This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update : ኮልፌ አጣና ተራ ታይዋን ገበያ አከባቢ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ ሙሉ ለሙሉ ባይጠፋም በቁጥጥር ስር መዋሉን በአከባቢው ያሉ የቲክቫህ ቤተሰቦች አሳውቀውናል።
📹 Fasil/ #TikvahFamily
@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
📹 Fasil/ #TikvahFamily
@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
ኢትዮ ቴሌኮም ለ66 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የዲጂታል መማሪያ ማዕከላትን አቋቋመ።
ኢትዮ ቴሌኮም በ45 ሚሊዮን ብር ወጪ በአዲስ አበባ እና በክልል ባሉ በ66 የመንግስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከ140ሺህ በላይ ተማሪዎችን መድረስ የሚችል የዲጂታል መማሪያ ማዕከላትን ገንብቶ በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
ማዕከላቱ "ተማሪዎች ከሌላ ት/ቤት ተማሪዎች ጋር መረጃ በቀላሉ መለዋወጥ እንዲችሉ ፣ የምርምር ስራዎችን ለማከናወን እዲሁም የመማር ማስተማር ሂደቱን ውጤታማና የተሻለ ለማድረግ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል ተብሏል።
ለእያንዳንዱ ትምህርት ቤት 21 ብሮድባንድ ኮምፒውተሮች የተከፋፈለ ሲሆን በአጠቃላይ 1 ሽህ 386 ኮምፒውተሮች ለትምህርት ቤቶቹን ተሠጥተዋል።
እነዚህ ትምህርት ቤቶች ከአዲስ አበባ እና ከክልል ትምህርት ቢሮዎች በተገኘ መረጃ መሠረት የተመረጡ ሲሆን ከ66ቱ ትምህርት ቤቶች 18ቱ በአዲስአበባ ቀሪዎቹ 48 ትምህርት ቤቶች ደግሞ በክልሎች ይገኛሉ።
ኢትዮ ቴሌኮም ማዕከላቱን ከመገንባት በተጨማሪ በቀጣይ በጥገናም እንደሚያግዝ ሀላፊዋ ገልፀዋል።
#TikvahFamily

📸Photo: የማዕድን ሚኒስቴር በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያዘጋጀው "ማዕድን ጋለሪ" በዛሬው እለት በይፋ መከፈቱን ሚኒስቴሩ ኢ/ር ታከለ ኡማ አስታውቀዋል። ይህ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን አካቶ ይዟል የተባለለት የማዕድን ጋለሪ ከዛሬ ጀምሮም ስለኢትዮጵያ የማዕድን ሀብት የማወቅ ፍላጎት ላለው ሁሉ ክፍት ሆኖ አገልግሎት እንደሚሰጥም ነው የጠቆሙት።
📸 #TikvahFamily
@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
📸 #TikvahFamily
@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📹 ደሴ - አዝዋ ገደል (ደመና ጨፌ ) በሚባለው አካባቢ የተከሰተው ጎርፍ በቪዲዮ (11 MB)
አህመድ ከደሴ / #TikvahFamily❤
@tikvahethmagazine
አህመድ ከደሴ / #TikvahFamily❤
@tikvahethmagazine
#DigitalPeacebuilding
የዲጂታል ክህሎት እንዲሁም ሰላም ግንባታ ላይ ያተኮረው Bootcamp ዛሬ ጀምሮ ለሦስት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን ዋና ዓላማውም ወጣቶች ለወጣቶች የቀረበ የመማሪያ ካሪኩለም ላይ አበርክቶ እንዲኖራቸውና በዘርፉ ላይ ያላቸውን እውቀት ለማሳደግ ያለመ ነው።
በቀጣይ በተለያዩ አከባቢዎች ሥልጠናዎች የሚዘጋጁ ሲሆን ለወጣቱ የቀረቡ ስልጠናዎች እንዲኖሩ ከጅምሩ አንስቶ አሳታፊ መሆናቸው ለውጤታማነቱ ትልቅ አበርክቶ ይኖረዋል።
#TikvahFamily❤️

Forwarded from Tikvah-University
በሁለተኛው ዙር የመፅሀፍት እና የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ማሰባሰብ ስራ ፦
- አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል (ስሙ እንዲገለፅ ያልፈለገ) አንድ Hp ላፕቶፕ ኮምፒዩተር አበርክቷል።
- አንድ የቤተሰባችን አባል 3000 ብር ወጪ የተደረገባቸውን አጋዥ መፅሀፍት ገዝቶ አበርክቷል።
በዚሁ አጋጣሚ ጃፋር መፅሀፍት ቤትን እናመሰግናለን።
ውድ ቤተሰቦቻችን የሁለተኛው ዙር የማሰባሰብ ስራ ጦርነት ለጎዳቸው ት/ቤቶች የሚውል ሲሆን ፦
- ከ9-12 ክፍል ያሉ ማንኛውም መፅሀፍት
- ከ1-8 ያሉ አጋዥ መፅሀፍት
- ቤት ውስጥ ያገለገለ ኮምፒዩተር
- ፕሪንተር
- የፕሪንተር ቀለም
- ነጭ ወረቀት
በተጨማሪ ለአንድ የህዝብ ቤተ መፅሀፍ ትውልድን የሚያንፁ ልብወልደ ሆነ ማንኛውም መፅሀፍ ማበርከት ትችላላችሁ።
አዲስ አበባ ያላችሁ ነገ ቅዳሜ እና እሁድ ያላችሁበት ድረስ መምጣት እንችላለን ደውሉልን ፦ 0919743630
ከሰሞኑን በሀዋሳ ያሉ አስተባባሪዎችን እናሳውቃለን።
#TikvahFamily
@tikvahethiopia

#ትንሳኤ
እንኳን አደረሳችሁ !
ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ የቲክቫህ አባላት በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።
በዓሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።
በዓሉን ስናከብር ፤ የተቸገሩ ወገኖቻንን አለንላችሁ በማለት ፣ የወደቁትን በማንሳት ፣ በሀዘን ላይ ያሉ ወገኖችን በማፅናናት፣ ከክፉ ድርጊትና ሀሳብ ርቀን ሊሆን ይገባል።
በተጨማሪም ፤ በዓሉን በሰላም እጦት ፣ በግጭት ፣ በጥቃት፣ በድርቅ ክፉኛ የተጎዱ ወገኖቻችንን እያሰብን ፤ በገዛ ቄያቸው ከሞቀው ቤታቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ የወደቁትን ፤ በፀሃይና ዝናብ የሚንከራተቱትን ፤ የሚወዱትን ተነጥቀው በጥልቅ ሀዘን ላይ የሚገኙትን ፣ ታመው በየሆስፒታሉ የተኙትን ፣ በየሰው ሀገር በስደት ስቃያቸውን እያዩ ያሉ ወገኖቻችንን እያሰብን ፤ በግልም ፤ በሀገርም ላለብን ችግር ሁሉ አምላክ መፍትሄ እንዲያበጅልን እየተማፀንን እንድናሳልፍ አደራ እንላለን።
የሰላም፣ የመተሳሰብና የበረከት በዓል ያድርግልን !
ፈጣሪ ሀገራችን ሰላም ያድርግልን !
መልካም በዓል !

ለብዙዎች ትምህርት የሆነው ተግባር
በከምባታ ዞን ዱራሜ ከተማ በሂጋ ሞዴል አዳሪ ት/ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው አዲስ ዓለም ከጓደኞቹ ጋር አንድ ላይ ባነበረበት በትናናው ዕለት 5 ሰዓት ላይ በአካዉንቱ (CBO) 1.1 ሚሊዮን ብር ይገባላታል።
ይህ ብር የገባለት ተማሪ አዲስዓለም ከጎደኞቹ ጋር በመሆን አቅራቢያው ወዳለ የባንኩ ብራንች በመሄድ "የሰዉ ሀቅ ነዉ" ብለዉ ገንዘቡ ወደ ባለቤቱ እንድመለስ አርገዋል።
ተማሪዎቹ ይህ ነለሌሎች ማስተማሪያ ይሆናል በሚል መረጃውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አጋርተዋል።
አዲስአለምና ጓደኞቹን በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ስም እናመሰግናለን!
#TikvahFamily❤️
👋 @TikvahethMagazine

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-MAGAZINE
የቴሌግራም የፕሪሚየም ሽልማት (Giveaway Prize )
ቴሌግራም የፕሪሚየም አገልግሎት ከጀመረ በኋላ ተያይዞ የተለያዩ አገልግሎቶችን አስተዋውቋል። ከዚህም ውስጥ አንዱ 'Giveaway' ሲሆን ለሰዎች የፕሪሚየም አገልግሎት በስጦታ መልክ ማበርከት የሚያስችል ነው።
በተጨማሪም ቴሌግራም የግሩፕ ወይም የቻናል ተከታዮች የፕሪሚየም አገልግሎት ተጠቃሚ ሲሆኑ ቻናሉን "Boost" ማድረግ ይችላሉ። በዚህም ቻናሉ ወይም ግሩፑ Boost በተደረገው መጠን የተለያዩ ተጨማሪ ይዘቶችን መፍጠር ያስችለዋል።
ለምሳሌ በተከታዮቹ ልክ በወጣው ደረጃ መሰረት የሚያስፈልገውን የBoost መጠን ያገኘ ቻናል/ግሩፕ Story መፍጠር ይችላል። በዚህም ቻናሎች/ግሩፖች ለተከታዮቻቸው በስጦታ መልክ የፕሪሚየም አገልግሎት እንዲሰጡ አባላት ደሞ ቤተሰብ የሆኑበትን ቻናላቸውን/ ግሩባቸውን Boost በማድረግ ያግዛሉ።
ከላይ ሼር የተደረገው Give Away @tikvahethmagazine ከዛሬ ጀምሮ እስከ መጋቢት 18 ወደ ቻናልችን ከሚቀላቀሉ አዳዲስ አባላት ውስጥ እንደ መጀመሪያ አንድ ሰው የሦስት ወር የፕሪሚየም ተሸላሚ ይሆናል። ምርጫውን ቴሌግራም መተግበሪያው በራሱ ይመርጣል። ምርጫው ምንም አይነት የሰው ንክኪ የለውም። ውጤቱንም ራሱ የሚያስታውቅ ይሆናል።
በቀጣይ ለነባር እንዲሁም አዲስ ለሚቀላቀሉን ቤተሰቦቻችን ሽልማቶችን ይዘን እንቀርባለን።
መልካም ዕድል!
#TikvahFamily 🩵
@TikvahethMagazine

#TikvahFamily: "ሰላም የቲክቫህ ቤተሰቦች አንድ ጉዳይ ተባበሩኝ ዛሬ በሐዋሳ ከተማ 5:00 ሰዓት አከባቢ ከአዲሱ ስታዲየም ወደ ወደ አሮጌ መናህሪያ ተሳፍሬ ስሄድ የትምህርት ዶክመንት ጥያለሁ እባካችሁ ያገኛችሁ አሳውቁኝ"
Via @tikvahmagbot
ስም፦ ጽዮን አዳነ / 0972782977
@TikvahethMagazine
Via @tikvahmagbot
ስም፦ ጽዮን አዳነ / 0972782977
@TikvahethMagazine
ለልማት በሚል በግለሰብ የባንክ አካውንት ገንዘብ መሰብሰብ ይቻላል ወይ?
"በግለሰብ ባንክ አካውንት ለልማት ተብሎ የሕዝብ ገንዘብ እየተሰበሰበ ነው። ለአብነት በሸገር ሲቲ ገላን ጉዳ በዳለቲ ወረዳ በያንዳንዱ ቤት 4500 ብር ለልማት በሚል በግለሰብ አካውንት ይሰበሰባል።
በርግጥ ትክክለኛ ከሆነ በመሰረታዊ የመንግሰት ተቋም ሥራው ይካሄድ እንጂ እንዴት በግለሰቦች አካውንት ገንዘቡ ይገባል? ሕዝቡ በዚህ መኃል ይጭበረበራል።"
#TikvahFamily 👉 @tikvahmagbot

ችግሩ የማነው?
የፍሳሽ ማስተላለፊያዎች በቆሻሻዎች ተደፍነው፤ ቆሻሻዎች በየመፍሰሻው ተጥለው መተላለፊያውን ዘግተውታል። ይህ ተግባር መሰረተ ልማቶቹን ከማበላሸት በተጨማሪ ከፍተኛ ብክለት ይፈጥራሉ።
ህብረተሰቡ ተጠያቂ ነው?
አዎ ተጠያቂ ነው! ቆሻሻ የሚያስወግድበት መንገድ ትክክል አይደለም። በተለይ ለአከባቢ ንጽሕና የማኅበረሰብ መፍትሔ መስጠት ላይ የሚሰጠው ትኩረት አነስተኛ ነው።
የአከባቢ ጽዳት ልክ ህብረተሰቡ በእድር እንደሚረዳዳው በራሱ ተነሳሽነት በየጊዜው ሊያከናውነው የሚገባ ተግባር ነው።
መንግስትስ?
መንግስትም አዎ ተጠያቂ ነው! መንግስት በመጀመሪያ ደረጃ ከፍተኛ የቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት መዘርጋት አለበት። አንዳንድ ከተሞች ላይ ቆሻሻን እንኳን በአግባቡ የሚሰበሰብበት ሥርዓት የለም።
ቆሻሻ የሚሰበስብ መኪና በ2 ወር የሚመጣበት አከባቢ አለ፤ ታዲያ ሰው ቆሻሻውን በበቤቱ 2 ወር ሊያስቀምጠው ነው? ይሄ ህብረተሰቡ ቆሻሻን ወደ ውጪ አውጥቶ የሚጥልበት ዋነኛው ገፊ ምክንያት ጭምር ስለሆነ መስተካከል አለበት።
የትምህርት ተቋማት ?
የትምህርት ተቋማት የጽዳት ደረጃ ዝቅተኛ ከሆነ ጽዳትን የሚወድ ትውልድ መፍጠር አስቸጋሪ ነው። የትምህርት ተቋማቶቻችን መጸዳጃ ቤቶችን መመልከት እንደ ሀገር ያለብንን ችግር በጥቂቱም የሚጠቁም ነው።
ትምህርት ቤቶች ማሳያዎች ናቸው፤ ማስተማሪያዎች ናቸው። እዛ ውጤታማ የሆነ ወደ ሌሎች ቦታዎች ወስዶ መተግበር ቀላል ነው።
ዘመቻ!
አሁን ላይ ጽዳትን በዘመቻ ለመተግበር ሙከራ ይደረጋል። በየአካባቢው የግዴታ ዘመቻዎች ይጠራሉ። ኃላፊዎች ይመጣሉ ከፊት ቀድመው ሲያጸዱ ፎቶ ይነሳሉ የሚቀጥለው ጊዜም ተመሳሳይ ነገር ይደረጋል ለውጥ ማየት ግን ከባድ ነው።
ይህ በራሱ ግንዛቤ ለመፍጠር ጥሩ አማራጭ ሊሆን ይችላል፤ ሆኖም መሰረታዊ ችግሩ ሥርዓት ሳይዘረጋለት ከምን ወደ ምን መቀየር እንደሚቻል በቂ ዝግጅት ሳይደረግበት፤ ዋና ተሳታፊ የሆነውን ማኅበረሰብን ሳያወያይ በሆታ የሚሰራ ሥራ የሪፖርት ፍጆታ እንጂ መደበኛ ለውጥ ያመጣል የሚል እምነት የለኝም። በዚህ ረገድ በፌደራል ደረጃ ያለው ተሞክሮ ጥሩ ማሳያ ይሆናል።
የመፍትሔ ሀሳቦች ፦
- ዘመቻዎቻችን በግልጽ ዓላማ እና ግብ መካሄድ አለባቸው!
- ጽዱ ትምህርት ቤት ሳይኖረን ጽዱ ከተማ አይኖረንም!
- በከተሞቻችን ህብረተሰቡ ቆሻሻን በቀላሉ የሚያስወግድበት ሥርዓት ይዘርጋ!
- ንጽሕና ፖለቲካ አይደለም!
[ ይህ ጹሑፍ ከፎቶ ጋር ከ #አሰላ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ የተላከ ሲሆን የይዘት ማስተካከያ ሳይደረግበት የተወሰነ ቅርጽ ለውጥ ተደርጎበታል ]
የእርሶንም ትዝብት ይላኩልን 👉 @tikvahmagbot

#FireAlert
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ስሙ ማርያም ማዞሪያ አካባቢ በመኖሪያ ቤቶች ላይ እሳት አደጋ አጋጥሟል።
ዛሬ ከቀኑ 6:38 ላይ ቆርቆሮ በቆርቆሮ ከሆኑ መኖሪያ ቤቶች የተነሳው እሳቱን ለመቆጣጠር ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ የእሳት እና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
አደጋውን ለመቆጣጠር 11 የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪዎች ተሰማርተዋል ተብሏል።
እሳቱ ከዚህ በኋላ ሊስፋፋ የሚችልበት እድል አለመኖሩን የጠቆሙት አቶ ንጋቱ እሳቱ በተነሳበት አካባቢ ት/ቤት እንዳለ እና ወደዛ የመስፋፋት እድሉ ዜሮ መሆኑን ነግረውናል።
እሳቱ ምክንያት እስካሁን በሰው ላይ ያጋጠመ ጉዳት የለም።
ተጨማሪ ይኖረናል።
📹 AbenezerMat / #TikvahFamily

Forwarded from Concept Hub Ethiopia
#ሐሳብአለኝ
ሐሳብ አለኝ ዲጂታል መጽሔት ቅጽ 1 በነገው ዕለት ለአንባቢያን ይደርሳል፤ ይጠብቁን!
#አዳዲስድምጾች: የሐሳብ መሪነትና ሙያዊ ብቃት የሚንጸባረቅበት መድረክ
#EmergingVoice : A hub for thought leadership and professionalism
#TikvahFamily 🩵
@Concepthubeth

ኮንሰፕት ሀብ (Concept Hub) የሐሳብ መድረክ ነው።
ዛሬ በይፋ እንድታነቡት የምንጋብዛችሁ "ሐሳብ አለኝ" የተሰኘው ዲጂታል መጽሔት እና በብሎግ አማራጭ የቀረቡት የጹሑፍ ሥራዎች ወጣቶች እድሉ ቢኖራቸው ለሚሰሩት ሥራ ጥቂቱ ማሳያ ነው።
ወጣቶች ተቀባይ ብቻ አይደሉም። ከሌሎች የሚማሩት ብዙ ነገር እንዳለ ሁሉ ሐሳባቸውን የሚገልጹበት፤ የሚሞክሩበትና ፈጠራቸውን የሚያጎለብቱበት መድረክም ያስፈልጋል።
ይህ መድረክም ወጣቶች ሐሳባቸውን እንዲያካፍሉ፤ ለማኅበረሰባቸው ጠቃሚ የሚሉትን ሐሳብ እንዲያዋጡ፤ አዲስ እይታና የፈጠራ ክህሎታቸውን የሚያዳብሩበት ነው።
በተጨማሪም፥ ወጣቶችን እንዲጽፉ፤ ጥናትና ምርምር እንዲያደርጉ፤ የመፍትሔ ሐሳቦችን እንዲያፈላልጉና ለማኅበረሰብ ለውጥ እንዲሰሩ እድሉን መስጠትና ያስፈልጋል ይህ መድረክም ለዚህ የታሰበ ነው።
የተለያዩ ክህሎት ያላቸው ወጣቶች፤ ወጣት ባለሞያዎች፤ ወጣት መምህራንና ጸሐፊያን፤ ጋዜጠኞች፣ የጤና እና የኢኮኖሚ ባለሞያዎች፤ የሰብዓዊ መብትና የአከባቢ ጥበቃ ተሟጋቾች ሌሎች ብዙ ወጣት ሞያተኞችን አሉን ይህ መድረክ ማኅበረሰብ የሚጠቅም ሐሳባቸውን የሚያካፍሉበትም መድረክ ጭምር ነው።
ኮንሰፕት ሀብ ኢትዮጵያ (Concept Hub Ethiopia ) በቲክቫህ ኢትዮጵያ የተጀመረ ተነሳሽነት ሲሆን በዲጂታል መጽሔት ብቻም ሳይሆን በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በወጣቶች የሚደረጉ ውይይቶች፤ ዶክመንተሪዎች፤ የዲጂታል አጫጭር ሥልጠናዎች ወደፊት ይዞ ይመጣል።
🖥 www.concepthub.net

#ተለቀቀ
"ሐሳብ አለኝ" ቅጽ 1 መጽሔት በዚህ Telegram Mini App ላይ ያገኙታል 👉 @ConceptHubeth_bot
ይጎብኙን www.concepthub.net
#TikvahFamily 🩵
@TikvahethMagazine
"ሐሳብ አለኝ" ቅጽ 1 መጽሔት በዚህ Telegram Mini App ላይ ያገኙታል 👉 @ConceptHubeth_bot
ይጎብኙን www.concepthub.net
#TikvahFamily 🩵
@TikvahethMagazine
በተለይ የግል ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸው ላይ የሚያሳድሩት ጫና ተማሪዎች ትምህርት እንዲሰለቹ እያደረገ ነው በሚል በተነሳው ኃሳብ ላይ የቲክቫህ ቤተሰቦች የተለያዩ ሀሳቦችን አንስተው ተወያይተዋል።
በአንድ በኩል ከመደበኛው የትምህርት ሰዓት ውጪ የሚሰጡት ትምህርቶች አስገዳጅ አይደሉም በፍላጎት የሚሰጡ ናቸው፤ የሚል ሐሳብ ሲነሳ በሌላ በኩል ይህ በውስጡ በፍቃደኝነት ቢባልም አስገዳጅ ነገሮች አሉት ብለው የገለጹም አሉ።
በሌላ በኩል በትምህርት ለምን ጫና ተፈጠረ ብሎ መጠየቅን ተገቢ አለመሆኑና ይልቅም ልጆቹን ጠንካራ ያደርጋቸዋል የሚል ሐሳብ ሲነሳ፥ በአንጻሩ ጫናው ሲበዛ መሰልቸትን የሚያመጣና ውጤት አልባ ይሆናል የሚልም መከራከሪያ ቀርቧል።
አንድ ቤተሰባችን "ልጆች እኮ ዕድሜያቸው በሚፈቅድላቸው ልክ ነው መማር ያለባቸው፣ ከአቅም በላይ የክፍል ስራ እና የቤት ስራ አግባብ የለውም፣ እንደ እድሚያቸው ጨዋታ እየተቀላቀለ ትምህርቱን እየወደዱት መማር አለባቸው እንጂ ምን በወጣቸው በልጅነት ትምህርት ቤት መሄድ እስከሚጠሉ ድረስ የሚማሩት።" ሲሉ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።
ሌላኛው ቤተሰባችን በአንጻሩ "በእኛ ደካማ የሥራ ባህል አጭር ሰዓት ሰርተን ረጅም ሰአት ማረፍ ለምንፈልግ ማህበረሰብ ይህንን ብናወራ አይፈረድብንም። ምናለ ልጆቻችን በጥንካሬ ተኮትኩተው ቢያድጉ ?" ሲል ይጠይቃል።
"የግል ትምህር ቤቶች በሚያደርጉት የእርስበርስ ፉክክር ልጆቹ መሞታቸው ነው።" ሲሉ ያነሱት አንድ አስተያየት ሰጪ ደግሞ "የ 3ኛ እና የ 4ኛ ክፍል ተማሪዎች 13 ትምህርት እየተማሩ! መጽሀፍት፣ ደብተር፣ የምሳ ዕቃ፣ ውሃ... በለጋ እድሚያቸው መሸከሙ ብቻ ወገባቸውን ከጥቅም ውጭ እያረገው ነው።" ሲሉም ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
ሌላኛው ሐሳብ ያቀረቡ ቤተሰባችን በበኩላቸው "ትምህርት አሰጣጥ ( ጊዜ፣ የትምህርት ብዛት፣ እድሜ፣ በቀን ያለው ክፍለ ጊዜ፣ በየትኛው ደረጃ ወዘተ) የራሱ ሳይንስ አለው። መንግሥት ራሱ ለምን በቀን ፰ ክፍለ ጊዜ፣ ከ፲ በላይ ትምህርት እንደሚሰጥ አይገባኝም" ሲሉ ይጠይቃሉ።
እንዲሁ አንድ ቤተሰባችንም፥ "ምንም እንኳን እዉነታዉ እነዚህ የግል ት/ት ቤቶች 12ኛ ክፍል የማሳለፍ ዉጤታቸዉ ከ90 % በላይ ቢሆንም (እንደ አገር 3% መሆኑ እንዳይረሳ) ተማሪዎቹ ላይ የተወሰነ ጫና መኖሩ አያጠያይቅም።
በተለይ አንዳንድ ት/ት ቤቶች After school የሚባል ፕሮግራም በግድ እንዲማሩ ያስገድዳሉ ( ለ 6፣ 8 እና 12ኛ ) ክፍል ይህም የሚሆነዉ አንድም የተማሪዎች የማለፍ ችሎታቸዉን ከፍ ለማድረግ እና የአስተማሪዎችን ተጨማሪ ገቢ በመፍጠር ት/ት ቤቱን እንዳይለቁ ማበረታቻ ነዉ።
ዋናዉ ጥያቄ ግን መሆን ያለበት ልጆቹ ጫና ይበዛባቸዋል ሲባል መለክያዉ ምንድነዉ ? የተማሪዎች አቅም እስከምንድነዉ የሚለዉ በጥናት የተደገፈ ነገር ሊቀርብ ግድ ይላል" የሚል ሐሳባቸውን አካፍለውናል።
ሌላኛው ቤተሰባችን ደግሞ "ከወቅታዊው ተምሮ ለውጤት ያለመብቃት ሁነት በንግግርና መሰል መንገዶች ወደ ልጆቻችን አእምሮ ውስጥ ተስፋ ቢስነትን አጭሮ ይሆን ?" ሲሉ ይጠይቃሉ።
#TikvahFamily 🩵
@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ጥያቄ አሎት?
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ የሚቀርቡ ጥያቄዎች በተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ መሆኑን ገልጾልናል።
በመሆኑም ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች የሚኖሯችሁን ጥያቄዎች በግልጽ እና በተብራራ መንገድ እንዲሁም ማስረጃ ማቅረብ በሚያስፈልጋቸው ጥያቄዎች ላይ ማስረጃችሁን በማጣቀስ ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ።
ጥያቄዎቻችሁን በዚሁ ፖስት ኮመንት ስር ወይም በውስጥ መስመር በ @tikvahmagbot ላይ ማቅረብ ትችላላችሁ።
ጥያቄዎቻችሁን በጹሑፍ፤ በድምጽ እንዲሁም ማስረጃዎችን በማንኛውም የፋይል መልክ መላክ ይችላሉ።
#Ask_AACARB
#TikvahFamily 🩵
@Tikvahethmagazine

የመርካቶ ቁጥር 1 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት 2 ሰራተኞች በቁጥጥር ሥር ዋሉ።
የግብር ተመን በአስተያየት እንገምትላችኋለን በማለት ከ1.7 ሚሊዮን ብር በላይ የተቀበሉ ሁለት የመርካቶ ቁጥር 1 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ተጠርጣሪ ሰራተኞችና ገንዘቡን ከንግዱ ማህበረሰብ ሲያሰባስቡ የነበሩ አምስት ተጠርጣሪ ነጋዴዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ ገልጿል።
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ሲዳሞ ተራ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ከሚገኙ አሮጌ ዕቃ እየገዙ ከሚሸጡ ነጋዴዎች ሁለት የመርካቶ ቁጥር 1 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሰራተኞች ነጋዴዎቹን በማነጋገር ለመንግስት የምትከፍሉትን የግብር የዋጋ ተመን አስተካክለን እንሰራላችኋለን በማለት ይነግሯቸዋል።
የቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሰራተኞቹም ይህንን ለማስፈጸም እናንተ በአምስት ሰዎች አስተባባሪነት ከእያንዳንዱ ነጋዴ ብር አሰባስባችሁ የድርሻችንን ስጡን በማለት ከ89 ነጋዴዎች ከ1.7 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰባቸው ተገልጿል።
ይህ መረጃ እንደደረሰው የገለጸው ፖሊስ፥ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሁለቱን የመርካቶ ቁጥር 1 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሰራተኞችና አምስቱን ነጋዴዎች መጋቢት 9 ቀን 2017 ዓ/ም ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እያጣራባቸው እንደሚገኝ አስታውቋል።
ሰሞኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከቤተሰቦቹ የሚቀርቡ ጥያቄዎችን እየሰበሰበ እንደሚገኝ ይታወሳል አሁንም ጥያቄዎቻችሁን በዚሁ ፖስት ኮመንት ስር ወይም በውስጥ መስመር በ @tikvahmagbot ላይ ማቅረብ ይቻላል።