TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#update የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ባሳለፍነዉ 2011 በጀት አመት በተለያዩ ቁልፍ የሀገሪቱ ተቋማት እና መሰረተ ልማቶች ላይ ሊፈጸሙ የነበሩ 791 የሚደርሱ የሳይበር ጥቃቶችን ማክሸፍ መቻሉን ገልጿል፡፡

በኢመደኤ የኢትዮጵያ ሳይበር የድንገተኛ ዝግጁነት እና ምላሽ ሰጪ ዲቪዥን ሃላፊ የሆኑት አቶ አብርሃም ገ/ጻዲቅ እንደገለጹት በአገራችን ላይ ሊቃጡ የሚችሉ የሳይበር ጥቃቶችን አስቀድሞ በመከላከል እና ቢከሰቱም እንኳን የከፋ ጉዳት ከማድረሳቸዉ በፊት በአፋጣኝና በአጭር ጊዜ ምላሽ በመስጠት ረገድ ኢመደኤ አይነተኛ ሚናን መጫወት መቻሉን ገልጸዋል፡፡

ሃላፊዉ ጨምረዉ እንደገለጹት በ2011 በጀት አመት በአገሪቱ ላይ የተቃጡ የሳይበር ጥቃቶችን አስቀድሞ መከላከል በመቻሉ ሊደርስ ከነበረው የደህንነት እና የገንዘብ ኪሳራ በድምሩ ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት ማዳን መቻሉን የገለጹ ሲሆን፤ ከዚህም በላይ በገንዘብ የማይተመን ሰላምን እና ፍትህ ማስጠበቅ ተችሏል ብለዋል፡፡

በቀጣይ 2012 በጀት አመት አገራዊ የሳይበር ጥቃትን የመከላከል ሽፋን በማሳደግ እና ዓለም አቀፍ ትስስርንና ቅንጅትን በማጠናከር የአገሪቱን ቁልፍ የሳይበር መሰረት ልማቶችን ደህንነት የማስጠበቅ ስራ እንደሚሰራም ሃላፊዉ ገልጸዋል፡፡

Via #AMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮጵያና ኬንያን ባወዛገበው #የጁባላንድ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሕመድ ማዶቤ 2/3ኛውን ድምፅ በማግኘት ማሸነፋቸውን ጋራዌ ፅፏል። ማዶቤ ለመጀመሪያ ጊዜ ሥልጣን የያዙት ከ6 አመታት በፊት ነበር። ለምርጫው የኪስማዮ አውሮፕላን ማረፊያ ተዘግቶ ነበር።

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeBot በኢትዮ ቴሌኮም ስም!

ትላንት በንግድ ባንክ ስም ዛሬ ደግሞ በኢትዮ ቴሌኮም ስም #ሀሰተኛ መልዕክቶች ሲሰራጩ እየተመለከትን ነው።

"Ethio Telecom ካርድ ልናንበሸብሽዎት በ ቴሌግራም መጥተናል። ይህ bot ቁጭ ብለው ገንዘብ የሚያፍሱበት ነው። በዚህ ቦት 1 ሰዉ ሲጋብዙ 1 ብር ያገኛሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉን።"

#የኢትዮቴሌኮምን ስምን እየተጠቀሙ የሚሰራጩ የተሳሳቱ መልዕክቶችን በርካታ የቴሌግራም ተጠቃሚዎች ሲቀባበሉት ተመልክተናል ይህ ፍፁም #ሀሰት ነው። መልዕክቱም የሚሰራጨው በሀሰተኛ ገፅ ነው!!

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸አሸንድዬ፣ ሻደይ ሶለል አከባበር በአዲስ አበባ 6 ኪሎ የስብሰባ ማዕከል! #ሲራጅ #TIKVAH_ETHIOPIA
በ18 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የኩላሊት ህክምና ሆስፒታል ሊገነባ ነው!

የኳታር መንግስት በ18 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በአዲስ አበባ ከተማ የኩላሊት ህክምና ሆስፒታል ሊገነባ ነው። በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳዮች ዳይሬክተር አምባሳደር ተበጀ በርሄ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን ከኳታር ልማት ፈንድ የፕሮጀክት ኃላፊዎች ጋር በሀገራችን የኩላሊት ህክምና ሆስፒታል ለማቋቋም ዝርዝር ውይይት አድርጓል።

Via ኤፍ ቢ ሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ ያስገነባው ትምህርት ቤት ነገ ይመረቃል!

በዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ከሚገኙ የዳስ ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ የሆነው እና በአትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ መልሶ የተገነባው ‘ገልኩ’ ትምህርት ቤት ነገ እንደሚመረቅ የዞኑ የትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሽታው አዳነ ለቢቢሲ ገለፁ። አዲስ የተገነባው ይህ ትምህርት ቤት ስምንት የመማሪያ ክፍሎች ያሉት ሲሆን ወደ 350 ተማሪዎችን ሊያስተናግድ እንደሚችል ይገመታል። ትምህርት ቤቱ ኃይሌ ገብረሥላሴ ተብሎ እንደተሰየመም ኃላፊው አክለዋል። በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ አትሌት ኃይሌን ጨምሮ ሌሎች የትምህርት አመራሮች እንደሚገኙ ይጠበቃል።

በዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በአጠቃላይ 874 የመማሪያ ክፍሎችን የያዙ 7 የዳስ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ሲሆን በእነዚህ ትምህርት ቤቶችም ከ1500 በላይ ተማሪዎች ይማሩባቸዋል። በነገው ዕለት የሚመረቀው ትምህርት ቤትም ከእነዚህ መካከል አንዱ ነው። "ወቅቱ ክረምት በመሆኑ ግንባታቸውን ለመጀመር አልተመቸም" የሚሉት ኃላፊው አትሌት ኃይሌ ሌላ ሁለት የዳስ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት ርክክብ ማድረጉን ለቢቢሲ ገልፀዋል።

Via #BBC
ፎቶ📸AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸የውጭ ሀገር ዜጎች እየተከበረ በሚገኘው የአሸንዳ በዓል ላይ! #ትግራይ #ETHIOPIA

©ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የከተማ ልማትና ኮንስራክሽን ሚኒስትር ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በባሊ ኢንዶኔዢያ በመካሄድ ላይ ባለው የኢንዶኔዢያ- አፍሪካ የመሰረተ ልማት ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡

በጉባዔው ላይ በተካሄደው የፓናል ውይይት ላይ ማብራሪያ የሰጡት ክበርት ኢንጂነር አይሻ ባለፉት አስርተ ዓመታት ኢትዮጵያ ጠንካራ የኤከኖሚ ዕድገት ማሰመዝገቧን ተናግረዋል፡፡ በተለይም በመሰረተ ልማት ልማት ላይ ያላትን ተሳትፎ ይበልጥ ውጤታማና ተወዳዳሪ ለማድረግ እየሰራች መሆኗንም ገልፀዋል፡፡

በመንገድ መሰረተ ልማት ፣ በባቡር ሐዲድ ፣ በብሔራዊ ሎጅስቲክስ ልማት ፣ በትራንስፖርት ዘርፍ እና በአየር ትራንስፖርት ዘርፎች የተመዘገቡት ውጤቶች አስደናቂ መሆናቸውን ለጉባኤው ተሳታፊዎች ያብራሩት ክብርት ሚኒስትሯ የባቡር ሐዲድ ኮርፖሬሽን መዘርጋቱንና ዘመናዊ የሆነ ክልላዊና አገራ አቀፋዊ የባቡር ኔትወርክን በመገንባት ላይ መሆኗንም ተናግረዋል፡፡ የባቡር ኮርፖሬሽኑ ዋና ከተማዋን ከጂቡቲ ወደብ ጋር የሚያገናኝ የ 656 ኪሎ ሜትር የባቡር መስመር መዘርጋቱንና ይህም ወደጅቡቲ ወደብ ለመድረስ ይፈጅ የነበረውን የ 84 ሰዓታት ቆይታ ጊዜ ወደ 10 ሰዓታት ድረስ ለመቀነስ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ET-08-22

Via Negede
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለእነ ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ የክስ መዝገብ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ!

