TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
19K photos
292 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
加入频道
#Update

° እስራኤል በዛሬው እለት ሂዝቦላ ይንቀሳቀስባቸዋል ባለቻቸው ከ800 በላይ ቦታዎች ላይ ጥቃት ከፍታለች።

° የሊባኖስ የጤና ሚኒስቴር በጥቃቱ ቢያንስ 270 ሰዎች መሞታቸውን ሲግልጽ፤ 21 ህጻናት ናቸው ብሏል።

እስራኤል በዛሬው እለት "የሂዝቦላ ታጣቂዎች የሚንቀሳቀሱባቸው ቦታዎች ናቸው" ባለቻቸው ከ8 መቶ በላይ በሚቆጠሩ ኢላማዎች ላይ የአየር ጥቃት ከፍታለች።

ጥቃቱ የጋዛ ግጭት ከጀመረ በኋላ ከፍተኛው ነው ሲባል በቀጠናው ውጥረት ነግሷል።

ከሟቾቹ መካከል ምን ያህሉ ሲቪሎች ወይም የሂዝቦላህ ታጣቂዎች እንደሆኑ ግልፅ ባይሆንም እስራኤል ጥቃቶቹ ያነጣጠሩት ሂዝቦላ በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች እንደሆኑ ገልጻለች።

እስራኤል የጥቃት ትኩረቷን ወደ ሰሜናዊ ድንበር አዙራለች የተባለ ሲሆን በኢራን ይደገፋል የተባለው የሂዝቦላ ጦር ሃማስን በመደገፍ ወደ እስራኤል ሮኬቶችን እያስወነጨፈ ነው ተብሏል።

የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት ባሰራጩት የቪዲዮ መልእክት "የሰሜን አካባቢ ነዋሪዎችን በሰላም ወደ ቤታቸው በመመለስ ሂደት ውስጥ ግባችን ላይ እስክንደርስ ድረስ ጥቃቶቹ ይቀጥላሉ" ሲሉ ተናግረዋል።

በጥቃቱ ቢያንስ 270 ሰዎች መሞታቸው ሲገልፅ ከ1,024ሰዎች በላይ መቁሰላቸውን የሊባኖስ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ከተጎጂዎቹ መካከል ሴቶች እና ህጻናትን እንደሚገኙነት የሊባኖስ የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል። የሊባኖስ ነዋሪዎች ሂዝቦላህ የጦር መሳሪያውን ከሚያከማችባቸው ቦታዎች ለቀው እንዲወጡ እስራኤል ማሳሰቢያ ሰጥታለች ተብሏል።

የሂዝቦላ ጦር ለጥቃቱ ሰጠሁት ባለው አፀፋዊ ምላሸ በእስራኤል ወታደራዊ ካምፖች ላይ ሮኬቶችን ማስወንጨፉን ገልጿል።

እስራኤል ይህን መሰል ጥቃት ስትፈጽም ከ2006 በኋላ ይኽ የመጀመሪያው ነው ተብሏል።

@tikvahethmagazine
#ሊባኖስ

በሊባኖስ እና በቀጠናው ያለው ወቅታዊ የፀጥታ
ውጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ በመምጣቱ
በሊባኖስ፤ የቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ፅ/ቤት የጥንቃቄ መልዕከት አስተላልፏል።

ፅ/ቤቱ "በተለይም በደቡባዊ ሊባኖስ እንዲሁም በቤይሩት አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ተጠናከረው ቀጥለዋል" ብሏል።

ቆንስላ ጄኔራል ፅ/ቤቱ የሁኔታውን አሳሳቢነት ተረድቶ፣ የዜጎቻችን ደህንነት ለማስጠበቅ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን እየተከታተለ እንደሚገኝም አሳውቋል።

ስለሆነም የሚከተሉትን የጥንቃቄ እርምጃዎች ዜጎች እንድትወስዱ ሲል አሳስቧል።

1. በአብዛኛው የጥቃት ዒላማ ሊሆኑ ይቻላሉ ተብለው ከሚታሰቡ ቦታዎች እራስን ማራቅ፣

2. ከሊባኖስ መንግስት የሚሰጡ መመሪያዎችን እና አቅጣጫዎችን መተግበር ወይም ማከበር፤

3. አሁን ያለው ነባራዊ ሁኔታ የበለጠ እየከፋ የሚሄድ ከሆነ በቀጣይ የምንወስዳቸውን እርምጃዎችን ይፋ ስለምናደግ ከቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤቱ የፌስ-ቡክ ፔጅ የሚለቀቁ መረጃዎችን በየጊዜው መከታተል፣

4. ማንኛውንም የከፋ ሁኔታ በሚገጥማችሁ ወቅት በቆንስላው ቀጥታ የስልክ መስመር +9615467166 እና በWhatsapp ቁጥር ማሳወቅ ጠቃሚ ይሆናል።

@tikvahethmagazine
በደመራ እና በኢሬቻ በዓላት ለሚያስተባብሩ 310ሺህ ወጣቶች ስምሪት ተሰጠ።

የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት በሰላም እንዲከበር ለሚያስተባብሩ 310 ሺህ ለሚሆኑ የከተማው ወጣቶች የስራ ስምሪት ተሰጥቷል።

ስምሪቱን የሰጡት፥ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም ፀጥታ ቢሮ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን በጋራ በመሆን ነው።

ወጣቶቹ፥ ከፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅተው በተሰጣቸው ስምሪት መሰረት እንዲሰሩና በበዓላቱ እንዳይያዙ የተከለከሉ ነገሮችን እና በኮሪደር ልማት የተሰሩ የልማት ስራዎችን  እንዲቆጣጠሩ ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸዋል።

መረጃው የአ/አ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።

@tikvahethmagazine
#Canada 🇨🇦

የካናዳ መንግስት የትምህርት እና የስራ ፈቃድን ለመገደብ ያወጣው ፖሊሲ ከሁለት ቀናት በኋላ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል

የካናዳ መንግስት የትምህርት ፈቃዶችን ቁጥር መገደብን ጨምሮ አንዳንድ የኢሚግሬሽን ፖሊሲዎቹን አዘምኗል።

ይህም በሺዎች በሚቆጠሩ የውጭ ተማሪዎችን ያስቆጣ ሲሆን በመላው ካናዳ ከአገር ልንባረር እንችላለን በሚል ስጋት ተቃውሞአቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል።

በፖሊሲው ለውጥ መሰረት መንግስት የቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ የሚሰጣቸው እጩዎች ቁጥር በ25 በመቶ እንዲቀንስ የሚያደርግ ሲሆን የትምህርት ፈቃዶችንም ይገድባል።

ለፖሊሲው መሻሻል ሀገሪቱ ባለፉት ጥቂት አመታት ፈጣን የህዝብ ቁጥር መጨመር ማስመዝገቧ ምክንያት መሆኑን ተነግሯል።

አንዳንድ የተማሪዎች ተሟጋች ቡድን ተወካዮች የውጭ ሀገር ተመራቂዎች የስራ ፈቃዳቸው በ2024 መጨረሻ ሲያልቅ ከአገር የመባረር ስጋት እንዳለባቸው አስጠንቅቀዋል።

ካናዳ ከትምህርት ፈቃዶች በተጨማሪ ጊዜያዊ የውጭ ሀገር የስራ ፈቃዶችን በ65,000 ለመቀነስ አቅዳለች።

እ.ኤ.አ. በ 2023 የካናዳ መንግስት 183,820 ለሚሆኑ የውጭ ዜጎች ጊዜያዊ የስራ ፈቃድ ሰጥቶ ነበር።

ይህም  በ 2019 ከነበረው የስራ ፈቃድ ቁጥር በ 88 በመቶ ጭማሪ ነበረው።

በሌላ በኩል፣ በካናዳ ያለው የስራ አጥነት መጠን ባለፉት ሁለት ወራት በ 6.4 በመቶ የጨመረ ሲሆን 1.4 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች ስራ አጥ መሆናቸው ተነግሯል።

ከመስከረም 16 ጀምሮ  በሥራ ላይ የሚውለው አዲሱ ፖሊሲ ይህንን ችግር  ለመቅረፍ  ያለመ ነው ተብሏል።

@tikvahethmagazine
TIKVAH-MAGAZINE
#Mpox_Update የዝንጀሮ ፈንጣጣ (Mpox) የዓለም የህብረተሰብ የጤና ሥጋት ተብሎ ከተበየነ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከአፍሪካ ውጪ በስዊድን በበሽታው የተያዘ ሰው መገኘቱ ሪፖርት ተደርጓል። የሀገሪቱ የህብረተሰብ ጤና ኤጀንሲ እንዳስታወቀው የተያዘው ግለሰብ በሽታው ሪፖርት በተደረገበት የአፍረካ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው ሲሆን አሁን ላይ በስቶክሆልም የማገገሚያ ሥፍራ ክትትል እየተደረገለት ነው ተብሏል።…
በህንድ የመጀመሪያ የኤምፖክስ (Mpox) ታማሚ መገኘቱ ሪፖርት ተደረገ።

ህንድ በአዲሱ የኤምፖክስ ዝርያ የተያዘ ታማሚ በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ መመዝገቡን ይፋ  አድርጋለች።

በህንድ የተመዘገበወሰ #ክላድ 1 ለ (Clade_1 B) ተብሎ የሚጠራው አዲሱ ተለዋጭ እና ተላላፊ ዝርያ በአፍሪካ ውስጥ ካለው የMpox ወረርሽኝ ጋር ተመሳስይ ባህርይ ያለው እንደሆነ ሮይተርስ ዘግቧል።

በበሽታ የተያዘው ግለሰብ ወንድ ሲሆን እድሜው 38 አመቱ ነው። የደቡብ ኬራላ ግዛት ነዋሪ እና በቅርቡ ከዱባይ የተመለሰ እንደሆነ ተገልጿል።

የዓለም ጤና ድርጅት በነሀሴ ወር የMpox ወረርሽኝን በአፍሪካ ድንገተኛ የጤና አደጋ መሆኑን ካወጀ በኋላ ከአፍሪካ ውጪ ወደ ስዊድን፣ ታይላንድ እና ፓኪስታን መሰራጨቱ ተነግሯል።

@tikvahethmagazine
#ጥቆማ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቻይንኛ ቋንቋ ስልጠና ሊሰጥ መሆኑን አሳውቋል።

ሥልጠናው በሳምንት አንድ ቀን ቅዳሜ ጠዋት ከ3:00-5:00 ሰዓት፤ ለአስር ተከታታይ ሳምንት የሚሰጥ ይሆናል።

ለስልጠናው የግቢው ተማሪ ለሆኑ 500 ብር ከውጭ ለሚመዘገቡ 2000 ብር ያስከፍላል።

ስልጠናውን ለሚያጠናቅቁ ሰርተፊኬት እንደሚሰጥ አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ: አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮንፊሽየስ ኢንስቲትዩት፥ 6 ኪሎ ዋና ግቢ፣ 8ኛ ፍሉር ፎረም ህንጻ

ምዝገባ የሚያበቃው: መስከረም 21/2017 ዓ.ም

ስልጠናው የሚጀምረው: መስከረም 25/2017 ዓ.ም

የስልጠናው ቦታ: አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6 ኪሎ ካምፓስ

@tikvahethmagazine
TIKVAH-MAGAZINE
#Update ° እስራኤል በዛሬው እለት ሂዝቦላ ይንቀሳቀስባቸዋል ባለቻቸው ከ800 በላይ ቦታዎች ላይ ጥቃት ከፍታለች። ° የሊባኖስ የጤና ሚኒስቴር በጥቃቱ ቢያንስ 270 ሰዎች መሞታቸውን ሲግልጽ፤ 21 ህጻናት ናቸው ብሏል። እስራኤል በዛሬው እለት "የሂዝቦላ ታጣቂዎች የሚንቀሳቀሱባቸው ቦታዎች ናቸው" ባለቻቸው ከ8 መቶ በላይ በሚቆጠሩ ኢላማዎች ላይ የአየር ጥቃት ከፍታለች። ጥቃቱ የጋዛ ግጭት ከጀመረ…
#Update

እስራኤል በሂዝቦላህ ላይ በፈጸመችው መጠነ ሰፊ ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 558 ደርሷል።

የሊባኖስ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በእስራኤል በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 558 ሰዎች መሞታቸውን እና ከ1,835 በላይ መቁሰላቸውን ገልጿል።

እስራኤል በትላንትናው እለት ሂዝቦላ ይንቀሳቀስባቸዋል ባለቻቸው ከ800 በላይ ቦታዎች ላይ ጥቃት መክፈቷ ይታወቃል።

ይህም በጥቅምት ወር በእስራኤል እና በሂዝቦላ መካከል የተኩስ ልውውጥ ከተደረገ በኋላ በሊባኖስ ውስጥ የተደረገ ከፍተኛው ገዳይ ጥቃት ሆኖ ተመዝግቧል።

የሊባኖስ ነዋሪዎች በሀገሪቱ ደቡብ እና ምስራቅ በሚገኙ ቤቶች፣ መኪናዎች እና መንገዶች ላይ ያነጣጠረ ቀጣይነት ያለው የቦምብ ጥቃት መፈጸሙን ገልጸዋል።

የሊባኖስ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሟቾችን እና የተጎዱትን ሲቆጥሩ በሲቪሎች እና በተዋጊዎች መካከል ያለውን ልዩነት ሳይገልጽ ቆይቷል።

ሰኞ ማምሻውን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ ከሟቾቹ መካከል 50 ህጻናት, 58 ሴቶች እና ሁለት የህክምና ባለሙያዎች መሆናቸውን ገልጿል።

@tikvahethmagazine
TIKVAH-MAGAZINE
#ሊባኖስ በሊባኖስ እና በቀጠናው ያለው ወቅታዊ የፀጥታ ውጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ በመምጣቱ በሊባኖስ፤ የቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ፅ/ቤት የጥንቃቄ መልዕከት አስተላልፏል። ፅ/ቤቱ "በተለይም በደቡባዊ ሊባኖስ እንዲሁም በቤይሩት አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ተጠናከረው ቀጥለዋል" ብሏል። ቆንስላ ጄኔራል ፅ/ቤቱ የሁኔታውን አሳሳቢነት ተረድቶ፣ የዜጎቻችን ደህንነት ለማስጠበቅ…
ምን ያህል ኢትዮጵያዊያን በሊባኖስ ይኖራሉ?

በቤሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ በሊባኖስ እና ቀጠናው ያለው ወቅታዊ ሁኔታ እየከፋ መምጣቱን ተከትሎ ዜጎች የጥንቃቄ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ማሳሰቡ ይታወሳል።

በሊባኖስ በእስራኤል ሃይሎች እና በሂዝቦላህ መካከል የነበረውን ውጥረት ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር #ከወር በፊት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ኮሚቴ ማቋቋሙን አስታውቆ ነበር።

ግጭቱ የሚባባስ ከሆነም መንግስት እስከ 150,000 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ዜጎችን ወደ አገራቸው ለመመለስ መዘጋጀቱን አሳውቋል።

የወቅቱ ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብዩ ተድላ “ህጋዊም ይሁኑ ሕገወጥ፣ ተዘጋጅተው መጠበቅ አለባቸው ፣የጸጥታው ጉዳይ ተባብሶ ከቀጠለ የኢትዮጵያ መንግስት በሊባኖስ ያሉትን ህገወጥ እና ህጋዊ ዜጎቹን ወደ አገራቸው ይመልሳል" ማለታቸው ይታወሳል።

በሌላ መረጃ የአለማቀፉ ፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) እ.አ.አ በኦገስት 2023 ባወጣው ሪፖርት 160,738 የሌላ ሀገር ዜጎች በሊባኖስ እንደሚኖሩ ይገልጻል። ከነዚህ ውስጥም 119,154 የሚሆኑት በከተማ ውስጥ የሚኖሩ ናቸው።

ከስደተኞቹ መካከል ፦

- 37 በመቶ ወይም 58,772 የሚሆኑት እና  ኢትዮጵያውያን ናቸው።

- ከኢትዮጵያውያን ስደተኞች መካከል 94 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ሲሆኑ፤ 5 መቶ ደግሞ ወንዶች ናቸው።

በተለያዩ ቁጥራዊ መረጃዎች በአጠቃላይ በሀገሪቱ ካሉ ስደተኞች ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዙት የኢትዮጵያ ዜጎች ሲሆኑ አብዛኞቹ ደግሞ ሴቶች ናቸው።

@tikvahethmagazine
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በጥራትም:በብራንድም:በባትሪ ቆይታም  አስተማማኝ  የሆኑ የተለያዩ  ሞዴል ያላቸዉ  በፈለጉት ስክሬን መጠን : ኮር እና ጀነሬሽን   አሉን።

ላፕቶፕ  ከመገዛቶ በፌት ማወቅ ያለባቹሁን ወሳኝ ነገሮች   እናስረዳለን።
ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች ፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች  ወ.ዘ.ተ ሁሉም አሉን ።
በላፕፖቻችን ጥራት ላይ አንደራደርም!
!
የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።

@sww2844 0928442662 / 0940141114

https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17
የተሳትፎ ጥሪ

ሐሳብ ያላቸው ወጣቶች የሚጽፉበትና ሐሳባቸውን የሚገልጹበት የወጣቶች መጽሔት የመጀመሪያ ዕትም ለሚቀርቡ ጹሑፍ ማቅረብ ተጀምሯል።

ብጽፈው ብላችሁ የምታስቡት ሐሳብ አላችሁ ? እንግዲያውስ ተቀላቀሉንና ሐሳባችሁን አጋሩን!

ጹሑፉቸው ለሚታተምላቸው ወጣቶች መጠነኛ ክፍያ ተዘጋጅቷል፤ በዓመቱ ምርጥ ጸሐፊም ተለይቶ ልዩ ሽልማት የሚበረከትም ይሆናል።

በየዘጋጁ ጹሑፎች ላይ የተለያዩ የውይይት እና የትውውቅ መድረኮችም ይኖሩናል።

የሐሳብ መድረካችንን ይቀላቀሉ 👉 https://yangx.top/ihaveanidea1
TIKVAH-MAGAZINE
#ሊባኖስ በሊባኖስ እና በቀጠናው ያለው ወቅታዊ የፀጥታ ውጥረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ በመምጣቱ በሊባኖስ፤ የቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ፅ/ቤት የጥንቃቄ መልዕከት አስተላልፏል። ፅ/ቤቱ "በተለይም በደቡባዊ ሊባኖስ እንዲሁም በቤይሩት አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ተጠናከረው ቀጥለዋል" ብሏል። ቆንስላ ጄኔራል ፅ/ቤቱ የሁኔታውን አሳሳቢነት ተረድቶ፣ የዜጎቻችን ደህንነት ለማስጠበቅ…
#Update

በሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት በተለይ በደቡብ እና ምሥራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርቧል።

በዚህም በአካባቢው የሚኖሩ ወገኖች ስማቸውን ፓስፖርት ላይ እንደተፃፈው፣ የፓስፖርት ቁጥር፣ ስልክ ቁጥራቸውን እንዲያስመዘግቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በደቡብ ሊባኖስ (ታየር ፣ ሱር ፣ ቢንት ጅቤል ፣ ማርጃዩን፣ ነበትዬ፣ ሳይዳ እና አካባቢው) የሚገኙ ወገኖች በስልክ ቁጥር 03-7354 51 ወይም 03-87-10-89

በምሥራቅ ሊባኖስ (አልቤክ፣ ቤካ ሸለቆ እና አካባቢው) የሚገኙ ደግሞ በስልክ ቁጥር 81 77-62-51 ወይም 81-63-07-98 በመደወል እንዲመዘገቡ ጄኔራል ጽሕፈት ቤት አሳስቧል፡፡

@tikvahethmagazine
TIKVAH-MAGAZINE
#Update እስራኤል በሂዝቦላህ ላይ በፈጸመችው መጠነ ሰፊ ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 558 ደርሷል። የሊባኖስ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በእስራኤል በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 558 ሰዎች መሞታቸውን እና ከ1,835 በላይ መቁሰላቸውን ገልጿል። እስራኤል በትላንትናው እለት ሂዝቦላ ይንቀሳቀስባቸዋል ባለቻቸው ከ800 በላይ ቦታዎች ላይ ጥቃት መክፈቷ ይታወቃል። ይህም በጥቅምት ወር በእስራኤል እና በሂዝቦላ…
#Update

🟢 የእስራኤል ጦር ዛሬ ጠዋት ለመጀመሪያ ጊዜ ቴል አቪቭ የደረሰና በሂዝቦላ የተወነጨፈው የባሊስቲክ ሚሳኤል ማክሸፉን አስታውቋል።

የሊባኖስ ታጣቂ ቡድን ኢላማ ያደረገው በቴል አቪቭ አቅራቢያ በሚገኘው የእስራኤል የስለላ ድርጅት ዋና መስሪያ ቤትን ሲሆን የተመዘገበ ጉዳት እስካሁን ሪፖርት አልተደረገም።

🟢 ዛሬ የእስራኤል ጦር በደቡባዊ ሊባኖስ እና ቤቃ አካባቢ አዲስ ጥቃት መፈጸሙን ገልጿል።

የእስራኤል ጦር የሂዝቦላ የጦር መሳርያ ቦታዎች ናቸው ያለውን የአየር ዘመቻ ከማስፋፋቱ በፊት በምስራቅ እና በደቡብ ሊባኖስ የሚገኙ ነዋሪዎችን ለቀው እንዲወጡ ማስጠንቀቁ ይታወሳል።

🟢 በቤሩት የሚገኘው የአሜሪካ ኢንባሲም ዜጎች በተገኘው የአየር ትራንስፖርት አማራጭ ሊባኖስን ለቀው እንዲወጡ አዟል።

ኢንባሲው በመልዕክቱ፤ "ብዙ አየር መንገዶች በረራዎችን አግደዋል፤ ወይም ሰርዘዋል። ብዙ በረራዎችም ትኬታቸው ተሸጦ አልቋል። ሆኖም ከሊባኖስ ለመውጣት ውስን የንግድ መጓጓዣ አማራጮች አሁንም ይገኛሉ" ሲል አስታውቋል።

🟢 ብሪታንያ ዜጎቿን ከሊባኖስ ለማስወጣት 700 ወታደሮች ወደ ቆጵሮስ የብሪታኒያ ጦር ሰፈሮች አሰማርታለች። በአሁኑ ጊዜ የሀገሪቱ ሁለት የጦር መርከቦች በደቡባዊ ቆጵሮስ የባህር ዳርቻ ላይ ያሉ ሲሆን የሮያል አየር ኃይል አውሮፕላኖች እና ሄሊኮፕተሮችም ዜጎችን ከሊባኖስ ለማውጣት ዝግጁ ናቸው ተብሏል።

🟢 ሩሲያ ዜጎቿ ለደህንነታቸው ሲሉ በንግድ በረራዎች ሊባኖስን ለቀው እንዲወጡ አሳስባለች። የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ በሰጡት መግለጫ፥ እስራኤል በሊባኖስ በሂዝቦላህ ኢላማዎች ላይ የምታደርሰው ጥቃት የመካከለኛው ምስራቅ ያለውን አለመረጋጋት የሚያባብስና የሰፉ ግጭት የመፍጠር አቅም እንዳለው ገልጻለች።

@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-MAGAZINE
#ወባ ° " ወባ ሰው እየገደለ ነው " - የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ነዋሪዎች ° " በበሽታው የሰው ሕይወት እያለፈ ነው በተባለው ላይ ግን እስከአሁን በመረጃ የተገመገመ ነገር የለም “ - የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲቲዩት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተቀሰቀሰ የወባ በሽታ በርካቶችን ለህመም እና ለሞት እየዳረገ እንደሚገኝ ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል። ነዋሪዎች " በበሽታው ተይዘው…
" የወባ ሕሙማን ቁጥር እየጨመረ ነው " - የአማራ ክልል የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

በአማራ ክልል ከሐምሌ 2016 ዓ.ም ጀምሮ 415 ሺህ 173 የወባ ሕሙማን ሪፖርት መደረጉን የክልሉ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የወባ መከላከል እና መቆጣጠር ፕሮግራም አሥተባባሪ ዳምጤ ላንተ ለአሚኮ ገልፀዋል።

በክልሉ የወባ ስርጭት በ18 ነጥብ 4 በመቶ የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ቀዳሚውን እንደሚይዝ ሲገለፅ ደቡብ ጎንደር ዞን (18 በመቶ)፣ ማዕከላዊ ጎንደር ዞን (11 በመቶ) እንደሚሸፍኑ አስተባባሪው ተናግረዋል፡፡ ቀሪዎቹ ምዕራብ ጎጃም፣ ምሥራቅ ጎጃም እና ምዕራብ ጎንደር በወባ ስርጭት በቅደም ተከተል ተቀምጠዋል፡፡

ለስርጭቱ የአየር ንብረት መለወጥ፣ የማኅበረሰቡ የአካባቢ ቁጥጥር ሥራ እየቀነሰ መምጣት፣ የአጎበር አጠቃቀም እና ለታለመለት ዓላማ የማዋል ግንዛቤ አናሳ መሆን፣ የልማት ቀጠናዎች ላይ ያለው የሰው ፍሰት እና ለወባ ምቹ ሁኔታ መኖር እንዲሁም የተፈናቃይ መኖር እና ለበሽታው ተጋላጭ መሆናቸው ለቁጥሩ መጨመር እንደምክንያት ተቀምጧል፡፡

@tikvahethmagazine
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በጥራትም:በብራንድም:በባትሪ ቆይታም  አስተማማኝ  የሆኑ የተለያዩ  ሞዴል ያላቸዉ  በፈለጉት ስክሬን መጠን : ኮር እና ጀነሬሽን   አሉን።

ላፕቶፕ  ከመገዛቶ በፌት ማወቅ ያለባቹሁን ወሳኝ ነገሮች   እናስረዳለን።
ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች ፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች ፣ ለጌመሮች  ወ.ዘ.ተ ሁሉም አሉን ።
በላፕፖቻችን ጥራት ላይ አንደራደርም!
!
የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት ይሄን 👉 @samcomptech ተጭነው በቴሌግራምው ማየት ይችላሉ።

@sww2844 0928442662 / 0940141114

https://maps.app.goo.gl/H3PM1NrTcQ4SWkK17