TIKVAH-SPORT
259K subscribers
52.1K photos
1.48K videos
5 files
3.46K links
加入频道
ቪክቶር ኦሲሜን ወደ ቼልሲ ?

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ናይጄሪያዊውን የፊት መስመር አጥቂ ቪክቶር ኦሲሜን ለማስፈረም በዛሬው ዕለት ከተጨዋቹ ወኪሎች ጋር እንደሚነጋገሩ ተገልጿል።

ቪክቶር ኦሲሜንን ለማስፈረም በአሁን ሰዓት ቼልሲ እና አል አህሊ እያነጋገሩ መሆኑ ሲገለፅ ፒኤስጂ ከዝውውሩ መውጣቱ ተዘግቧል።

የሰዑዲ ዓረቢያው ክለብ አል አህል ኦሲሜንን በ 65 ሚልዮን ዩሮ ለማስፈረም ከናፖሊ ጋር ከስምምነት ደርሰው የተጫዋቹን ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸው ተነግሯል።

ቼልሲ ከናፖሊ ጋር ከስምምነት የማይደርስ ከሆነ ቪክቶር ኦሲሜን ከሰዑዲ ዓረቢያው ክለብ አል አህል የቀረበለትን ጥያቄ ሊቀበል እንደሚችል ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
በርንሌይ ሀኒባል ሜጅብሪን ማስፈረም ይፈልጋል ! የሻምፒዮን ሺፑ ክለብ በርንሌይ ቱኒዚያዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሀኒባል ሜጅብሪ ከማንችስተር ዩናይትድ ለማስፈረም ማሰባቸው ተገልጿል። እንደ ዘ አትሌቲክስ ዘገባ በርንሌይ ተጫዋቹን በቋሚ ዝውውር ወይም የመግዛት ግዴታ ባካተተ የውሰት ውል ለማስፈረም ማሰባቸው ተገልጿል። ባለፈዉ አመት በውሰት በሲቪያ ያሳለፈው የ 21ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሀኒባል…
በርንሌይ ሀኒባል ሜጅብሪን በይፋ አስፈረመ !

የሻምፒዮን ሺፑ ክለብ በርንሌይ ቱኒዚያዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሀኒባል ሜጅብሪን ከማንችስተር ዩናይትድ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ ከተጨዋቹ ዝውውር ዘጠኝ ሚልዮን ፓውንድ የዝውውር ሒሳብ መቀበላቸው ተዘግቧል።

የ 21ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሀኒባል ሜጅብሪ ያለፈዉን አመት በውሰት በሲቪያ ማሳለፉ ይታወሳል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች ከተጨዋቹ የወደፊት ሽያጭ ሀምሳ በመቶ ተጠቃሚ የሚሆኑበት ውል መካተቱ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል ግብ ጠባቂ ማስፈረም ይፈልጋል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የዊጋን አትሌቲኩን ግብ ጠባቂ ሳም ቲክል ማስፈረም እንደሚፈልግ ዘ አትሌቲክስ ዘግቧል።

መድፈኞቹ የ 22ዓመቱን የእንግሊዝ ወጣት ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ሳም ቲክል የቡድኑ ሶስተኛ ግብ ጠባቂ አድርገው ለማስፈረም ማሰባቸው ተገልጿል።

ወጣቱን ግብ ጠባቂ ቶሚ ሴትፎርድ ከአያክስ ያስፈረመው አርሰናል የዝውውር መስኮቱ ከመጠናቀቁ በፊት ሁለት ግብ ጠባቂዎችን ማስፈረም እንደሚፈልግ ተነግሯል።

መድፈኞቹ አሮን ራምስዴል ክለቡን ከለቀቀ ሁዋን ጋርሺያን ከእስፓኞል እንደሚያስፈርሙ ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሊቨርፑል ተጨዋች ማስፈረም ይፈልጋል ! የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ጣልያናዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ፌዴሪኮ ኬሳ ከጁቬንቱስ ለማስፈረም በመመልከት ላይ መሆናቸው ተገልጿል። ሊቨርፑል ዛሬ በፌዴሪኮ ኬሳ ዝውውር ዙሪያ ጁቬንቱስን ማነጋገራቸውን የዝውውር ጉዳዮችን የሚዘግበው ጋዜጠኛ ፋብሪዝዮ ሮማኖ አስነብቧል። የ 26ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ፌዴሪኮ ኬሳ ወደ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የማምራት ፍላጎት…
ሊቨርፑል ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ጣልያናዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ፌዴሪኮ ኬሳ ከጣልያኑ ክለብ ጁቬንቱስ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል።

ሊቨርፑል ተጫዋቹን በ 13 ሚልዮን ዩሮ ለማስፈረም ከጁቬንቱስ ጋር ከስምምነት መድረሱን ጣልያናዊው ጋዜጠኛ ፋብሪዝዮ ሮማኖ አስነብቧል።

ተጨዋቹ በአሁን ሰዓት ወደ መርሲሳይድ ለመብረር በዝግጅት ላይ መሆኑ ሲገለፅ በቀጣይ የህክምና ምርመራውን እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

የ 26ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ፌዴሪኮ ኬሳ የሊቨርፑል የክረምት ሁለተኛ ፈራሚ ተጨዋች እንደሚሆን ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሊቨርፑል ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ ! የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ጣልያናዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ፌዴሪኮ ኬሳ ከጣልያኑ ክለብ ጁቬንቱስ ለማስፈረም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። ሊቨርፑል ተጫዋቹን በ 13 ሚልዮን ዩሮ ለማስፈረም ከጁቬንቱስ ጋር ከስምምነት መድረሱን ጣልያናዊው ጋዜጠኛ ፋብሪዝዮ ሮማኖ አስነብቧል። ተጨዋቹ በአሁን ሰዓት ወደ መርሲሳይድ ለመብረር በዝግጅት ላይ መሆኑ ሲገለፅ…
“ የሊቨርፑል ተጨዋች እስከምሆን ጓጉቻለሁ “ ፌዴሪኮ ኬሳ

የመርሲሳይዱን ክለብ ሊቨርፑል ለመቀላቀል የህክምና ምርመራ ብቻ የሚቀረው ጣልያናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ፌዴሪኮ ኬሳ በዝዉዉሩ ደስተኛ መሆኑን ገልጿል።

“ በጣም ተደስቻለሁ ፣ አዲሱ የሊቨርፑል ተጨዋች እስከምሆን ጓጉቻለሁ ቤተሰቦቼም በጣም ተደስተዋል “ ሲል ወደ ሊቨርፑል ለመጓዝ የተዘጋጀው ፌዴሪኮ ኬሳ ተናግሯል።

ጁቬንቱሴን እና ደጋፊዎቹን ማመስገን እንደሚፈልግ ጨምሮ የገለፀው ፌዴሪኮ ኬሳ “ እነሱ ሁልጊዜም ለእኔ የተለዩ ነበሩ አሁን ሰዓቱ ሊቨርፑልን የመቀላቀል ነው “ ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የዩራጓይ ተጨዋቾች ቅጣት ሊጣልባቸው ይችላል ! የደቡብ አሜሪካ እግርኳስ ማህበር ትላንት ሌሊት በዩራጓይ ተጨዋቾች እና ኮሎምቢያ ደጋፊዎች መካከል የተፈጠረውን ክስተት እየመረመረ እንደሚገኝ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ አስታውቋል። በጨዋታው ዳርዊን ኑኔዝን ጨምሮ የዩራጓይ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ወደ ተመልካች መቀመጫ ወንበር በመግባት ከኮሎምቢያ ደጋፊዎች ጋር ተደባድበው ነበር። ተጨዋቾቹ ከደጋፊዎች ጋር…
የዩራጓይ ተጨዋቾች ቅጣት ተጣለባቸው !

በቅርቡ በዩራጓይ ተጨዋቾች እና ኮሎምቢያ ደጋፊዎች መካከል የተፈጠረውን ክስተት ተከትሎ የዩራጓይ ተጨዋቾች ቅጣት እንደተጣለባቸው ተገልጿል።

በጨዋታው ዳርዊን ኑኔዝን ጨምሮ የዩራጓይ ብሔራዊ ቡድን ተጨዋቾች ወደ ተመልካች መቀመጫ ወንበር በመግባት ከኮሎምቢያ ደጋፊዎች ጋር ተደባድበው ነበር።

በዚህም ምክንያት በፀቡ የተሳተፈው የሊቨርፑሉ ተጨዋች ዳርዊን ኑኔዝ የአምስት የብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች እገዳ እና 20,000 ዶላር ቅጣት እንደተጣለበት ተገልጿል።

እንዲሁም ሮድሪጎ ቤንታንኩር አራት ጨዋታ ሲቀጣ ኦሊቬራ ፣ ሮናልድ አራውሆ እና ሂምኔዝ እያንዳንዳቸው ሶስት ጨዋታዎች ተቀጥተዋል።

በተጨማሪ የዩራጓይ እግርኳስ ፌዴሬሽን የ 20,000 የገንዘብ ቅጣት እንደተጣለበት ተገልጿል።

ተጨዋቾቹ ከደጋፊዎች ጋር ፀብ ውስጥ የገቡት የኮሎምቢያ ደጋፊዎች ቤተሰቦቻቸውን ለማጥቃት መሞከራቸውን ተከትሎ እንደሆነ መግለፃቸው ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማድሪድ ለኤንድሪክ ግብ ክፍያ ይፈፅማል !

ሪያል ማድሪድ ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኤንድሪክ ግብ ማስቆጠሩን ተከትሎ ለቀድሞ ክለቡ ፓልሜራስ ክፍያ እንደሚፈፅሙ ተገልጿል።

ኤንድሪክ የመጀመሪያ የላሊጋ ግቡን ማስቆጠሩን ተከትሎ ሎስ ብላንኮዎቹ 35,000 ዩሮ ለፓልሜራስ እንደሚከፍሉ ተነግሯል።

በቀጣይ ተጨዋቹ ግብ ካስቆጠረ ሪያል ማድሪድ በአንድ ግብ 35,000 ዩሮ ለፓልሜራስ መክፈል እንደሚጠበቅባቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ 1000 ግቦች ማስቆጠር እፈልጋለሁ “ ሮናልዶ

ፖርቹጋላዊው ተጨዋች ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአዲሱ የዩቲዩብ ማህበራዊ ገፁ ከቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች ሪዮ ፈርዲናንድ ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ አጋርቷል።

ሮናልዶ በቃለ ምልልሱ ምን ጉዳዮችን አነሳ ?

- “ የሳውዲ አረቢያ ሊግ እንደሚባለው ቀላል አይደለም።

- በቅርቡ 900ኛ ግቤን አስቆጥራለሁ ነገርግን 1000 ግቦች ላይ መድረስ እፈልጋለሁ።

- ሰዑዲ ዓረቢያ የሚወደድ ሀገር ነው ለመላመድ ምንም አላስቸገረኝም እዚህ መሆኔን እወደዋለሁ ቤተሰቦቼም ይወዱታል።

- በዚህ አመት ሶስት ውድድሮችን በመለያ ምት ነው ያጣነው ነገርግን እግርኳስ ነው።

- በአለም ላይ በርካታ ተከታዮች ያሉት ሰው ነኝ ነገርግን ቆንጆ ስለሆንኩ ሳይሆን በእግርኳስ ፣ በግቦች ፣ በሽልማቶች ፣ በአኗኗር ዘይቤዬ እና ሌሎች ነገሮች ያገኘሁት ነው።

- የሰዑዲ ሊግ እያደገ የሚገኘው በእኔ ምክንያት መሆኑን አውቃለሁ አሁንም ሊጉን አሳድገዋለሁ ተጨዋቾች እንደሚከተሉኝ አውቃለሁ።

- በአውሮፓ ዋንጫ ምንም ግብ አላስቆጠረም የሚሉ ሰዎች አሉ እና ምን ? እኔ እኮ ለብሔራዊ ቡድኑ 140 ግቦች አስቆጥሪያለሁ።

- ፍላጎት እና ተነሳሽነት ካለ እድሜ ቁጥር ብቻ ይሆናል።"ሲል በቃለምልልሱ ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🌼🌼🌼 እንኳን አደረሳችሁ🌼🌼🌼

🆕አዳዲስ እንዲሁም በመጠኑ ያገለገሉ ስልኮችን ከተሟላ ዋስትና እና ጥገና ጋር ይዘን ቀርበናል 🍏 ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎበኙ

📣 https://yangx.top/sellphone2777

📞 0929008292

✉️ inbox @bina27

📌 አድራሻ- ቦሌ ከሸገር ህንፃ አጠገብ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ባርሴሎና ለሊቨርፑል ጥያቄ አቀረቡ !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ስፔናዊውን የሊቨርፑል የመሐል ሜዳ ተጨዋች ስቴፋን ባቼቲች ለማስፈረም የዝውውር ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል።

ባርሴሎና ተጫዋቹን በውሰት ለማስፈረም ለሊቨርፑል አራት ሚልዮን ዩሮ የውሰት ክፍያ ማቅረባቸውን የዝውውር ጉዳዮችን የሚዘግበው ጋዜጠኛ ፋብሪዝዮ ሮማኖ አስነብቧል።

ከባርሴሎና በተጨማሪም ሳልዝበርግ ተጫዋቹን በውሰት ውል ለማስፈረም ለሊቨርፑል የዝውውር ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የዩናይትድ የራሂም ስተርሊንግ ዝውውር ?

እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጨዋች ራሂም ስተርሊንግ በቼልሲ እቅድ ውስጥ አለመኖሩን ተከትሎ ስሙ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር እየተያያዘ ይገኛል።

ማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋቹን የሚያስፈርሙ ከሆነ በቼልሲ ከሚያገኘው በግማሽ ቀንሰው ሳምንታዊ 150,000 ፓውንድ ክፍያ ሊያቀርቡለት ማዘጋጀታቸው ተገልጿል።

ተጨዋቹ ማንችስተር ዩናይትድን ለመቀላቀል ፍቃደኛ ከሆነ በተጨማሪም ተጠባባቂ እንደሚሆን አምኖ መቀበል እንደሚጠበቅበት ተነግሯል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች ራሂም ስተርሊንግ ቡድኑን ከተቀላቀለ በእያንዳንዱ ጨዋታ ላይ ቋሚ የማድረግ እቅድ እንደሌላቸው ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
“ ለብቻቸው የሚሰሩ ሁሉም ተጨዋቾች ከቆዩ አይጫወቱም “ ማሬስካ

የለንደኑ ክለብ ቼልሲ ዋና አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ሁሉም ለብቻቸው በመስራት ላይ የሚገኙ የክለቡ ተጨዋቾች ክለቡን ቢለቁ እንደሚሻላቸው መክረዋል።

“ በቡድኑ እቅድ ውስጥ አለመኖር የሚመለከተው ስተርሊንግ እና ቻሎባህን ብቻ አይደለም “ ያሉት አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ለብቻቸው የሚሰሩ ሁሉንም ተጨዋቾች ይመለከታል ብለዋል።

አሰልጣኙ በቅርቡ ከሀያ አንድ ተጨዋቾች ውጪ ያሉትን አይተዋቸው እንደማያውቁ መግለፃቸው የሚታወስ ሲሆን ዛሬ “ ክለቡን የማይለቁ ከሆነ አንድም ደቂቃ አይጫወቱም “ ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
•PlayStation 5, 73,000 Birr
•Playstaion 5 Slim, 78,000 Birr

•PlayStation 4 Slim, 37,000 Birr
•PlayStation 4 Pro, 43,000 Birr

•Playstaion portal, 25,000 Birr
•Meta Quest 2, 45,000 Birr
•Meta Quest 3, 73,000 Birr

Contact
0953964175 @heymobile

@heyonlinemarket
መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው!
Las Palmas - Real Madrid
Besiktas - Lugano
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
ሪያል ማድሪድ ተጫዋቹን መሸጥ ይፈልጋል !

ሪያል ማድሪድ ስፔናዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዳኒ ሴባዮስ የዝውውር መስኮቱ ከመጠናቀቁ በፊት መሸጥ እንደሚፈልግ ተገልጿል።

ሎስ ብላንኮዎቹ ተጨዋቹ በክለቡ እንዲቆይ ጥረት እንደማያደርጉ እና ጥሩ የዝውውር ሒሳብ ከቀረበላቸው እንደሚሸጡት ዘ አትሌቲክስ ዘግቧል።

በሎስ ብላንኮዎቹ ቤት በቂ የጨዋታ ጊዜ ያላገኘው ዳኒ ሴባዮስ የጨዋታ ጊዜን ለማግኘት ክለቡን መልቀቅ እንደሚፈልግ ከዚህ በፊት መዘገቡ አይዘነጋም።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ኬፓ አሪዛባላጋ በርንማውዝን ሊቀላቀል ነው ! ስፔናዊው የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባላጋ በርንማውዝን በውሰት ለመቀላቀል ከጫፍ መድረሱን ዘ አትሌቲክስ ዘግቧል። ያለፈውን አመት በውሰት በሪያል ማድሪድ ቤት ያሳለፈው ኬፓ አሪዛባላጋ በርንማውዝን በውሰት ለመቀላቀል የህክምና ምርመራውን በማድረግ ላይ መሆኑ ተገልጿል። ኬፓ አሪዛባላጋ በርንማውዝን በውሰት ከሚቀላቀሉ በፊት በቼልሲ…
ኬፓ አሪዛባላጋ በርንማውዝን ተቀላቀለ !

በርንማውዝ ስፔናዊውን የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባላጋ በውሰት ውል ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ያለፈውን አመት በውሰት በሪያል ማድሪድ ቤት ያሳለፈው ኬፓ አሪዛባላጋ በርንማውዝን ለአንድ የውድድር አመት በውሰት ተቀላቅሏል።

ኬፓ አሪዛባላጋ በርንማውዝን በውሰት ከመቀላቀሉ በፊት በቼልሲ ቤት ያለውን ኮንትራት ለአንድ ተጨማሪ አመት ማራዘሙ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ዎልቭስ ራምስዴልን ለማስፈረም ጥያቄ አቀረበ ! ዎልቭስ እንግሊዛዊውን ግብ ጠባቂ አሮን ራምስዴልን ለማስፈረም ለአርሰናል ይፋዊ የዝውውር ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል። ዎልቭስ የአሮን ራምስዴልን አብዛኛውን ደሞዝ በመክፈል የመግዛት አማራጭ ባካተተ የውሰት ውል ለማስፈረም ለአርሰናል ጥያቄ ማቅረባቸውን ዘ አትሌቲክስ አስነብቧል። አርሰናል በበኩሉ የእስፓኞሉን ግብ ጠባቂ ሁዋን ጋርሽያ ለማስፈረም በግል…
አሮን ራምስዴል ሳውዝሀምፕተንን ሊቀላቀል ነው  !

እንግሊዛዊው የአርሰናል ግብ ጠባቂ አሮን ራምስዴል ሳውዝሀምፕተንን በቋሚ ዝውውር ለመቀላቀል የህክምና ምርመራውን በማድረግ ላይ መሆኑ ተገልጿል።

የ 26ዓመቱ ግብ ጠባቂ አሮን ራምስዴል ሳውዝሀምፕተንን በአራት አመት ኮንትራት እንደሚቀላቀል ተዘግቧል።

መድፈኞቹ ከግብ ጠባቂው ዝውውር አጠቃላይ 25 ሚልዮን ፓውንድ የሚደርስ የዝውውር ሒሳብ እንደሚቀበሉ ተገልጿል።

አርሰናል በአሮን ራምስዴል ምትክ የእስፓኞሉን ግብ ጠባቂ ሁዋን ጋርሽያ በቀጣይ ቀናት ያስፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የዩናይትድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል

በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የሚመሩት ማንችስተር ዩናይትዶች የወርሀ ነሐሴ የወሩ ምርጥ ተጨዋች #ሶስት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ናስር ማዝራዊ ፣ አማድ ዲያሎ እና አሌሀንድሮ ጋርናቾ የአመቱ የመጀመሪያ ወር የማንችስተር ዩናይትድ ምርጥ ተጨዋች እጩ ሆነው መቅረብ ችለዋል።

የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል የዝውውር ጥያቄ አቀረበ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በአሮን ራምስዴል ምትክ ስፔናዊውን የእስፓኞል ግብ ጠባቂ ሁዋን ጋርሽያ ለማስፈረም ይፋዊ የዝውውር ጥያቄ ማቅረባቸው ተገልጿል።

መድፈኞቹ ለግብ ጠባቂው 20 ሚልዮን ዩሮ ማቅረባቸው ሲገለፅ እስፓኞል በበኩሉ 30 ሚልዮን ዪሮ መጠየቁን ፋብሪዝዮ ሮማኖ ዘግቧል።

በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚመራው አርሰናል ከሁዋን ጋርሽያ ጋር ቀደም ብሎ በግል ከስምምነት መድረሱ አይዘነጋም።

መድፈኞቹ በተጨማሪም የዝውውር መስኮቱ ሳይጠናቀቅ የ 22ዓመቱን እንግሊዛዊ ሳም ቲክል የቡድኑ ሶስተኛ ግብ ጠባቂ አድርገው ለማስፈረም ማሰባቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሰማያዊዎቹ ግብ ጠባቂዎቻቸውን በውሰት እየሰጡ ነው !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በአሁን ሰዓት በክለቡ ዝርዝር ውስጥ ተመዝግበው ካሉት ስምንት ግብ ጠባቂዎች ውስጥ የተወሰኑትን በውሰት በመስጠት ላይ ናቸው።

ስፔናዊው ግብ ጠባቂ ኬፓ አሪዛባላጋ በአንድ የውድድር አመት ውሰት ውል በርንማውዝን መቀላቀሉ አይዘነጋም።

ሌላኛው ግብ ጠባቂ ፒትሮቪች በአንድ አመት የውሰት ውል ስትራስቡርግን ለመቀላቀል የህክምና ምርመራውን በማድረግ ላይ ይገኛል።

አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ በዚህ አመት ሮበርት ሳንቼዝን የክለቡ ቁጥር አንድ ግብ ጠባቂ አድርገው መምረጣቸው ተገልጿል።

ሰማያዊዎቹ ካሏቸው ስምንት ግብ ጠባቂዎች ውስጥ ስድስቱ በዋናው ቡድን ስብስብ ውስጥ የተያያዙ ግብ ጠባቂዎች ናቸው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe