TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
19K photos
296 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
加入频道
"በ6 ወሩ ፌስቡክና ቴሌግራም የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃዎች ማስተላለፊያ ዋነኛ መድረኮች ነበሩ" - ኢመብባ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በዛሬው ዕለት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ያለ የጥላቻ ንግግር እና ሀሰተኛ መረጃ ሀገራዊ ሪፖርት ይፋ አድርጓል። ባለሥልጣኑ ሪፖርቱን ይፋ ሲያደርግ ይህ ለ2ኛ ጊዜ ነው።

ሪፖርቱ ከሀምሌ 2015 - ጥር 2016 ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ሲሆን 5 የማኅበራዊ ትስስር መድረኮች (ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ቲክቶክ፣ ዩቲዩብ እና ኤክስ) ላይ ያተኮረ ነው።

ℹ️ መረጃ የተሰበሰበው እንዴት ነው?

ባለሥልጣኑ ሪፖርቱን ለማውጣት በ9192 ነጻ የስልክ መስመር የተሰበሰቡና የተመረጡ 1400 ጥቆማዎችን እንዲሁም በአዲስ አበባና በአምስት ክልሎች 2 ሺ መጠይቆችን በመበተን የተሰበሰቡ 1776 የማኅበረሰብ ምላሾች ላይ ያደረገ ነው።

📌 የሪፖርቱ ያካተታቸው ዋና ዋና ነጥቦች

- ሪፖርቱ ባካተተው 6 ወራት የብሔር ማንነት ላይ ካተኮረ የጥላቻ ንግግር ይልቅ #ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ የጥላቻ ነግግሮች ጎልተው ወጥተዋል ይላል።

- በዚህ 6 ወር ሃይማኖታዊና ጾታዊ ማንነቶች ላይ የሚደርሱ የጥላቻ ይዘቶች #ዝቅተኛ ሆነው መመዝገባቸውን ጠቅሷል።

- የጥላቻ ንግግር ስጋት ደረጃ ከፍተኛ ደረጃ ደርሷል የሚለው ሪፖርቱ የጥላቻ መልዕክቶችን ከማስተላለፍ ለጥቃትና #ለአመጽ ወደ ማነሳሳት መሻገሩን ጠቁሟል።

- በ6 ወሩ የዳሰሳ ጥናት መሰረት የጭካኔ አገላለጽ በከፍተኛ ደረጃ ተሰራጭቶ የታየ ሲሆን ይህ ስርጭት #በቴሌግራም በ65% እንደተሰራጨ ይገልጻል።

- የተጠቃሚዎች ገጽ ስያሜ በአመዛኙ ትክክለኛ ማንነታቸውን በመደበቅ በሌላ ሥያሜ የሚጠቀሙ ናቸው።

- በአስተያየት መስጫ ከሚሰጡ አስተያየቶች 86.33 % የሚሆነው የጥላቻ መልዕክቱን የሚደግፍ ሲሆን፤ 11.57 % የሚቃረኑ ግን የጥላቻ ንግግሮች እንዲሁም 2.1% ገለልተኛ አስተያየቶች ናቸው።

- ሐሰተኛ መረጃን በሚመለከት ጥናቱ በከፍተኛ ሁኔታ ተስተውሏል ያለው የተሳሳተ መረጃ እና በተሳሳተ አውድ የቀረቡ ይዘቶችን ሲሆን የተቀነባበረ ይዘት በመጠኑ መስተዋሉን ጠቅሷል።

- መጠይቁን ከመለሱትና የጥላቻና ሀሰተኛ መረጃን ሪፖርት ካደረጉ 70 በመቶዎቹ ሪፖርቱ እንዳልወረደ ገልጸዋል፤ የክትትል ቡድኑም ሪፖርት ካደረጋቸው ውስጥ 2 በመቶው ብቻ መውረዳቸውን ጠቅሷል።

⛔️ የሪፖርቱ ውስንነቶች ምንድን ናቸው?

በሪፖርቱ እንደተጠቀሰው አሰራሩ #በቴክኖሎጂ ባለመታገዙና መረጃ የማሰባሰቡ ሂደት በሰው ኃይል በመሰራቱ በውስንነት ያስቀመጠ ሲሆን፤ የተለያዩ ሀገራዊ ቋንቋዎችን መሸፈን አለመቻሉን አንስቷል።

ሪፖርቱ ይህንን ይበል እንጂ ሀገራዊ የችግሩን ጥልቀት ከማሳየት አንጻር ሪፖርቱ የተጠናቀረበት መንገድና የተጠቀመው የመረጃ ምንጭ ላይ ውስንነት መኖሩን ከመድረክ በተሰጡ ሀሳቦች ተመላክቷል።

የባለሥሥልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር ዮናታን ተስፋዬ፥ "ሪፖርቱ ብዙ ጉድለቶች ሊኖሩበት ይችላል . . . የመረጃ አሰባሰብና ትንተናው አሁን ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ያሳያል" ሲሉ ገልጸዋል።

አክለውም በአዋጁ የተሰጣቸው ኃላፊነት ውስን መሆኑን በመጥቀስ፥ "አዋጁ በራሱ ክፍተት አለበት  . . . ማስፈጸሚያ ደንብ አልተዘጋጀለትም" ሲሉም አንስተዋል።

በሪፖርቱ እንደተገለጸው፥ ከባለፈው ዓመት የጥላቻ ንግግር አንጻር ሲታይ መረጃዎቹ ከስድብ ወደ ስብእናን መጉዳት/ character assassination/ ከፍረጃ ወደ አግላይ ጥቅል ፍረጃ /segregation/ ከማስፈራሪያ ወደ ስጋትነት፣ ከጭካኔ አገላለጽ ወደ #ጥቃት ማነሳሳትና የግድያ ጥሪ ከፍ ብለው ታይተዋል፤ ችግሩ ሁኔታ አጣዳፊ መፍትሄ የሚፈልግ ሆኖም ታይቷል ሲል አስቀምጧል፡፡

@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በ2023 አምስት ምርጥ እንግሊዝኛ ተናጋሪ የአፍሪካ ሀገራት የትኞቹ ናቸው?

"ኢዱኬሽን ፈርስት" የተባለ ዓለማቀፍ የትምህርት ተቋም እድሜአቸው ከ 18 - 20 የሆኑ 2.1 ሚሊዮን ወጣቶችን ከ113 ሀገራት የእንጊሊዘኛ ቋንቋ ችሎታቸውን በመገምገም የሀገራትን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪ ብቃት ደረጃ አውጥቷል።

ተቋሙ የቋንቋውን ተናጋሪዎች ብቃት በጣም የላቀ፣ ከፍተኛ፣ መካከለኛ፣ ዝቅተኛ እና በጣም ዝቅተኛ በሚሉ አምስት የብቃት ደረጃዎች በመክፈል ነው ሪፖርቱን ይፋ ያደረገው።

በሪፖርቱ መሰረትም ከ1ኛ እስከ 5ኛ የተቀመጡ የአፍሪካ ሀገራት በቅደም ተከተል፦

🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ
🇰🇪 ኬንያ
🇳🇬 ናይጄሪያ
🇬🇭 ጋና
🇺🇬 ኡዳንዳ መሆን ችለዋል።

ከአፍሪካ በቋንቋ ተናጋሪነት ብቃት የመጀመሪያ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ደቡብ አፍሪካ  "#በጣም_የላቀ" በተባለው ከፍተኛ የእንግሊዘኛ ብቃት ያላችው ሀገራት ምድብ ውስጥ ተካትታለች።

2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ኬንያ እንዲሁም 3ኛዋ ናይጄሪያ "#ከፍተኛ" በተባለው እንዲሁም  ዩጋንዳ እና ጋና "#መካከለኛ" በተባለው የቋንቋ ተናጋሪነት ምድብ ተመድበዋል።

ሀገራችን #ኢትዮጵያ🇪🇹 #ዝቅተኛ የእንጊሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪነት ምድብ ውስጥ ከታንዛኒያ፣ ሞሮኮ፣ አልጄሪያ፣ ማዳጋስካር፣ ማላዊ፣ ግብፅ ጋር መመደቧ በሪፖርቱ ተመላክቷል።

ኔዘርላንድስ፣ ሲንጋፖር፣ ኦስትሪያ፣ ዴንማርክ እና ኖርዌይ ከአለም ከ1 እስከ 5 ያለውን የኢንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪነት ብቃት ደረጃ መያዝ ችለዋል።

@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM