TIKVAH-MAGAZINE
#MoSHE የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ከሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር በተያያዘ ነገ ሐምሌ 01/2013 ዓ.ም መግለጫ እሰጣለሁ ብሏል። ጋዜጣዊ መግለጫው ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት በሚኒስቴር መስሪያቤቱ አዳራሽ እንደሚሰጥ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተሯ አመለወርቅ ህዝቅኤል ለ @tikvahuniversity ገልፀዋል። @tikvahethmagazine @tikvahmagbot
#ማስተካከያ
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ከሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር በተያያዘ ዛሬ ሐምሌ 01/2013 ዓ.ም መግለጫ እንደሚሰጥ አሳውቆ ነበር።
ወደ ከሰዓት 8:00 ተላልፎ የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫው፤ በድጋሜ ወደሚቀጥለው ሳምንት ሰኞ ሐምሌ 05/2013 ዓ.ም መዛወሩን ሚኒስቴሩ ገልጿል።
በአስቸኳይ ስራዎች ምክንያት የቀን ለውጥ መደረጉን የገለፁት የሚኒስቴሩ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተሯ አመለወርቅ ህዝቅኤል ለተፈጠረው የጊዜ ለውጥ ይቅርታ ጠይቀዋል።
ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መረጃዎች https://yangx.top/TikvahUniversity ይከታተሉ
@tikvahethmagazine @tikvahmagbot

ብስራት ኤፍ ኤም ድረ-ገጽ እንዲሁም በፌስቡክ ገጽ ላይ "በሸኖ ከተማ የአትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ተሽከርካሪ ላይ አደጋ ደረሰ" በሚል ዘገባ ተሰርቶ የነበር ቢሆንም አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ የትራፊክ አደጋ እንዳልደረሰበት ለአል ዐይን አማርኛ ተናግሯል።
አትሌቱ ዛሬ ጠዋት ላይ በብስራት ሬድዮ ከሚሰራጨው አውቶሞቲቭ የሬድዮ ፕሮግራም ጋር በስልክ ተደውሎልኝ ስለፍጥነት መገደቢያ ወይም ስፒድ ብሬከር ችግር መሆኑን አስተያየት እንደሰጠ ገልጿል።
አትሌቱ እንዳለው "ያለንበት ሁኔታ እጅግ ከባድ ነው፣ ሌላም ነገር ቢሆን እንዲህ ነው የውሸት መረጃ የሚሰራጨው" ሲልም አክሏል።
ጠዋት ላይ የብስራት ኤፍ ኤም ዘገባን ዋቢ አድርገን መረጃውን ያደረስናችሁ ሲሆን ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ እንጠይቃለን።
NB: መረጃው ይህ ማስተካከያ በእኛ በኩል እስከተደረገበት ድረስ ከጣቢያው ኤፍ ኤም ገጽ እንዲሁም ድረ ገጽ ላይ አልተነሳም።
@tikvahethmagazine

በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ ለሚገነባው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በ20 ሚሊዮን ብር ወጪ ለሚገነባው የኦሞራቴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሠረት ድጋይ አስቀመጡ። የግንባታው አጠቃላይ ወጪ 20 ሚሊዮን ብር የሚፈጅ ሲሆን ወጪው ሰዎች ለሰዎች በተሰኘው ግብረ-ሠናይ ድርጅት እንደሚሸፈን ተገልጿል።…
#ማስተካከያ
በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ 20 ሚሊዮን ብር ወጪ ለሚገነባው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ መቀመጡን ተዘግቦ ነበር።
ለትምህርት ቤቱ የሚውለው ወጪ ሙሉ ለሙሉ የሚሸፈኘው ሰዎች ለሰዎች (Menschen für Menschen) በተሰኘው ድርጅት መሆኑን የድርጅቱ የኢትዮጵያ ተጠሪ አቶ ይልማ ታዬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
"ወጪው በደቡብ ክልል መንግስትና ሰዎች ለሰዎች በተሰኘው ግብረ-ሠናይ ድርጅት በጋራ እንደሚሸፈን ተገልጿል።" በሚለው ዘገባ ላይ ማስተካከያ እንዲደረግም ጠይቀዋል።
ሰዎች ለሰዎች (Menschen für Menschen) ድርጅት የኢትዮጵያ እውነተኛ ወዳጅ በሆኑት በዶ/ር ካርል ሄይንዝ በም ተቋቁሞ ላለፉት 40 ዓመት በላይ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን እና ድጋፎችን ሲያከናውን ቆይቷል።

የሩዋንዳ የፓርላማ አባላት የአባትነት የሥራ ፍቃድ ወደ አንድ ወር ከፍ እንዲል ጥያቄ ማቅረባቸው ተሰምቷል።
ህግ አውጭዎች ለታችኛው ምክር ቤት የማኅበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡት ረቂቅ አሁን በሀገሪቱ ያለው የ4 ቀን የአባትነት የሥራ ፍቃድ (Paternity leave)በቂ እንዳልሆነና የሥራ ፈቃዱ ወደ 30 ቀን ከፍ እንዲል ነው የጠየቁት።
ይህም እናት ከወሊድ በኋላ በሚኖራት ጊዜ በቂ የሆነ የባሏ [አባት] እንክብካቤ እንድታገኝና አባት አዲሱ ከሚወለደው ልጁ ጋር የመጀመሪያዎቹን ወቅቶች በአግባቡ እንዲያሳልፍና ጠንካራ ግንኙነት እንዲኖረው በማሰብ እንደሆነ አስታውቀዋል።
በሀገሪቱ የወሊድ ፈቃድ በተመለከተ እ.ኤ.አ በ2018 ለእናትም ሆነ ለአባት በሰራተኛ ህጉ ላይ በግልጽ የተቀመጠ ነገር የለም።
የዕረፍት ቀናቶቹ ውሳኔም በሚኒስቴሩ በኩል የወጡ ህጎች ናቸው። ጠያቂዎቹ ይኽ እንዲሻሻልና የወሊድ ፍቃድ ለእናትም ለአባትም በሰራተኛ ህጉ በግልጽ እንዲቀመጥም ጠይቀዋል።
ጋንቢያ፣ ሲሼልስና ኬንያ ለአባቶች የ2 ሳምንታት የሥራ ፈቃድ ከሙሉ ክፍያ ጋር ፈቃድ የሰጡ ሀገራት ናቸው። [ከላይ የተያያዘውን ቁጥራዊ መረጃ ይመልከቱ #WB]
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ 515/1999 መሰረት የወሊድ ፍቃድ [የእናቶች] ሦስት ወር ነበር፤ በ2010 ዓ.ም በተሻሻለው አዋጅ ይህ ወደ 120 ተከታታይ ቀናት ማደግ ችሏል። ይህ በግሉ ዘርፍ ያሉ ሴቶችን የሚያካትት አይደለም።
ከአባቶች ጋር ተያይዞ በሀገራችን በሰራተኛ ህጉ የተቀመጠው #አስር የሥራ ቀናት ከሙሉ ክፍያ ጋር እንዲያገኙ ነው።
[#ማስተካከያ፦ በኢትዮጵያ ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ የትዳር ጓደኛው ስትወልድ ደመወዝ የሚከፈልበት 10 የሥራ ቀን ፈቃድ ይሰጠዋል፡፡ ]

በመዲናዋ በወሊድና በእናቶች ላይ የሚፈጠር ህክምና ስህተት ቁጥሩ ትልቅ መሆኑንን ጥናት ጠቆመ። የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የጤና ባለሙያዎች የሙያ ሥነ-ምግባር (የህክምና ስህተት መከታተያ) ኮሚቴ በ7 ዓመት ውስጥ የታዩ አቤቱታዎችንና ጥቆማዎችን በማጥነት ሪፖርት አውጥቷል። በ7 ዓመት ውስጥ 282 አቤቱታዎች ለባለሥልጣኑ እንደቀረቡ የተገለጸ ሲሆን 210 በትክክል እንዳታዩ የሥነ-ምግባር…
#ማስተካከያ
የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን የጤና ባለሙያዎች የሙያ ስነ-ምግባር (የህክምና ስህተት መከታተያ) ኮሚቴ በ7 ዓመት ውስጥ የታዩ አቤቱታዎችንና ጥቆማዎችን በመሰብሰብ ያጠናውን ጥናት አውጥቶ ነበር።
ባለሥልጣኑ በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ ላይ እንዳሰፈረው በዚህ ጊዜ ውስጥ 282 አቤቱታዎች እንደቀረቡ እና 210 በትክክል እንዳታዩ ገልጿል።
ሆኖም ቀደም ሲል ከጥቆማዎቹ " ችግሮች ሲታዩም 64% ከእናቶች፣ ወሊድና ከማህፀን ጋር የተያያዘ " ነው ሲል አንስቶ ነበር።
የሥነ-ምግባር ኮሚቴ አባል የሆኑት የህክምና ባለሙያው አቶ እያያለም መለስ በፐርሰነት ሲቀመጥ ስህተት እንደነበረውና ስህተቱም በተቋሙ የፌስቡክ ገጽ ላይ ሲወጣ እንደሆነ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።
አሁን ላይ ተቋሙ መረጃውን ያስተካከለ ሲሆን በዚህም "ከ210 አቤቱታዎች 66 ወይንም 31.4% እናቶች ከወሊድና ከማህፀን ጋር የተያያዘ፣ ከ210አቤቱታዎች 41 ወይንም 20% ደግሞ በአጠቃላይ ሰርጀሪ ምክኒያት በሚያጋጥም የሞት አደጋ እና ከ210 አቡቱታዎች 32 ወይንም 15% በአጥንት ህክምና የሚመጡ አቤቱታዎች እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡" ሲል አስተካክሎታል።
@TikvahethMagazine

የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ " በኢትዮጲያ የመጀመሪያ ነው " ያለውን የሙሉ ዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ ከፍተኛ ቀዶ ጥገና በኘራይቬት ዊንግ ማከናወኑን በመግለፅ በፌስቡክ ገጹ መረጃውን አስተላልፎ ነበር።
@tikvahethmagazine ቻናልን ጨምሮ በርካቶች ይህንን የሆስፒታሉን መረጃ አጋርተው የነበረ ሲሆን የጤና ባለሞያ የሆኑ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ህክምናው የመጀመሪያ ባለመሆኑ እና " መረጃው የቀረበበት መንገድ #አሳሳች ነው " በማለት ተጨማሪ ማብራያ ጠይቀዋል።
ለዚህ ጉዳይ ምላሽ እንዲሰጡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የየካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ የኮሚኒኬሽን ክፍል ኃላፊ የሆኑትን አቶ ቤንኦን ጌታቸውን ጠይቋል።
አቶ ቤንኦን ጌታቸውን ምን አሉ ?
- ሆስፒታሉ ያጋራውን መረጃ " የተወሰነ ስህተት አለው ፅሁፉ " ብለዋል። ህክምናው ' በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ነው ' ተብሎ የተገለፀውን በተመለከተ " በኢትዮጵያ በግልም በመንግስትም ይሄ አገልግሎት ይሰጣል " በማለት አዲስ እንዳልሆነ አስረድተዋል።
ኃላፊው አክለውም " በመንግስት ሆስፒታሎች የፕራይቬት ዊንግ የሚባል አለ። ፕራይቬት ዊንግ ማለት ከ11 ሰዓት በኋላ በግል እንደ ቅዳሜ እና እሁድ እንደ ግል መስራት ማለት ነው " በማለት " ስለዚህ ህክምናው በፕራይቬት ዊንግ የመጀመሪያው ነው " ሲሉ ጠቁመዋል።
በተጨማሪም " በመንግስት ሆስፒታሎች ከዚህ በፊት የትም እየተሰራ አይደለም። አሁንም እየተሰራ አይደለም [በፕራይቬት ዊንግ] የዚህ የዳሌ አጥንት የዳሌ አጥንት እና የጉልበት መገጣጠሚያ ገጠማ " ሲሉ አክለዋል።
" ስለዚህ በመንግስት ሆስፒታሎች በፕራይቬት ዊንግ ነው እንጂ በሌሎች ሆስፒታሎች አሁንም እየተሰጠ ነው። መሰጠት ከጀመረም በጣም ቆይቷል። የመጀመሪያው አይደለም " በማለት ማስተካከያ ሰጥተዋል።

#እንድታውቁት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት እስከ ህዳር 30/ 2017 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ የነባር አባላት እድሳት እና የአዲስ አባላት ምዝገባ እያከናወነ ይገኛል። ለምዝገባ ሲመጡ ለነባር አባላት - የታደስ የቀበሌ መታወቂያ - የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የአባልነት ካርድ - የአባልነት ክፍያ 1500 ብር እና - እድሜያቸው 18 አመት…
#Update
ከጥቅምት 1 እስክ ህዳር 30 በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ ጤና ጣቢያዎች የሚካሄደውን የ2017 ዓ.ም የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የአባልነት የምዝገባ አስመልክቶ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ መግለጫ ሰጥተዋል።
ኃላፊው፥ በዘንድሮው ዓመት አዳዲስ አባላቶችን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ2.5 ሚሊዮን በላይ የከተማዋን ነዋሪዎች ተጠቃሚ ለማድረግ እቅድ መያዙን ነው የገለጹት።
ክፍያው ስንት ነው ?
በከተማ አስተዳደሩ በጸደቀው መዋጮ መጠን መሠረት መደበኛ መዋጮ መጠን አንድ ሺህ 500 ብር ሲሆን የድሀ ድሃ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ሙሉ በሙሉ በከተማ አስተዳደሩ እንደሚሸፈን ተናግረዋል።
ይህ ማለት - ነባር አባል መዋጮ 1,500 ብር፣ አዲስ አባል መዋጮ 1,500 ብር እና የመመዝገቢያ 200 ብር በአጠቃላይ 1,700 ብር አመታዊ መዋጮ ይክፍላል ነው ያሉት፡፡
ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆነ ልጆች እና በአባሉ ጥላ ስር ለሚኖሩ ተጨማሪ ቤተሰብ 750 ብር ይከፈላል ብለዋል።
በኢ-መደበኛ ክፍለ ኢኮኖሚ የተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተቀመጠውን መዋጮ በመክፈል ዓመቱን ሙሉ በሁሉም ውል በተገባባቸው የጤና ተቋማቶች አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉም ተናግረዋል።
በ2016 ዓ.ም ከ2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዜጎች በላይ በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አባል የሆኑ ሲሆን ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ አባላትና ቤተሰቦቻቸው በተመላላሽ እና በተኝቶ ህክምና ከጤና ጣቢያ ጀምሮ እስከ ፌደራል ሆስፒታሎች ባሉት የጤና ተቋሞች የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል ተብሏል።
#ማስተካከያ : ቢሮው ከቀናት በፊት በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ በአዲስ አበባ መደበኛ የጤና መድህን የመዋጮ መጠን 1,500 ብር እንደሆነ እንዲሁም 500 ብር በከተማ አስተዳደሩ የሚሸፈን የገለጸ ቢሆንም በዛሬው መግለጫ ተስተካክሏል።
ይህ መረጃ እስከወጣበት ድረስ ግን ቀድሞ የወጣው መረጃ በተቋሙ የፌስቡክ እንዲሁም የቴሌግራም ገጽ ላይ ይገኛል።
credit : EPA