TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
19K photos
293 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
加入频道
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ሐረማያ_ዩኒቨርስቲ | በዘንድሮው አመት 4200 ተማሪዎችን ለማስተናገድ ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ ለኢቢኤስ ቴሌቭዥን ገልጻል፡፡ በተለይ ሰላምን ከማስጠበቅ አንጻር ትኩረት ሰጥቶ እንደሰራ ነው የገለጸው፡፡

#ቲክቫህ_ዩኒቨርስቲ
@tikvahethmagazine @emush21
#ሐረማያ_ዩኒቨርሲቲ

UPDATE| ዛሬ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ካምፓስ DMC2 የሚባለው የወንዶች ብሎክ አንድ ዶርም ላይ የእሳት አደጋ የደረሰ ሲሆን አሁን በተማሪዎች ርብርብ መቆጣጠር መቻሉን ቤተሰቦቻችን ገልጸውልናል፡፡ በቦታው የጸጥታ ሀይሎችና የግቢው ፕሬዝዳንት መጥተው ሁኔታውን ተመልክተዋል፡፡

#ቲክቫህ_ዩኒቨርስቲ
@tikvahethmagazine @emush21
#ሐረማያ_ዩኒቨርሲቲ

ዛሬ ሀሙስ ህዳር 4 ቀን 2012 ዓ.ም በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ከቀኑ 7፡45 አካባቢ DMC 1B ተብሎ በሚታወቀው የወንድ ተማሪዎች መኖሪያ ህንፃ ውስጥ በሚገኘው የመኝታ ክፍል 09 ለጊዜው ምክንያቱ በውል ባልታወቀ ምክንያት በተነሳ እሳት በመኝታ ክፍሉ ውስጥ የነበሩ ዕቃዎች በሙሉ ተቃጥለዋል። በዚህ እንድ ክፍል ውስጥ የተነሳው እሳት ወደሌሎች ክፍሎች እንዳይዛመት የዩኒቨርሲቲያችን ሰራተኞችና ተማሪዎች እንዲሁም የፀጥታ አካላት ባደረጉት ርብርብ በቁጥጥር ስር ውሏል። በቃጠሎው ምክንያት በሰው ላይ ምንም አይነት አደጋ አልደረሰም። የቃጠሎውን መንስኤ ፖሊስ በማጣራት ላይ ይገኛል።

Via የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ

#ቲክቫህ_ዩኒቨርስቲ
@tikvahethmagazine @emush21
#ሐረማያ_ዩኒቨርሲቲ

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ላይ ባወጣው ማስታወቂያ በዩኒቨርሲቲው ተቋርጦ የነበረው ትምህርት ለሦስት ተከታታይ ሳምንታት ቀጥሎ የነበር ቢሆንም ታህሳስ 20 ጀምሮ ግን ተቋርጧል ብሏል፡፡ ዛሬ ላይ የዩኒቨርስቲው ሴኔት ባደረገው ስብሰባ ተማሪዎች ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ከታህሳስ 23 ጀምሮ አስከ ታህሳስ 27 ድረስ ትምህርት እንዲጀምሩና ይህ የማይተገበር ከሆነ ተማሪው/ዋ በራሷ ፍቃድ ከዩኒቨርስቲው እንደለቀቀ/ች ይታሰባል ሲል አስታውቋል፡፡

ተማሪዎች በበኩላቸው ይህ ማስታወቂያ ዩኒቨርሲቲው ለትክክለኛው ችግር ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ማለፉን የሚያመለክት ነው...ወደ ቤታችን ከተመለስን ቆይተናል የኛን ጉዳይ ችላ ብሎ ትምህርትም ሲሰጥ የነበረው ለትንሽ ተማሪዎች ነበር አንድም ጊዜ ግን ዩኒቨርሲቲው ተማሪን ከተማሪ አቀራርቦ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለመፍጠር የጎላ ስራ አልሰራም....ስለጸጥታው ጉዳይ እንኳን ምንም ያለው የለም ስለዚህ ለመመለስ ደኅንነታችን የተጠበቀ ለመሆኑ ትልቅ ስጋት አለን ሲሉ ገልጸውልናል፡፡

#ቲክቫህ_ዩኒቨርስቲ
@tikvahethmagazine @emush21
#ሐረማያ_ዩኒቨርሲቲ
#ትኩረት

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከ7:30 በኀላ በግቢው ውስጥ አለመረጋጋት መከሰቱን ቤተሰቦቻችን እየጠቆሙን ይገኛሉ፡፡ የተከሰተውን ነገር አጣርተን የምንመለስ ይሆናል፡፡

ጥቆማዎችን ለማድረስ @emush21

#ቲክቫህ_ጥቆማ
@tikvahethmagazine @emush21
#ሐረማያ_ዩኒቨርሲቲ

የዩኒቨርሲቲውን ሰላማዊ መማር ማስተማርን ለማስቀጠል እንዲቻል በተለያዩ ጊዜያት በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ስራው እንዲስተጓጎል ምክንያት በሆኑ 77 ተማሪዎች ላይ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ሲል ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል፡፡

ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ 👉 https://telegra.ph/ሐረማያ-ዩኒቨርሲቲ-01-10

( ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ )

#ቲክቫህ_ዩኒቨርስቲ
@tikvahethmagazine @emush21
#ሐረማያ

የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ሕይወት ፋና ኮምፕርሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በዘመናዊ የህክምና መሳሪያ የጭንቅላት ቀዶ ህክምና (Endoscopic Third Ventriculostomy) አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

በዚህም በምስራቅ ኢትዮጵያ ብቸኛ የሆነውን የህፃናት ጭቅላት ውሰጥ የውሀ መጠን መጨመር ህመም (Hydrocephalus) ቀዶ ህክምና አገልግሎት ተጀምሯል።

ሪች አናዘር ፋውንዴሽን የዘመናዊ ህክምና መሳሪያ (Endoscopy) ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በተጨማሪ ባለሞያዎችን በመላክ በሆስፒታሉ ላሉ የጭንቅላት ቀዶ ህክምና ቡድን በማሽኑ አጠቃቀም ዙሪያ ለአንድ ሳምንት ስልጠና ሰጥቷል ።

በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የአንጎል እና ህብለ ሰረሰር ቀዶ ህክምና እስፔሻሊስት ዶ/ር ዮርዳኖስ አሻግሬ በአንድ ሳምንት ቆይታቸው የ Endoscopic Third Ventriculostomy አጠቃቀምን በሚገባ በሆስፒታሉ ላሉ የቀዶ ህክምና ቡድን ስልጠና መስጠት መቻሉን እና በዚህም ሂደት ለሰባት ታካሚዎች በመሳሪያው አገልግሎት መሰጠቱን ገልፀዋል።

የአገልግሎቱ መጀመር ቀደምሲል ለህፃናቱ ህመማቸውን ለማከም ይደረግላቸው ከነበረው ከጭንቅላታቸው እሰከ ሆድ የሚደርስ ትቦ የማስገባት ሂደትን የሚያስቀር እና ሊፈጠሩ ይችላሉ ተብለው የሚገመቱትን የኢፌክሽን እና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች ስጋት እንደማይሆኑ የአንጎል እና ህብለሰረሰር ቀዶ ህክምና እስፔሻሊስት ዶ/ር መሀመድኑር አብዱላሂ አስረድተዋል።

@tikvahethmagazine