TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
19K photos
292 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
加入频道
የሩዋንዳ የፓርላማ አባላት የአባትነት የሥራ ፍቃድ ወደ አንድ ወር ከፍ እንዲል ጥያቄ ማቅረባቸው ተሰምቷል።

ህግ አውጭዎች ለታችኛው ምክር ቤት የማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡት ረቂቅ አሁን በሀገሪቱ ያለው የ4 ቀን የአባትነት የሥራ ፍቃድ (Paternity leave)በቂ እንዳልሆነና የሥራ ፈቃዱ ወደ 30 ቀን ከፍ እንዲል ነው የጠየቁት።

ይህም እናት ከወሊድ በኋላ በሚኖራት ጊዜ በቂ የሆነ የባሏ [አባት] እንክብካቤ እንድታገኝና አባት አዲሱ ከሚወለደው ልጁ ጋር የመጀመሪያዎቹን ወቅቶች በአግባቡ እንዲያሳልፍና ጠንካራ ግንኙነት እንዲኖረው በማሰብ እንደሆነ አስታውቀዋል።

በሀገሪቱ የወሊድ ፈቃድ በተመለከተ እ.ኤ.አ በ2018  ለእናትም ሆነ ለአባት በሰራተኛ ህጉ ላይ በግልጽ የተቀመጠ ነገር የለም።

የዕረፍት ቀናቶቹ ውሳኔም በሚኒስቴሩ በኩል የወጡ ህጎች ናቸው። ጠያቂዎቹ ይኽ እንዲሻሻልና የወሊድ ፍቃድ ለእናትም ለአባትም በሰራተኛ ህጉ በግልጽ እንዲቀመጥም ጠይቀዋል።

ጋንቢያ፣ ሲሼልስና ኬንያ ለአባቶች የ2 ሳምንታት የሥራ ፈቃድ ከሙሉ ክፍያ ጋር ፈቃድ የሰጡ ሀገራት ናቸው። [ከላይ የተያያዘውን ቁጥራዊ መረጃ ይመልከቱ #WB]

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ 515/1999 መሰረት የወሊድ ፍቃድ [የእናቶች] ሦስት ወር ነበር፤ በ2010 ዓ.ም በተሻሻለው አዋጅ ይህ ወደ 120 ተከታታይ ቀናት ማደግ ችሏል። ይህ በግሉ ዘርፍ ያሉ ሴቶችን የሚያካትት አይደለም።

ከአባቶች ጋር ተያይዞ በሀገራችን በሰራተኛ ህጉ የተቀመጠው #አስር የሥራ ቀናት ከሙሉ ክፍያ ጋር እንዲያገኙ ነው።

[#ማስተካከያ፦ በኢትዮጵያ ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ የትዳር ጓደኛው ስትወልድ ደመወዝ የሚከፈልበት 10 የሥራ ቀን ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡ ]

@tikvahethmagazine