የእነ ብርጋዴር ጄነራል ተፈራ ማሞ የክስ መዝገብ ለነሃሴ 17/2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ፡፡ የባሕር ዳር ከተማና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩ ውስብስብና መርማሪ ቡድኑ ለጠየቀው ይግባኝ ውሳኔ ለመስጠት ተጨማሪ ጊዜ በማስፈለጉ ለነገ ነሐሴ 17/2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ነሐሴ 15/ 2011 ዓ.ም በነበረዉ ችሎት ከሳሽ አካል ቅድመ ምርመራ በማቋረጡ ኮሎኔል አለባቸዉ ብዙነህ ክሱ ተነስቶላቸዋል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከUK መንግስት ሴክሩተሪ አሎክ ሻርማ ጋር ኢስተርን ኢንደስተሪ ዞን በመገኘት ዩኒሌቨር ኩባንያን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡ ከጉብኝቱ በኃላ በዱክም ከተማ በጋራ ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል፡፡

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የከፍተኛ ትምህርት አግባብነት እና ጥራት ኤጀንሲ በአዲስ አበባና ዙሪያ ብቻ 18 ካምፓሶችን በጥራት ጉድለት ዘግቻለሁ አለ።

የኤጀንሲው ም/ል ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምራት እንዳሉት በአዲስ አበባ እና ዙሪያ ብቻ በተደረገ ፍተሻ እና ምርመራ በጥራት ጉደለት 18 የግል ካምፓሶች እንዲዘጉ ተደርገዋል ብለዋል። ኤጀንሲው በተዘጉት ካምፓሶች እየተማሩ ያሉትን ተማሪዎች እጣ ፈንታ አለመወሰኑንም እክለዋል።

በክልል ደረጃም ቢሆን መቀሌ፣ሀረር እና ሌሎችም ቦታዎች ላይ ከጥራት እና ፍቃድ ጋር በተያያዛ የዘጋቸው ካንፓሶች መኖራቸውን ምክትል ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በክልል ደረጃም መሰል እርምጃዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አቶ ታምራት ተናግረዋል።

ኤጀንሲው ከቀናት በፊት እኔ ሳላውቅ ከግል ኮሌጆች ጋር በትብብር ሲሰሩ አግኝቻቸዋለሁ ያላቸውን 4 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን ካምፓስ መዝጋቱ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢራን በራሷ አቅም እንዳመረተችው የገለጸችውን የረጅም ርቀት የምድረገፅና የአየር ላይ የሚሳኤል መቃወሚያ መሳሪያን ለዕይታ አብቅታለች። ባቫር-373 የተሰኘው የሚሳኤል መቃወሚያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሮሃኒ በተገኙበት በይፋ ለዕይታ ክፍት ሆኗል።

የኢራን መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት መሳሪያው ሲነጻጸር ከሩሲያው ኤስ-300 የሚሳኤል መቃወሚያ ጋር እኩል የሚሆን ነው። የመከላከያ ሚኒስትሩ አሚር ሃታሚ በቴሌቪዥን በተላለፈው ንግግራቸው በዚህ የረጅም ርቀት የሚሳኤል መቃወሚያ የአየር ላይ የጥቃት ኢላማዎችን እስከ 300 ኪሎሜትር ርቀት የሚጠቁም፣ በ200 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ደግሞ ጄቶችን መምታት የሚችል ነው ብለዋል። የጦር መሳሪያው ይፋ የሆነው የኢራን ብሔራዊ የመከላከያ ኢንዱስትሪ ቀንን አስመልክቶ ነው።

ምንጭ፦ ሬውተርስ/#ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ በቁጥጥር ሥር ዋለ!

33 ሰዎች በተከሰሱበት የክስ መዝገብ ለአንድ ዓመት በፖሊስ ሲፈለግ የነበረው የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ቴድሮስ ገቢባ በትናንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ተከሳሹ ከሰኔ 05 እስከ 12/2010 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ የወላይታና ሲዳማ ብሔሮችን በማጋጨት ለሰው ሕይወት መጠፋት እና ንብረት መውደም እንዲከሰት የዕርስ በርስ ግጭት በማነሳሳትና በመጠንሰስ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተከሶ ሲፈለግ የቆየ መሆኑ ይታወሳል፡፡

ከአንድ ዓመት በኃላ የፌዴራል ፖሊስ ባደረገው ክትትል ነሃሴ 15 ቀን 2011 ዓ.ም በቁጥጥር ሥር የዋለ ሲሆን ተከሳሹ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 13ኛ የወንጀል ችሎት ሆሳዕና ተዘዋዋሪ ችሎት ቀርቧል፡፡

Via የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀሰተኛ መረጃ ነበር!

