TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
19K photos
296 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
加入频道
#CholeraUpdate

በጎንደር ከተማ ሰሞኑን በተከሰተው የኮሌራ በሽታ ከ69 በላይ ሰዎች መያዛቸውን የጎንደር ከተማ ጤና መምሪያ ገልጿል፡፡ በከተማዋ የበሽታው ምልክት መታየት የጀመረው ከባለፈው ሐምሌ ወር አጋማሽ ጀምሮ መሆኑን የመምሪያው ኃላፊ በለጠ ፈንቴ ተናግረዋል።

ኃላፊው ከዚህ ቀደም በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ በሚገኘው በርሚል ጊዮርጊስ ገዳም ውስጥ ለጸበል በሄዱ ሰዎች ላይ ድንገተኛ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ፤ ከጸበሉ ቆይተው ወደ ጎንደር ከተማ በመጡ ሰዎች አማካኝነት ወረርሽኙ መዛመቱን ነው የጠቆሙት።

በጸበል ቦታው በተከሰተ አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት የአንድ እናት ሕይወት ማለፉን የጠቀሱት ኃላፊው፤ የሟች ቤተሰብ አስከሬኑን ወደ ጎንደር ከተማ ይዘው በመጡበት ወቅት በሽታው መዛመቱን አስረድተዋል።

በጎንደር ከተማ በተከሰተው የኮሌራ በሽታ እስካሁን የሞተ ሰው አለመኖሩን የገለጹት የጤና መምሪያው ኃላፊ፤ ከተያዙት ሰዎች ውስጥ እያገገሙ የሚወጡ ሰዎች ቢኖሩም በምትኩ ተይዘው የሚገቡ መኖራቸውን ተናግረዋል።

"በሽታው ከዚህ በላይ እንዳይስፋፋም ባለሙያዎችን በማዋቀር የመከላከል ሥራ እየተሰራ ነው።" ሲሉም አመላክተዋል።

በቋራ ወረዳ ከወራት በፊት በተከሰተ የኮሌራ በሽታ ከ1 ሺሕ 500 በላይ ሰዎች መያዛቸው እና የኹለት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተጠቁሟል።

ይህን ተከትሎ በሽታው ወደ ሌሎች ቦታዎች እንዳይስፋፋ በሚል ወደ ቋራ ወረዳ መግባትና መውጣት ተከልክሎ ቢቆይም፤ ከባለፈው ሐምሌ ወር አጋማሽ ጀምሮ የእንቅስቃሴ ገደቡ እንዲነሳ በመደረጉ በሽታው ጎንደር ከተማ እንዲከሰት ምክንያት መሆኑ ነው የተጠቀሰው። 

( ምንጭ: አዲስ ማለዳ )

✅️@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
September 5, 2023
#CholeraUpdate

1️⃣

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሐምሌ 24 ቀን፣ 2015 ዓ.ም አንስቶ በየኮሌራ ወረርሺኝ ከተከሰተ በኋላ በ3 ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ 9 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የክልሉ ጤና መሥሪያ ቤት አስታውቋል።

የጤና መሥሪያ ቤቱ የመርኃ ግብር ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ አብዱልሙኒየም አልበሽር ወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ በታየበት መተከል ዞን #ዳንጉር ወረዳ ውስጥ በሚገኙ የተወሰኑ ቀበሌዎችም በፀጥታ ችግር ምክንያት ማዳረስ አለመቻላቸውን አብራርተዋል።

በተጨማሪም አባይ ዳር የተባለ አንድ ቀበሌ ደግሞ በመንገድ እና ፀጥታ ችግር ሳቢያ ሙሉ በሙሉ የሕክምና ድጋፍ እንዳላገኙ ጠቁመዋል።

2️⃣

በዐማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ውስጥ በተቋቋመ የኩመር መጠለያ ጣቢያ፣ የኮሌራ ወረርሽኝ እንደተከሠተና ዘጠኝ ሱዳናውያን ስደተኞች እንደሞቱ፣ 395 ሰዎች ደግሞ እንደታመሙ፣ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር/UNHCR/ አስታውቋል።

3️⃣

በአማራ ክልል በ28 ወረዳዎች በተከሰተ የኮሌራ ወረርሽኝ ከ3ሺህ 8መቶ በላይ ሰዎች መጠቃታቸውን፣ ከ70 በላይ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን እንዲሁም በየቀኑ ከ15 እስከ 20 ሰዎች በአዲስ በበሽታው እንደሚጠቁ የክልሉ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በላይ በዛብህ ተናግረዋል።

በክልሉ ባሕር ዳርና ጎንደር ከተማን ጨምሮ 9 ወረዳዎ፥ ዕድሚያቸው አንድ ዓመትና ከዚያ በላይ ለኾኑ ሰዎች ከመስከረም 5 እስከ መስከረም 10 ድረስ ለ1 ነጥብ 8 ሚሊየን ሰዎች የኮሌራ ክትባት ለመስጠት ታቅዷል ተብሏል።

መረጃው ከዶይቼ ቬሌ፣ ቪኦኤ፣ አሚኮ የተጠናቀረ ነው።

✅️@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
September 16, 2023
#CholeraUpdate

በኢትዮጵያ የኮሌራ ወረርሽኝ ተባብሷል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (OCHA) ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባሳለፍነው ሳምንት በኩመር የስደተኞች መጠለያ ወደ 400 የሚጠጉ ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን ገልጿል።

በበሽታው የተያዙት ሰዎች ወደ ኩመር ኮሌራ ህክምና ማዕከል መግባታቸው ሲገለፅ በሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር 50 በመቶ መጨመሩ ተገልጿል።

ሆስፒታሎች በአካባቢው የኮሌራ ህሙማንን ለማስተናገድ የሚያስችል ሁኔታ ላይ እንዳልሆኑ ሲገልፅ ምግብ እና ንፁህ የመጠጥ ውሃ አለመኖሩ በህብረተሰቡ ውስጥ የኮሌራ ስርጭትን እየጨመረው እንደሆነ ኦቻ አሳውቋል።

በኩመር የኮሌራ ሕክምና ማዕከል ዶክተር የሆኑት  አብዱልባሪይ መሐመድ ከአናዶሉ ጋር ባደረጉት ቆይታ አፋጣኝ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ጠቁመው ብዙ ሰዎችን ለማስተናገድ የሚያስችል በቂ የሰው ኃይል ባለመኖሩ ሰዎች በየቀኑ እየሞቱ መሆኑን ተናግረዋል።

ዶ/ር አብዱልባሪይ ሁኔታው የታካሚዎችን ስቃይ እያከፋ እንደሆነ ሲገልፁ የምግብ እና ንጹህ ውሃ እጥረት በጣም አሳሳቢ በመሆኑ አስፈላጊውን የህክምና አገልግሎት ለመስጠት አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው አስረድተዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ  እየተባባሰ የመጣው የኮሌራ ወረርሽኝ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስቧል።

እንደ ዓለም ጤና ድርጅት የቅርብ ጊዜ መረጃ ከሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ በሰባት ክልሎች ከ20ሺ በላይ ሰዎች በኮሌራ ሲያዙ  271 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል።

✅️@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
September 22, 2023
#CholeraUpdate

የዓለም ጤና ድርጅት እየተባባሰ የመጣውን የኮሌራ ስርጭት ለመከላከል 16 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ መልቀቁን አስታውቋል።

የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ከዓለም ጤና ድርጅት ድንገተኛ ፈንድ 16 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ መልቀቁን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በአለም አቀፍ የጤና ጉዳዮች ላይ በመከረ የቨርቹዋል ስብሰባ ገልፀዋል።

ድርጅቱ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት አስፈላጊ ድጋፎችን በማቅረብ ከአጋር አካላት ጋር በመስራት ኮሌራን ለመከላከል የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ዶ/ር ቴዎድሮስ ተናግረዋል።

ዶ/ር ቴዎድሮስ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት  160 ሚሊዮን ዶላር እንዲለቀቅ ጥረት መደረጉን ጠቅሰው በአሁኑ ወቅት ከ16 ሚሊዮን ዶላር ገንዘብ ከ አለም ጤና ድርጅት የድንገተኛ አደጋ ፈንድ መለቀቁን አሳውቀዋል።

በአሁኑ ወቅት የኮሌራ በሽታ ስርጭት ከፍተኛ ስጋት ከሆነባቸው ሀገራት መሃከል ሃገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ ሄይቲ፣ ኢራቅ እና ሱዳን እንደሚገኙበት ነው የተጠቀሰው።

የዓለም ጤና ድርጅት በቅርብ ጊዜ ባወጣው መረጃ በኢትዮጵያ ውስጥ በሰባት ክልሎች ከ20ሺ በላይ ሰዎች በኮሌራ ሲያዙ 271 ሰዎች መሞታቸውን የተገለፀ ሲሆን ባሳለፍነው ሳምንት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (OCHA) በኢትዮጵያ የኮሌራ በሽታ ስርጭት መጨመሩን መግለፁም ይታወሳል።

✅️@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
September 29, 2023
TIKVAH-MAGAZINE
#CholeraUpdate 🇪🇹 በኢትዮጵያ በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ እስካሁን የ156 ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል ሲል የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት (UNOCHA) ሰሞኑን ባወጣው መረጃ አስታውቋል። በአሁኑ ወቅት የተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ በምስራቅ አፍሪካ ሀገር ከተከሰቱት ረጅሙ አንዱ ነውም ተብሏል። የወረርሽኙ አጠቃላይ የገዳይነት መጠንም 1.36 በመቶ ሲሆን በዓለም አቀፍ…
#CholeraUpdate

በኢትዮጵያ በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ እስከ  መስከረም 22  ባለው መረጃ 300 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። በሐምሌ 5 በተመዘገበው መረጃ የሟቾች ቁጥር 172 ነበር።

የኮሌራ ተጠቂዎች ቁጥር ሐምሌ ወር ላይ ከነበረው 13,118 ጨምሮ አሁን ላይ  24,197  ሆኖ ተመዝግቧል።

በአንጻሩ የወረርሽኙ አጠቃላይ የገዳይነት መጠን (Case Fatality Rate) ሐምሌ ወር ላይ ከነበረው 1.36 በመቶ ወደ 1.24 ዝቅ ብሏል።  ሆኖም ይህ ቁጥር በዓለም አቀፍ ደረጃ ስምምነት ከተደረሰበት የ 1 በመቶ መጠን ከፍ ያለ ነው።

አብዛኛዎቹ የኮሌራ ተጠቂዎች ሪፖርት የሚደረገው ከኦሮሚያ (33%) ሲሆን ከአማራ (19%)፣ ከሲዳማ (13%)፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ(12%)፣ ከድሬዳዋ (9%)፣ ከአፋር (7%)፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ (4%)፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ (3%) እና ሀረሪ (1%) ቀጣዮችቹን ደረጃዎች በቅደም ተከተል ይይዛሉ።

እስካሁን ከ6 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አንድ ዙር በአፍ  የሚወሰድ የኮሌራ ክትባት መከተብ የቻሉ ሲሆን ይህም በሶማሌ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፤ ሲዳማ፣ ኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች ባሉ 54 ወረዳዎች የተሰራጨ ነው።

የጸጥታ ገደቦች ቢኖሩም በአማራ ክልል በኩመር መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ 8,098 ስደተኞችን ጨምሮ ወደ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ክትባት ወስደዋል ተብሏል።

በተጨማሪም ለአፋር፣ ለሲዳማ፣ ለደቡብ ኢትዮጵያ እና ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ተጨማሪ 1.5 ሚሊዮን ዶዝ ክትባት መፈቀዱም ተጠቅሷል።

[ በዚህ ዙሪያ በተከታታይ የተሰሩ ዜናዎችን ለማግኘት 👉 #CholeraUpdate ይጠቀሙ። ]

👋  @TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
October 7, 2023
TIKVAH-MAGAZINE
#CholeraUpdate በኢትዮጵያ በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ እስከ  መስከረም 22  ባለው መረጃ 300 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። በሐምሌ 5 በተመዘገበው መረጃ የሟቾች ቁጥር 172 ነበር። የኮሌራ ተጠቂዎች ቁጥር ሐምሌ ወር ላይ ከነበረው 13,118 ጨምሮ አሁን ላይ  24,197  ሆኖ ተመዝግቧል። በአንጻሩ የወረርሽኙ አጠቃላይ የገዳይነት መጠን (Case Fatality…
#CholeraUpdate

በአዲስ አበባ አንድ አንድ ቦታዎች የኮሌራ በሽታ መከሰቱን "ካፒታል" ስማቸዉ እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ምንጮቼ ያላቸውን በጤና ላይ የሚሰሩ መግንስታዊ ያለሆኑ ተቋማት (NGO) አረጋግጠዋል ሲል ዘግቧል።

ይህን አስመልክቶ "ካፒታል" ያናገራቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ምክትል የቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉጌታ እንዳለ "መረጃዉ ሀሰተኛ ነዉ" ወደ ከተማዋ እንዳይገባ አሁን ላይ እየሰራን" እንገኛለን ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

[ በዚህ ዙሪያ በተከታታይ የተሰሩ ዜናዎችን ለማግኘት 👉 #CholeraUpdate ይጠቀሙ። ]

👋  @TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
November 8, 2023
TIKVAH-MAGAZINE
#CholeraUpdate በአዲስ አበባ አንድ አንድ ቦታዎች የኮሌራ በሽታ መከሰቱን "ካፒታል" ስማቸዉ እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ምንጮቼ ያላቸውን በጤና ላይ የሚሰሩ መግንስታዊ ያለሆኑ ተቋማት (NGO) አረጋግጠዋል ሲል ዘግቧል። ይህን አስመልክቶ "ካፒታል" ያናገራቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ምክትል የቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉጌታ እንዳለ "መረጃዉ ሀሰተኛ ነዉ" ወደ ከተማዋ እንዳይገባ አሁን ላይ…
#CholeraUpdate

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከ 393 ሺ ለሚልቁ የህብረተሰብ ክፍሎች የኮሌራ በሽታ መከላከያ ክትባት ተደራሽ ለማድረግ ማቀዱን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታውቋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን በሽታው በ19 ወረዳዎች ላይ ተከስቶ የነበረ መሆኑን ጠቅሰው በየደረጃው በተደረገው ከፍተኛ ርብርብ 17 ወረዳዎችን ከወረርሽኙ ነፃ ማድረግ መቻሉን አንስተዋል።

በአሁኑ ሰዓት በክልሉ 2 ወረዳዎች ላይ በሽታውን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ከፍተኛ ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑን ያነሱት ዳይሬክተሩ በአፍ የሚሰጠው የኮሌራ በሽታ መከላከያ ክትባት( OCV) ለ393,463 ያህል የህብረተሰብ ክፍሎች ለመስጠት መታቀዱን አስረድተዋል።

አክለውም፥ ዕድሜያቸው ከአንድ ዓመት በታች ከሆኑ ህጻናት በስተቀር ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች የክትባቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚገባቸው ያሳሰቡ ሲሆን በክልሉ የክትባት ዘመቻውን ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አንስተዋል።

[ በዚህ ዙሪያ በተከታታይ የተሰሩ ዜናዎችን ለማግኘት 👉 #CholeraUpdate ይጠቀሙ። ]

👋  @TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
November 8, 2023
#CholeraUpdate: የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የኮሌራ ወረርሽኝን ለመከላከል 1 ሚሊዮን ዩሮ እንደሚሰጥ አስታወቀ።

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ የሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ ላለው የኮሌራ ወረርሽኝ ቀጣይነት ያለው ሰብዓዊ ምላሽ ለመስጠት አንድ ሚሊዮን ዩሮ አዲስ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚሰጥ አስታውቋል።

የአውሮፓ ህብረት ገንዘቡን የሚሰጠው ከድንገተኛ አደጋ ጊዜ መጠባበቂያ ፈንድ እንደሆነ ሲጠቀስ በህብረቱ የሰብአዊ መርሃ ግብር አካል ተደርጎ በሀገሪቱ በበሽታው በተጎዱ አካባቢዎችና በሀገሪቱ ውስጥ ለሚገኙ ተጋላጭ ማህበረሰቦች የሚውል እንደሆነ ተገልጿል።

የኮሌራ ወረርሽኝ በሀገሪቱ በግጭትና ከአየር ንብረት ጋር በተያያዘ ምክንያት ከፍተኛ የሰብአዊ ፍላጎት ባለባቸው አካባቢዎች እርዳታ መድረስ እንዳልቻለ ህብረቱ ሲጠቁም በ 2023 በኢትዮጵያ በግጭትና በድርቅ የተጎዱ ሰዎችን ለመደገፍ 82.5 ሚሊዮን ዩሮ ለኢትዮጵያ መስጠቱን የአውሮፓ ህብረት አስታውሷል።

በቅርቡ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (OCHA) ባወጣው መረጃ ፥ በኢትዮጵያ ከጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በአፋር፣ በአማራ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ በመካከለኛው ኢትዮጵያ ክልል (CER) ፣ በሐረሪ፣ በሲዳማ፣ በሶማሌ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል (SER) በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም በ85 ወረዳዎች ከ24,700 በላይ ሰዎች የኮሌራ በሽታ እንደተገኘባቸው ተመዝግቧል።

👋  @TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
November 15, 2023
February 27, 2024
April 30, 2024
#CholeraUpdate 🇪🇹

ኢትዮጵያ በሐምሌ ወር ብቻ (በፈረንጆቹ) 2,086 የሚሆኑ ሰዎች በኮሌራ መያዛቸውንና እንዲሁም በበሽታው ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈ 43 ሰዎች መኖራቸውን ሪፖርት ተደርጓል። የሞት ምጣኔውም 2.1% ሆኖ ተመዝግቧል።

ከባለፈው ወር ጋር ሲነጻጸር በበሽታው ​​የተያዙ ሰዎች ቁጥር 26 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን የሟቾች ቁጥርም በ 258 በመቶ ከፍ ብሏል።

በኢትዮጵያ ከታኅሣሥ መጨረሻ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 21፣ 2016 ዓ.ም ድረስ በድምሩ 21,254 ሰዎች በኮሌራ መያዛቸው የተገለጸ ሲሆን፥ 182 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል። በዚህ በ7 ወር ውስጥ ያለው የሞት ምጣኔም (CFR) 0.9 በመቶ መሆኑ ተጠቅሷል።

#አፍሪካ

ከታኅሣሥ መጨረሻ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 21፣ 2016 ዓ.ም ድረስ የኮሌራ በሽታ በ14 የአፍሪካ ሀገራት ሪፖርት የተደረገ ሲሆን በድምሩ 111,168 የኮሌራ ተጠቂዎች ተመዝግበዋል።

በዚህ ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ሪፖርት የተደረገባት ሀገር ኢትዮጵያ (21,254 ኬዝ) መሆኗ ተገልጿል። ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ (DRC) 20 659፤ እንዲሁም ዛምቢያ 20,219 ኬዞችን በማስመዝገብ ይከተላሉ።

በተመሳሳይ ጊዜ በአጠቃላይ 1,899 ሰዎች ከ12 የአፍሪካ ሀገራት በኮሌራ በሽታ የሞቱ ሲሆን በዛምቢያ ከፍተኛው ቁጥር ተመዝግቧል (637 ሞት)፣ ዚምባብዌ (399 ሞት)፣  እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ (274 ሞት) ተመዝግቧል።

በአንጻሩ ባለፈው ሐምሌ ወር ብቻ (በፈረንጆቹ) በአፍሪካ 7,241 ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን ከ7 ሀገራት ሪፖርት የተደረገ ሲሆን ይህ ቁጥር ካለፈው ወር ጋር ሲነጻጸር የ9 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል።

ሆኖም በተጠቀሰው ጊዜ የሟቾች ቁጥር 162 ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን ይህም ካለፈው ወር ጋር ሲነጻጸር በ76 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ከፍተኛው የሟቾች ቁጥር የተመዘገበው በናይጄሪያ (102) ሲሆን ኢትዮጵያ 43 ሰዎችን በበሽታው በማጣት ተከታይ ነች።

Source : WHO

@tikvahethmagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
August 15, 2024
September 18, 2024
October 19, 2024
October 23, 2024