TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
19K photos
292 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
加入频道
TIKVAH-MAGAZINE
Photo
#Update

የስም ቀይሩ ውሳኔው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለአሻም ከላክው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ጋር የሚገናኝ አለመሆኑን የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን ገልጿል።

የፍርድ ቤት ትእዛዙ የወጣው በብስራት ራድዮ ሲተላለፍ ከነበረው አሻም አፍሪካ የተሰኘ ፕሮግራም አዘጋጆች ተቋሙ ላይ ባቀረቡት ክስ መሰረት መሆኑን  የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ፈቃድ፣ ምዝገባና እውቅና ዴስክ ሃላፊ አቶ ደሴ ከፍያለው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የስሙ ጉዳይ ቆየት ያለ ክስ እንደነበር ገልጸው ይግባኝ ተጠይቆበት እስከ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የደረሰ እና ለፕሮግራሙ አዘጋጆች ተፈርዶ ውሳኔ የተሰጠበት ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።

ፍርድ ቤቱ የመገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን ውሳኔውን እንዲያስከብር በጠየቀው መሰረት ደብዳቤ ለአሻም ቴሌቪዥን መጻፉን ገልጸዋል።

አሻም ቴሌቪዥን በአዲስ የስም ስያሜ እና  በተጨማሪ አዳዲስ ዝግጅቶች ወደ ተመልካቾች እንደሚደርስ ከመግለፅ ውጪ ስለውሳኔው ያለው ነገር የለም።

ተጨማሪ ያንብቡ 👉 https://yangx.top/tikvahethiopia/91330?single

@tikvahethmagazine
TIKVAH-MAGAZINE
ዛሬ ጠዋት በአዋሽ እንዲሁም በመተሀራ አከባቢዎች የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቷል። በኢትዮጵያ ከሳምንት በፊት 4.9 ሬክተር ስኬል የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ በአዋሽ ፣ መተሀራ ፈንታሌ ተራራ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ መድረሱን ሪፖርት መደረጉ ይታወሳል። በዛሬው ዕለት ደግሞ ላይ ከጠዋቱ 1:40 አከባቢ በድጋሜ ተመሳሳይ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን በአከባቢው ያለ የቲክቫህ ቤተሰብ አረጋግጦልናል። ሳቡሬ…
#Update: በሬክተር ስኬል 4.6 አካባቢ የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ዛሬ ጠዋት 1 ሰዓት ከ37 ደቂቃ ከ50 ሴኮንድ ላይ ባለፈው በተከሰተበት አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ መከሰቱን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር ዶክተር ኤሊያስ ሌዊ ለብሔራዊ ጣቢያ ተናግረዋል።

የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት አዲስ አበባ ድረስ መሰማቱንም ነው የገለጹት። ለመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት የሆነው ቅልጥ አለት መሬት ውስጥ መምጣቱ መሆኑ የተናገሩት ዶክተር ኤሊያስ ይሄው እንቅስቃሴ ወደላይ አለመወጣቱን ነው የተናገሩት።

ላለፉት 19 ተከታታይ ቀናት ያህል ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች መኖራቸውን እና አሁንም ያለውን ሁኔታ እየተከታተልን ነው ብለዋል።

@tikvahethmagazine
TIKVAH-MAGAZINE
#እንድታውቁት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት እስከ ህዳር  30/ 2017 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ  የነባር አባላት እድሳት እና  የአዲስ  አባላት ምዝገባ እያከናወነ ይገኛል። ለምዝገባ ሲመጡ ለነባር አባላት - የታደስ የቀበሌ መታወቂያ - የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የአባልነት ካርድ - የአባልነት ክፍያ 1500 ብር እና - እድሜያቸው 18 አመት…
#Update

ከጥቅምት 1 እስክ ህዳር 30 በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ ጤና ጣቢያዎች የሚካሄደውን የ2017 ዓ.ም የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የአባልነት የምዝገባ አስመልክቶ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ መግለጫ ሰጥተዋል።

ኃላፊው፥ በዘንድሮው ዓመት አዳዲስ አባላቶችን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ2.5 ሚሊዮን በላይ የከተማዋን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ለማድረግ እቅድ መያዙን ነው የገለጹት።

ክፍያው ስንት ነው ?

በከተማ አስተዳደሩ በጸደቀው መዋጮ መጠን መሠረት መደበኛ መዋጮ መጠን አንድ ሺህ 500 ብር ሲሆን የድሀ ድሃ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ሙሉ በሙሉ በከተማ አስተዳደሩ እንደሚሸፈን ተናግረዋል።

ይህ ማለት - ነባር አባል መዋጮ 1,500 ብር፣ አዲስ አባል መዋጮ 1,500 ብር እና የመመዝገቢያ 200 ብር በአጠቃላይ 1,700 ብር አመታዊ መዋጮ ይክፍላል ነው ያሉት፡፡

ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆነ ልጆች እና በአባሉ ጥላ ስር ለሚኖሩ ተጨማሪ ቤተሰብ 750 ብር ይከፈላል ብለዋል።

በኢ-መደበኛ ክፍለ ኢኮኖሚ የተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተቀመጠውን መዋጮ በመክፈል ዓመቱን ሙሉ በሁሉም ውል በተገባባቸው የጤና ተቋማቶች አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉም ተናግረዋል።

በ2016 ዓ.ም ከ2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዜጎች በላይ በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አባል የሆኑ ሲሆን ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ አባላትና ቤተሰቦቻቸው በተመላላሽ እና በተኝቶ ህክምና ከጤና ጣቢያ ጀምሮ እስከ ፌደራል ሆስፒታሎች ባሉት የጤና ተቋሞች የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል ተብሏል።

#ማስተካከያ : ቢሮው ከቀናት በፊት በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ በአዲስ አበባ መደበኛ የጤና መድህን የመዋጮ መጠን 1,500 ብር እንደሆነ እንዲሁም 500 ብር በከተማ አስተዳደሩ የሚሸፈን የገለጸ ቢሆንም በዛሬው መግለጫ ተስተካክሏል።

ይህ መረጃ እስከወጣበት ድረስ ግን ቀድሞ የወጣው መረጃ በተቋሙ የፌስቡክ እንዲሁም የቴሌግራም ገጽ ላይ ይገኛል።


credit : EPA

@tikvahethmagazine
#Update

ኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ሽያጩ ሁለት ዙር እንዳለው አስታውቋል።

በመጀመሪያው ዙር የመደበኛ አክሲዮን ሽያጭ፦

- በ2016 በወጣው የሂሳብ ሪፖርት የድርጅቱ ካፒታል = 100 ቢሊዮን ብር

- በአለም አቀፍ የ3ተኛ ወገን የገበያ ተመን መሰረት ድርጅቱ የሚያወጣው ዋጋ = 300 ቢሊዮን ብር

- በመጀመሪያው ዙር መደበኛ የአክሲዮን ሽያጭ የቀረበው = 100 ሚሊዮን

- የአንድ ሼር ዋጋ 300 ብር

- 100 ሚሊዮን ሼር በ300 ብር ሲሸጥ ኢትዮ ቴሌኮም ከሼር ሽያጭ 30 ቢሊዮን ብር ያገኛል።

- ዝቅተኛ መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን  = 33 ሼር ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 9,900 ብር ይሆናል።

- ከፍተኛው መግዛት የሚቻለው የሼር መጠን 3,333 ሲሆን ይህን በገንዘብ ሲቀመጥ 999,900

- መግዛት የሚቻለው ከዛሬ ጥቅምት 6 እስከ ታህሳስ 25 ድረስ ይሆናል።

- የሼር አባላቱ የሚታወቁት = ጥር 23/2017

- ሽያጩ በቴሌብር ብቻ የሚደረግ ይሆናል።

- ክፍያውን በ48 ሰዓት ውስጥ መክፈል ይቻላል።

- አንድ አክሲዮን ገዢ ሲፈጸም ከአክስዮኑ ዋጋ በተጨማሪ 1.5% የአገልግሎት ክፍያ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ የሚከፍል ይሆናል።

- ከከፍተኛው የአክሲዮን መጠን በላይ መግዛት አይቻልም።

- ግብይቱ የሚካሄደው በኢትዮጵያ ብር ብቻ ነው።

#Note: ይህ ዜና ማስተካከያ ተደርጎበት የወጣ ነው።

@tikvahethmagazine
TIKVAH-MAGAZINE
በናይጄሪያ በነዳጅ ጫኝ ቦቴ ላይ በደረሰ የፍንዳታ አደጋ በትንሹ 94 ሰዎች ሞቱ በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ ነዳጅ ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ቦቴ ላይ በደረሰ ፍንዳታ በትንሹ 90 ሰዎች ሲሞቱ 50 ሰዎች መቁሰላቸውን አናዱሉ ዘግቧል። የነዳጅ ማጠራቀሚያው የፈነዳው በሀገሪቱ ጂጋጋ ግዛት፤ በፍጥነት መንገድ ላይ እንደሆነ ሲነገር ሲኤን ኤን በበኩሉ የሟቾች ቁጥር 94 መድረሱን ዘግቧል። አደጋው የተከሰተው ትላንት…
#Update: በናይጄሪያ ነዳጅ ጫኝ ቦቴ ላይ በደረሰው ፍንዳታ የሟቾች ቁጥር ከ150 አልፏል

አደጋው የተከሰተው ሹፌሩ በአገሪቱ የማጂያ ከተማ አቅራቢያ ሊደርስ ሲል ተሽከርካሪውን መቆጣጠር ባለመቻሉ መሆኑን የፖሊስ ቃል አቀባይ ላዋን ሺዩ አደም ለአናዱሉ ተናግረዋል።

በተከሰተው አደጋ ቦቴው የያዘውን ነዳጅ ማፍሰስ መጀመሩ ሲስተዋል፤ ቦቴው የያዘው ነዳጅ መፍሰስ መጀመሩን የተመለከቱ ነዋሪዎች ነዳጁን ለመቅዳት ሲሞክሩ ፍንዳታ በመከሰቱ ምክንያት በርካታ የአንድ አካባቢ ነዋሪዎች ለህልፈት ተዳርገዋል።

በፍንዳታው ለሞቱ ከ150 በላይ ሰዎች የጅምላ የቀብር ስነስርአት መካሄዱን አልጀዚራ ዘግቧል። የሟቾች ቁጥር የጨመረውም በርካቶች በመንገድ ላይ የፈሰሰውን ቤንዚን ለመቅዳት ሲሞክሩ በመሆኑ ነው።

በዛሬው እለት በአደጋው ​​የሞቱት ሰዎች ቁጥር 157 መድረሱን የዘገበው አልጀዚራ በጂጋጋ ግዛት የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ከ100 በላይ ተጎጂዎች በሆስፒታሎች ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል። የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችልም ተነግሯል።

አሽከርካሪው ጉዳት እንዳልደረሰበት ሲገለፅ ፖሊስ ምርመራ ለማድረግ ወደ እስር ቤት ወስዶታል።

የሀገሪቱ ምክትልፕሬዝዳንት ካሺም ሼቲማ ለተጎጂ ቤተሰቦች የሐዘን መግለጫ ያስተላለፉ ሲሆን በናይጄሪያ የነዳጅ ትራንስፖርት ደህንነት ፕሮቶኮሎችን በተመለከተ አጠቃላይ ግምገማ እንዲደረግ ጠይቀዋል።

@tikvahethmagazine
TIKVAH-MAGAZINE
#Update የስም ቀይሩ ውሳኔው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ለአሻም ከላክው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ጋር የሚገናኝ አለመሆኑን የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን ገልጿል። የፍርድ ቤት ትእዛዙ የወጣው በብስራት ራድዮ ሲተላለፍ ከነበረው አሻም አፍሪካ የተሰኘ ፕሮግራም አዘጋጆች ተቋሙ ላይ ባቀረቡት ክስ መሰረት መሆኑን  የባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ፈቃድ፣ ምዝገባና እውቅና ዴስክ ሃላፊ አቶ ደሴ ከፍያለው ለቲክቫህ…
#Update

አሻም ቴሌቪዥን የተያዘ የንግድ ምልክትን በመጠቀም በቀረበበት ክስ ሲጠቀምበት የነበረውን "አሻም" የሚለውን ስያሜ መጠቀም አንዲያቆም ፍርድ ቤት ወሳኔ አስተላለፎ የነበረ መሆኑ ይታወሳል።

አሁን ላይ ከከሳሽ ጋር እርቅ በመፈጸሜ ስያሜውን መጠቀሜን እቀጥላለሁ ሲል ጣቢያው አስታውቋል።

ፍርድ ቤቱም የእርቅ ሥምምነቱ ህግንና ሞራልን የማይቃወም መሆኑን በመረዳት እርቁን ተቅበሎታል ብሏል፡፡ 

@tikvahethmagazine
TIKVAH-MAGAZINE
የሃማስ መሪ ያህያ ሲንዋር በጋዛ መገደላቸውን የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተናገሩ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ የሃማስ መሪ ያህያ ሲንዋር መሞቱን ስለመናገራቸው አለማቀፍ ብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል። እስራኤል ከአመት በፊት " በኦክቶበር 7 ሀማስ ከፈፀመብኝ ጥቃት ጀርባ የነበረው ቁልፉ ሰው እሱ ነው " በማለት የተፈላጊ ዝርዝር ውስጥ ያካተተችው ያህያ ሲንዋር ዛሬ በተደረገ ኦፕሬሽን…
#Update: ሃማስ ያህያ ሲንዋር መገደሉን አረጋገጠ

በትላንትናው እለት የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ የሃማስ መሪ ያህያ ሲንዋር እስራኤል በከፈተችው ጥቃት መገደሉን ገልፀው ነበር።

በዛሬው እለት ደግሞ የሃማስ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ካህሊል አል-ሃያ የ62 አመቱ ያህያ ሲንዋር መሞቱን ባስተላለፉት የቪዲዮ መልእክት አረጋግጠዋል። " የሲንዋር መሞት ቡድኑን ያጠነክረዋል " ሲሉም ተናግረዋል።

ጆ ባይደን ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት አስተያየል  የሲንዋር ግድያ በጋዛ ለአንድ አመት በዘለቀው ጦርነት ውስጥ የተኩስ ማቆም ስምምነት ተስፋን ከፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ደግሞ "የሐማስ መሪ መሞት የጋዛ ጦርነት ያበቃል ማለት አይደለም" ሲሉ ተደምጠዋል።

የሲንዋርን ሞት ተከትሎ ሂዝቦላህ ከእስራኤል ጋር የሚደረገው ግጭት ተባብሶ እንደሚቀጥል የገለፀ ሲሆን ኢራን በበኩሏ "የሲንዋር ሞት ሀማስ እንዲጠናከር  ያደርገዋል" ብላለች።

@tikvahethmagazine
TIKVAH-MAGAZINE
Photo
#Update

ወደ ሶማሊያ የባህር ዳርቻ የተላከችው ኦሩክሪየስ (Oruç Reis) የተሰኘችው የቱርክዬ የአሰሳ መርከብ በሶማሊያ ሞቃዲሾ ወደብ ደርሳለች።

መርከቧ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ፤ የቱርክ ኢነርጂ ሚኒስትር አልፓርስላን ባይራክታር ጨምሮ የሀገሪቱ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት አቀባበል ተደርጎላታል።

የቱርክ ኢነርጂ ሚኒስትር አልፓርስላን ባይራክታር በዚሁ ወቅት "በዚህ ስምምነት በሶማሊያ ግዛት ላይ የነዳጅ እና ጋዝ ፍለጋ ስራዎችን እንሰራለን" ሲሉ ተናግረዋል።

በዕለቱ መርከቧ አሰሳ ታከናውንበታለች ተብሎ የተቀመጠ ካርታ በፎቶ ከወጣ በኋላ የፑንት ላንድ አመራሮች ካርታው "ማዱድ" የተሰኘውን የፑንት ላንድን ግዛት የድንበር ውዝግብ ያለበት በሚል ማስቀመጡን ተችተዋል።

@tikvahethmagazine