ከዚህ ቀደም/ሀምሌ 18/ ዋዜማ ራድዮን ጨምሮ የተለያዩ አክቲቪስቶችና የፌስቡክ ገፆች የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ቴዎድሮስ ገቢባ ታሰሩ ብለው ያሰራጩት መረጃ ሀሰተኛ ነበር። በወቅቱ የትኛውም የመንግስት አካል ስለመታሰራቸው በይፋ አላረጋገጠም። ዋዜማ ሬድዮም #የሲአንን የፌስቡክ ገፅ ጠቅሶ ያሰራጨው መረጃ ከሀሰተኛ ገፅ የተወሰደ ነበር። አቶ ቴዎድሮስ በቁጥጥር ስር የዋሉት #ትላንት ነው።

ከሀሰተኛ የፌስቡክ ገፆች እንጠንቀቅ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኒውዚላንድ አፈ ጉባኤ በፓርላማ ክርክር ወቅት ለህፃን ጡጦ አጠቡ!

ትሪቮር ማላርድ የተባሉት የኒውዚላንድ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ በምክር ቤቱ እየተካሄደ በነበረ ክርክር ወቅት የአንድን የፓርላማ አባል ልጅ በማቀፍና ጡጦ በማጥባት አግራሞትን ፈጥረዋል፡፡ ዘጋርዲያን #በተንቀሳቃሽ ምስል ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያሳየው አፈ ጉባኤው ልጁን ያጠቡት ታማቲ ኮፊ የተባለችው የምክር ቤት አባል ክርክር እያደረገች በነበረበት ወቅት ነው፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የአፋን ኦሮሞ ትምህርት #ለድርድር የሚቀርብ አይደለም" የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአፋን ኦሮሞ ትምህርት ለድርድር የማይቀርብና ለቋንቋው እድገት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያን ስርዓተ ትምህርት አስመልክቶ በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠው መግለጫ የአፋን ኦሮሞን  ተጨባጭ  ሁኔታ የማይገልጽ መሆኑንና የክልሉ መንግስት በቋንቋ ጉዳይ ላይ የማያወላዳ አቋም እንዳለው  ህዝቡ ሊረዳ እንደሚገባም ተናግረዋል።

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤትን የማስተዳደር፣ የትምህርት ስርዓትን ማዘጋጀት፣ የስምንተኛ ክፍል ፈተና ማዘጋጀትና አርሞ ውጤት መወሰን  ለክልል የተሰጠ ስልጣን በመሆኑ በዚህ ላይ ጫና የሚያሳድር  ማንም ሊኖር እንደማይገባ ገልጸው፤ እንደ ከዚህ በፊቱ ሁሉ በአፋን ኦሮሞ የሚሰጥ ትምህር እንደሚቀጥልም ነው ያሳወቁት።

የክልሉ መንግስት የአፋን ኦሮሞ ቋንቋን ለማሳደግ ከዚህ በፊት በቋንቋው ትምህርት በማይሰጥባቸው አካባቢዎች ጭምር መማሪያ እንዲሆን እየሰራ በመሆኑ ሁሉም ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ነው አቶ ሽመልስ የገለጹት።

በተጨማሪም በክልሉ ውስጥ ከክልሉ ስርዓተ ትምህርት ውጪ የሚያስተምሩ የግል  ትምህርት ቤቶች ላይም በዚህ ዓመት የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወሰድ ተጠቅሷል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ!

የቁልቢ ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪ መልዓከኃይል ቆሞስ አባ እንቁስላሴ ድንገተኛ ህልፈተ ሕይወት ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 11 ሰዎችን በመያዝ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ። የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ድቪዝን ኃላፊ ኮማንደር ስዩም ደገፋ ለኢዜአ እንደገለጹት የገዳሙን አስተዳዳሪ የአሟሟት ሁኔታ ለማጣራት ከዞንና ከሜታ ወረዳ አቃቤ ህግና ፖሊስ የተውጣጣ ቡድን ተቋቁሞ ምርመራ በመደረግ ላይ ነው።

በዚህም እስካሁን የተጠረጠሩ 11 ሰዎችን በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነም አመልክተዋል። መርማሪ ቡድኑም ወደዳግማዊ ምኒሊክ ሆስፒታል የተላከውን የአስክሬን ምርመራ ውጤት በመጠባበቅ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

