TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.7K photos
1.48K videos
5 files
3.41K links
加入频道
54 ' ሊቨርፑል 6 - 1 ስፓርታ ፕራግ

ኑኔዝ
ክላርክ
ሳላህ
ጋክፖ
ስቦዝላይ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
75 ' ባየር ሊቨርኩሰን 1 - 2 ካራባህ

ፍሪምፖንግ       ዙቢር
                              ጁኒንሆ

ድምር ውጤት :- 3 - 4

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊቨርፑል ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅሏል !

በዩሮፓ ሊግ ጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ ሊቨርፑል ከስፓርታ ፕራግ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግቦች ኮዲ ጋክፖ 2x ፣ መሐመድ ሳላህ ፣ ዳርዊን ኑኔዝ ፣ ስቦዝላይ እና ክላርክ ከመረብ አሳርፈዋል።

ሊቨርፑል ስፓርታ ፕራግን በድምር ውጤት 11 ለ 2 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ የዩሮፓ ሊግ ዙር መቀላቀሉን አረጋግጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
90+6 ' ባየር ሊቨርኩሰን 3 - 2 ካራባህ

ፍሪምፖንግ       ዙቢር
ሺክ             ጁኒንሆ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባየር ሊቨርኩሰን ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅሏል !

በዩሮፓ ሊግ ጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ ባየር ሊቨርኩሰን ከካራባህ ጋር ያደረገውን ጨዋታ በመጨረሻ ደቂቃዎች ባስቆጠረው ግብ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የባየር ሊቨርኩሰንን የማሸነፊያ ግቦች ፓትሪክ ሺክ 2x እና ፍሪምፖንግ ከመረብ ሲያሳርፉ ዙቢር እና ጁኒንሆ አስቆጥረዋል።

ባየር ሊቨርኩሰን በተጨማሪ ሰዓት ባስቆጠሩት ሁለት ግቦች ታግዘው በድምር ውጤት 5ለ4 በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።

የዩሮፓ ሊግ ሩብ ፍፃሜ እነማን ተቀላቀሉ ?

- ኤሲ ሚላን                      - ሊቨርፑል
- ዌስትሀም ዩናይትድ          - ባየር ሊቨርኩሰን
- ማርሴይ                         - ሮማ
- ቤኔፊካ                           - አታላንታ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
BeGet Engineering PLC.

Advanced Level Training Package (2months)

1)  Building Advanced Structural Design 
2) Bridge Design 
3) Project Planning & Contract Administration 
4) Interior Design 
5) Water Supply & Sewerage 
6) Highway Design 
7) Accounting
for Engineering companies
8) Graphic Design

🔸Registration is active!
🔸Class begins on March 23/2024
📲  +251920933016 / +251712273536
📌 Megenagna,Marathon Bldg, No. 614
https://yangx.top/BeGetEngineering
-Meta Quest 2 & Meta Quest 3
-PlayStation Portal & Accessories
-PS 5 Slim, PS 5, PS5 Digital
-PS Games& Extra Controllers

0953964175 @heymobile
@heyonlinemarket
የአውሮፓ ታላላቅ ውድድሮች እጣ ማውጣት ዛሬ ይካሄዳል !

የተጠባቂው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፣ ዩሮፓ ሊግ እና ኮንፈረንስ ሊግ የእጣ ማውጣት በዛሬው ዕለት ከቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ የሚካሄድ ይሆናል።

በስዊዘርላንድ ኒዮን ከተማ በሚደረገው የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ቡድኖች እስከ ፍፃሜው ሊያገኟቸው የሚችሏቸውን ቡድኖች የማወቅ እድልን ያገኛሉ።

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ መርሐ ግብር ጨዋታዎች ከሳምንታት በኋላ ሚያዚያ 1 እና 2 መደረጋቸውን ይጀምራሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባየር ሌቨርኩሰን በአሸናፊነታቸው ቀጥለዋል !

በአሰልጣኝ ዣቪ አሎንሶ የሚመራው የቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሌቨርኩሰን ተከታታይ ድላቸውን ማስመዝገበቸውን ቀጥለዋል።

ሌቨርኩሰኖች በአለም ላይ ከሚገኙ ክለቦች በሁሉም ውድድሮች ሳይሸነፉ መጓዝ ከቻሉ ሶስት ክለቦች መካከል ቀዳሚው መሆን ችለዋል።

በዚህም መሰረት :-

1. ኒው ሴንት ዌልስ :- 4⃣0⃣ ጨዋታ

2. ባየር ሌቨርኩሰን :- 3⃣7⃣ ጨዋታ

3. አል ሂላል :- 3⃣6⃣ ጨዋታዎችን ሳይሸነፉ በመጓዝ ላይ ይገኛሉ።

ባየር ሌቨርኩሰን ባልተሸነፉበታቸው 37 ጨዋታዎች 106 ጎሎችን በተጋጣሚ ቡድን ላይ ማስቆጠር ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሳውዲ አረቢያ መሄድ አልነበረብኝም " ሄንደርሰን

እንግሊዛዊው የአያክስ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጆርዳን ሄንደርሰን ባለፈው ክረምት የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊግ መሄዱ ስህተት እንደነበር ገልጿል።

የሳውዲ አረቢያ ሊግ ከፍተኛ እድገት እያሳየ እንደሚገኝ እና በቀጣይ ጥሩ ሊግ እንደሚሆን የገለፀው ሄንደርሰን " ነገርግን ለእኔ አይሆንም ወደዛ በመሄድ ስህተት ሰርቼ ነበር በአያክስ ቤት ደስተኛ ነኝ።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#QUIZ

በሳምንቱ መጨረሻ እሁድ የሚደረገውን የሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ ውድድር ጥያቄዎች አስቀድሞ ለመለሱ
#ሁለት አሸናፊዎች ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የውድድሩ ቲሸርቶችን ይሸለማሉ።

1. ባለፈው አመት የተሰበረው የኮርስ ሪከርድ ባለቤት ማን ናት?

2. የውድድሩ መነሻ እና መድረሻ የት ነው?

🔴 ተወዳዳሪዎች ምላሻቸውን ከጥያቄው ስር ባለው የሀሳብ መስጫ ( Comment ) ስር #ብቻ መላክ ይጠበቅባቸዋል።

🔴 ሁሉም መልሶች በአንድ ላይ መላክ ሲኖርባቸው #በተናጥል የሚመጡ ምላሾች ፣ #ግማሽ መልስ እንዲሁም #ኤዲት የተደረጉ መልሾች ተቀባይነት #አይኖራቸውም
ጋና የቀድሞ አሰልጣኟን በሀላፊነት ሾመች !

የጋና እግርኳስ ፌዴሬሽን አሰልጣኝ ኦቶ አዶን የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርገው በድጋሜ ለመሾም መወሰናቸውን ይፋ አድርገዋል።

አሰልጣኝ ኦቶ አዶ በጋና ብሔራዊ ቡድን ለተጨማሪ ሁለት አመት የማራዘም አማራጭ ያካተተ የሶስት አመት ኮንትራት እንደሚፈርሙ ተገልጿል።

በኳታሩ አለም ዋንጫ ውድድር ጋናን በጊዜያዊ አሰልጣኝነት የመሩት አሰልጣኝ ኦቶ አዶ ከአስራ አምስት ወራት በኋላ በድጋሜ የሚመለሱ ይሆናል።

የ 48ዓመቱ አሰልጣኝ ኦቶ አዶ አሁን ላይ በቦርስያ ዶርትመንድ ቤት በ " talent coach " ሀላፊነት እየሰሩ የሚገኝ ሲሆን ቀጣይ ክረምት ከሀላፊነት እንደሚለቁ ክለቡ አሳውቋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ከ 17ዓመት በታች አለም ዋንጫ በየአመቱ ይካሄዳል !

የአለም እግር ኳስ የበላይ ፊፋ በሁለቱም ፆታዎች የሚካሄዱ ከ 17ዓመት በታች አለም ዋንጫ ውድድሮች በየአመቱ እንዲካሄዱ መወሰኑን ይፋ አድርጓል።

የሚቀጥሉትን #አምስት ከ 17ዓመት በታች የወንዶች አለም ዋንጫ ውድድሮች #ኳታር እንዲሁም የሴቶቹን #ሞሮኮ በተመሳሳይ ጊዜ እንደሚያዘጋጁ ተገልጿል።

ከ 2025 ጀምሮ መካሄዱን የሚጀምረው ውድድሩ የወንዶች ውድድር ተሳታፊ ሀገራት ወደ 48 እንዲሁም የሴቶች ወደ 24 ከፍ እንደሚሉም ይፋ ተደርጓል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Live

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ መርሐ ግብር የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት በአሁን ሰዓት በስዊዘርላንድ ኒዮን ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በዚህም መሰረት በቀጣይ መርሐ ግብሮች :-

- አርሰናል ከ ባየር ሙኒክ

- አትሌቲኮ ማድሪድ ከ ዶርትመንድ

- ሪያል ማድሪድ ከ ማንችስተር ሲቲ

- ፒኤስጂ ከ ባርሴሎና

የሩብ ፍፃሜ መርሐ ግብር ጨዋታዎች ከሳምንታት በኋላ ሚያዚያ 1 እና 2 መደረጋቸውን ይጀምራሉ።

የዘንድሮው የውድድር ዘመን የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታ በዌምብሌይ ስታዲየም ይደረጋል።

🔴 መርሐ ግብሮቹ በዚሁ ፖስት ላይ #Update ይደረጋሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ምን ይመስላሉ ?

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የቀጣይ ዙር ጨዋታዎች መርሐ ግብር ይፋ ሲደረጉ አሸናፊዎች በግማሽ ፍፃሜው የሚያገኟቸው ቡድኖች ተለይተው ታውቀዋል።

በዚህም መሰረት :-

1️⃣ አትሌቲኮ ማድሪድ / ዶርትመንድ ከ ፒኤስጂ / ባርሴሎና

2️⃣ አርሰናል / ባየር ሙኒክ ከ ሪያል ማድሪድ / ማንችስተር ሲቲ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የኤፍ ኤ ካፕ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ💥

ማን ዩናይትድ ከሊቨርፑል ጋር የሚያረጉትን አጓጊ ፍልሚያ በቀጥታ በሱፐርስፖርት ቻናሎች እሁድ መጋቢት 8 ከምሽቱ 12፡30 በቀጥታ ይከታተሉ!

🔥 ማን ዩናይትድ ወደ ግማሽ ፍፃሜ መቀጥል ይችላል?
🔥 ሊቨርፑል የሶስትዮሽ ዋንጫ እድሉን ይዞ መቀጠል ይችላል?

👉ከጥር 6 እስከ መጋቢት 22 ደንበኝነትዎን ሲያሳድጉ...
እኛም ቀጣዩን ለአንድ ወር እንጋብዝዎታለን!

ለሚሰጡን አስተያየት በቅድሚያ እያመሰገንን፣ ስለ አገልግሎታችን ጥራት የሚደርስዎትን የፅሁፍ መልዕክት ሊንኩን በመጫን መጠይቁን እንዲሞሉ በትህትና እንጠይቃለን።

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/eth2

#FACupAllOnDStv #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvSelfServiceET
Forwarded from WANAW SPORT
🇪🇹🇰🇷 እውነተኛ ቁርጠኝነት፣ ታላቅ ማስታወሻ! 🇪🇹🇰🇷

ታላቅ ክብር በደቡብ ኮሪያ፣ ሴኡል ማራቶን የኮሪያ ዘማች ወታደሮቻችንን ለማክበር በመጪው እሁድ በባዶ እግሩ ለሚሮጠው ኤርሚያስ አየለ። የተሳካ እና የማይረሳ ሩጫ እንዲሆንልህ ጥንካሬና ጉልበትን ዋናው ስፖርት ይመኛል።

Huge respect to Ermias Ayele who is running barefoot in the Seoul Marathon this Sunday to honor our Korean War Veterans! That's true dedication and a powerful tribute. Sending you strength and positive energy for a safe and memorable run.

#SeoulMarathon #Ethiopia #BarefootForHeroes
#ሴኡልማራቶን #ኢትዮጵያ
#የባዶእግርጀግኖች

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
የዩሮፓ ሊግ ሩብ ፍፃሜ ተጋጣሚዎች ታውቀዋል !

የዩሮፓ ሊግ የሩብ ፍፃሜ መርሐ ግብር የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ከደቂቃዎች በፊት ተካሂዷል።

በዚህም መሰረት በቀጣይ መርሐ ግብሮች :-

- ኤሲ ሚላን ከ ሮማ

- ሊቨርፑል ከ አታላንታ

- ባየር ሊቨርኩሰን ከ ዌስትሀም ዩናይትድ

- ቤኔፊካ ከ ማርሴይ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

የግማሽ ፍፃሜ ድልድል ምን ይመስላል ?

1️⃣ ቤኔፊካ / ማርሴይ ከ ሊቨርፑል / አታላንታ

2️⃣ ኤሲ ሚላን / ሮማ ከ ባየር ሊቨርኩሰን / ዌስትሀም ዩናይትድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
#Live የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የሩብ ፍፃሜ መርሐ ግብር የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት በአሁን ሰዓት በስዊዘርላንድ ኒዮን ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በዚህም መሰረት በቀጣይ መርሐ ግብሮች :- - አርሰናል ከ ባየር ሙኒክ - አትሌቲኮ ማድሪድ ከ ዶርትመንድ - ሪያል ማድሪድ ከ ማንችስተር ሲቲ - ፒኤስጂ ከ ባርሴሎና የሩብ ፍፃሜ መርሐ ግብር ጨዋታዎች ከሳምንታት በኋላ ሚያዚያ 1 እና…
ባየር ሙኒክ ደጋፊዎቹ ወደ ለንደን አያመሩም !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ሩብ ፍፃሜ መርሐ ግብር ከቡንደስሊጋው ክለብ ባየር ሙኒክ ጋር ተደልድሏል።

አርሰናል በኤምሬትስ ስታዲየም ከባየር ሙኒክ ጋር የሚያደርገው የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ያለ ባየር ሙኒክ ተጓዥ ደጋፊዎች የሚያደርግ ይሆናል።

ባየር ሙኒክ በቅርቡ ደጋፊዎቹ ተቀጣጣይ ነገር ይዘው መግባታቸውን ተከትሎ ከሜዳው ውጪ የሚያደርገውን የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ያለ ደጋፊ እንዲያደርግ መታገዱ ይታወቃል።

ባየር ሙኒክ ከተጣለበት ቅጣት በኋላ ባወጣው መግለጫ " ቅጣቱን መቀበል አለብን ህጉ ተጥሷል ይግባኝ አንጠይቅም ፣ ያለደጋፊ ከሜዳ ውጪ መጫወታችን ትልቅ ጉዳት ነው።"ብሎ ነበር።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ የተጫዋቾቹን ግልጋሎት ያገኛል !

ማንችስተር ዩናይትድ እሁድ ከሊቨርፑል ጋር በሚያደርገው ተጠባቂ የኤፌ ካፕ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ የወሳኝ ተጨዋቾቹን ግልጋሎት ሊያገኝ እንደሚችል አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ አረጋግጠዋል።

ራስሙስ ሆይሉንድ ፣ ሀሪ ማጓየር እና አሮን ዋን ቢሳካ ለእሁዱ የሊቨርፑል ጨዋታ ወደ ሜዳ ይመለሳሉ ብለው እንደሚጠበቁ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ማድሪድን ከመግጠም ውጪ ምርጫ የለንም " ጋርዲዮላ

ማንችስተር ሲቲ በነገው ዕለት ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር ከሚያደርገው የእንግሊዝ ኤፌ ካፕ ጨዋታ በፊት አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ አድርገዋል።

በቅድሚያ ቡድናቸው ከሪያል ማድሪድ ጋር ስለ ተደለደለበት የሻምፒየንስ ሊግ መርሐ ግብር ያነሱት ፔፕ ጋርዲዮላ " ሌላ ምርጫ የለንም ድልድሉ ባህል ይመስላል ከውድድሩ ንጉሥ ጋር ለሶስት ተከታታይ አመት እንጫወታለን።"ብለዋል።

" ኬቨን ዴብሮይን ከነገው የኒውካስል ዩናይትድ ጨዋታ ውጪ ነው ፣ ኤደርሰን ከብሔራዊ ቡድኖች እረፍት በኋላ ይመለሳል " ጋርዲዮላ

አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በነገው ጨዋታ ደጋፊዎች ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር እንደነበረው አይነት ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጠይቀዋል " ከዩናይትድ ጋር የነበረው ድጋፍ አይቼው የማላውቀው ነው " ሲሉም ገልፀውታል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe