ዶክተር ደብረፂዮን🔝
የትግራይ ክልል ፕሬዝደንት ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል ዛሬ በሰጡት መግለጫ፦
"መንግስት በሙስናና የሰብኣዊ መብቶች ጥሰት ስም የጀመረው እንቅስቃሴ አቅጣጫውን ስቶ የትግራይ ህዝብ #ለማንበርከክ የሚደረግ ጥረት ስለሆነ አንቀበለውም" ሲሉ ተናግረዋል።
በተጨማሪም ፕሬዝደንቱ ዘመቻው #የውጭ ጣልቃ ገብነት አለበት ብለን እናምናለን ሲሉ ቅሬታቸውን ገልጸዋል።
በህግ የበላይነት ላይ አንደራደርም፡፡ ነገር ግን ሁሉም መጠየቅ አለበት፡፡ ለሌላ ፖለቲካዊ አላማ መጠቀሚያ መሆን የለበትም፡፡ ሜቴክ ይሁን ደህንነት ሀገርን የሚመለከት እንጂ እኛን የሚመለከት አይደለም፡፡ የኛ ሰው ለምን ታሰረ አንልም ነገር ግን ህግ እየተጣሰ ነው፡፡ ትግራይን ለማዳከም የውጪ ሀይሎች ጣልቃ ገብነት እየታየ ነው፡፡ በትግራይ ህዝብ ላይ አዲስ ዘመቻ ተጀምሯል፡፡ ኢህአዴግ ከገመገመው ውጪ ነው እየተደረገ ያለው፡፡" ብለዋል።
ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን፣ ኡትዮ ላይቭ ሀፕዴት
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ሰላም፣ ፍቅር እና አንድነት!
‹‹ዩኒቨርሲቲዎች የሰላም፣ ፍቅር እና አንድነት መጠናከሪያ እንጂ #የነውጥ እና #የጥላቻ መነሻ መሆን #አይገባቸውም፡፡›› የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
‹‹ማኅበረሰቡ፣ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገረ ሽማግሌዎች የተቋሙን #ሰላም ለማስጠበቅ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በመቀናጀት እየተሠሩ ነው›› የደሴ ከተማ ነዋሪዎች
‹‹ዩኒቨርሲቲውን እየፈተኑ ያሉት በውስጥ የሚፈጠሩ ችግሮች ሳይሆኑ #የውጭ ተፅዕኖዎች ናቸው፡፡›› የወሎ ዩኒቨርሲቲ
https://telegra.ph/ውሎ-ዩኒቨርሲቲ-01-10

Telegraph
ውሎ ዩኒቨርሲቲ፦
ዩኒቨርሲቲዎች የሰላም ተምሳሌት እንጅ የችግር መነሻ መሆን እንደማይገባቸው ነው የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተናገሩት። የወሎ ዩኒቨርሲቲ ባለፉት ዓመታት በሰላማዊ የመማር ማስተማሩ ዙሪያ ትልቅ ሥራ ሠርቷል። የወሎ የኒቨርሲቲ የሦስተኛ ዓመት ተማሪ የሆነው በየነ ሰጠኝ እንደተናገረው የዩኒቨርሲቲው ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት መረጋገጥ የተማሪዎች ሰላም ወዳድነት ትልቁን ቦታ ይይዛል። የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር፣…
የአሸንድዬ ጨዋታ አከባበር በላልይበላ!
በአሸንድዬ በዓል #የሀገር ውስጥ እና #የውጭ ሀገራት ጎብኝዎች እየታደሙ ነው። የአሸንድዬ በዓል "የባህል እሴቶቻችን የአብሮነታችን መሠረት ናቸው" በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ ነው።
የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የላልይበላና አካባቢው ነዋሪዎች በበዓሉ እየታደሙ ነው። የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት ጎብኝዎችም ተገኝተዋል። ይህም በዓሉን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለማስተዋዎቅ እና ተጠቃሚ ለመሆን ያስችላል።
Via #AMMA

TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ቦዴፓ
የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦዴፓ) በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ልኮልናል።
ፓርቲው በላከልን መግለጫ እስካሁን ትጥቃቸውን ያልፈቱ የጉህዴን ታጣቂዎች በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ግልገል በለስ ከተማ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ/ም በፈፀሙት ጥቃት በርካታ ንፁኃን ዜጎች መገደላቸውና በርካቶች መቁሰላቸውን ገልጿል።
ድረጊቱ በየትኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የለለው አስነዋሪና አሳፋሪ መሆኑን በመግለፅ አውግዟል።
በንፁሀን ዜጎች ላይ ይህን የመሰለ ወንጀል የፈጸሙ አካላት በአፋጣኝ ለህግ እንዲቀርቡ ፓርቲው አጥብቆ ጠይቋል።
ከዚህ በተጨማሪ እነዚህ የታጣቂ ቡድን አባላት በመተከል እና ከማሽ ዞኖች ትጥቅ ሳይፈቱ በከተሞችና በገጠር ቀበሌዎች በመንግስት ሎጀስትክስ እየተንቀሳቀሱ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ስጋት እየፈጠሩ ይገኛሉ ሲል አሳውቋል።
ፓርቲው ወቅታዊ የሆነውን ክልላዊ ሁኔታን በማስመልከት ፦
- የመተከልን ህዝብ ማህበራዊ እረፍት በመንሳት ቀጠናውን የጦረነት ማዕከል ለማድረግ የሚሰሩ አካላት ከድርጊታቸው እንድቆጠቡ ፤ አረሶ አደሩን ለማስራብ በማለም የእርሻና የምርት ወቅት በመጠበቅ የሚደረግ አመራር ፈጠር ግድያ በእጅጉ እንደሚያወግዝ ገልጿል።
- ጥቅምት 9 ቀን 2015 ዓ/ም ከጉህዴን ጋር የክልሉ መንግስት በደረሰው ስምምነት መሰረት የታጠቁ የጉህዴን ኃይሎች ተሃድሶ ስልጠና ከወሰዱ በኃላ ትጥቅ ፈተው ወደ ህብረተሰቡ ይቀላቀላሉ ቢባልም ትጥቅ ሳይፈቱ ማህበረሰቡ ውስጥ የሚያደረጉት እንቅስቃሴ በተለይም የመንግስት የፀጥታ አካላትን ሚና #ተክተው የሚያደረጉት እንቅስቀሴ በአስቸኳይ እንዲቆምና ትጥቅ በአስቸኳይ እንዲፈቱ አሳስቧል።
- በመተከል ዞን ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አጀንዳቸውን በኃይል ለማስፈጸም የሚታትሩ #የውስጥ እና #የውጭ ሃይሎች ከድረጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስቧል።
- ሰሞኑን በግልገል በለስ ከተማ በዜጎች ላይ የተፈፀመውን ዘግናኝ ግድያና ከድርጊቱ ጀርባ ያሉ አካላትን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ የክልሉና የፌደራል ፖሊስ በማጣራት አጥፊዎችን ለህግ እንዲያቀርቡና ለህዝቡ ይፋ እንዲያደረጉ ጠይቋል።
- የክልሉ መንግስት በሰላም ውስጥ ልማትን ማሰብና መፈፀም የማይችሉ፣ በግጭት ውስጥ በህዝብ ደም በስልጣን ላይ ለመኖር የሚፈልጉ ሀሳብና ውጤት አልባ ጊዜ ያለፈባቸው አመራሮችን በአስቸኴይ በማጥራት እንዲያስተካክል ፓርቲው አሳስቧል።
(ከቦዴፓ የተላከው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia

#Update
ኢትዮጵያ #ድምፀ_ተአቅቦ ያደረገችበት የተመድ አስቸኳይ እና ልዩ ጉባኤ ተካሄደ።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዓርብ ምሽት በእስራኤል እና ሃማስ የጋዛ ጦርነት ጉዳይ አስቸኳይ እና ልዩ ጉባዔ አካሂዷል።
በዚህም ጉባኤ በ " ዮርዳኖስ " አቅርቢነት በጋዛ " አስቸኳይ የሰብአዊ ተኩስ አቁም " እንዲደረግ የሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ ቀርቦ ነበር።
የሰብዓዊ ተኩስ አቁም ጥሪ የቀረበበት የውሳኔ ሀሳቡ ፦
- በ120 ድጋፍ፣
- በ14 ተቃውሞ
- በ45 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ጸድቋል።
በዚህም መሰረት ተመድ በጋዛ አስቸኳይ የሰብዓዊ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ውሳኔ አሳልፏል።
የውሳኔ ሃሳቡን ከተቃወሙት ውስጥ አሜሪካ ፣ እራሷ እስራኤል ፣ ሃንጋሪ ፣ ኦስትሪያ ይገኙበታል።
ድምፅ ተአቅቦ ካደረጉት መካከል ደግሞ ሀገራችን #ኢትዮጵያ ፣ ጀርመን ፣ ካናዳ፣ ግሪክ፣ ፊንላንድ፣ ዴንማርክ፣ ስውዲን፣ ኢራቅ፣ ጃፓን፣ ጣልያን፣ ሕንድ ፣ዩናይትድ ኪንግደም፣ ዩክሬን፣ ቱኒዝያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ዛምቢያ ይገኙበታል።
የተመድ አስቸኳይ እና ልዩ ጉባዔ የተካሄደው በእስራኤል እና ሃማስ መካከል ጦርነቱ ተባብሶ በቀጠለበት ሁኔታ ነው።
እስራኤልም በጋዛ የምድር ዘመቻ ማካሄድ ጀምራለች።
የእስራኤል ጠ/ሚ ቤንያሚን ኔታንያሁ አማካሪ ማርክ ሬጅቭ የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን #ሃማስ በሰብአዊነት ላይ በርካታ የግፍ ወንጀሎችን መፈፀሙን ገልጸው ለዚህም ደግሞ ከዓርብ ምሽት (ትላንት) ጀምሮ ክፍያውን #እንደሚከፍል እና እስራኤልም መመለስ መጀመሯን ተናግረዋል።
ሀማስ እስራኤል ለምታካሂደው የምድር ላይ ዘመቻ አፀፋውን ለመስጠት ሙሉ ዝግጁነት እንዳለው ገልጿል።
የሀማስ የፖለቲካ ቢሮ ከፍተኛው አመራር ኢዛት አል-ሪሻቅ " ኔታንያሁ ወደ ጋዛ ለመግባት ከወሰነ እኛም ዝግጁ ነን " ያሉ ሲሆን " የወታደሮቹ ሬሳ በጋዛ ምድር ይዋጣል " ብለዋል።
21ኛ ቀኑን በያዘው በእስራኤልና ሃማስ ጦርነት በእስራኤል ጥቃት ጋዛ የተገደሉ ሰዎች ከ7300 መብለጣቸውን በሃማስ ስር ያለው የጤና ሚኒስቴር የገለፀ ሲሆን በእስራኤል በኩል በሃማስ የተገደሉም ከ1400 በልጠዋል።
ℹ️ ተጨማሪ #የውጭ_ሀገር_መረጃዎችን በዚህ መከታተል ይችላሉ 👉https://yangx.top/+LM-bJ8NzZMcxMjA8

#Puntland #Somalia
ፑንትላንድ ለሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ዕውቅና መስጠት ማቆሟን ይፋ አድርጋለች።
ከፊል ራስ ገዝ የሆነችው #ፑንትላንድ በሞቃዲሾ ለሚገኘው ለሶማሊያ የፌደራል መንግሥት ከዚህ ቀደም ሰጥታው የነበረውም ዕውቅና አንስታለች።
የፑንትላንድ መንግሥት ካቢኔ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዶ ፑንትላንድ የሶማሊያ ፌደራል መንግሥት ተቋማት ላይ የነበራትን መተማመን በማጣቷ ትሰጥ የነበረውን ዕውቅና እንዳነሳች አሳውቋል።
ምክንያቱ ምንድነው ?
የሶማሊያ መንግሥት ፓርላማ ብዙ ባወዛገበ ሂደት በአገሪቱ ሕገ መንግሥት ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ ውሳኔ አሳልፏል።
የሕገ መንግሥት ማሻሻያው ፕሬዝዳንቱ የአገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር የማሰናበትን ሙሉ ሥልጣን የሚሰጥ ሲሆን ‘ አንድ ሰው አንድ ድምጽ ’ የሚለውን ዓለም አቀፍ የምርጫ መርህ ተግባራዊ እንዲሆን የሚያደርግና ሌሎችም ማሻሻያዎች አሉበት።
NB. በሶማሊያ #ውስብስብ የሆነውን እና በጎሳ መሠረት የሚደረገውን ምርጫ ከ50 ዓመታት በላይ ስትጠቀምበት ቆይታለች፡፡ አሁን ' አንድ ሰው አንድ ድምፅ ' የሚለው ማሻሻያ በፑንትላንድ ባለልስጣናት ተቃውሞ ገጥሞታል።
በአጠቃላይ የፌዴራል መንግሥት ያካሄደው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ በፑንትላንድ አልተወደደም ውድቅም ተደርጓል።
ፑንትላንድ ፤ " በጋራ መግባባት ላይ የሚደረስበት ሕገ መንግስታዊ ሂደት እስከሚፈጠር ድረስ የፑንትላንድ አስተዳደር ለፌዴራል ተቋማት እውቅና አይሰጥም፣ ተቋማቱ ላይም እምነት የለውም " ብላለች።
ሕዝበ ውሳኔ (#ሪፈረንደም) የሚደረግበት ሕገ መንግስት እስከሚወጣ ድረስ፣ ፑንትላንድ የራሷ የሆነ መንግስታዊ ስልጣን እንደሚኖራት አስታውቃለች፡፡
ከአሁን በኋላ ፍላጎቷን ለማስጠቅ ከማዕከላዊ የሶማሊያ መንግሥት እውቅና ውጪ በራሷ አማካይነት #የውጭ_ግንኙነቶችን እንደምታደርግ ገልጻለች።
ይህ የፑንትላንድ ውሳኔ ከሶማሊያ ተነጥሎ ነጻ አገርነትን ከማወጅ ጋር ሊስተካከል እንደሚችል በመጥቀስ #ከሶማሊላንድ ቀጥሎ ለፌደራል መንግሥቱ ሌላ ራስ ምታት እንደሚሆን ተንታኞች እየገለጹ ነው።
ፑንትለንድ በተፈጥሮ ሃብቶችና #በቦሳሶ_ወደቧ በመተማመን እ.አ.አ 1998 ነው ከፊል ራስ ገዝ መሆኗን ያወጀችው። እራሷን እንደ ነጻና ሉኣላዊ ሀገር የምትቆጥረው የሶማሊላንድ ጎረቤትም ናት።
መረጃው ከቪኦኤ እና ቢቢሲ የተውጣጣ ነው።