TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
18.9K photos
292 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
加入频道
#Bonga 🦟

የካፋ ዞን የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽህፈት ቤት እስካሁን በተገኘው መረጃ ባለፉት አንድ ወር አጋማሽ 213 ሰዎች በከተማ አስተዳደሩ በወባ በሽታ መጠቃታቸውን አስታውቋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ በሽታውን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲያስችል ''ሱምሺልድ'' የተባለ አዲስ የኬሚካል ርጪት ሥራ ለመሥራት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን፤ በአሁን ሰዓትም ኬሚካሉን ቤት ለቤት ዞረው ለሚረጩ አካላት ስልጠና እየተሰጠ እንደሆነ የጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሪት መቅደስ ተረፈ ገልጸዋል።

በዚህም 20 ሰዎች ስልጠናውን እየወሰዱ ሲሆን ስልጠናው ሲጠናቀቅ ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ የኬሚካል ርጭቱ ሥራ እንደሚጀመር አክለዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ነዋሪዎችም የአልጋ አጎበር በአግባቡ መጠቀምና በየአከባቢው ለወባ መራቢያ ምቹ የሆኑ ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን የማፋሰስና የመድፈን ሥራዎችን በትኩረት በመስራት የበሽታውን መከላከል ስራ መደገፍ እንዳለባቸው ጽህፈት ቤቱ አሳስቧል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
#Bonga 🛬

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ቦንጋ ከተማ ለሚገነባው ቀላል የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ቀዳማዊት እመቤተ ዝናሽ ታያቸው እና የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በተገኙበት የመሰረት ድንጋይ በዛሬው ዕለት ተቀምጧል።

@tikvahethmagazine