተደጋጋሚ የዘረኝነት ጥቃቶች ሲደርሱበት ነበር።

በዚህ ጉዳይ ከክለቡ ጋር መነጋገሩን የገለፀው ቪንሰስ ጁኒየር ሌሎች ተጨዋቾችም መነጋገራቸውን እና ዘረኝነት ከተፈፀመ ሜዳውን ለመልቀቅ መወሰናቸውን አስረድቷል።

በአሁን ሰዓት ስፔን ውስጥ እየተደረጉ የሚገኙ እርምጃዎች ዘረኝነትን ባያጠፋውም ቀስ በቀስ እንዲቀንስ ያደርጋል የሚል እምነት እንዳለው ቪንሰስ አያይዞ ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኬራን ትሪፔር ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ አገለለ !

እንግሊዛዊው የመስመር ተጨዋች ኬራን ትሪፔር በ 33ዓመቱ ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ራሱን ማግለሉን በይፋ አስታውቋል።

የኒውካስል ዩናይትዱ የመስመር ተጨዋች ኬራን ትሪፔር ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን 54 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወት ችሏል።

" ሀገሬን በአራት ትልልቅ ውድድሮች ላይ መወከል ለእኔ በህይወቴ ከምኮራባቸው ነገሮች አንዱ ነው ፣ ሁሉም አመሰግናለሁ።" ሲል ትሪፔር ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጄሱስ ናቫስ ራሱን ከብሔራዊ ቡድኑ አገለለ !

ስፔናዊው የመስመር ተጨዋች ጄሱስ ናቫስ በ 38ዓመቱ ከስፔን ብሔራዊ ቡድን ራሱን ማግለሉን ይፋ አድርጓል።

ጄሱስ ናቫስ ባለፉት አስራ አምስት አመታት ለስፔን ብሔራዊ ቡድን ግልጋሎት መስጠት ሲችል የአለም ዋንጫ ፣ አውሮፓ ዋንጫ እና ኔሽንስ ሊግ ያሸነፈ ብቸኛው ተጨዋች ነው።

ጄሱስ ናቫስ በብሔራዊ ቡድኑ ምን አሳካ ?

2️⃣ አውሮፓ ዋንጫ

1️⃣ አለም ዋንጫ

1️⃣ ኔሽንስ ሊግ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሻምፒዮን ሆኗል !

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች ቡድን በሀገራችን ኢትዮጵያ የተዘጋጀውን የካፍ የሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ የሴካፋ ሀገራት ማጣሪያ ውድድር በአሸናፊነት አጠናቋል።

ንግድ ባንክ የውድድሩን የፍፃሜ ጨዋታ ከኬንያ ፖሊስ ቡሌትስ ጋር አድርጎ በሴናፍ ዋቁማ ግብ 1ለ0 በማሸነፍ ሻምፒዮን መሆን ችሏል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያን ወክሎ በአፍሪካ ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር የሚሳተፍ ይሆናል።

በውድድሩ ኬንያ ፖሊስ ቡሌትስ ሁለተኛ እንዲሁም የዩጋንዳው ክለብ ካዌምፔ ሙስሊም ሌዲስ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንኳ ተጨዋች ሴናፍ ዋቁማ በስድስት ግቦች የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን ማጠናቀቅ ችላለች።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከዚህ በፊት በውድድሩ ሁለት ጊዜ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ሲያጠናቅቅ አንድ ጊዜ ደግሞ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። 

የ 2025 የአፍሪካ ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር የሚካሄድበት ሀገር በሚቀጥለው ሳምንት ዲሞክራቲክ ኮንጎ ላይ በሚደረገው የካፍ ስራ አስፈፃሚ ስብስባ ላይ የሚታወቅ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሊቨርፑል ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ ! የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ጣልያናዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ፌዴሪኮ ኬሳ ከጣልያኑ ክለብ ጁቬንቱስ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። ሊቨርፑል ተጫዋቹን በ 13 ሚልዮን ዩሮ ለማስፈረም ከጁቬንቱስ ጋር ከስምምነት መድረሱን ጣልያናዊው ጋዜጠኛ ፋብሪዝዮ ሮማኖ አስነብቧል። ተጨዋቹ በአሁን ሰዓት ወደ መርሲሳይድ ለመብረር በዝግጅት ላይ መሆኑ ሲገለፅ…
“ ሊቨርፑልን ስቀላቀል ህልሜ እውን ሆኗል “ ኬሳ

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ጣልያናዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ፌዴሪኮ ኬሳ ከጣልያኑ ክለብ ጁቬንቱስ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ሊቨርፑል ተጫዋቹን በ 13 ሚልዮን ዩሮ የዝውውር ሒሳብ ማስፈረማቸው ተገልጿል።

“ ለዚህ ማልያ እና ለደጋፊዎቹ ሁሉንም ነገር እሰጣለሁ “ ያለው ፌዴሪኮ ኬሳ “ የክለቡን ፍላጎት ስሰማ በፍጥነት ነው የተቀበልኩት “ በማለት ተናግሯል።

" ለሊቨርፑል መጫወት ህልሜን እውን አድርጎልኛል “ ሲል የተደመጠው ተጨዋቹ ሊቨርፑል የሚለውን ስም ስሰማ ዋንጫ እና አንፊልድ ነው የሚታየኝ በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ናፖሊ በይፋ ተጨዋች አስፈረመ !

