#ሐረማያ
የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ሕይወት ፋና ኮምፕርሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በዘመናዊ የህክምና መሳሪያ የጭንቅላት ቀዶ ህክምና (Endoscopic Third Ventriculostomy) አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
በዚህም በምስራቅ ኢትዮጵያ ብቸኛ የሆነውን የህፃናት ጭቅላት ውሰጥ የውሀ መጠን መጨመር ህመም (Hydrocephalus) ቀዶ ህክምና አገልግሎት ተጀምሯል።
ሪች አናዘር ፋውንዴሽን የዘመናዊ ህክምና መሳሪያ (Endoscopy) ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በተጨማሪ ባለሞያዎችን በመላክ በሆስፒታሉ ላሉ የጭንቅላት ቀዶ ህክምና ቡድን በማሽኑ አጠቃቀም ዙሪያ ለአንድ ሳምንት ስልጠና ሰጥቷል ።
በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የአንጎል እና ህብለ ሰረሰር ቀዶ ህክምና እስፔሻሊስት ዶ/ር ዮርዳኖስ አሻግሬ በአንድ ሳምንት ቆይታቸው የ Endoscopic Third Ventriculostomy አጠቃቀምን በሚገባ በሆስፒታሉ ላሉ የቀዶ ህክምና ቡድን ስልጠና መስጠት መቻሉን እና በዚህም ሂደት ለሰባት ታካሚዎች በመሳሪያው አገልግሎት መሰጠቱን ገልፀዋል።
የአገልግሎቱ መጀመር ቀደምሲል ለህፃናቱ ህመማቸውን ለማከም ይደረግላቸው ከነበረው ከጭንቅላታቸው እሰከ ሆድ የሚደርስ ትቦ የማስገባት ሂደትን የሚያስቀር እና ሊፈጠሩ ይችላሉ ተብለው የሚገመቱትን የኢፌክሽን እና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች ስጋት እንደማይሆኑ የአንጎል እና ህብለሰረሰር ቀዶ ህክምና እስፔሻሊስት ዶ/ር መሀመድኑር አብዱላሂ አስረድተዋል።
@tikvahethmagazine

በናይጄሪያ በነዳጅ ጫኝ ቦቴ ላይ በደረሰ የፍንዳታ አደጋ በትንሹ 94 ሰዎች ሞቱ
በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ ነዳጅ ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ቦቴ ላይ በደረሰ ፍንዳታ በትንሹ 90 ሰዎች ሲሞቱ 50 ሰዎች መቁሰላቸውን አናዱሉ ዘግቧል።
የነዳጅ ማጠራቀሚያው የፈነዳው በሀገሪቱ ጂጋጋ ግዛት፤ በፍጥነት መንገድ ላይ እንደሆነ ሲነገር ሲኤን ኤን በበኩሉ የሟቾች ቁጥር 94 መድረሱን ዘግቧል።
አደጋው የተከሰተው ትላንት ምሽት ላይ ሲሆን የነዳጅ ማጠራቀሚያ ቦቴው ተቀጣጥሎ ከባድ የቃጠሎ አደጋ ያደረሰው በዛሬው እለት መሆኑም ነው የተነገረው።

TIKVAH-MAGAZINE
#የቀጠለ ° "በሆስፒታሉ ደም እየፈለገ ባለመገኘቱ ሳምንት በድንገተኛ ክፍል ውስጥ የተኛ ታማሚ አለ" ° "ከጤና ሚኒስቴር የተላኩ የባለሞያዎች ቡድን ለወባ ታማሚዎች ድንኳን ተዘጋጅቶ ለብቻ ቢታከሙ የሚል ምክረ ሐሳብ አስቀምጧል" - የኦቶና ሪፈራል ሆስፒታል አመራር በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ስር ያለው የኦቶና ሪፈራል ሆስፒታል የሚገኙ የወባ ታማሚዎች የደም ልገሳ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ የደም እጥረት…
#ወባ
° "ፈዋሽነቱ ያልተረጋገጠ መድኃኒት በኮንትሮባንድ ወደ በኢትዮጵያ እየገባ ነው"
° "ሆስፒታል ገብተው መታከም የሚያስፈልጋቸው የወባ ታማሚዎች ቁጥር በጣም በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል"
° "መድኃኒቶችን ከተቀበሉ በኋላ ይሸጥ ወይስ ለታካሚ ይዋል ማረጋገጫ የለንም " -የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት
