TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
19K photos
296 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
加入频道
#SUDAN

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ አገር መከላከያ ምክትል የኢታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ የተመራ የልዑካን ቡድን በሱዳን የሥራ ጉብኝት በማድረግ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብደላ ሐምዶክ ላይ የተቃጣውን ግድያ ሙከራ አስመልክቶ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ መልዕክትን አድርሷል።

የልዑካን ቡድኑ በጉብኝቱ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብደላ ሐምዶክ፣ የሱዳን መከላከያ ሚኒስትር ጄኔራል ጀማለዲን ኦማር እና የሱዳን ኤታማዦር ሹም ጄኔራል መሃመድ ኡስማን አልሃሰን ጋር ውይይቶችን በማካሄድ በቅርቡ በሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ላይ የተቃጣው የግድያ ሙከራ አውግዘዋል። ኢትዮጵያ እንዲህ አይነት ባለው አስቸጋሪ ሁኔታ ከሱዳን ጎን እንደምትቆም ያረጋገጡ ሲሆን የሱዳን ሰላም የኢትዮጵያ እንደሆነ ሁሉ የሱዳንም ችግር እንዲሁ የኢትዮጵያ እንደሆነ አስምረውበታል።

በሱዳን በኩልም ኢትዮጵያና ሱዳን የረጅም ጊዜ ግንኙነት ያላቸውና ኢትዮጵያ ለሱዳን ችግር ፈጥና የምትደርስ መሆኗን እና ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በሱዳን የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም የነበረው የሰላም ድርድር ውጤታማ እንዲሆን የተጫወቱትን ቁልፍ ሚና በማስታወስ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሱዳንን ብሔራዊ ጥቅምን የሚያስጠብቅ በመሆኑ ድጋፍ እንዳላቸው ተገልጿል።

[ በሱዳን የኢትዮጵያ ኢንባሲ ]

#ቲክቫህ_ወቅታዊ
@tikvahethmagazine @emush21
#Ethiopia #Sudan

መንግሥት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ከአካባቢ ሚሊሻ ጋር የተፈጠረውን ክስተት በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን ጠቅላይ ሚስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ፡፡

"ሁለቱ ሀገራት እንዲህ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ሁሌም የውይይትን አማራጭ የሚከተሉ በመሆናቸው ክስተቱ የሁለቱን ሀገራት ጥብቅ ትስስር አያላላውም" ብለዋል ጠቅላይ ሚስትሩ በትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት አስተያየት፡፡

"ክስተቱን እንደ መልካም አጋጣሚ ወስደው በማራገብ ልዩነትን ለማስፋት የሚጥሩ አካላት የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊ ትስስር ያልተረዱ ናቸው" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡ (ኢቲቪ)

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot
#ETHIOPIA #SUDAN

በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ሱዳንና ኢትዮጵያ በሚዋሰኑበት የድንበር አካባቢ የተከሰተውን ጉዳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለቢቢሲ ለቀረበላቸው ጥያቄ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አምባሳደሩ "የተወሰኑ የሱዳን ታጣቂዎች ድንበር ተሻግረው የአርሶ አደሩን ንብረት ለመውሰድ ሙከራ በሚያደርጉበት ወቅት ለመከላከል የተደረገ ክስተት ነው" ሲሉ ግጭቱን ገልጸውታል።

አክለውም ታጣቂዎቹ "የአርሶ አደር ማሳ ውስጥ ገብተው አንዳንድ ነገሮችን የመውሰድ፣ ወደዚያ የማስፋፋትና ከሕግ አግባብ ውጪ የመሄድ ሁኔታ ስለታየ ይህንን ነገር መመለስ ስለሚያስፈልግ እርምጃ ተወስዷል" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ሁለቱ አገራት በጉዳዩ ላይ በመንግሥት ደረጃ ግንኙነት ማድረጋቸውን ገልፀው፤ ግጭቱን "ይህ የሱዳን መንግሥት ፍላጎት አይደለም" ብለዋል።

የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ባለፈው እሁድ በኢትዮጵያ የተሳካ ጉብኝት ማድረጋቸውን የገለፁት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ይህ ችግር "የሱዳን መንግሥት የታችኛው እርከን ችግር ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

ይህንን ችግር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት በአጭር ጊዜ የሁለቱ አገራት ከፍተኛ አመራሮች ለመነጋገር ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ለቢቢሲ አስታውቀዋል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagBot
#Sudan

የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ ሃገሪቱን ከውድቀት ለመታደግ በሚያስችል መልኩ ወቅታዊ ቀጣናዊ ስጋቶችን ታሳቢ አድርጎ ተዋቅሯል ያሉትን አዲስ የካቢኔ አባላት ዝርዝር ይፋ አድርገዋል።

አዲሱ መንግሥታቸው 25 ሚኒስትሮች እንደሚኖሩት ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የትምህርት ሚኒስትር ማን ይሁን በሚለው ላይ ገና ስምምነት አለመደረሱን ተናግረዋል።

ከአዲሱ ተሿሚ ሚኒስተሮች መካከል ከዚህ ቀደም ፍትሕና እኩልነት እንቅስቃሴ የተሰኘ አማፂ ቡድን ይመራ የነበረው ጂብሪል ኢብራሂም ይገኝበታል።

ሌሎች አማጺያንም የማእድን፣ የላይቭስቶክ፤ የማህራዊ ልማት፤ የትምህርትና የፌደራል ሚኒስትሪዎችን እንዲመሩ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት ሶስት የአማጺ መሪዎች የሽግግር ምክርቤቱ አባል እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሹመት ለቀድሞው የአልበሽር ተቃዋሚ ኡማ ፓርቲ መሪ ሳዲቅ አልማሃዲ ልጅ መሪየም ሳልዲቅ አልማሃዲ ተሰጥቷል፡፡

አዲሱ መንግሥት አገሪቱ ምርጫ እስከምታካሄድበት 2024 ድረስ በሥልጣን ላይ ይቆያል ተብሏል። (AlAin, BBC)

@tikvahethmagazine @tikvahmagBOT
#Sudan

ከዳቦ ፣ ከዱቄት ፣ ከነዳጅ እና ከምግብ ማብሰያ ጋዝ ጥያቄ ጋር ተያይዞ በሱዳን የነበረው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ባለፉት ጥቂት ቀናት ተባብሶ ቀጥሏል፡፡

በተቃውሞ ሰልፈኞቹ የተለያዩ ዘረፋዎች የተፈጸሙ ሲሆን የፀጥታ ኃይል ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ንብረቶችም በእሳት ወድመዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ በደቡብ እና በሰሜን ዳርፉር እንዲሁም በሰሜን ኮርዶፋን ግዛቶች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን የሱዳን ዜና ወኪል ዘግቧል፡፡

በደቡብ ዳርፉር ግዛት የተቋቋመው የፀጥታ ኮሚቴ በግዛቱ ዋና ከተማ ኒያላ ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከ ማለዳው 12 ሰዓት መንቀሳቀስ እንደማይቻል አስታውቋል፡፡ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችም እንዲዘጉ መወሰኑም ከእርምጃዎቹ መካከል ናቸው፡፡

ሌላው ከፍተኛ ተቃውሞ የነበረበት የሰሜን ዳርፉር ግዛት የፀጥታ ኮሚቴም እንዲሁ ማክሰኞ ዕለት በመላ ክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል፡፡ ከምሽት 12 ሰዓት እስከ ማለዳ 12 ሰዓት የእንቅስቃሴ ገደብ በተጣለበት በዚሁ ግዛት ፣ ትምህርት ቤቶች ፣ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እና የገበያ ስፍራዎች እንዲዘጉም ተወስኗል፡፡

በምስራቅ ሱዳን እና በሌሎችም አንዳንድ አካባቢዎች አሁንም ህዝባዊ ተቃውሞው መቀጠሉን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ከሰልፎቹ ጋር ተያይዞ በሰው ላይ ስለደረሰው ጉዳት በዘገባው የተባለ ነገር የለም፡፡

ፕሬዝዳንት ኡመር አል በሽር ከስልጣን ተወግደው ከተመሰረተው ሽግግር በኋላ ከዶላር አንጻር የሱዳን ፓውንድ ዋጋ በከፍተኛ መጠን የወደቀ ሲሆን በሀገሪቱ የዋጋ ግሽበት እና አጠቃላይ የኢኮኖሚ አለመረጋጋት ተከስቷል፡፡ (AlAin)

@tikvahethmagazine @tikvahmagBOT
#Sudan 🇸🇩

ትናንት የዓለም የሴቶች ቀን ሱዳን ውስጥ ሲታሰብ በሀገሪቱ ያለውን ወታደራዊ አገዛዝ ተቃውመው አደባባይ የወጡ ሰልፈኞች አስለቃሽ ጪስ ተተኮሰባቸው።

የተቃውሞ ሰልፉ የተጠራው በሴቶች የመብት ተማጋች ስብስቦች እና ካለፈው ጥቅምት ወር ወዲህ ሥልጣን የተቆጣጠረበትን ወታደራዊ ኃይል የሚቃወሙ ሰልፎች አስተባባሪዎች ነው።

ካለፈው ጥቅምት ወር መፈንቅለ መንግሥት ወዲህ ባሉት አራት ወራት ውስጥ በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ ቢያንስ 85 ሰዎች መገደላቸውንና በመቶዎች የሚቆጠሩት ደግሞ መጎዳታቸውን ዘገባዎች ያሳያሉ።

በትናንት ዕለትም የተቃውሞ ሰልፈኞቹ ወደ ፕሬዝደንቱ መኖሪያ ሲቃረቡ የጸጥታ ኃይሎች ከአካባቢው እንዲበተኑ አስለቃሽ ጭስ መተኮሳቸው ተገልጿል፤ የተጎዱ ስለመኖራቸው የተባለ ነገር የለም።

የሱዳን ሕዝብ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሀገሪቱ የኤኮኖሚ ውድቀት ውስጥ በምትገኝበት በዚህ ወቅት ተባብሷል። ከትናንት ማክሰኞ ዕለት ጀምሮ የሀገሪቱ መገበያያ የሆነው የሱዳን ፓውንድ 19 በመቶ ዋጋው ወርዷል። (DW)

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
#Sudan 🇸🇩

በሱዳን በዚህ የክረምት ወቀት በተከሰተው የጎርፍ አደጋ የ105 ዜጎቿን ህይወት ያጣች ሲሆን 96 ሰዎችም ተጎድተዋል።

የሀገሪቱ የሲቪል መከላከያ ብሔራዊ ምክር ቤት ሪፖርት እንደሚያሳየው በአደጋው 34,328 ቤቶች ሲፈርሱ ፤ 46,428 ሱቆች ከፊል ውድመት ደርሶባቸዋል።

ሀገሪቱ ከ1940ዎቹ ወዲህ የከፋ የተባለውን አደጋ አስተናግዳለች የተባለ ሲሆን የክረምቱ ወራት ባለመጠናቀቁ የጉዳቱ መጠን እንደሚጨምር ተሰግቷል። (SUNA)

@tikvahethmagazine
TIKVAH-MAGAZINE
#Sudan 🇸🇩 በሱዳን በዚህ የክረምት ወቀት በተከሰተው የጎርፍ አደጋ የ105 ዜጎቿን ህይወት ያጣች ሲሆን 96 ሰዎችም ተጎድተዋል። የሀገሪቱ የሲቪል መከላከያ ብሔራዊ ምክር ቤት ሪፖርት እንደሚያሳየው በአደጋው 34,328 ቤቶች ሲፈርሱ ፤ 46,428 ሱቆች ከፊል ውድመት ደርሶባቸዋል። ሀገሪቱ ከ1940ዎቹ ወዲህ የከፋ የተባለውን አደጋ አስተናግዳለች የተባለ ሲሆን የክረምቱ ወራት ባለመጠናቀቁ የጉዳቱ…
#Sudan 🇸🇩

በሱዳን የደረሰውን ከባድ ጎርፍ ተከትሎ ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 134 የደረሰ ሲሆን በርካታ ቤቶች ደግሞ ወድመዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት ብቻ በሱዳን 20 ሰዎች በጎርፍ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል።

ይህም በሱዳን ጎርፍ ከጀመረ ግንቦት በኋላ የሞቱ ሰዎችን ቁጥር ወደ 134 ከፍ አንዲል ያደረገ ሲሆን በጎርፉ ህይወታቸው ካለፉት በተጨማሪ 120 ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ተነግሯል፡፡

(AlAin 📸 Reuters , African News)

@tikvahethmagazine
#Sudan

በጀነራል አልቡርሃን በሚመራው የሱዳን ጦር እና በጀነራል መሀመድ ሀምዳን ደጋሎ ወይም ሄሚቲ በሚመራው ታጣቂ ቡድን መካከል የተጀመረው ጦርነት ወደ ሁለተኛ ዓመቱ እየተጠጋ ነው።

ቅዳሜ ዕለት የሱዳን ጦር በደቡባዊ ዋና ከተማ ካርቱም በፈጸመው የአየር ጥቃት በትንሹ 23 ሰዎች ሲገደሉ ከ40 በላይ መቁሰላቸው ተገልጿል።

በዚህ የአየር ድብደባ በደቡባዊ ካርቱም በሚገኘው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን (RSF) ዋና ካምፕ ኢላማ ያደረገ ነው ቢባልም ጥቃቱ በገበያ ላይ ያሉ ንጹሃን ላይ ጉዳት አድርሷል።

ለ18 ወራት በዘለቀው የእርስ በርስ ጦርነት እስከ 150,000 የሚደርሱ ሰዎች ህይወት ሳያልፍ እንዳልቀረ ሲገመት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችንም ያፈናቀለ ነው።

እንደ ተመድ ተቋማት ግምት በዚህ ጦርነት 10 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች ተፈናቅለዋል። ከዚህም ውስጥ 2.4 ሚሊዮን የሚሆኑት ወደ ኢትዮጵያ እና ሌሎች ሀገራት የተሰደዱ ናቸው ተብሏል።

የውጭ ጣልቃ ገብነት

የሱዳን ጦር የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን (RSF) በማስታጠቅ ትደግፋለች በሚል ይወቅሳል። ዩኤኢ ግን ይህንን አስተባብላለች።

በአንጻሩ የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን (RSF) ግብጽ የሱዳን ጦርን በመደገፍ በአየር ላይ ጥቃት እያደረሰች ነው ሲሉ  በጀነራል መሀመድ ሀምዳን ደጋሎ ከሰዋል። ግብጽ ግን ይህን አስተባብላለች።

ግብጽ ላይ የተጣለው እገዳ

የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ (RSF) መሪ መሀመድ ሀምዳን ዳሎ ( ሄሜቲ ) ካይሮ በሀገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብታለች በሚል ከሱዳን ወደ ግብፅ የሚደረጉ ምርቶች ላይ እገዳ መጣሉን በትላትናው ዕለት አስታውቀዋል።

ሱዳን የግብርና እንዲሁም የቁም እንስሳትን ወደ ግብጽ የምትልክ ሲሆን እገዳውን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በተቆጣጠረባቸው አከባቢዎች ተፈጻሚ የሚሆን እንደሆነ ተገልጿል።

የብሉ ናይል ክልል መሪ እና የRSF አባል የሆኑት አቡ ሹውታል ነጋዴዎች ወደ ግብፅ ምንም አይነት ምርት እንዳይልኩ አስጠንቅቀዋል። "ነጋዴዎቹ ከምርታቸው አንድ ኪሎ እንኳን ቢልኩ ይቀጣሉ" ሲሉ ነው የገለጹት። 

"የእኛ ምርት ከግብፅ በስተቀር ለሁሉም ጎረቤቶቻችን መላክ ይቻላል" ያለ ሲሆን "በአል-ዳባ መሻገሪያ በኩል ወደ ግብፅ የሚሄድ ማንኛውም የጭነት መኪና እንደ ጠላት ሊወሰድ ይገባል" ሲል አክሏል።

ምንጭ: BBC , Asharq Al-Awsat

@tikvahethmagazine
#Sudan 🇸🇩

የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ከ14 ሚሊየን በላይ ሰዎች በሱዳን በተቀሰቀሰው ግጭት ምክንያት መፈናቀላቸውን አስታውቋል። 

ከዚህ ውስጥ 11 ሚሊየን የሚሆኑት የሀገር ውስጥ ተፈናቃይ ሲሆኑ፤ 3.1 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ድንበር አቋርጠው የተሰደዱ ናቸው ተብሏል።

ከ1 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው ተፈናቃይ ከአንድ ጊዜ በላይ የተፈናቀሉ ናቸው።  ካለፈው ወር ጀምሮ ደግሞ 200,000 ሰዎች መፈናቀላቸውንም ነው የገለጸው።

በሱዳን አሁን ላይ ከ25 ሚሊዮን ህዝብ በላይ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልገዋል ሲል ነው ድርጅቱ ያስታወቀው።

@tikvahethmagazine
ኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጭ ስደተኞችን የምታስተናግድ ሀገር ናት። ከአንድ ሚሊዮን በላይ የውጭ ስደተኞች በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ተጠልለው ይገኛሉ።

በልዩነትም ሁለት ዓመት ሊሞላው ወራቶች በቀሩት የሱዳን ጦርነት ምክንያት ከ67,775 ሰዎች በላይ ወደ ኢትዮጵያ ተሰደዋል።

ከዚህ ውስጥ ከ16ሺ በላይ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በነበረው ጦርነት ተሰደው የወጡ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛው የሥደተኞች ኮሚሽን (UNHCR) ሪፖርት ያመለክታል።

#Sudan  #Ethiopia   #UNHCR

@tikvahethmagazine