TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
19K photos
296 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
加入频道
ኢትዮጵያ በ11 ወራት ውስጥ ወደ ውጪ ከተላከ የቡና ምርት 1.2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷ ተነገረ

በበጀት ዓመቱ 11 ወራት ውስጥ ወደ ውጪ ከተላከው አጠቃላይ የቡና ምርት 1 ቢሊየን 208 ሚሊየን 73 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ገቢ መገኘቱን የቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ።

በባለስልጣኑ መረጃ መሰረት ፦

- በበጀት ዓመቱ 11 ወራት በአጠቃላይ 252,466.98 ቶን የቡና ምርት ወደ ውጪ ተልኳል።

- በግንቦት ወር ብቻ 43,481.02 ቶን በመላክ የእቅዱ 105% ማሳካት ሲቻል በወሩ ብቻ 209.54 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል።

- የግንቦት ወር ውጥል ከ 2013/2014/2015 ዓ/ም በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወራት ከተላከው ምርት ከፍተኛ ውጤት የታየበት እንደሆነ ባለስልጣኑ ገልጿል።

#Coffee #Ethiopia

@tikvahethmagazine
#Coffee ☕️

የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን በሰኔ ወር 46 ሺ ቶን ቡና ኤክስፖርት ማድረጉን አስታውቋል። ይህም 218 ሚሊዮን ዶላር ገቢ በማስገኝት ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።

በተያዘው በጀት ዓመትም 285,500 ቶን ቡና ለውጪ ገበያ በማቅረብ 1.43 ቢሊዮን ዶላር የተገኘ ሲሆን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በገቢ ደረጃ 7.5 በመቶ እንዲሁም ከምርት አንጻር የ20 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

@tikvahethmagazine