TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#ሼር #share

የንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ነሃሴ 18 አገልግሎት አይሰጡም!!

"...ባንካችን የቴክኖሎጂ አቅሙን በማሳደግ ረገድ ፕሮጀክት ቀርፆ የድርጊት መርሃ ግብር በመንደፍ የፊታችን ነሀሴ 18 ቀን 2011 ዓ/ም ተግባራዊ ስለሚያደርግ ሁሉም የባንካችን ቅርንጫፎች አገልግሎት የማይሰጡ መሆናቸውን በታላቅ አክብሮት እየገለፅን፣ የኤቲ ኤም ማሽኖቻችንና የሲ.ቢ.ኢ ብር በዕለቱ የተለመደውን የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ መሆኑን እናሳውቃለን።" የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Photoshop

ከሰሞኑን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች #ISIS የለቀቀው ተብሎ እየተሰራጨ የሚገኘው #የኢትዮጵያ ስም ያለበት ፎቶ #ሀሰተኛና በphotoshop የተሰራ ነው።

NB. በፎቶው ላይ የምትመለከቷቸው ታጣቂዎች #የISIS ሳይሆኑ #የአልሸባብ ታጣቂዎች ናቸው። #TIKVAH_ETH

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በድሬዳዋ የተከሰተውን የቹኩን- ጉንያ የትኩሳት ህመም ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያግዝ የጽዳት ዘመቻ ሊካሄድ መሆኑ ተገለጸ። ከተያዘው ወር ጀምሮ በተከሰተው የቹኩን- ጉንያ ቫይረስ ወረርሽኝ ህመም ከ7ሺህ በላይ ሰዎች መጠቃታቸው ታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አከራካሪው የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ!

ዶክተር ገረመው ሁሉቃ(ከትምህርት ሚኒስቴር)፦


"ከቋንቋ ጋር በተያያዘ የፌደራል እና የክልል መንግስታት ስልጣንን በሚመለከት አሁንም መጣራት ያሉባቸው ነገሮች እንዳሉ እያየን ነው። ፍኖተ ካርታው ገና እየተሰራበት ያለ ሰነድ ነው። የፌደራል መንግስት የስራ ቋንቋ ከ3ኛ ክፍል ጀምሮ ይሰጣል ይላል፤ የ8ኛ ክፍል ፈተናም ብሄራዊ ፈተና ሆኖ ግን ተተርጉሞ ለክልሎች ይሰጣል ይላል እነዚህ ሁለቱ ጉዳዮች የክልል መንግስታትን ስልጣን ይነካሉ ህገመንግስቱ እንደሚለው ከ1ኛ ክፍል - 8ኛ ክፍል ያለውን የትምህርት መስጫ ቋንቋ የሚወስነው የክልሉ መንግስት ነው። ይህ መታየት ያለበት ጉዳይ ስለሆነ ትምህርት ሚኒስቴር እየሰራበት ይገኛል።"

▫️ጉዶዮቹ የመጨረሻ ውሳኔ ያልተላለፈባቸው ከሆኑ ትላንት በትምህርት ሚኒስትሩ የተሰጠው መግለጫስ ተብለው ከቢቢሲ የተጠየቁት ዶክተር ገረመው ተከታዩን ምላሽ ሰጥተዋል፦

"የትላንቱ መግለጫ በ2012 ዓ/ም ፍኖተ ካርታው ተግባራዊ እንደሚሆን ለማስተዋወቅ እንጂ ስሱ ተብለው የተያዙና ውሳኔ ያልተሰጠባቸው ጉዳዮች አሉ። ፍኖተ ካርታው ገና እየተጠና ያለ ነገር ነው #የመጨረሻ አይደለም። በቀጣዩ ሳምንት በጅግጅጋ በሚደረገው የትምህርት ኮንፈረንስ ውይይት ይደረግበታል። ክልሎችም ስለሚሳተፉ እነዚህ ጉዳዮች #መፍትሄ ያገኛሉ።"

#BBCአማርኛ

#TIKVAH_ETH

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በአስቸኳይ እረፍታቸውን አቋርጠው እንዲመጡ ተጠሩ። የምክር ቤቱ አባላት ሰኔ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ነበር ስራቸውን አጠናቀው ለእረፍት የተበኑት።

ይሁንና የምክር ቤቱ አባላት ነገ ለአስቸኳይ ስብሰባ እረፍታቸውን አቋርጠው እንደተጠሩ የምክር ቤቱ ህዝብ ግንኙነት ስራ ክፍል ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል። የምክር ቤቱ አባላት ነገ ሐሴ 18 ቀን 2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በሚያካሂደው 3ኛ አስቸኳይ ስብሰባው እንዲገኙ ተጠርተዋል።

ምክር ቤቱ በነገው ውሎውም የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ረቂቅ አዋጅን መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡ በዚህ አዋጆች ላይ ከዚህ በፊት የተለያዩ ውይይቶች የተካሄዱ ሲሆን የተወሰኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጁን እንደማይቀበሉት ማሳወቃቸው ይታወሳል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአሸንድዬ ጨዋታ አከባበር በላልይበላ!

በአሸንድዬ በዓል #የሀገር ውስጥ እና #የውጭ ሀገራት ጎብኝዎች እየታደሙ ነው። የአሸንድዬ በዓል "የባህል እሴቶቻችን የአብሮነታችን መሠረት ናቸው" በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ ነው።

የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የላልይበላና አካባቢው ነዋሪዎች በበዓሉ እየታደሙ ነው። የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት ጎብኝዎችም ተገኝተዋል። ይህም በዓሉን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለማስተዋዎቅ እና ተጠቃሚ ለመሆን ያስችላል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update ከተሰጣቸዉ እዉቅናና ፍቃድ ዉጪ የትምህርት አገልግሎት የሚሰጡ የግልና የመንግስት ኮሌጆችና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከድርጊታቸዉ እንዲቆጠቡ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ አሳሰበ፡፡ ኤጀንሲዉ ከእዉቅናዉ ዉጪ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የትምህርት ተቋማት ላይ እርምጃ ወስዷል፡፡

በአዲስ አበባና አካባቢዋ 18 የግል ኮሌጆችና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ካምፓሶችን መዝጋቱን አስተዉቋል፡፡ እንዲሁም 4 የመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከእዉቅናዉ ዉጪ ከግል የትምህርት ተቋማት ጋር በትብብር ሲሰጡ የነበረዉን አገልግሎት እንዲቋረጥ መደረጉን የኤንጀንሲዉ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምራት ሞታ ተናግረዋል፡።

በተለይም በግል ዘርፍ የትምህርት አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት አብዛኞቹ ደረጃቸዉን ባለጠበቁ የትምህረት ቅጥር ግቢ ዉስጥ እንደነበር ጠቁመው የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ኤጀንሲዉ ቁርጠኛ አቋም መያዙንም ምክትል ዳሬክተሩ አስታዉቀዋል።

Via #AMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸አትሌት ኃይሌ ገብረ ስላሴ ያስገነባውን ትምህርት ቤት ለማስመረቅ ዋግ ኽምራ ገብቷል። ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ስላሴ ሚያዝያ 27ቀን 2011 ዓመተ ምህረት ነበር በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ፃግብጂ ወረዳ የሚገኘውን የገልኩ የዳስ ትምህርት ቤት ሙሉ በሙሉ ደረጃውን የጠበቀ አድርጎ ለማስገንባት የመሠረት ድንጋይ ያስቀመጠው፡፡

በወቅቱ “ትምህርት ቤቱን ለ2012 የትምህርት ዘመን ሙሉ በሙሉ ከዳስ ለማላቀቅ ጥረት አደርጋለሁ” ሲል ቃል ገብቶ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ በዚህም ግንባታው አራት ወራት ባልሞላ ጊዜ ተጠናቅቆ ለምረቃም ለማስተማርም ተዘጋጅቷል።

ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ስላሴ ትናንት ማታ በሰቆጣ፣ ዛሬ ደግሞ ፃግብጂ ወረዳ ገልኩ ትምህርት ቤት ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል ፡፡ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በሦስት ወራት ውስጥ በሁለት ሕንፃዎች የተከፈሉ ስምንት ክፍሎችን ማስገንባቱ ነው የተገለጸው፡፡

በትምህርት ቤቱ ምርቃ ስነ ስርዓት ላይም የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ይልቃል ከፋለ እና የሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ስላሴ ባለቤት እንደሚገኙም አመብድ ዘግቧል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፌስቡክ በርካታ በማይናማር የሚገኙ አካውንቶችን መዝጋቱን አስታወቀ!

ፌስቡክ በትክክለኛ ማንነት አልተከፈቱም ያላቸውን 216 የሚሆኑ በማይናማር የሚገኙ የፌስቡክ አካውንቶችን መዝጋቱን አስታወቀ፡፡ 89 የሚሆኑ የግል አካውቶች፣ 107 ገፆች፣ 15 የፌስቡክ ቡድኖችና 5 የኢንስታግራም አካውንቶችን መዝጋቱን ነው ኩባንያው ያስታወቀው፡፡

የተዘጉት አንዳንድ የፌስቡክ ገጾች ከወታደራዊ አካላት ጋር የተያያዙና ህዝባዊ ውይይትን የሚያዛቡ መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡ ከጥላቻ ንግግር በተለይም ሮሂንጊያ ሙስሊሞች ላይ ከደረሰው ጥቃት ጋር በተያያዘ የማይናማር ወታደራዊ ሓላፊ አካውንትን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ አካውንቶችን መዘጋታቸው ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡- ሮይተርስ/ETV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የኢትዮጵያውያን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ኢዜማን ልከስ ነው! Via የጀርመን ራድዮ @tsegabwolde @tikvahethiopia
''ኢዜማ ያለምንም ህጋዊ መሰረት ንብረቶቻችንን እየተጠቀመ ስለሆነ ሊመልስልን ይገባል''- #ኢዴፓ

''በህገወጥ መንገድ የያዝሁት ምንም ንብረት የለም'' - ኢዜማ
.
.
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ /ኢዜማ/ ከኢዴፓ አፈንግጠው በወጡ አራት አባላት የተሰጠውን የፓርቲው ንብረቶች ያለምንም ህጋዊ መሰረት እየተጠቀመ ስለሆነ ሊመልስልን ይገባል ሲል ኢዴፓ ጥሪ አቅርቧል፤ ኢዜማ በበኩሉ በህገወጥ መንገድ የያዝሁት ምንም ንብረት የለም ብሏል፡፡

ከኢዴፓ አፈንግጠው የወጡ አራት ግለሰቦች በምርጫ ቦርድ ፍፁም ህገወጥ የሆነ ትብብር የፓርቲውን ፅህፈት ቤቶች፣ በባንክ የተቀመጠ ገንዘብ፣ መዛግብትና ማህተም ያለአግባብ በህገወጥ መንገድ እንዲረከቡ ተደርጓል ያለው ኢዴፓ ግለሰቦቹ ኢዴፓ ከግንቦት 7 ጋር እንዲዋሀድ የኢዴፓ ጠቅላላ ጉባኤ ተሰብስቦ እንደወሰነ አድርገው የሀሰት መረጃ በማቅረብ ንብረቶቹን በፓርቲዎች ውህደት ሳይሆን በግለሰቦች ስብስብ ለተቋቋመው ኢዜማ ማስረከባቸውን የኢዴፓ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከትናንት በስቲያ በሰጠው መግለጫ ጠቅሷል፡፡

#ኢዜማም ያለምንም ህጋዊ መሰረት እነዚህን የኢዴፓ ንብረቶች እየተጠቀመባቸው እንደሚገኝ የጠቀሰው ማእከላዊ ኮሚቴው በዚህ የተነሳ የእለት ከእለት ስራዎችን በአግባቡ ለማከናወን መቸገሩን ገልፆ ኢዜማ ግለሰቦቹ የፈፀሙትን #የማጭበርበር ወንጀል ተረድቶ ንብረቶችን እንዲመልስ ጠይቋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ET-08-23

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሶማሊያው ፕሬዝዳንት መሐመድ አብዱላሂ ፋርማጆ የቀድሞውን የጦር አበጋዝ እና የመንግሥት ሚኒስትር የነበሩትን ግለሰብ የሞቃዲሾ ከንቲባ እና የባዲር ግዛት አስተዳደሪ አድርገው ሾሙ። ሹመቱ ባለፈው ወር ውስጥ በአጥፍቶ ጠፊዎች ህይወታቸው ያለፈውን የቀድሞ ከንቲባ አብዱረህማን ኦማር ኦስማንን ለመተካት መሆኑ ተገልጿል፡፡

Via #BBC/etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር በአገሪቱ ከሚያስገነባቸው 6 እስር ቤቶች መካከል ይኸ በድሬዳዋ የሚገኝ ነው። እስከ 6 ሺሕ ታራሚዎች ይይዛል የተባለው እስር ቤት በሚቀጥለው አመት ሥራ ይጀምራል ተብሏል። ያዩት እንደሚሉት VIP ክፍሎች ጭምር አለው።

Via እሸት በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ፈተና በክልል ደረጃ በአፍ መፍቻ ቋንቋ የሚሰጥ መሆኑን አስታውቀዋል።

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በእነብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ የክስ መዝገብ ላይ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ!

በእነብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ የክስ መዝገብ ላይ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ። መዝገቡን በሚገባ በመመርመር ትክክለኛ ውሳኔ ለመስጠት ተጨማሪ መረጃ ስለሚያስፈልግ በማለት የባሕር ዳር ከተማና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለነሃሴ 21/ 2011 ዓ.ም ጠዋት 3:00 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። የተጠርጣሪዎች #ጠበቆች ከምርመራ ሂደቱ ጋር በቀጥታ ተያያዥነት የሌላቸው የባንክ ደብተርና አልባሳት እንዲመለሱላቸዉ ለፍርድ ቤቱ ጥያቄ አቅርበዋል።

የምርመራ ቡድኑም አልባሳትም ሆነ የባንክ ደብተር ለተጠርጣሪዎች ቢመለስላቸው እንደማይቃወም ገልጿል፤ ነገር ግን አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ሂሳብ ደብተር ላይ ያለው ገንዘብ እንዳይንቀሳቀስ ማድረግ ይቻላል ብሏል። ፍርድ ቤቱም ተጠርጣሪዎቹና ቤተሰቦቻቸው ሌላ ምንም አይነት የገቢ ምንጭ ከሌላቸው የባንክ ደብተሩ እንዲሁም አልባሳቱም በህግ አግባብ ሊሰጣቸው ይገባል በሚል ወስኗል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኦሮሚያ ክልል የዜግነት አገልግሎት ምክር ቤት ምስረታ ስነ ስርዓት እየተካሄደ ነው፡፡ የምክር ቤቱ ምስረታ ስነ ስርዓት በአዲስ አበባ ከተማ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በስነ ስርዓቱ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ አባገዳዎች፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ አርቲስቶች እና ሌሎች ባለድርሻ አካለት ተገኝተዋል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ያስገነባው ት/ቤት ተመረቀ!

ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ስላሴ የቀድሞውን የዳስ ትምህርት ቤት ደረጃውን በጠበቀ መልኩ አስገንብቶ አስመርቋል። ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ስላሴ ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳድር ፃግብጂ ወረዳ ላይ ያስገነባውን ገልኩ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አሁን አስመርቋል፡፡

ስያሜውም ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረ ስላሴ አጠቃላይ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተብሏል፡፡ ትምህርት ቤቱ ሁለት #ብሎኮች እና ስምንት የመማሪያ ክፍሎች አሉት፡፡ ኃይሌ በሦስት ወራት አስገንብቶ ነው ትምህርት ቤቱን ለመጭው የትምህርት ዘመን ማስተማሪያ ዝግጁ ያደረገው፡፡

በምረቃ ሥነ ስርዓቱ እንደተገለጸው ነዋሪነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ አንድ ግለሰብ 8 ሽህ 500 የማጣቀሻ መጻህፍትን ለትምህርት ቤቱ ማበርከታቸው ታውቋል፡፡

Via አብመድ
@tsegabwplde @tikvahethiopia
ታንዛኒያዊው ጋዜጠኛ በ'ሀሰተኛ ዜና' ታሰረ!

ታንዛኒያዊው ጋዜጠኛ 'ፖሊስ በእስር ቤት የሚገኙ ተጠርጣሪዎችን ያሰቃያል' በሚል የሰራው ዘገባ 'ሀሰተኛ ነው' በሚል ለእስር መዳረጉ ተገለፀ። ጋዜጠኛ ጆሴፍ በታንዛኒያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ጥምረት በተቋቋመው ዋቴቴዚ ቴሌቪዥን ጣቢያ ነው የሚሰራው።

የቴሌቪዥን ጣቢያው የጋዜጠኛውን መታሰር አጥብቆ ያወገዘ ሲሆን በትዊተር ገፁ ላይ ጋዜጠኛው በዚህ ወር መጀመሪያ ሪፖርቱን አጠናቅሮበት ወደነበረው ኢሪንጋ መወሰዱን አስታውቋል። ጣቢያው እንዳለው ከሆነ የኢሪንጋ ፖሊስ የተሰራውን ዘገባ አስመልክቶ " ሀሰተኛና አሳሳች ሪፖርት ሲሆን የታንዛኒያን የፖሊስ ኃይል እና መንግሥትን የሚያጣጥል ነው" ሲል ማስጠንቀቂያ አዘል ምላሽ ሰጥተዋል።

"ለደህንነት ኃላፊው አሳሳችና ሀሰተኛ ዜና የሚያሰራጩ ሰዎችን እንዲከታተሉ ትዕዛዝ አስተላልፌያለሁ፤ በቁጥጥር ሥር ከዋሉ በኋላም ሕጋዊ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል " ማለታቸውን የቴሌቪዥን ጣቢያው የአካባቢውን ፖሊስ ጠቅሶ ዘግቧል። ከአንድ ወር በፊት በዚያው ታንዛኒያ ታዋቂው የምርመራ ጋዜጠኛው ኤሪክ ካቤንደራ ለእስር ተዳርጎ ነበር።

ጋዜጠኛው በእስር ላይ ሳለ በተፈፀመበት የሰብዓዊ መብት ጥሰትም በአገሪቷ የሚገኙ የአሜሪካና የእንግሊዝ ኤምባሲዎችን ትኩረት ስቦ ነበር። ፕሬዚደንት ጆን ማጉፋሊ በቅፅል ስማቸው 'ዘ ቡልዶዘር' በአውሮፓዊያኑ 2015 ሥልጣን ላይ ከወጡ ጀምሮ ለሚዲያና የሚዲያ ባለሙያዎች ፈታኝ እንደሆነባቸው ይነገራል። ጋዜጦች እና የራዲዮ ጣቢያዎችም ሕግ ጥሰዋል በሚል ሰበብ መታገዳቸው ተጠቅሷል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ ዩኒቨርስቲ ባዘጋጀው የበጎ አድራጎት ሳምንት ለተሳተፉ በጎ አድራጊዎች ምስጋናውን አቅርቧል። #JimmaUni

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታን አስመልክቶ ስለ ክልሉ የትምህርት ስርዓት የሰጡት መግለጫ፦

#10MB

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ ከእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ሚኒስትር አሎክ ሸርማ ጋር ዛሬ ተወያይተዋል፡፡ የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ሚኒስትር አሎክ ሸርማ፣ በኢትዮጵያ ያለው አገር በቀል ሪፎርምን አድንቀው፣ አገራቸው ለኢትዮጵያ ልማት የምታደርገውን ድጋፍ እንደምትቀጥል ተናግረዋል፡፡

#PMO
@tsegabwolde @tikvahethiopia