#CholeraUpdate 🇪🇹
ኢትዮጵያ በሐምሌ ወር ብቻ (በፈረንጆቹ) 2,086 የሚሆኑ ሰዎች በኮሌራ መያዛቸውንና እንዲሁም በበሽታው ሳቢያ ህይወታቸው ያለፈ 43 ሰዎች መኖራቸውን ሪፖርት ተደርጓል። የሞት ምጣኔውም 2.1% ሆኖ ተመዝግቧል።
ከባለፈው ወር ጋር ሲነጻጸር በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር 26 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን የሟቾች ቁጥርም በ 258 በመቶ ከፍ ብሏል።
በኢትዮጵያ ከታኅሣሥ መጨረሻ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 21፣ 2016 ዓ.ም ድረስ በድምሩ 21,254 ሰዎች በኮሌራ መያዛቸው የተገለጸ ሲሆን፥ 182 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል። በዚህ በ7 ወር ውስጥ ያለው የሞት ምጣኔም (CFR) 0.9 በመቶ መሆኑ ተጠቅሷል።
#አፍሪካ
ከታኅሣሥ መጨረሻ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 21፣ 2016 ዓ.ም ድረስ የኮሌራ በሽታ በ14 የአፍሪካ ሀገራት ሪፖርት የተደረገ ሲሆን በድምሩ 111,168 የኮሌራ ተጠቂዎች ተመዝግበዋል።
በዚህ ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ሪፖርት የተደረገባት ሀገር ኢትዮጵያ (21,254 ኬዝ) መሆኗ ተገልጿል። ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ (DRC) 20 659፤ እንዲሁም ዛምቢያ 20,219 ኬዞችን በማስመዝገብ ይከተላሉ።
በተመሳሳይ ጊዜ በአጠቃላይ 1,899 ሰዎች ከ12 የአፍሪካ ሀገራት በኮሌራ በሽታ የሞቱ ሲሆን በዛምቢያ ከፍተኛው ቁጥር ተመዝግቧል (637 ሞት)፣ ዚምባብዌ (399 ሞት)፣ እና ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ (274 ሞት) ተመዝግቧል።
በአንጻሩ ባለፈው ሐምሌ ወር ብቻ (በፈረንጆቹ) በአፍሪካ 7,241 ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን ከ7 ሀገራት ሪፖርት የተደረገ ሲሆን ይህ ቁጥር ካለፈው ወር ጋር ሲነጻጸር የ9 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል።
ሆኖም በተጠቀሰው ጊዜ የሟቾች ቁጥር 162 ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን ይህም ካለፈው ወር ጋር ሲነጻጸር በ76 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል። ከፍተኛው የሟቾች ቁጥር የተመዘገበው በናይጄሪያ (102) ሲሆን ኢትዮጵያ 43 ሰዎችን በበሽታው በማጣት ተከታይ ነች።
Source : WHO
@tikvahethmagazine

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM