TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.7K photos
1.48K videos
5 files
3.41K links
加入频道
የፕርሚየር ሊግ የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ማን ይሆናል ?

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ2023/24 የውድድር አመት የወርሀ የመስከረም የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ #አምስት እጩዎች ይፋ ተደርገዋል።

በዚህም መሰረት :-

👉 ሚኬል አርቴታ

👉 ኡናይ ኤምሬ

👉 ኤዲ ሀው

👉 የርገን ክሎፕ

👉 አንሄ ፖስቴኮግሉ በእጩነት መቅረብ የቻሉ አሰልጣኞች ናቸው።

የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ማን ይሆናል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የላሊጋ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ?

አስረኛ ሳምንቱ ላይ የሚገኘው የ 2023/24 የውድድር አመት የስፔን ላሊጋ የወርሀ ጥቅምት የወሩ ምርጥ ተጨዋች #አምስት እጩዎችን ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት ጁድ ቤሊንግሀም ፣ ጇ ፊሊክስ ፣ አንቷን ግሪዝማን ፣ ኢስኮ እና አሌክስ ጋርሺያ በእጩነት መቅረብ የቻሉ ተጨዋቾች ናቸው።

የወሩ ምርጥ ማን ይሆናል ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የፕርሚየር ሊግ ክለቦች ድምፅ ሰጥተዋል !

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ክለቦች አዲስ ኮንትራት የሚፈርሙ ተጨዋቾችን የዝውውር ገንዘብ በክለቡ ሂሳብ ውስጥ የመከፋፈል ስርዓት በአምስት አመት ጊዜ ለመገደብ ድምፅ መስጠታቸው ተገልጿል።

ክለቦቹ በሰጡት ድምፅ መሰረት ቼልሲን ጨምሮ አስራ አምስት ክለቦች ሀሳቡን ሲደግፉ ሁለቱ እንዳልተስማሙ እና ሶስቱ ደግሞ እንዳልተሳተፉ ተነግሯል።

ይህንንም ተከትሎ ከዚህ በኋላ ተጨዋቾች በክለቡ ለምን ያህል ጊዜም ኮንትራት ቢፈርሙ የዝውውር ገንዘቡ ግን በክለቡ ሂሳብ ውስጥ የሚከፋፈለው ለ#አምስት አመት ብቻ እንደሚሆን ተገልጿል።

ክለቦቹ በሰጡት ድምፅ መሰረት ተጨዋቾች የሚፈልትን ጊዜ ያህል ውል መፈረም እንደሚችሉ እና ከዚህ በፊት የነበሩ ውሎችን እንደማይመለከት ተጠቁሟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የላሊጋ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ?

አስራ ስምንተኛ ሳምንቱ ላይ የሚገኘው የ 2023/24 የውድድር አመት የስፔን ላሊጋ የወርሀ ታህሳስ የወሩ ምርጥ ተጨዋች #አምስት እጩዎችን ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት ሮድሪጎ ፣ ኢናኪ ዊሊያምስ ፣ አልቫሮ ቫሌስ ፣ ቦርጃ ማዮራል እና ዶቭቢክ በእጩነት መቅረብ የቻሉ ተጨዋቾች ናቸው።

የወሩ ምርጥ ማን ይሆናል ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የላሊጋ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ?

ሀያ አንደኛ ሳምንቱ ላይ የሚገኘው የ 2023/24 የውድድር ዘመን የስፔን ላሊጋ የወርሀ ጥር የወሩ ምርጥ ተጨዋች #አምስት እጩዎችን ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት ዳኒ ካርቫል ፣ ፌራን ቶሬስ ፣ ኢስኮ ፣ ኪሪያን ሮድሪጌዝ እና ዶቭቢክ በእጩነት መቅረብ የቻሉ ተጨዋቾች ናቸው።

የወሩ ምርጥ ማን ይሆናል ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ከ 17ዓመት በታች አለም ዋንጫ በየአመቱ ይካሄዳል !

የአለም እግር ኳስ የበላይ ፊፋ በሁለቱም ፆታዎች የሚካሄዱ ከ 17ዓመት በታች አለም ዋንጫ ውድድሮች በየአመቱ እንዲካሄዱ መወሰኑን ይፋ አድርጓል።

የሚቀጥሉትን #አምስት ከ 17ዓመት በታች የወንዶች አለም ዋንጫ ውድድሮች #ኳታር እንዲሁም የሴቶቹን #ሞሮኮ በተመሳሳይ ጊዜ እንደሚያዘጋጁ ተገልጿል።

ከ 2025 ጀምሮ መካሄዱን የሚጀምረው ውድድሩ የወንዶች ውድድር ተሳታፊ ሀገራት ወደ 48 እንዲሁም የሴቶች ወደ 24 ከፍ እንደሚሉም ይፋ ተደርጓል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የላሊጋ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ?

ሀያ ዘጠነኛ ሳምንቱ ላይ የሚገኘው የ 2023/24 የውድድር ዘመን የስፔን ላሊጋ የወርሀ መጋቢት የወሩ ምርጥ ተጨዋች #አምስት እጩዎችን ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት ቪኒሰስ ጁኒየር ፣ ሮበርት ሊዋንዶውስኪ ፣ ብራይስ ሜንዴዝ ፣ ሶርሎት እና ጉሩዜታ በእጩነት መቅረብ የቻሉ ተጨዋቾች ናቸው።

የወሩ ምርጥ ማን ይሆናል ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የማድሪድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል

በአሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ የሚሰለጥነው የላሊጋው መሪ ሪያል ማድሪድ የወርሀ መጋቢት የወሩ ምርጥ ተጨዋች #አምስት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ሮድሪጎ ፣ ቪንሰስ ጁኒየር ፣ ቶኒ ክሩስ ፣ ዳኒ ካርቫል እና ሩዲገር የወርሀ መጋቢት የሪያል ማድሪድ ወሩ ምርጥ ተጨዋች እጩ ሆነው መቅረብ ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የላሊጋ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ?

ሰላሳ ሁለተኛ ሳምንቱ ላይ የሚገኘው የ 2023/24 የውድድር ዘመን የስፔን ላሊጋ የወርሀ ሚያዝያ የወሩ ምርጥ ተጨዋች #አምስት እጩዎችን ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት ቪኒሰስ ጁኒየር ፣ ኢስኮ ፣ አስፓስ ፣ ኢን ነስሪ እና ሳቭዮ በእጩነት መቅረብ የቻሉ ተጨዋቾች ናቸው።

የወሩ ምርጥ ማን ይሆናል ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የማድሪድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል

በአሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ የሚሰለጥነው የላሊጋው መሪ ሪያል ማድሪድ የወርሀ ሚያዚያ የወሩ ምርጥ ተጨዋች #አምስት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ሮድሪጎ ፣ ቪንሰስ ጁኒየር ፣ ዳኒ ካርቫል ፣ ሩዲገር ፣ እና ቫልቬርዴ የወርሀ ሚያዝያ የሪያል ማድሪድ ወሩ ምርጥ ተጨዋች እጩ ሆነው መቅረብ ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ?

የፈረንሳይ በውጪ ሀገር የሚጫወቱ ተጨዋቾች የውድድር አመቱ ምርጥ ተጨዋች #አምስት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ኤድዋርዶ ካማቪንጋ ፣ አንቷን ግሪዝማን ፣ ዊሊያም ሳሊባ ፣ ኦርሊየን ቹዋሜኒ እና ማይግናን የአመቱ ምርጥ ተጨዋች እጩ ሆነው መቅረብ ችለዋል።

የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቡንደስሊጋ ተጨማሪ ክለብ ያሳትፋል !

ቦርስያ ዶርትመንድ ፒኤስጂን ማሸነፉን ተከትሎ የጀርመን ቡንደስሊጋ በቀጣይ የውድድር አመት ተጨማሪ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ቦታ እንደሚያገኙ ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ በቀጣይ የውድድር አመት በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ #አምስት የጀርመን ቡንደስሊጋ ክለቦች ተሳታፊ የሚሆኑ ይሆናል።

በቡንደስሊጋው እነማን ደረጃውን ይዘዋል ?

1️⃣ ባየር ሊቨርኩሰን :- 81 ነጥብ

2️⃣ ባየር ሙኒክ :- 69 ነጥብ

3️⃣ ስቱትጋርት :- 64 ነጥብ

4️⃣ ሌፕዚግ :- 62 ነጥብ

5️⃣ ዶርትመንድ :- 57 ነጥብ ተሳታፊ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🏆🏆CHAMPION 🏆🏆

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ሪያል ማድሪድ ከቦርስያ ዶርትመንድ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሻምፒዮን መሆን ችለዋል።

የሎስ ብላንኮዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ዳኒ ካርቫል እና ቪንሰስ ጁኒየር ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር ስድስተኛ የሻምፒየንስ ሊግ ግቡን አስቆጥሯል።

ጣልያናዊው አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ #አምስት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ በማሸነፍ በውድድሩ ታሪክ ቀዳሚው አሰልጣኝ መሆን ችለዋል።

ቪንሰስ ጁኒየር በሁለት የተለያዩ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜ ጨዋታዎች ላይ ግብ ማስቆጠር የቻለ በእድሜ ትንሹ ተጨዋች መሆን ችሏል።

ሪያል ማድሪድ አስራ አምስተኛ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫውን ማሳካት ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ማድሪድ የምባፔን ዝውውር ይፋ ሊያደርጉ ነው ! ሪያል ማድሪድ ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔን ከፒኤስጂ በነፃ ዝውውር ማስፈረማቸውን ዛሬ ወይም በሚቀጥሉት ቀናት በይፋ  እንደሚያሳውቁ ተገልጿል። በቅርቡ ፒኤስጂን ከሰባት አመት በኋላ እንደሚለቅ ይፋ ያደረገው ኪሊያን ምባፔ ለሪያል ማድሪድ የአምስት አመት ኮንትራት መፈረሙን ለክለቡ ቅርበት ያላቸው ምንጮች አረጋግጠዋል። ኪሊያን ምባፔ…
ሪያል ማድሪድ ኪሊያን ምባፔን በይፋ አስፈረመ !

የስፔኑ ሀያል ክለብ ሪያል ማድሪድ ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ከፒኤስጂ በነፃ ዝውውር ማስፈረማቸውን ከደቂቃዎች በፊት ይፋ አድርገዋል።

የ 25ዓመቱ የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ለሪያል ማድሪድ እስከ 2029 የውድድር ዘመን የሚያቆየውን የ#አምስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ይፋ ሆኗል።

ኪሊያን ምባፔ ለሪያል ማድሪድ በመፈረሙ ምክንያት የፊርማ ጉርሻ በአምስት አመታት ተከፋፍሎ የሚከፈል 100 ሚልዮን ዩሮ እንደሚያገኝ ተገልጿል።

ኪሊያን ምባፔ በሪያል ማድሪድ ቤት የዘጠኝ ቁጥር ማልያ እንደሚለብስ ሲገለፅ በቀጣይ የሉካ ሞድሪችን አስር ቁጥር እንደሚረከብ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የማድሪድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል

በአሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ የሚሰለጥነው የላሊጋው ክለብ ሪያል ማድሪድ የወርሀ ነሐሴ የወሩ ምርጥ ተጨዋች #አምስት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ሮድሪጎ ፣ ቪንሰስ ጁኒየር ፣ ቫልቬርዴ ፣ ኪሊያን ምባፔ ፣ ብራሂም የወርሀ ነሐሴ የሪያል ማድሪድ ወሩ ምርጥ ተጨዋች እጩ ሆነው መቅረብ ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe