ቲክ ቶክ በአፍሪካ የአማካሪ ቡድን ማቋቋሙን አስታወቀ።
ቲክቶክ የተሰኘው የቪድዮ ማጋሪያ የማህበራዊ ሚዲያ በአፍሪካ የአማካሪ ምክር ቤት ማቋቋሙን ተገልጿል። በዚህ ምክር ቤት ፕሮፌሰር መድኅኔ ታደሰን ጨምሮ 8 አባላት ያሉት ነው።
መተግበሪያው የሀገራትን ባህልና እሴት እንዲጠብቅ ሲደርስ ለነበረበት ጫና ምላሽ ለመስጠት እንደሆነ ተገልጿል።
ይህ አማካሪ ቡድን የቲክቶክ ፖሊሲ ከአፍሪካ ሀገራት ህጎች ጋር አብረው እንደሚሄዱ፤ እንዴት ሀሰተኛ እና ጥላቻ ንግግሮቾን መቆጣጠር እንደሚችል፤ ከአከባቢው ማኅበረሰብ ጋር መተባበር በሚቻልበት መልኩ እና የዲጂታል ክህሎትን ከማሳደግ አንጻር ያማክራሉ ተብሏል።
@tikvahethmagazine

የደመራ በዓል እንዴት መከበር ጀመረ?
በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ንግስት እሌኒ ከልጇ ከንጉስ ቆስጠንጢኖስ ጋር በመሆን የኢየሱስ ክርስቶስን መስቀል አይሁድ ከቀበሩት ለመፈለግ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዛለች።
በዚያም በደረሰች ጊዜ የተቀበረበትን ቦታ የሚያሳያት አጥታ በመፈለግ ብዙ ጊዜ አሳልፋለች፡፡ መስቀሉ የተቀበረበትን ቦታ ለ300 ዓመታት ያህል የቆሻሻ መጣያና ማከማቻ በማድረጋቸው በቀላሉ አልተገኘም ነበር።
በኋላ ግን አንድ ኪራኮስ የሚባል አረጋዊ አካባቢውን ነግሯት ደመራ አስደምራ ዕጣን አጢሳ ወደ ፈጣሪዋ ብትማፀን የዕጣኑ ጢስ ወደ ሰማይ ከወጣ በኋላ መንበረ ጸባዖት ደርሶ ተመልሶ መስቀሉ የተቀበረበትን ስፍራ አመለከታት፡፡
ደመራ ማለት መጨመር፣ መሰብሰብ፣ መከመር ነው። ኪዳነ ወልድ ክፍሌም በመዝገበ ቃላት መጽሐፋቸው ደመራ የሚለውን ቃል ደመረ ከሚለው የግእዝ ቃል አውጥተው ደመራ ግእዝና አማርኛን ያስተባበረ መሆኑን ገልጸው የበዓለ መስቀል ዋዜማ እንጨቶች የሚደመሩበት መሆኑን አስረድተዋል፡፡
መስከረም 16 ቁፋሮ አስጀምራ መጋቢት 10 ቀን መስቀሉን አግኝታ አስወጥታ የቤተ ክርስቲያኑም መሠረት ወዲያው እንዲጣል አደረገች፤ የደመራ ሥርዓት ከዚህ ሲያያዝ የመጣ መሆኑ እንደሆነ ይገለጻል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ መስከረም 16 ቀን የምትደምረው ደመራ ቁፋሮው የተጀመረበትን ዕለት መሰረት አድርጋ ነው።
የመስቀል ደመራ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት(ዩኔስኮ) እውቅና ተሰጥቶት በዓለም አቀፍ ቅርስነት ተመዝግቧል።