የጣልያን ሴርያው ክለብ ናፖሊ ቤልጂየማዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ሮሜሉ ሉካኩን ከቼልሲ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ናፖሊ ተጫዋቹን 30 ሚልዮን ዩሮ በማውጣት በሶስት አመት ኮንትራት ማስፈረማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

በአሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ የሚመራው ናፖሊ በቀጣይ ስኮትላንዳዊውን አማካይ ስኮት ማክ ቶሚናይን ዝውውር ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ ተጨዋቹ ጉዳት አጋጠመው !

የማንችስተር ዩናይትዱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሜሰን ማውንት የጡንቻ ጉዳት እንዳጋጠመው ዘ አትሌቲክስ በዘገባው አስነብቧል።

እንግሊዛዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሜሰን ማውንት በጉዳቱ ምክንያት ከአራት እስከ አምስት ሳምንታት ከሜዳ እንደሚርቅ ተገልጿል።

ተጨዋቹ ማንችስተር ዩናይትድ በብራይተን በተሸነፈበት ጨዋታ መጠነኛ ጉዳት እንዳጋጠመው እና ተቀይሮ እንደወጣ ሲገለፅ ነበር።

ተጨዋቹ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው መልዕክት በቅድመ ውድድር ዝግጅት ወቅት ጥሩ አቋሙን ለመመለስ ጠንክሮ ሰርቶ እንደነበር ገልጿል።

" ይሁን እንጂ ባጋጠመኝ ጉዳት ለተወሰኑ ተጨዋቾች ባለመኖሬ አዝኛለሁ ፣ በድጋሜ ጠንክሬ ለመመለስ እና ቡድኑን ለማገዝ የቻልኩትን ሁሉ አደርጋለሁ “ ሲል ማውንት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሮናልዶ ልዩ ሽልማት ሊበረከትለት ነው ! የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በመጪው ሐሙስ ከአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ልዩ ሽልማት ሊበረከትለት መሆኑ ተገልጿል። ሮናልዶ ሐሙስ በሚካሄደው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ እጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ላይ ሽልማቱ ከዩኤፋ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሴፈሪን እንደሚበረከትለት ተነግሯል። ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአውሮፓ ሻምፒየንስ…
#UCLDraw

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የ 2024/25 የውድድር ዘመን የመጀመሪያ ዙር እጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ከደቂቃዎች በኋላ በሞናኮ ይካሄዳል።

በእጣ ማውጣት ስነ ስርዓቱ ላይ የዩኤፋ ልዩ ተሸላሚው ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአሁን ሰዓት ሞናኮ ተገኝቷል።

በተጨማሪም ጣልያናዊው ታሪካዊ ግብ ጠባቂ ጂያንሉጂ ቡፎን በአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ልዩ ሽልማት እንደሚበረከትለት ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🌼🌼🌼 እንኳን አደረሳችሁ🌼🌼🌼

🆕አዳዲስ እንዲሁም በመጠኑ ያገለገሉ ስልኮችን ከተሟላ ዋስትና እና ጥገና ጋር ይዘን ቀርበናል 🍏 ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎበኙ

📣 https://yangx.top/sellphone2777

📞 0929008292

✉️ inbox @bina27

📌 አድራሻ- ቦሌ ከሸገር ህንፃ አጠገብ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from WANAW SPORT
⚽️ ደግሞ ሌላ #ዋና ቀን #ከዋናው...

🇪🇹 ዋናው × ታሪካዊ የሀገራችን ክለብ 🇪🇹

📆 ታላቅ ስምምነት በነገው ዕለት!

Instagram | Facebook | TikTok

🏅ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear‌‌
TIKVAH-SPORT
የአውሮፓ ውድድሮች ተጋጣሚዎች መቼ ይታወቃሉ ? በዚህ አመት በአዲስ አቀራረብ የሚመጡት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፣ ዩሮፓ ሊግ እና ኮንፈረንስ ሊግ ውድድሮች እጣ ማውጣት ቀጣይ ሳምንት ሐሙስ እንደሚካሄድ ይፋ ሆኗል። የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓቱ ከዚህ በፊት እንደነበረው በእጅ ሳይሆን ለዚህ አላማ በተዘጋጀ ሶፍትዌር እንደሚደረግ ተገልጿል። ሶፍትዌሩ በተጨማሪም ክለቦች የትኛውን ጨዋታ ከሜዳቸው ውጪ…
የሻምፒየንስ ሊግ እጣ አወጣጥ ምን ይመስላል ?

የዘንድሮው የ 2024/25 የውድድር ዘመን የአውሮፓ ውድድሮች በአዲስ አቀራረብ ሲካሄድ በአሁን ሰዓት የእጣ ማውጣት ስነስርዓቱ እየተካሄደ ይገኛል።

በእጣ ማውጣቱ ምን ህጎች ይተገበራሉ ?


- ሁሉም ክለቦች ስምንት ቡድኖችን ይገጥማሉ

- አራቱን በሜዳቸው አራቱን ከሜዳቸው ውጪ ያደርጋሉ

- የአንድ ሀገር ክለቦች እርስ በርስ አይገናኙም

- ክለቦች ከሚገጥሟቸው ስምንት ቡድኖች ከአንድ ተመሳሳይ ሀገር ቢበዛ ሁለት ክለብ ያገኛሉ።

- አሁን ከሚገኙት ቋት ጨምሮ ከቀረቡት አራት ቋቶች ሁለት ክለቦች ይደርስባቸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሮናልዶ ልዩ ሽልማት ሊበረከትለት ነው ! የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በመጪው ሐሙስ ከአውሮፓ እግርኳስ ማህበር ልዩ ሽልማት ሊበረከትለት መሆኑ ተገልጿል። ሮናልዶ ሐሙስ በሚካሄደው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ እጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ላይ ሽልማቱ ከዩኤፋ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሴፈሪን እንደሚበረከትለት ተነግሯል። ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአውሮፓ ሻምፒየንስ…
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ልዩ ሽልማት ተበርክቶለታል !

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከዩኤፋ ልዩ ሽልማት ተበርክቶለታል።

ሮናልዶ በሽልማቱ ላይ ባደረገው ንግግር “ ሻምፒየንስ ሊግ ለእኔ የእግርኳስ ትልቁ መድረክ ነው ለእኔ ደግሞ ልዩ ነው ምክንያቱም በርካታ ጊዜ አሳክቼዋለሁ “ ብሏል።

" በሻምፒየንስ ሊግ የማይረሳ ትዝታ አለኝ " የሚለው ሮናልዶ የመጀመሪያ ጨዋታዬን አሁንም አስታውሰዋለሁ በማለት ተናግሯል።

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ በድጋሜ የመጫወት እድል ይኖረው እንደሆነ የተጠየቀው ሮናልዶ ማን ያውቃል የወደፊቱን በማለት ምላሽ ሰጥቷል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ባደረጋቸው 183 ጨዋታዎች 140 ግቦችን በማስቆጠር የውድድሩ የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#UCLDraw                       

የማንችስተር ሲቲ ተጋጣሚዎች :-

*በሜዳው የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች

- ኢንተር ሚላን
- ፊኖርድ
- ክለብ ብርሀ
- ስፖርቲንግ ሊስበን

*ከሜዳው ውጪ የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች

- ፒኤስጂ
- ጁቬንቱስ
- ስፓርታ ብርሀ
- ብራቲስላቫ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#UCLDraw                       

የባርሴሎና ተጋጣሚዎች :-

*በሜዳው የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች

- ባየር ሙኒክ
- አትላንታ
- ያንግ ቦይስ
- ብረሴት

*ከሜዳው ውጪ የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች

- ዶርትመንድ
- ቤኔፊካ
- ክርቬና ቬዝዳ
- ሞናኮ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#UCLDraw                       

የሊቨርፑል ተጋጣሚዎች :-

*በሜዳው የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች

- ሪያል ማድሪድ
- ባየር ሌቨርኩሰን
- ሊል
- ቦሎኛ

*ከሜዳው ውጪ የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች

- ሌፕዚግ
- ኤሲ ሚላን
- ፒኤስቪ
- ጂሮና

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#UCLDraw                       

የሪያል ማድሪድ ተጋጣሚዎች :-

*በሜዳው የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች

- ዶርትመንድ
- ኤሲ ሚላን
- ሳልዝበርግ
- ስቱትጋርት

*ከሜዳው ውጪ የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች

- ሊቨርፑል
- አታላንታ
- ሊል
- ብረስት

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#UCLDraw                       

የአርሰናል ተጋጣሚዎች :-

*በሜዳው የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች

- ፒኤስጂ
- ሻካታር
- ዳይናሞ
- ሞናኮ

*ከሜዳው ውጪ የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች

- ኢንተር ሚላን
- አታላንታ
- ስፖርቲንግ ሊስበን
- ጂሮና

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#UCLDraw                       

የባየር ሙኒክ ተጋጣሚዎች :-

*በሜዳው የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች

- ፒኤስጂ
- ቤኔፊካ
- ዳይናሞ
- ብራቲስላቫ

*ከሜዳው ውጪ የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች

- ባርሴሎና
- ሻክታር
- ፊኖርድ
- አስቶን ቪላ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#UCLDraw                       

የአስቶን ቪላ ተጋጣሚዎች :-

*በሜዳው የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች

- ጁቬንቱስ
- ሴልቲክ
- ቦሎኛ
- ባየር ሙኒክ

*ከሜዳው ውጪ የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች

- ያንግ ቦይስ
- ክለብ ብርሀ
- ሌፕዚግ
- ሞናኮ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe