TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
#update ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የፖላንድ አምባሳደር ሚስተር አሌክሳንደር ክሮፕዊንኪን ተቀብለው አነጋገሩ፡፡ በኢትዮጵያ እና በፖላንድ መካከል የሁለትዮሽ ግንኙነት በሚጠናክርባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል፡፡

ምንጭ:- የፕሬዝዳንት ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ሠራዊቱ አሁንም #መስዋትነት እየከፈለ የዜጎችን ሰላም እና ደኅንነት ለማረጋገጥ እየሠራ ነው፡፡›› ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን
.
.
የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀን ለ7ኛ ጊዜ በአዳማ ከተማ ተከብሯል፡፡ በበዓሉ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል #ሰዓረ_መኮንን ‹‹በዓሉን የምናከብረው በትግል መስዋትነት ከፍለው ያለፉ ሠራዊቶችን ለመዘከር፣ በክብር ለተሰናበቱት ክብር ለመስጠት እና በማገልገል ላይ ያሉ ሠራዊቶችን ለማሰብ ነው›› ብለዋል፡፡

የመከላከያ ሠራዊት ቀን ሠራዊቱ ሕገ-መንግሥታዊ ቃሉን የሚያድስበት እና ሕዝባዊ ወገንተኝነቱን የሚያጠናክርበት እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡ ለተጀመረው ተስፋ ሰጪ ሀገራዊ ለውጥ የመለከላከያ ሠራዊት ግንባር ቀደም ባለቤት ሆኖ በተቋማዊ ለውጥ ውስጥ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡ ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንደሚሠሩም ጀኔራል ሰዓረ አረጋግጠዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር የጀመረችው ሰላማዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲጎለብት የመከላከያ ሠራዊት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ እንደሆነና ወደፊትም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

የመከላከያ ሠራዊት አሁንም መስዋትነት እየከፈለ የዜጎችን ሰላም እና ደኅንነት ለማረጋገጥ እየሠራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በበዓል አከባበሩ ላይ የጅቡቲ፣ የኬንያ፣ የሱዳን፣ የደቡብ ሱዳን፣ የቡሩንዲ፣ የሩዋንዳ እና የሌሎች ጎረቤት ሀገራት የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡

ምንጭ፦ AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጭላሎ ተራራ በእሳት እንዲወድም ያደረገው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ‼️

የጭላሎ ተራራ ደን በእሳት እንዲወድም ያደረገው ግለሰብ #በፅኑ_እስራት ተቀጣ፡፡ ተከሳሹ የአርሲ ተራራ የጭላሎ ፓርክ ደን ለጊዜው ካልተያዙ ሁለት ግለሰቦች ጋር በመሆን ጥር 23 ቀን 2011 ዓ.ም 11 ሰዓት ላይ በእሳት እንዲያያዝ ማድረጋቸውን አቃቤ ህግ በክሱ ጠቅሷል።

ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ለጊዜው ከአካባቢው ሲሰወሩ ተከሳሹ በአካባቢው ነዋሪዎች እጅ ከፍንጅ መያዙ ነው የተገለጸው።

ለሶስት ቀናት የዘለቀውን የእሳት ቃጠሎ የአካባቢው ነዋሪዎች ለማጥፋት ርብርብ ያደረጉ መሆኑ በክሱ የገለፀው አቃቤ ህግ እሳቱን ለማጥፋት የሰው ኃይልን ጨምሮ ከ210 ሺ ብር በላይ ወጪ እንዲወጣም ተከሳሹ ምክንያት ሆኗል ብሏል።

ተከሳሹና ግብረ አበሮቹ በጭላሎ ተራራ በለኮሱት እሳት ከ800 ሄክታር በላይ ደን መውደሙን በመግለፅ አቃቤ ህግ በጢዮ ወረዳ ፍርድ ቤት ክስ መመስረቱም ነው የተገለጸው።

በዚህም ተከሳሹ የወንጀል ድርጊቱ መፈፀሙን ቢያምንም ለአካባቢው እንግዳ መሆኑና ከብቶችን ጅብ በልቷል በሚል ሊያቃጥሉ የሄዱ ሁለት ሰዎችን ተከትሎ ከቤት መውጣቱን ለፍርድ ቤት ገልጿል።

የግራና ቀኙ ክርክር ያደመጠው የጢዮ ወረዳ ፍርድ ቤትም ተከሳሹ አቃቤ ህግ ያቀረበበትን ማስረጃ ማስተባበል ባለመቻሉ በ7 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

እጃቸው ያልተያዙ ሁለት ተከሳሾችን ህዝብ አሳልፎ እንዲሰጥና ፖሊስም ለህግ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤቱ ማዘዙም ታውቋል፡፡

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኤል ቻፖ ጉዝማን‼️

#ሜክሲካዊው የዕፅ ነጋዴ #ዮአኪን ''ኤል ቻፖ'' ጉዝማን በኒው ዮርክ ፌደራል ፍርድ ቤት በቀረቡበት 10 ክሶች በሙሉ ጥፋተኛ ተባለ።

የ61 ዓመቱ ''ኤል ቻፖ'' በሚል ቅጽል ስሙ የሚታወቀው ዮአኪን ጉዝማን ኮኬይን እና ሄሮይን በማስራጨት፣ በህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ባለቤትነት እና በህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ክሶች ቀርበውበታል።

የፍርድ ቤቱን ውሳኔ የሚጠባበቀው ኤል ቻፖ የተቀረውን እድሜውን በእስር ሊያሳልፍ እንደሚችል ተገምቷል።

ኤል ቻፖ ከሜክሲኮ ወደ አሜሪካ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት ከፍተኛ ጥበቃ ከሚደረግላቸው ሁለት የሜክሲኮ እስር ቤቶች ማምለጥ ችሎ ነበር።

በድጋሚ ታህሣሥ 2008 በቁጥጥር ሥር የዋለው ኤል ቻፖ 2009 ላይ ለአሜሪካ ተላልፎ ተሰጥቷል። ኤል ቻፖ በብዛት ወደ አሜሪካ ለሚገቡ ዕፆች ተጠያቂ ሆኖዋል።

ሲቢኤስ ኒውስ እንደዘገበው ከሆነ ጥቁር ጃኬት እና ክራቫት አስሮ ከፍርድ ቤቱ የተገኘው ኤል ቻፖ የጥፋተኝነት ውሳኔ ሲተላለፍበት ምንም አይነት የስሜት መለዋወጥ አላሳየም።

ከፍርድ ቤቱ በፖሊስ ኃይል ታጅቦ ሲወጣ የፍርድ ሂደቱን ስትከታተል ለነበረችው የ29 ዓመቷ ባለቤቱ ኤማ ኮርኔል የቅንጡ ሰላምታ ሰጥቷታል።

የጉዝማን ጠበቆች ይግባኝ እንደሚጠይቁ ተናግረዋል።
.
.
#ኤል_ቻፖ ጉዝማን ማነው?

"ኤል ቻፖ'' ማለት ''አጭሩ'' እንደማለት ሲሆን በሰሜናዊ ሜክሲኮ ሲናሎአ የተሰኘ የዕፅ አዘዋዋሪ ቡድን መሪ ነበረ።

ኤል ቻፖ የሚመራው ቡድን ወደ አሜሪካ ለሚላከው ዕፅ ትልቁን ድርሻ ይዞ ነበር። እአአ 2009 ፎርብስ ኤል ቻፖ ጉዝማን የተጣራ 1ቢሊዮን ዶላር ያስመዘገበ ከበርቴ ነው በማለት የዓለማችን 701ኛው ሲል የሃብታሞች ዝርዝር ውስጥ አካቶታል።

የፍርድ ሂደቱ ተደብቆ የቆየውን የኤል ቻፖ ጉዝማን ህይወትን አደባባይ ያወጣ እንደሆነ በርካቶች ይስማማሉ። በፍርድ ሂደቱ ላይ የቀድሞ የቅርብ አጋሩ የነበሩ ሁሉ መስክረውበታል።

ከተሰጡበት ምስክርነቶች አንዳንዶቹ ሰዎችን በድንጋጤ ጭው ያደረጉ ነበሩ። ዕድሜያቸው ለጋ የሆኑና እስከ 13 ዓመት የሚደርሱ ሴቶችን ከመድፈሩ በፊት አደንዛዥ ዕፅ እንዲጠቀሙ ያደርግ ነበር ተብሏል።

ጉዝማን ለቀድሞው የሜክሲኮ ርዕሰ ብሔር ኤንሪክ ፔና ኒቶ በ2012 ስልጠን ከያዙ በኋላ እርሱ ላይ የሚደረገው ክትትል እንዲቆም በመጠየቅ አንድ መቶ ሚሊየን ዶላር ጉቦ መክፈሉም የተሰማው በዚያው ችሎት ላይ ነው። ርዕሰ ብሔሩ ግን ይህ ውንጀላ እውነትነት የለውም ሲሉ አስተባብለዋል።

ገድሎ ያቃጠላቸው የአደንዛዥ ዕፅ ከበርቴ ተፎካካሪዎች እንዳሉ ከዘመዶቹ መካከልም የገደላቸው እንዳሉ ተገምቷል።

ችሎቱ ኤል ቻፖ በ2015 በሜክሲኮ እጅግ ጥብቅ ከሆነው እስር ቤት እንዴት እንዳመለጠም በዝርዝር አድምጧል። ልጁ በእስር ቤቱ አቅራቢያ የሚገኝ ቤት እንደተከራየና ጂፒኤስ ያለው ሰዓት ወደ እስር ቤቱ በድብቅ ማስገባቱ ተመስክሯል።

በሚስቱ እና በቅምጦቹ ላይ ለመሰለል በስልኩ ላይ ሶፍትዌር ይጠቀም እንደነበርም ተመስክሮ፤ ኤፍ ቢ አይ የተለዋወጣቸውን የፅሑፍ እንዲያቀርብ ተደርጓል።

በአንድ የፅሁፍ መልዕክቱ ላይም ከነበረበት ቤት አሜሪካዊያንና ሜክሲኳዊያን ከከፈቱበት ድንገተኛ ዘመቻ እንዴት እንዳመለጠ የሚገልጽና ልብስ፣ ጫማ እና ጥቁር ሪዝ እንዲመጣለት የጠየቀበት መልዕክቱም ተነቧል።

ጉዝማን በአሜሪካ የፍትህ አደባባይ ለፍርድ ከቀረቡ የሜክሲኮ የአደንዛዥ ዕፅ ከበርቴዎች መካከል ትልቁ ነው።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አሜሪካ ለኢትዮጵያ የ40 ሚሊየን ዶላር #ድጋፍ ይፋ አደረገች፡፡ ድጋፉ ለሀገሪቱ የጤና ዘርፍ የሚውል ነው ተብሏል፡፡ ድጋፉ ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት እንደሚቀጥልም ተገልጿል፡፡

Via Ahadu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምዕራብ ጎንደር‼️

"ለከባድ ምሽግ ማጥቂያ የሚያገለግሉ የጦር መሳሪያዎች በግለሰቦች ቤት ተገኝተዋል።"

"37 ሰዎች በነፍስ ግድያ፣ 101 ግለሰቦች ደግሞ በስርቆትና በሌሎች ወንጀሎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡"
.
.
በምዕራብ ጎንደር ዞን ተከስቶ በነበረው ግጭት ጥቅም ላይ ሲውሉ የነበሩ የቡድን የጦር መሣሪያ ጥይቶች በግለሰቦች ቤት #መገኘታቸውን የ33ኛ ዓባይ ክፍለ ጦር ገለጸ፡፡

የ33ኛ ዓባይ ክፍለ ጦር 1ኛ ብርጌድ 1ኛ ሻለቃ አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል #አንገሶም_አርአያ ለአብመድ እንደተናገሩት መሣሪያዎቹ የተያዙት #በመተማ ዮሐንስ ከተማ በተቃጠሉ ግለሰቦች ቤት ውስጥ ነው፡፡ ከጥይቶቹ በተጨማሪ ሀሰተኛ የብር ኖቶች፣ አደንዛዥ ዕፆች፣ የቅስቀሳ መሣሪያዎች (ድምጽ ማጉያ) እና የተለያዩ ሰነዶች ተገኝተዋል፡፡ በአካባቢው ነባርና አዳዲስ ምሽጎች መገኘታቸውንም አስታውቀዋል፡፡

ጥይቶቹ የቅንቡላ፣ የአርፒጂ (የላውንቸር) እና የብሬን ናቸው፤ የእጅ ቦንብም ማግኘታቸውን ነው ሌተናል ኮሎኔል አንገሶም የተናገሩት፡፡ መሣሪያዎቹ ለታንክ እና ለከባድ ምሽግ ማጥቂያ የሚያገለግሉ ሆነው ለሀገር መከላከያ ሠራዊት እና ለተፈቀደላቸው የፀጥታ አካላት ብቻ የሚፈቀዱ እንደሆኑም ገልጸዋል፡፡

ክላሽ፣ ሽጉጦች፣ ስለታማ መሣሪያዎች፣ የፌዴራል ፖሊስና የሀገር መከላከያ የደንብ ልብሶችም በተቃጠሉ ቤቶች ውስጥ መገኘታቸንም ነው ሌተናል ኮሎኔሉ ያረጋገጡት፡፡

አሁን የተገኙት የቡድን መሣሪያዎቹ ጥይቶቹ ናቸው፡፡ ሌሎች መሣሪያዎች አሁንም በግለሰቦቹ እጅ እንዳሉ እንደሚታመን ሌተናል ኮሎኔል አንገሶም ተናግረዋል ፡፡ በቀጣይ የኅብረተሰቡን ሰላም ለመጠበቅ ከክልሉ ፖሊስና ከአካባቢው የፀጥታ አካላት ጋር የሀገር መከላከያ ሠራዊት ተቀናጅቶ እየሠራ እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡

ሰላም ለማደፍረስ የሚሠሩ ተጠርጣሪ ግለሰቦች በቁጥጥር በሚውሉበት ጊዜ መንግሥት በቶሎ ለህግ አለማቅረቡን መገምገማቸውንም ነው ሌተናል ኮሎኔል አንገሶም የተናገሩት፡፡

ውሳኔዎች የዘገዩት የፍትህ ስርዓቱን ተከትሎና ማስረጃዎችን ከማሰባሰብ በኋላ የሚሰጡ በመሆናቸው መሆኑን የምዕራብ ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የሰላምና የህዝብ ደኅንነት ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ተናግረዋል፡፡

ከግጭቱ ጋር በተያያዘ 37 ሰዎች በነፍስ ግድያ፣ 101 ግለሰቦች ደግሞ በስርቆትና በሌሎች ወንጀሎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር እንደሚገኙም ታውቋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia