"የሁለት ወር ደሞዝ ስላልተከፈለን ችግር ውስጥ ገብተናል"- የዛባ ገዞ ወረዳ የመንግስት ሰራተኞች
በዳውሮ ዞን በዛባ ገዞ ወረዳ በተለያዩ የሴክተር መስሪያ ቤቶች ለአብነትም በግብርና፣ በኢንተርፕራይዝ፣ ገቢዎች፣ ባህልና ቱሪዝምን ጨምሮ ሌሎች አስር በሚደርሱ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚሰሩ የመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች የነሐሴና የመስከረም ወር ደሞዝ ሳይከፈላቸው መዘግየቱን ለቲክቫህ ባሳወቁት ቅሬታ ለማወቅ ተችሏል።
በወረዳው የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች ምን አሉ?
አንድ ስሙ እንዲጠቀስ ያልፈለገ በወረዳው ካሉ መስሪያ ቤቶች በአንዱ የሚሰራ ግለሰብ "እንኳን ያለ ደሞዝ ይቅርና ደሞዝ ተከፍሎንም ኑሮን መግፋት አልቻልንም፤ ይኸው ደሞዝ ሳይከፈለን ሁለት ወር ተቀምጠናል፤ በዚህም የሰው አይን ለማየት ተገደናል" ሲል ቅሬታውን አቅርቧል።
"ወረዳ ላይ ስንጠይቅ የበጀት እጥረት ነው ዞን ከእኛ ቆርጧል ይሉናል ለምን ይቆረጣል ስንል በእዳ ምክንያት ብለው ይነግሩናል፤ ዞን ሄደን ቅሬታ ለማቅረብ እንኳን ብር የለንም ደውለን ስንጠይቅ ደግሞ ለወረዳ ተልኳል እንዴት አልተከፈላችሁም የሚል ምላሽ ይሰጡናል በመሀል ግን እኛ እየተጎዳን ነው። እንዴት እንደዚህ አይነት ስራ ይሰራል? እኛም ልጆቻችንም እየተጎዱ ነው ሌላ የገቢ ምንጭም የለንም ምን እንደምናደርግ ግራ ገብቶናል" ብሎናል።
ሌላኛው ቅሬታ አቅራቢም ደሞዝ መዘግየቱን በተመሳሳይ ያነሳሉ "በዚህ በኩል #በወባ ወረርሽኝ እንሰቃያለን ለመታከም ስንል ደሞዝ የለንም ሁለት ስቃይ በአንዴ ማየቱን ምን ይሉታል" ሲሉ እያሳለፉት ያለውን ችግር ያስረዳሉ።
"በርካቶች በበሽታ እየተሰቃዩ መታከሚያ አጥተው በየቤቱ አልጋ በያዙበት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ደሞዝ አለመከፈል በጣም ያማል፤ ከዚህ ቀደም እንደዚህ አይነት ነገር ገጥሞን አያውቅም አሁን ግን ግራ ተጋብተን ሰሚ አጥተን ቁጭ ብለናል" ሲሉም ቅሬታቸውን ነግረውናል።
ሌሎችም ቲክቫህ ያነጋገራቸው በወረዳው በተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች ተመሳሳይ ቅሬታን አቅርበዋል።
ደሞዝ እያለን በዚህ ኑሮ ውድነት፣ የወባ ወረርሽኝ ተጨምሮበት መሰቃየት የለብንም ያሉት ሰራተኞቹ፥ ሌላ የከፋ ጉዳት ሳይደርስብን የሚመለከተው አካል መፍትሔ ያበጅልን ሲሉም በአጽንኦት ጠይቀዋል።
እኛም በጉዳዩ ላይ ከዛባ ገዞ ወረዳ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ተደጋጋሚ ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።
@tikvahethmagazine💬 @tikvahmagbot

@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፕሮጀክት ቆሞ የመምህራን ደሞዝ ክፈሉ ተብሏል?
በርካቶች በማኅበራዊ መዲያ ላይ "ፕሮጀክት ቆሞ የመምህራን ደሞዝ ክፈሉ" ብለዋል በሚል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰውን በመጥቀስ መረጃዎችን እየተቀባበሉ ነው።
እነዚህ መረጃዎች በስፋት ትላንት እና ዛሬ እየተዘዋወሩ ሲሆን የት፣ መቼ፣ በምን ቦታ ይህንን እንደተናገሩ ግን አይጠቅሱም። ታማኝ ምንጭም አያስቀምጡም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ርዕሰ መስተዳደሩ ተናገሩት የተባለው ንግግር መቼ፣ የት፣ በምን መድረክ የሚለውን ለማወቅ ዳሰሳ አድርጓል።
ይህንን ንግግር ርዕሰ መስተዳደሩ የተናገሩት መስከረም 25 በማረቆ ልዩ ወረዳ ቆሼ ከተማ በተካሄደ የክልሉ የትምህርት ሴክተር ጉባዔ ላይ ነው። ለዚህ ማስረጃም ደሬቴአ መስከረም 28 እንዲሁም ከንባታ ቲቪ መስከረም 27 የሚዲያ ሽፋን ሰጥተውታል።
ለመሆኑ ርዕሰ መስተዳድሩ በመድረኩ ያሉት ምንድን ነው?
"ደሞዝ፣ ባክፔይመንት የመሳሰሉት ጉዳዮች ሌሎች ፕሮጀክቶችም ካሉ አቋርጣችሁ ክፈሉ። መምህራን ደሞዝ ላይ ካሁን በኋላ ጭቅጭቅ መነጋገር መግባት የለብንም" ብለዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም "አምና እስቀምጫለው አንድ ሶስት ዞኖችን አስቀምጫለው የዛን ጊዜ የሰራችሁት ስራ ጥሩ ነው አሁን ያደረጋችሁት ነገርም ጥሩ ነው ግን ፕሮጀክት ቆሞ ክፈሉ በቃ ፕሮጀክት ይቁም" ሲሉ ተደምጠዋል።
"የትምህርት ጥራትን ምናስብ ከሆነ መምህራን ጋር ክፍያ ሳናከናውን አንችልም" ያሉት ር/መስተዳድሩ "ስለዚህ 50 ፐርሰንት 60 ፐርሰንት አስር ሺህ ከምን ምን የተባለው የመምህራን ቁጥር የተለያየ ፐርሰንት ነው ያለው ያለባችሁ ቦታዎች ወስዳችሁ በጊዜ ገደብ በ3 ወር ውስጥ በጀታችሁን አስተካክላችሁ ሚቆም ነገር አቁማችሁ ክፈሉ" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
የክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ አንተነህ ፍቃዱም በመድረኩ በጉዳዩ ላይ ሀሳባቸውን ሰንዝረዋል።
በመልዕክታቸውም "የዞን እና የወረዳ አስተዳዳሪዎች እንዲሁም ከንቲባዎች ምን ያህል መምህራንን ጠጋ ብላችሁ እያወያያችሁ አንደሆነ አላውቅም ጠጋ ስትሉ በጣም ብዙ የሚያሳዝን ነገር አለ ውስጣችንን የሚነካ ነገር አለ የኑሮ ሁኔታቸው መሰል መሰል" ሲሉ ተደምጠዋል።
የመምህራንን ሲገልጹም " እነሱ ኢንጅን ናቸው እነሱን መለወጥ ካልቻልን መማር ማስተማሩን አንቀይርም ስለዚህ የመጀመሪያው ነገር መምህራንን ምን ያህል ቀርበን እናወያያለን ሚለው ነው" ብለዋል።
እንደተባለው የመምህራን ደሞዝ ፕሮጀክት ቆሞ ይከፈል ይሆን ? ተፈጻሚነቱስ እስከምን ድረስ ይሆን?

TIKVAH-MAGAZINE
ኢትዮጵያ ለኤምፖክስ የአደጋ ጊዜ ምላሽ እቅድ እያዘጋጀች ነው። የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት የዝንጀሮ ፈንጣጣ (Mpox) ወረርሽኝ ምላሽ እቅድ እያዘጋጀ መሆኑን አስታውቋል። ኢትዮጵያም በርካታ በረራ ካላቸው አገራት አንዷ በመሆኗ እና የወረርሽኙ ስጋት ከፍተኛ ስለሆነ የአደጋ ጊዜ እቅድ እጅግ አስፈላጊ መሆኑ ተጠቅሷል። ይህ የተገለጸው የረቂቅ እቅዱ ለውይይት በቀረበበት የተደረገውን አውደ…
#Mpox_Update: በኬንያ በ Mpox ምክንያት የመጀመሪያው ሞት ተመዝግቧል።
በኬንያ በ10 የሀገሪቱ ግዛቶች 13 በኤም ፖክስ የተያዙ ሰዎች ሲመዘገቡ በወረርሽኙ ምክንያት የመጀመሪያ ሞት መመዝገቡን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በሀገሪቱ በበሽታው ተይዘው የነበሩ 8 ታማሚዎች አገግመው መዳናቸው የተገለፀ ሲሆን 4 ሰዎች በህሙማን ማገገሚያ ክፍል እንደሚገኙ ተገልጿል።
የአለም ጤና ድርጅት የኤምፖክስ ወረርሽኝን ለማከም የህክምና ቁሳቁስ እንዲሁም በጥገኛ ህዋሶች የታመሙ ሰዎችን ለማከም የሚረዳ መድሃኒት ለኬንያ መለገሱ ተነግሯል።
@tikvahethmagazine💬 @tikvahmagbot
በኬንያ በ10 የሀገሪቱ ግዛቶች 13 በኤም ፖክስ የተያዙ ሰዎች ሲመዘገቡ በወረርሽኙ ምክንያት የመጀመሪያ ሞት መመዝገቡን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በሀገሪቱ በበሽታው ተይዘው የነበሩ 8 ታማሚዎች አገግመው መዳናቸው የተገለፀ ሲሆን 4 ሰዎች በህሙማን ማገገሚያ ክፍል እንደሚገኙ ተገልጿል።
የአለም ጤና ድርጅት የኤምፖክስ ወረርሽኝን ለማከም የህክምና ቁሳቁስ እንዲሁም በጥገኛ ህዋሶች የታመሙ ሰዎችን ለማከም የሚረዳ መድሃኒት ለኬንያ መለገሱ ተነግሯል።
@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ጥቆማ: 4ኛው የኢሰመኮ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል የጥበብ ሥራዎች ውድድር ተጀምሯል።
ውድድሩ በሕይወት የመኖር መብት በተለይም በሴቶች ሕይወት ላይ፣ በኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶች ዘርፍ ደግሞ በበቂ ምግብና ውሃ በማግኘት መብት ላይ የሚያተከኩር ሲሆን እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ለተወዳዳሪዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል።
- የሥዕልና የፎቶግራፍ ውድድሩ ትኩረቱን በቂ ምግብና ውሃ በማግኘት መብቶች ላይ ያደርጋል።
- የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ውድድር ደግሞ በሕይወት የመኖር መብት በተለይም በሴቶች ሕይወት ላይ የሚያተኩር ነው፡፡
በአጫጭር የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ዘርፍ ለውድድር የሚቀርብ ሥራ ከ 3 ገጽ ያልበለጠ (ከ600 ቃላት ያላነሰ፣ ከ1200 ቃላት ያልበለጠ) ሊሆን ይገባል።
በሁለቱም ዘርፎች የሚቀርቡ የጥበብ ሥራዎች ዘጋቢ፣ ምናባዊ ወይም እውነተኛ ታሪክ ላይ መሠረት ያደረጉ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል።
ለውድድሩ የኪነጥበብ ሥራዎችን የመላክ ሂደት ምን ይመስላል ?
ለውድድሩ እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም. እኩለ ለሊት ወይም ድረስ ለውድድር የሚቀርበውን የኪነጥበብ ሥራ እንዲሁም የተሞላ እና የተፈረመበት የተሳትፎ ቅጽ በማያያዝ፤
በኢሜል [email protected]
በቴሌግራም @EthioHRC መላክ ይቻላል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ቢሮዎች በአካል በመገኘት መላክ ይችላሉ ተብሏል።
#ተጨማሪ: ውድድሩ የሚካሄድባቸውን ከተሞችንና የውድድሩን ዘርፎች ከምስሉ ላይ ይመልከቱ።

➨ የተሻለ ትርፍ የሚያገኙበትና አዋጭነቱ የተረጋገጠ ኢንቨስትመንት እነሆ!
➨አያት አክሲዮን ማህበር በ2015 ዓ.ም ባስገኘው በኢትዮጵያ ትልቁን የአክሲዮን ትርፍ ክፍፍል 51.3% ለባለአክሲዮኖቹ እየከፈለ ይገኛል።
👉የ100 ሺ አክስዮን የገዙ በ2015 ብቻ ብር 51ሺ ትርፍ አግኝተዋል። የ1 ሚሊዮን የገዙ በ1 ዓመት ጊዜ ውስጥ ብር 513 ሺ ትርፍ አግኝተዋል።
👉 የ2016 የሂሳብ ሪፖርት በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን የትርፍ ክፍፍሉ በቅርቡ ይፋ እናደርጋለን።
➨የአክሲዮን ሽያጭ እየተጠናቀቀ ስለሆነ ፈጥነው በመምጣት የስምንት ትርፋማ ድርጅቶች ባለቤት ይሁኑ!
👉አያት አ.ማ. በሪል ስቴት ልማት፣ በሆቴልና ቱሪዝም፣ በማርብል ማምረቻ ኢንዱስትሪ፣ በጠጠር ማምረቻ ኢንዱስትሪ፣ በብሎኬት ማምረቻ ኢንዱስትሪ፣ በእንጨትና ብረታብረት ውጤቶች ማምረቻ ኢንዱስትሪ፣በትምህርት ኢንቨስትመንት እና፣ በፋይናንሻል ኢንቨስትመንት ዘርፎች ተሰማርቶ ይገኛል።
👌 ለሽያጭ ባቀረብናቸው በመኖሪያ አፓርትመንቶቻችንና በንግድ ቤቶቻችን ላይም ከፍተኛ የዋጋ ቅናሽ አድርገን እየጠበቅንዎ ነው!!!
⏱📞 ☎️ ለበለጠ መረጃ በ 0911141372/0910531565 (በቀጥታ ፣ በቴሌግራም፣ በዋትሳፕ) ተሰማ ብለው ይደውሉ።
አያትን የሰማ ሁልጊዜም ትርፋማ!

ለበርካታ አመታት በተከታታይ ለምግብ ዋስትና ወሳኝ የሆኑት የእንስሳት ተዋጸኦ ምርት ባለድርሻ አካላትን በአንድ ቦታ የሚያሰባስበው ኤክስፖ ደረሰ!!
በእንስሳት መኖ፣ በእንስሳት ጤና፣ በዶሮ እርባታ፣ በወተት፡ በስጋ እንዲሁም በንብ እና በአሳ ሃብት ልማት ላይ ያተኮሩ ከ17 ሀገራት የተወጣጡ ከ100 በላይ ዓለምዓቀፍ የቴክኖሎጂ እና ግብዓት አቅራቢዎች እንዲሁም
ገናና የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት አመታዊው አውደ ርዕይ እና ጉባኤ
ይካሄዳል።
በዚህ ልዩ መድረክ
ከዘርፉ መሪዎች ጋር የንግድ ትስስር ለመፍጠር ፣በአዲስ የስራ ሃሳብ መስኩን ለመቀላቀል በልምድ ልውውጥ መድረኩ ለማትርፍ
ከጥቅምት 21-23 በሚሊኒየም አዳራሽ አይቀርም ።
ዕውቀትዎን የሚያሳድጉበት፡ ልምድዎትን የሚያዳብሩበት ስልጠናዎችና ጉባዔዎችም ተሰናድተዋል
በድረ ገጻችን https://bit.ly/EAPEvents2024 ቀድመው ይመዝገቡ
ለበለጠ መረጃ - 0929308364/0996066631/0954986189 ይደውሉ
አዘጋጅ - ፕራና ኢቨንትስ

#ሐረማያ
የሐረማያ ዩኒቨርስቲ ሕይወት ፋና ኮምፕርሄንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በዘመናዊ የህክምና መሳሪያ የጭንቅላት ቀዶ ህክምና (Endoscopic Third Ventriculostomy) አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
በዚህም በምስራቅ ኢትዮጵያ ብቸኛ የሆነውን የህፃናት ጭቅላት ውሰጥ የውሀ መጠን መጨመር ህመም (Hydrocephalus) ቀዶ ህክምና አገልግሎት ተጀምሯል።
ሪች አናዘር ፋውንዴሽን የዘመናዊ ህክምና መሳሪያ (Endoscopy) ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በተጨማሪ ባለሞያዎችን በመላክ በሆስፒታሉ ላሉ የጭንቅላት ቀዶ ህክምና ቡድን በማሽኑ አጠቃቀም ዙሪያ ለአንድ ሳምንት ስልጠና ሰጥቷል ።
በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የአንጎል እና ህብለ ሰረሰር ቀዶ ህክምና እስፔሻሊስት ዶ/ር ዮርዳኖስ አሻግሬ በአንድ ሳምንት ቆይታቸው የ Endoscopic Third Ventriculostomy አጠቃቀምን በሚገባ በሆስፒታሉ ላሉ የቀዶ ህክምና ቡድን ስልጠና መስጠት መቻሉን እና በዚህም ሂደት ለሰባት ታካሚዎች በመሳሪያው አገልግሎት መሰጠቱን ገልፀዋል።
የአገልግሎቱ መጀመር ቀደምሲል ለህፃናቱ ህመማቸውን ለማከም ይደረግላቸው ከነበረው ከጭንቅላታቸው እሰከ ሆድ የሚደርስ ትቦ የማስገባት ሂደትን የሚያስቀር እና ሊፈጠሩ ይችላሉ ተብለው የሚገመቱትን የኢፌክሽን እና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች ስጋት እንደማይሆኑ የአንጎል እና ህብለሰረሰር ቀዶ ህክምና እስፔሻሊስት ዶ/ር መሀመድኑር አብዱላሂ አስረድተዋል።

በናይጄሪያ በነዳጅ ጫኝ ቦቴ ላይ በደረሰ የፍንዳታ አደጋ በትንሹ 94 ሰዎች ሞቱ
በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ ነዳጅ ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ቦቴ ላይ በደረሰ ፍንዳታ በትንሹ 90 ሰዎች ሲሞቱ 50 ሰዎች መቁሰላቸውን አናዱሉ ዘግቧል።
የነዳጅ ማጠራቀሚያው የፈነዳው በሀገሪቱ ጂጋጋ ግዛት፤ በፍጥነት መንገድ ላይ እንደሆነ ሲነገር ሲኤን ኤን በበኩሉ የሟቾች ቁጥር 94 መድረሱን ዘግቧል።
አደጋው የተከሰተው ትላንት ምሽት ላይ ሲሆን የነዳጅ ማጠራቀሚያ ቦቴው ተቀጣጥሎ ከባድ የቃጠሎ አደጋ ያደረሰው በዛሬው እለት መሆኑም ነው የተነገረው።
@tikvahethmagazine
በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ ነዳጅ ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ቦቴ ላይ በደረሰ ፍንዳታ በትንሹ 90 ሰዎች ሲሞቱ 50 ሰዎች መቁሰላቸውን አናዱሉ ዘግቧል።
የነዳጅ ማጠራቀሚያው የፈነዳው በሀገሪቱ ጂጋጋ ግዛት፤ በፍጥነት መንገድ ላይ እንደሆነ ሲነገር ሲኤን ኤን በበኩሉ የሟቾች ቁጥር 94 መድረሱን ዘግቧል።
አደጋው የተከሰተው ትላንት ምሽት ላይ ሲሆን የነዳጅ ማጠራቀሚያ ቦቴው ተቀጣጥሎ ከባድ የቃጠሎ አደጋ ያደረሰው በዛሬው እለት መሆኑም ነው የተነገረው።
@tikvahethmagazine
TIKVAH-MAGAZINE
#የቀጠለ ° "በሆስፒታሉ ደም እየፈለገ ባለመገኘቱ ሳምንት በድንገተኛ ክፍል ውስጥ የተኛ ታማሚ አለ" ° "ከጤና ሚኒስቴር የተላኩ የባለሞያዎች ቡድን ለወባ ታማሚዎች ድንኳን ተዘጋጅቶ ለብቻ ቢታከሙ የሚል ምክረ ሐሳብ አስቀምጧል" - የኦቶና ሪፈራል ሆስፒታል አመራር በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ስር ያለው የኦቶና ሪፈራል ሆስፒታል የሚገኙ የወባ ታማሚዎች የደም ልገሳ የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ የደም እጥረት…
#ወባ
° "ፈዋሽነቱ ያልተረጋገጠ መድኃኒት በኮንትሮባንድ ወደ በኢትዮጵያ እየገባ ነው"
° "ሆስፒታል ገብተው መታከም የሚያስፈልጋቸው የወባ ታማሚዎች ቁጥር በጣም በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል"
° "መድኃኒቶችን ከተቀበሉ በኋላ ይሸጥ ወይስ ለታካሚ ይዋል ማረጋገጫ የለንም " -የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት
___
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሰሞኑ በወላይታ ዞን ስለተከሰተው የወባ በሽታ ሥርጭት ተከታታይ ዘገባ እየሰራ ነው።
በዞኑ ስላለው የህመሙ ሁኔታ እና የበሽታው ስርጭት ባሻገር የወባ የመድሃኒት አቅርቦት ችግር አለ የሚል ቅሬታም ተቀብለናል።
በጉዳዩ ላይ ምላሻቸውን ለማካተት የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሐዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ተደጋጋሚ ሙከራ ብናደርግም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።
____
ቲክቫህ የኢትዮጵያ የመድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴን ጠይቋል።
በምላሻቸውም ተቋሙ በአሁኑ ሰዓት እንደሃገር ከወባ በሽታ ጋር በተገናኘ እየሰራ ያለውን ሥራ ነግረውናል።
ኃላፊው የወባ በሽታን በተመለከተ ሦስት ነገሮች መታየት አለባቸው ይላሉ:- ኬሚካል ርጭት ፣አጎበር እና መድኃኒት።
የአጎበር ስርጭትን እና የኬሚካል ርጭትን በተመለከተ ከዚህ በፊት እንደ ሃገር 19 ሚሊየን አጎበር መሰራጨቱን እና የኬሚካል ርጭትም መከናወኑን ገልጸው አሁንም ወቅቱን ጠብቆ የኬሚካል እና አጎበር ስርጭት ይከናወናል ብለዋል።
የወባ መድሃኒቶችን በተመለከተም በአሁኑ ሰዓት #Coaretm እና #Chloroquine የተሰኙ ሁለት ዓይነት የወባ መድሃኒቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል።
"ኢትዮጵያ ውስጥ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከ 70 በመቶ በላይ የወባ መነሻው Plasmodium falciparum በተሰኘው የወባ ፓራሳይት ሲሆን የሚታከመውም በ Coaretm በተሰኘ መድኃኒት ነው።
ኳርተምን በተመለከተም በቂ ክምችት አለ በግሎባል ፈንድ(Global Fund) ተገዝቶ የቀረበ ነበር መንግስትም በጀት ይዞ የተገዛ አለ በእርዳታም ከቻይና እየመጣ ያለ አለ። እነዚህ ተደምሮ ከአሁን በኋላ ቢያንስ ለአምስት ወር ሊቆይ የሚችል ክምችት አለ።
አሁን ላይ በገመገምነው የፍጆታ መጠን ፣ለአምስት ወር የሚበቃ ክምችት አለን፣ በቂ አይደለም አሁን ላይ ግን በሆስፒታሎች ላይ ችግር ይገጥማል ብለን አናስብም "የስርጭት እና የአጠያየቅ ችግር ከሌለ በስተቀር" ሲሉ ነው የገለጹት።
Chloroquine የተሰኘው እና በ Plasmodium Vivax በተሰኘች ፓራሳይት የሚመጣ የወባ በሽታን ለማከም የሚረዳ መድኃኒት በተመለከተም "ይሄ መድኃኒት ከዚህ ቀደም መጠቀም ቆሞ ነበር በተወሰነ ደረጃ በሌሎች ለጋሽ ድርጅቶች እና ገዢ አካላት እንዲገባ ለማድረግ ተሞክሯል በቂ አልነበረም የገባው በዚህ ምክንያት ስጋት አለ ስጋት ብቻ አይደለም አንዱ ጋር ኖሮ ሌላው ጋር ላይኖር ይችላል" ብለዋል።
በለጋሽ ድርጅቶች በኩል የመጣውም ተሰራጭቶ እያለቀ ሲሆን በመንግስት በጀት አስቸኳይ ግዢ ተከናውኖ ከሁለት ሳምንት በኋላ ሃገር ውስጥ እንደሚገባም ሰምተናል።
Chloroquine ብዙም ተጠቃሚ የለውም ብለን ነው የምንወስደው ያሉት ዳይሬክተሩ አሁን ባለው የወባ ሥርጭት ግን አዲስ ነገር እየታየ ነው በ Vivax ሳቢያ የሚታመሙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑ ገልጸዋል።
የአቅርቦት ችግር ስጋት ቢኖርም ነገር ግን ሙሉ በሙሉ መድሃኒቱ አለመጥፋቱን ችግሩን ለመቅረፍም እየተሰራበት መሆኑንም ነው የነገሩን።
የራሱ ጥናት ቢያስፈልገውም አሁን ባለው መረጃ ሆስፒታል ገብተው መታከም የሚያስፈልጋቸው የውባ ታማሚዎች ቁጥር በጣም በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል ቁጥር መጨመር ብቻ አይደለም ኢትዮጵያ ውስጥ የወባ የህመም መጠኑም ጨምሯል ብለዋል።
የህመም መጠኑ ሲጨምር ደግሞ Coaretm እና Chloroquine ላያድኑ ይችላሉ ያሉት ዳይሬክተሩ፥ በዚህ ሳቢያ #Artesunate_Injection የተሰኘ መድኃኒት ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ተናግረዋል።
Artesunate Injection የሚያስፈልጋቸው የወባ ታማሚዎች ቁጥር ከዚህ በፊት ቁጥሩም ሆነ መጠኑ አነስተኛ ስለነበር የተጠቀሰው መድኃኒት ፍጆታ በጣም ትንሽ የነበረ ሲሆን አሁን ግን በወባ መባባስ ምክንያት የመድሃኒቱ ፍላጎት #በስድስት_እጥፍ ማደጉን ገልጸዋል።
የተጠቀሰው መድሃኒት በሃገር ውስጥ የነበረው ክምችት አስቀድሞ በነበረው ፍጆታ መሰረት በመሆኑ ስጋት ነበረን በመሃል ላይም ተቆራርጦ ነበር አሁን በ UNICEF ድጋፍ ተገዝቶ መግባቱን እና በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ከቻይና የሚገቡ ተጨማሪ መድሃኒቶች ይኖራሉ ብለውናል።
ከፍል ሁለት ይቀጥላል . . .

#ክፍልሁለት
ቲክቫህ የኢትዮጵያ የመድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴን በአንዳንድ አካባቢዎች አለ የሚባለው የመድሃኒት እጥረት በምን ምክንያት የተከሰተ ነው ሲል ጠይቋል።
መድሃኒት ከዚህ ቀደም ካለው የመቆራረጥ አዝማሚያ አንጻር ስጋት ስላለ ጤና ጣቢያዎች ከሚያስፈልጋቸው በላይ ይጠይቃሉ በዚህ ጊዜ በቅርንጫፍ ላይ እጥረት ሊያጋጥም ይችላል ሲሉ አስረድተዋል።
"በእኛ ግምገማ ግን ያለቀ መድኃኒት የለም በ Chloroquine በኩል የተወሰነ ችግር ሊገጥመም ይችላል ከዚህ ውጪ ሁሉም መድሃኒቶች በበቂ ክምችት በቅርንጫፍ ላይ አሉ" ነው ያሉት።
ይሄ ማለት ግን መድኃኒቶቹ በጤና ተቋማት መድረሱን አያረጋግጥም ብለዋል።
ለአብነትም በወላይታ አካባቢ ስላላው ሁኔታ የምክር ቤት አባላትም ጭምር ባሉበት ገምግመናል ያገኘነው ውጤት ግን ከታማሚ ቁጥር በላይ መድሃኒት መሰራጨቱን ነው ሲሉ ጠቅሰዋል።
ጠንካራ ሲስተም በሌለበት መድሃኒት ከጤና ተቋማት ወጥቶም ሊሸጥ ይችላል ይህ አንዱ ስጋታችን ነው ያሉ ሲሆን በግል ፋርማሲዎችም የመንግስት መድኃኒቶች እየተገኙ ነው ሲሉ አቶ ሰለሞን ነግረውናል።
"የኛ መድኃኒቶች የተቋማችን አርማ አለባቸው ያሉት ሃላፊው ነገር ግን እነዚህ መድሃኒቶች በግል ፋርማሲዎች እያገኘን ነው" ብለዋል።
መድሃኒቶች ለጤና ተቋማት በሚሰጥበት ወቅት መቀበላቸውን የሚያረጋግጥ ወረቀት ወይም (Proof of Delivery) አለ። ይህ ማስረጃ እያለ እጥረት አለ መባሉ ያለ Proof of delivery የምንሰጠው መድኃኒት ስለሌለ የተሰጡ መድኃኒቶች ከሆስፒታል እና ጤና ጣቢያ እየወጡ መሆኑን አመላካች ነው።
Proof of Delivery "ጤና ጣቢያው ተረክቢያለሁ ብሎ የሚቀበለው ወረቀት ነው ከተቀበለ በኋላ ግን ይሸጥ ወይስ ለታካሚ ይዋል ማረጋገጫ የለንም " ብለዋል።
በተጨማሪም ፈዋሽነቱ ያልተረጋገጠ መድኃኒት በኮንትሮባንድ ወደ በኢትዮጵያ እየገባ ነው ያሉት ሃላፊው እነዚህ መድሃኒቶች የኢትዮጵያ ምግብ እና መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን ያለመዘገባቸው እና የማያውቃቸው ናቸው ብለዋል።
"Artemether injection 80 Mg ተብሎ ኢትዮጵያ ውስጥ የተገኘ መድኃኒት አለ በላብራቶሪ ሲመረመር ግን Artemether የተሰኘው መድኃኒት ውስጡ አልተገኘም ካርቶኑ ላይ ከመጻፉ ውጪ ነው ያሉት።
እንደዚህ አይነት ነገሮች እየታዩ በመሆኑ ጉዳዩ ከፍተኛ ቁጥጥር የሚያስፈልገው ነው ብለዋል።
የኛ መድሃኒት ወጥቶ መሸጡ ላላግባብ፤ ወጪ ይዳርጋል ፈዋሽነቱ ያልተረጋገጠ መድኃኒት በኮንትሮባንድ ገብቶ መሰራጨቱ ደግሞ ገንዘቡንም አውጥቶ ጤናውንም ያጣል" ሲሉ አክለዋል።
በወባ በሽታ ዙሪያ ጥቆማ፤ መረጃ እና ሐሳብ ካላችሁ ያካፍሉን💬 @tikvahmagbot

በወባ በሽታ ዙሪያ ጥቆማ፤ መረጃ እና ሐሳብ ካላችሁ ያካፍሉን
@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
⭕️ LIVE
ሙሉ በሙሉ በመንግሥት ባለቤትነት የተያዘው ኢትዮ ቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻውን ለሀገር ውስጥ ባለሀብቶች በራሱን የቴሌብር መተግበሪያ በመጠቀም ለመሸጥ የሚያስችለውን ፈቃድ ማግኘቱን ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በይፋ ያበስራል።
ይህንን ዝግጅት Voice Chat በቀጥታ ይከታተሉ