___
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሰሞኑ በወላይታ ዞን ስለተከሰተው የወባ በሽታ ሥርጭት ተከታታይ ዘገባ እየሰራ ነው።
በዞኑ ስላለው የህመሙ ሁኔታ እና የበሽታው ስርጭት ባሻገር የወባ የመድሃኒት አቅርቦት ችግር አለ የሚል ቅሬታም ተቀብለናል።
በጉዳዩ ላይ ምላሻቸውን ለማካተት የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሐዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።
____
ቲክቫህ የኢትዮጵያ የመድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴን ጠይቋል።
በምላሻቸውም ተቋሙ በአሁኑ ሰዓት እንደሃገር ከወባ በሽታ ጋር በተገናኘ እየሰራ ያለውን ሥራ ነግረውናል።
ኃላፊው የወባ በሽታን በተመለከተ ሦስት ነገሮች መታየት አለባቸው ይላሉ:- ኬሚካል ርጭት ፣አጎበር እና መድኃኒት።
የአጎበር ስርጭትን እና የኬሚካል ርጭትን በተመለከተ ከዚህ በፊት እንደ ሃገር 19 ሚሊየን አጎበር መሰራጨቱን እና የኬሚካል ርጭትም መከናወኑን ገልጸው አሁንም ወቅቱን ጠብቆ የኬሚካል እና አጎበር ስርጭት ይከናወናል ብለዋል።
የወባ መድሃኒቶችን በተመለከተም በአሁኑ ሰዓት #Coaretm እና #Chloroquine የተሰኙ ሁለት ዓይነት የወባ መድሃኒቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል።
"ኢትዮጵያ ውስጥ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከ 70 በመቶ በላይ የወባ መነሻው Plasmodium falciparum በተሰኘው የወባ ፓራሳይት ሲሆን የሚታከመውም በ Coaretm በተሰኘ መድኃኒት ነው።
ኳርተምን በተመለከተም በቂ ክምችት አለ በግሎባል ፈንድ(Global Fund) ተገዝቶ የቀረበ ነበር መንግስትም በጀት ይዞ የተገዛ አለ በእርዳታም ከቻይና እየመጣ ያለ አለ። እነዚህ ተደምሮ ከአሁን በኋላ ቢያንስ ለአምስት ወር ሊቆይ የሚችል ክምችት አለ።
አሁን ላይ በገመገምነው የፍጆታ መጠን ፣ለአምስት ወር የሚበቃ ክምችት አለን፣ በቂ አይደለም አሁን ላይ ግን በሆስፒታሎች ላይ ችግር ይገጥማል ብለን አናስብም "የስርጭት እና የአጠያየቅ ችግር ከሌለ በስተቀር" ሲሉ ነው የገለጹት።
Chloroquine የተሰኘው እና በ Plasmodium Vivax በተሰኘች ፓራሳይት የሚመጣ የወባ በሽታን ለማከም የሚረዳ መድኃኒት በተመለከተም "ይሄ መድኃኒት ከዚህ ቀደም መጠቀም ቆሞ ነበር በተወሰነ ደረጃ በሌሎች ለጋሽ ድርጅቶች እና ገዢ አካላት እንዲገባ ለማድረግ ተሞክሯል በቂ አልነበረም የገባው በዚህ ምክንያት ስጋት አለ ስጋት ብቻ አይደለም አንዱ ጋር ኖሮ ሌላው ጋር ላይኖር ይችላል" ብለዋል።
በለጋሽ ድርጅቶች በኩል የመጣውም ተሰራጭቶ እያለቀ ሲሆን በመንግስት በጀት አስቸኳይ ግዢ ተከናውኖ ከሁለት ሳምንት በኋላ ሃገር ውስጥ እንደሚገባም ሰምተናል።
Chloroquine ብዙም ተጠቃሚ የለውም ብለን ነው የምንወስደው ያሉት ዳይሬክተሩ አሁን ባለው የወባ ሥርጭት ግን አዲስ ነገር እየታየ ነው በ Vivax ሳቢያ የሚታመሙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ ገልጸዋል።
የአቅርቦት ችግር ስጋት ቢኖርም ነገር ግን ሙሉ በሙሉ መድሃኒቱ አለመጥፋቱን ችግሩን ለመቅረፍም እየተሰራበት መሆኑንም ነው የነገሩን።
የራሱ ጥናት ቢያስፈልገውም አሁን ባለው መረጃ ሆስፒታል ገብተው መታከም የሚያስፈልጋቸው የውባ ታማሚዎች ቁጥር በጣም በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል ቁጥር መጨመር ብቻ አይደለም ኢትዮጵያ ውስጥ የወባ የህመም መጠኑም ጨምሯል ብለዋል።
የህመም መጠኑ ሲጨምር ደግሞ Coaretm እና Chloroquine ላያድኑ ይችላሉ ያሉት ዳይሬክተሩ፥ በዚህ ሳቢያ #Artesunate_Injection የተሰኘ መድኃኒት ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ተናግረዋል።
Artesunate Injection የሚያስፈልጋቸው የወባ ታማሚዎች ቁጥር ከዚህ በፊት ቁጥሩም ሆነ መጠኑ አነስተኛ ስለነበር የተጠቀሰው መድኃኒት ፍጆታ በጣም ትንሽ የነበረ ሲሆን አሁን ግን በወባ መባባስ ምክንያት የመድሃኒቱ ፍላጎት #በስድስት_እጥፍ ማደጉን ገልጸዋል።
የተጠቀሰው መድሃኒት በሃገር ውስጥ የነበረው ክምችት አስቀድሞ በነበረው ፍጆታ መሰረት በመሆኑ ስጋት ነበረን በመሃል ላይም ተቆራርጦ ነበር አሁን በ UNICEF ድጋፍ ተገዝቶ መግባቱን እና በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ከቻይና የሚገቡ ተጨማሪ መድሃኒቶች ይኖራሉ ብለውናል።
ከፍል ሁለት ይቀጥላል . . .
@tikvahethmagazine💬 @tikvahmagbot

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ክፍልሁለት
ቲክቫህ የኢትዮጵያ የመድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴን በአንዳንድ አካባቢዎች አለ የሚባለው የመድሃኒት እጥረት በምን ምክንያት የተከሰተ ነው ሲል ጠይቋል።
መድሃኒት ከዚህ ቀደም ካለው የመቆራረጥ አዝማሚያ አንጻር ስጋት ስላለ ጤና ጣቢያዎች ከሚያስፈልጋቸው በላይ ይጠይቃሉ በዚህ ጊዜ በቅርንጫፍ ላይ እጥረት ሊያጋጥም ይችላል ሲሉ አስረድተዋል።
"በእኛ ግምገማ ግን ያለቀ መድኃኒት የለም በ Chloroquine በኩል የተወሰነ ችግር ሊገጥመም ይችላል ከዚህ ውጪ ሁሉም መድሃኒቶች በበቂ ክምችት በቅርንጫፍ ላይ አሉ" ነው ያሉት።
ይሄ ማለት ግን መድኃኒቶቹ በጤና ተቋማት መድረሱን አያረጋግጥም ብለዋል።
ለአብነትም በወላይታ አካባቢ ስላላው ሁኔታ የምክር ቤት አባላትም ጭምር ባሉበት ገምግመናል ያገኘነው ውጤት ግን ከታማሚ ቁጥር በላይ መድሃኒት መሰራጨቱን ነው ሲሉ ጠቅሰዋል።
ጠንካራ ሲስተም በሌለበት መድሃኒት ከጤና ተቋማት ወጥቶም ሊሸጥ ይችላል ይህ አንዱ ስጋታችን ነው ያሉ ሲሆን በግል ፋርማሲዎችም የመንግስት መድኃኒቶች እየተገኙ ነው ሲሉ አቶ ሰለሞን ነግረውናል።
"የኛ መድኃኒቶች የተቋማችን አርማ አለባቸው ያሉት ሃላፊው ነገር ግን እነዚህ መድሃኒቶች በግል ፋርማሲዎች እያገኘን ነው" ብለዋል።
መድሃኒቶች ለጤና ተቋማት በሚሰጥበት ወቅት መቀበላቸውን የሚያረጋግጥ ወረቀት ወይም (Proof of Delivery) አለ። ይህ ማስረጃ እያለ እጥረት አለ መባሉ ያለ Proof of delivery የምንሰጠው መድኃኒት ስለሌለ የተሰጡ መድኃኒቶች ከሆስፒታል እና ጤና ጣቢያ እየወጡ መሆኑን አመላካች ነው።
Proof of Delivery "ጤና ጣቢያው ተረክቢያለሁ ብሎ የሚቀበለው ወረቀት ነው ከተቀበለ በኋላ ግን ይሸጥ ወይስ ለታካሚ ይዋል ማረጋገጫ የለንም " ብለዋል።
በተጨማሪም ፈዋሽነቱ ያልተረጋገጠ መድኃኒት በኮንትሮባንድ ወደ በኢትዮጵያ እየገባ ነው ያሉት ሃላፊው እነዚህ መድሃኒቶች የኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ያለመዘገባቸው እና የማያውቃቸው ናቸው ብለዋል።
"Artemether injection 80 Mg ተብሎ ኢትዮጵያ ውስጥ የተገኘ መድኃኒት አለ በላብራቶሪ ሲመረመር ግን Artemether የተሰኘው መድኃኒት ውስጡ አልተገኘም ካርቶኑ ላይ ከመጻፉ ውጪ ነው ያሉት።
እንደዚህ አይነት ነገሮች እየታዩ በመሆኑ ጉዳዩ ከፍተኛ ቁጥጥር የሚያስፈልገው ነው ብለዋል።
የኛ መድሃኒት ወጥቶ መሸጡ ላላግባብ፤ ወጪ ይዳርጋል ፈዋሽነቱ ያልተረጋገጠ መድኃኒት በኮንትሮባንድ ገብቶ መሰራጨቱ ደግሞ ገንዘቡንም አውጥቶ ጤናውንም ያጣል" ሲሉ አክለዋል።
በወባ በሽታ ዙሪያ ጥቆማ፤ መረጃ እና ሐሳብ ካላችሁ ያካፍሉን💬 @tikvahmagbot

በወባ በሽታ ዙሪያ ጥቆማ፤ መረጃ እና ሐሳብ ካላችሁ ያካፍሉን
@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
⭕️ LIVE
ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ባለቤትነት የተያዘው ኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻውን ለሀገር ውስጥ ባለሀብቶች በራሱን የቴሌብር መተግበሪያ በመጠቀም ለመሸጥ የሚያስችለውን ፈቃድ ማግኘቱን ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በይፋ ያበስራል።
ይህንን ዝግጅት Voice Chat በቀጥታ ይከታተሉ

#Update
ኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ሽያጩ ሁለት ዙር እንዳለው አስታውቋል።
በመጀመሪያው ዙር የመደበኛ አክሲዮን ሽያጭ፦
- በ2016 በወጣው የሂሳብ ሪፖርት የድርጅቱ ካፒታል = 100 ቢሊዮን ብር
- በአለም አቀፍ የ3ተኛ ወገን የገበያ ተመን መሰረት ድርጅቱ የሚያወጣው ዋጋ = 300 ቢሊዮን ብር
- በመጀመሪያው ዙር መደበኛ የአክሲዮን ሽያጭ የቀረበው = 100 ሚሊዮን
- የአንድ ሼር ዋጋ 300 ብር
- 100 ሚሊዮን ሼር በ300 ብር ሲሸጥ ኢትዮ ቴሌኮም ከሼር ሽያጭ 30 ቢሊዮን ብር ያገኛል።
- ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን = 33 ሼር ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 9,900 ብር ይሆናል።
- ከፍተኛው መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን 3,333 ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 999,900
- መግዛት የሚቻለው ከዛሬ ጥቅምት 6 እስከ ታህሳስ 25 ድረስ ይሆናል።
- የሼር አባላቱ የሚታወቁት = ጥር 23/2017
- ሽያጩ በቴሌብር ብቻ የሚደረግ ይሆናል።
- ክፍያውን በ48 ሰዓት ውስጥ መክፈል ይቻላል።
- አንድ አክሲዮን ገዢ ሲፈጸም ከአክስዮኑ ዋጋ በተጨማሪ 1.5% የአገልግሎት ክፍያ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፍል ይሆናል።
- ከከፍተኛው የአክሲዮን መጠን በላይ መግዛት አይቻልም።
- ግብይቱ የሚካሄደው በኢትዮጵያ ብር ብቻ ነው።
#Note: ይህ ዜና ማስተካከያ ተደርጎበት የወጣ ነው።

Photo
#Summary: የአንድ ሼር ዋጋ 300 ብር ሲሆን100 ሚሊዮን ሼር መጠን ለሽያጭ ቀርቧል። በሽያጩም ኢትዮ ቴሌኮም 30 ቢሊዮን ብር ያገኛል።
ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን 33 ሼር ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 9,900 ብር ይሆናል።
ከፍተኛው መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን 3,333 ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 999,900 ብር ይሆናል።
የአክሲዮን ሽያጩ በቴሌብር ብቻ ከዛሬ ጥቅምት 6 እስከ ታህሳስ 25 ድረስ የሚቆይ ይሆናል።
#TikvahEthiopia