የገዳሙ አስተዳዳሪ ህይወታቸው ባለፈ በበነገታው የአካባቢው ነዋሪዎች ከወረዳው አስተዳዳሪ፣ ከአገር ሽማግሌዎችና ሃይማኖት አባቶች ጋር ውይይት ከዳረጉና የጋራ መግባባት ላይ ከተደረሰ በኋላ ከህግ አግባብነት ውጭ መንገድ መዝጋታቸውን ኮማንደር ስዩም አያይዘው ተናግረዋል።

ከእዚህ በተጨማሪ ሌሎች የጸጥታ ችግሮችን በመፈጸም ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በተፈጠረው ግጭት አንድ የስምንት ዓመት ታዳጊ ሕጻን ሕይወቱ ማለፉንና በአራት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን አመልክተዋል። ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች በአሁኑ ወቅት በድሬዳዋ ህክምናቸውን እየተከታተሉ መሆኑንም ገልጸዋል።

የገዳሙ አስተዳዳሪ መልዓከ ኃይል ቆሞስ አባ እንቁስላሴ ባለፈው ነሐሴ 12 ቀን 2011 ዓ.ም በገዳሙ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ድንገት ሕይወታቸው አልፎ መገኘቱ ይታወሳል። የቀብር ሥነስርአታቸውም ባለፈው ማክሰኞ በትውልድ ስፍራቸው መፈጸሙ ታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከመልዓከኃይል ቆሞስ አባ እንቁስላሴ ድንገተኛ ህልፈተ ሕይወት ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ 11 ሰዎችን በመያዝ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታ!

አክቲቪስት #ጃዋር_መሐመድ የኢትዮጵያ የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ-ካርታ «ግልፅ ያልሆነ፣ በቂ ጥናትና በቂ ውይይት ያልተካሔደበት» ነው ሲል ተቸ። በ2013 ዓ.ም. ሥራ ላይ ይውላል ተብሎ የሚጠበቀው ፍኖተ-ካርታ «ተድበስብሶና ተምታቶ የቀረበ» ነው ሲል ወርፎታል።

ለኦኤምኤን በሰጠው ማብራሪያ «የትምህርት ፍኖተ-ካርታ ከሀገር ግንባታ ጋር የተያያዘ ነው። የሀገር ግንባታ ደግሞ ፖለቲካዊ ፕሮጀክት ነው። ስለዚህ የትምህርት ፍኖተ-ካርታው ካገሪቷ የፖለቲካ ፍኖተ-ካርታ ጋ መዋሐድ መቻል አለበት» ብሏል

አዘጋጆች «ብቃት ያላቸው ባለሙያዎች መሆን ነበረባቸው፤ በሀገሪቷ ያሉ ብሔር ብሔረሰቦችን የተለያዩ ባለድርሻዎችን ያሳተፈ ሊሆን ይገባዋል» ያለው ጃዋር «ሀገሪቷ ከምትፈልገው የፖለቲካ ፍኖተ-ካርታ የሚጻረር» ነው የሚል ዕምነት እንዳለው ተናግሯል።

ጃዋር «እኔ እንደማስበው የታሪክ መፃህፍቶች ውስጥ ያለው ይዘት በምሁራን በደንብ ተገምግሞ ለሕዝብ ቀርቦ ውይይት እና ክርክር ሳይደረግበት ወደ መተግበር እንገባለን ካሉ ይኸቺን ሀገር ወደ መበታተን ለማቃረብ የሚደረግ ነው» ሲል አስጠንቅቋል።

Via #EsheteBekele

@tsegabwolde @tikvahethiopia
24 ሺህ የሚጠጋ ህዝብ ከቀዬው ተፈናቅሏል!

በክረምቱ ወራት በአንዳንድ የኢትዮጵያ ክፍሎች በደረሰ የጎርፍ አዳጋ 24 ሺህ የሚጠጋ ህዝብ ከቀዬው መፈናቀሉን የአደጋ ስጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ። በቀሪው የክረምት ወቅትም በአንዳንድ አካባቢዎች ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊከሰት ስለሚችል ህዝቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ በበኩሉ አሳስቧል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia