TIKVAH-MAGAZINE
#የቀጠለ ° "በሆስፒታሉ ደም እየፈለገ ባለመገኘቱ ሳምንት በድንገተኛ ክፍል ውስጥ የተኛ ታማሚ አለ" ° "ከጤና ሚኒስቴር የተላኩ የባለሞያዎች ቡድን ለወባ ታማሚዎች ድንኳን ተዘጋጅቶ ለብቻ ቢታከሙ የሚል ምክረ ሐሳብ አስቀምጧል" - የኦቶና ሪፈራል ሆስፒታል አመራር በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ስር ያለው የኦቶና ሪፈራል ሆስፒታል የሚገኙ የወባ ታማሚዎች የደም ልገሳ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ የደም እጥረት…
#ወባ
° "ፈዋሽነቱ ያልተረጋገጠ መድኃኒት በኮንትሮባንድ ወደ በኢትዮጵያ እየገባ ነው"
° "ሆስፒታል ገብተው መታከም የሚያስፈልጋቸው የወባ ታማሚዎች ቁጥር በጣም በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል"
° "መድኃኒቶችን ከተቀበሉ በኋላ ይሸጥ ወይስ ለታካሚ ይዋል ማረጋገጫ የለንም " -የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት
___
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሰሞኑ በወላይታ ዞን ስለተከሰተው የወባ በሽታ ሥርጭት ተከታታይ ዘገባ እየሰራ ነው።
በዞኑ ስላለው የህመሙ ሁኔታ እና የበሽታው ስርጭት ባሻገር የወባ የመድሃኒት አቅርቦት ችግር አለ የሚል ቅሬታም ተቀብለናል።
በጉዳዩ ላይ ምላሻቸውን ለማካተት የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሐዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።
____
ቲክቫህ የኢትዮጵያ የመድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴን ጠይቋል።
በምላሻቸውም ተቋሙ በአሁኑ ሰዓት እንደሃገር ከወባ በሽታ ጋር በተገናኘ እየሰራ ያለውን ሥራ ነግረውናል።
ኃላፊው የወባ በሽታን በተመለከተ ሦስት ነገሮች መታየት አለባቸው ይላሉ:- ኬሚካል ርጭት ፣አጎበር እና መድኃኒት።
የአጎበር ስርጭትን እና የኬሚካል ርጭትን በተመለከተ ከዚህ በፊት እንደ ሃገር 19 ሚሊየን አጎበር መሰራጨቱን እና የኬሚካል ርጭትም መከናወኑን ገልጸው አሁንም ወቅቱን ጠብቆ የኬሚካል እና አጎበር ስርጭት ይከናወናል ብለዋል።
የወባ መድሃኒቶችን በተመለከተም በአሁኑ ሰዓት #Coaretm እና #Chloroquine የተሰኙ ሁለት ዓይነት የወባ መድሃኒቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል።
"ኢትዮጵያ ውስጥ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከ 70 በመቶ በላይ የወባ መነሻው Plasmodium falciparum በተሰኘው የወባ ፓራሳይት ሲሆን የሚታከመውም በ Coaretm በተሰኘ መድኃኒት ነው።
ኳርተምን በተመለከተም በቂ ክምችት አለ በግሎባል ፈንድ(Global Fund) ተገዝቶ የቀረበ ነበር መንግስትም በጀት ይዞ የተገዛ አለ በእርዳታም ከቻይና እየመጣ ያለ አለ። እነዚህ ተደምሮ ከአሁን በኋላ ቢያንስ ለአምስት ወር ሊቆይ የሚችል ክምችት አለ።
አሁን ላይ በገመገምነው የፍጆታ መጠን ፣ለአምስት ወር የሚበቃ ክምችት አለን፣ በቂ አይደለም አሁን ላይ ግን በሆስፒታሎች ላይ ችግር ይገጥማል ብለን አናስብም "የስርጭት እና የአጠያየቅ ችግር ከሌለ በስተቀር" ሲሉ ነው የገለጹት።
Chloroquine የተሰኘው እና በ Plasmodium Vivax በተሰኘች ፓራሳይት የሚመጣ የወባ በሽታን ለማከም የሚረዳ መድኃኒት በተመለከተም "ይሄ መድኃኒት ከዚህ ቀደም መጠቀም ቆሞ ነበር በተወሰነ ደረጃ በሌሎች ለጋሽ ድርጅቶች እና ገዢ አካላት እንዲገባ ለማድረግ ተሞክሯል በቂ አልነበረም የገባው በዚህ ምክንያት ስጋት አለ ስጋት ብቻ አይደለም አንዱ ጋር ኖሮ ሌላው ጋር ላይኖር ይችላል" ብለዋል።
በለጋሽ ድርጅቶች በኩል የመጣውም ተሰራጭቶ እያለቀ ሲሆን በመንግስት በጀት አስቸኳይ ግዢ ተከናውኖ ከሁለት ሳምንት በኋላ ሃገር ውስጥ እንደሚገባም ሰምተናል።
Chloroquine ብዙም ተጠቃሚ የለውም ብለን ነው የምንወስደው ያሉት ዳይሬክተሩ አሁን ባለው የወባ ሥርጭት ግን አዲስ ነገር እየታየ ነው በ Vivax ሳቢያ የሚታመሙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ ገልጸዋል።
የአቅርቦት ችግር ስጋት ቢኖርም ነገር ግን ሙሉ በሙሉ መድሃኒቱ አለመጥፋቱን ችግሩን ለመቅረፍም እየተሰራበት መሆኑንም ነው የነገሩን።
የራሱ ጥናት ቢያስፈልገውም አሁን ባለው መረጃ ሆስፒታል ገብተው መታከም የሚያስፈልጋቸው የውባ ታማሚዎች ቁጥር በጣም በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል ቁጥር መጨመር ብቻ አይደለም ኢትዮጵያ ውስጥ የወባ የህመም መጠኑም ጨምሯል ብለዋል።
የህመም መጠኑ ሲጨምር ደግሞ Coaretm እና Chloroquine ላያድኑ ይችላሉ ያሉት ዳይሬክተሩ፥ በዚህ ሳቢያ #Artesunate_Injection የተሰኘ መድኃኒት ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ተናግረዋል።
Artesunate Injection የሚያስፈልጋቸው የወባ ታማሚዎች ቁጥር ከዚህ በፊት ቁጥሩም ሆነ መጠኑ አነስተኛ ስለነበር የተጠቀሰው መድኃኒት ፍጆታ በጣም ትንሽ የነበረ ሲሆን አሁን ግን በወባ መባባስ ምክንያት የመድሃኒቱ ፍላጎት #በስድስት_እጥፍ ማደጉን ገልጸዋል።
የተጠቀሰው መድሃኒት በሃገር ውስጥ የነበረው ክምችት አስቀድሞ በነበረው ፍጆታ መሰረት በመሆኑ ስጋት ነበረን በመሃል ላይም ተቆራርጦ ነበር አሁን በ UNICEF ድጋፍ ተገዝቶ መግባቱን እና በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ከቻይና የሚገቡ ተጨማሪ መድሃኒቶች ይኖራሉ ብለውናል።
ከፍል ሁለት ይቀጥላል . . .
@tikvahethmagazine💬 @tikvahmagbot

@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM