TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
19K photos
292 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
加入频道
#Assosa 📍

በጫት አጠቃቀም ገደብ ለመጣል እና ተዛማጅ ሱስ አምጭ ንጥረ ነገሮችን ለመከላከል በአሶሳ ከተማ አስ/ር ምክር ቤት ጸድቆ በወጣዉ መመሪያ ቁጥር 6/2013 ላይ ውይይት ተደርጓል።

መድረኩ የአሶሳ ከተማ አስ/ር ምክር ቤት ከተስፋ ብልጭታ በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ አቃቤ ህግ መምሪያ ቃቤ ህግ አቶ ገመቹ በመመሪያው ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በመመሪያዉ መሰረትም፡-

#ጫት፡-

- ከት/ቤት 1ኪ/ሜ ርቀት፣ ከጤና ተቋማት 800 ሜትር፣ ከሲቪክ ማህበራትና ተቋማት 600 ሜትር በት/ቤቶችና የመንግስት ተቋማት አካባቢ በማንኛዉም ሁኔታ መሸጥ ክልክል ነዉ፡፡

- ከ21 ዓመት በታች የሆነ ዕድሜ ያለዉ የጫት ንግድ ፍቃድ ማዉጣት፣ ጫት መሸጥ፣ ማሸጥ እንዲገዛ መላክም ሆነ አብሮ መቃም አይቻልም፡፡

- ንግድ ፈቃድ ሰጭ አካል የጫት ንግድ ፈቃድ ሲሰጥ የተቀመጠዉን ርቀትና የእድሜ ገደብ አጣርቶ መሆን አለበት፡፡

- ማንኛዉም የመንግስትም ሆነ የግል ድርጅት ለጫት መሸጫ ማከራየት አይቻልም፡፡

- ማንኛዉም የመንግስት ሰራተኛ በስራ ሰዓት ጫት መቃም አይቻልም፡፡

- ማንኛዉም የጫት ነጋዴ ጫት ወደ ከተማ ሲያስገባ ገረባዉን እዛዉ አስቀርቶ የምትቃመዉን ቅጠል ብቻ መሆን አለበት፡፡

#ሺሻ

- ማንኛዉም ሰዉ በመኖሪያ ቤት፣ በንግድ ተቋማት በማንኛዉም የመንግስትም ሆነ የግል ድርጅት እና የከተማ ክልል ዉስጥ ሽሻና ተዛማጅ ሱስ አምጭ ነገሮች ማጨስም ሆነ ማስጨስ በምንም አይነት ሁኔታ አይፈቀድም፡፡

- ለሽሻና ተዛማጅ ሱሶች የሚያገለግሉ ዕቃዎችን ለሽያች ማቅረብ የተከለከለ ነዉ፡፡

የሚሉና መሰል ክልከላዎችና ገደቦች በመመሪያዉ መካተታቸዉ ተገልጿል ሲል የአሶሳ ከተማ አስተዳደር አስታውቋል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot