TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
59.6K photos
1.52K videos
215 files
4.14K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
加入频道
ሰባራ ኬላ‼️

በህገ ወጥ መንድ ከመተማ ወደ መሀል ሀገር ሲዘዋወሩ የነበሩ 1 ሺህ 9 መቶ 97 የብሬን ጥይቶችና 100 የክላሽ ጥይቶች ዛሬ የካቲት 7/2011 ዓ.ም መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር ገልጧል፡፡

ጥይቶቹ #ሠራባ_ኬላ ላይ ነው በጉምሩክ ፈታሾች የተያዙት፡፡ የብሬንና የክላሽ ጥይቶች ሲጓጓዙ የነበሩት የሠሌዳ ቁጥር ኮድ-3- 26963 በሆነ ተሸከርካሪ እንደሆነም ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው፡፡

ምንጭ፡- ኢፕድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ወደ ደቡብ አፍሪቃ በመሰደድ ላይ ሳሉ ታንዛንያ ውስጥ #ታንጋ በተባለ አካባቢ ህይወታቸው ያለፈ 8 ኢትዮጵያውያንን ዛሬ ታንጋ ከተማ ውስጥ #መቅበሩን በታንዛንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ። ኤምባሲው ለዶቼ ቬለ በኤሜል እንዳስታወቀው ኢትዮጵያውያኑ የሞቱት ከ3 ወራት በፊት ነው። ይሁን እና እስካሁን ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት እየጠበቀ እንደነበር ገልጿል። ሟቾቹ በሙሉ ወንዶች መሆናቸውን ኤምባሲው ጠቁሟል። አስከሬኑ ወደ ኢትዮጵያ ያልተላከበትን ምክንያት ኤምባሲዉ አልገለፀም።

Via ዶቼ ቬለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ልዑክ በኢትዮጵያ የሚያደርገውን ጉብኝት ለመጀመር በዛሬው ዕለት #አዲስ_አበባ መግባታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። የፐብሊክ ዲፕሎማሲና የባህል ቡድን ልዑኩ 55 አባላትን ያካተተ ሲሆን÷ እውቁ አርቲስት በረከት መንግስትአብ እንደሚገኝበትም ነው የተገለጸው፡፡

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የገቢዎች ሚኒስቴር‼️

ግምታዊ ዋጋቸው 1 ሚሊየን 300 ሺህ ብር በላይ የሚሆኑ የኮንትሮባንድ ዕቃች በተለያዩ የጉምሩክ የፍተሻ ጣቢያዎች #በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ባዛሬው ዕለት በተለያዩ የጉምሩክ የፍተሻ ጣቢያዎች ላይ በተደረገ ክትትል ግምታዊ ዋጋቸው 1 ሚሊየን 315 ሺህ 310 ብር የሚሆኑ የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።

በዚህ መሰረትም በወልዲያ የጉምሩክ ፍተሻ ጣቢያ በተደረገ ፍተሻ ጊዜው ያለፈበት የፋፋ ዱቄት እና ግምታዊ ዋጋቸው 385 ሺህ 50 ብር የሆኑ 369 ሞባይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነው የተገለፀው።

በተመሳሳይ በድሬዳዋ ከተማ ውስጥ ዋጋቸው 76 ሺህ 500 ብር የሚገመቱ የመኪና ጎማዎችና የተለያዩ መድሃኒቶች በግለሰቦች ቤት ውስጥ በፌዴራል ፖሊስ፣ ጉሙሩክ ሠራተኞች እና ህብረተሰቡ ባደረገው ትብብር በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከዚህ ባለፈም በህገ ወጥ መንገድ ከመተማ ወደ መሀል ሀገር ሊገቡ የነበሩ ግምታዊ ዋጋቸው 167 ሺህ 760 ብር የሆኑ 1 ሺህ 997 የብሬን ጥይቶችና 100 የክላሽ ጥይቶች በሠራባ ኬላ ላይ በጉምሩክ ሰራተኞች በቁጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹን ሲያንቀሳቅሱ የነበሩ ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዱዓ እና ምህላ እየተደርገ ነው!

የሰዎች ህይዎት ላይ እየደረሰ ያለው በደል #እንዲቆም ምህላ እና ዱዓ እየተደረገ መሆኑን የሀይማኖት አባቶች አስታወቁ። በምዕራብ እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች በተፈጠረው #ግጭት ምክንያት በሰዎች ህይዎት እየደረሰ ያለው ጉዳት #ምህረት እንዲያገኝ ነው #ምህላ እና #ዱዓ እየተደረገ የሚገኘው። በሁለቱ ዞኖች እየተስተዋለ ያለውን የሰዎች #ሞት#መፈናቀል እና #መሰደድ በጎንደር ከተማ የሚገኙ የኦርቶዶክስ እና የእስልምና ሀይማኖት አባቶች አውግዘዋል።

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የሜጀር ጀኔራል ክንፈ ዳኛው ወንድም አቶ #ኢሳያስ_ዳኛው በ50 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲወጡ ተወስኖላቸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሀገር መከላከያ ሰራዊት ቀን!

7ኛው የኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሰራዊት በዓልን አስመልክቶ በሆመቾ አሚዩኔሽን የሚገኙ የአምስተኛ ሬጅመንት አባላት በምእራብ ሸዋ ዞን ጉደር ከተማ #አካል_ጉዳትኞችን በመደገፍ አክብረዋል፡፡

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ ትላንት በጠ/ሚ ጽ/ቤት ያካሄደውን ሰብሰባ ተከትሎ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የሰራዊቱን ስም #በማጠልሽተ የሚገኝ ምንም አይነት ቁምነገር የለም!"
.
.
መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ዩኒፎርም የለበሱና መለዮ አድርጎ በህዝብ መገልገያ ስፍራዎች ለሚገኙ ወታደሮች ከሁሉም ተገልጋይ በፊት ቅድሚያ በመስጠት፤ ለሞያውና #ለወታደሮቹ ያለንን #ክብር ማሳየት እንደሚኖርበት ጠቅላይ ሚስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ አሳሰቡ፡፡

ሚድያውን ጨምሮ አጠቃላይ የኪነ-ጥበብ ማህበረሰቡ መከላከያ ሰራዊቱ በሚፈለገው ደረጃ እንዲቀረፅና በህዝብ ዘንድ ያለው እምነት እንዲያድግ የማድረግ ሀላፊነት እንዳለውም ገልፀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በ7ኛው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ቀን በአል ላይ ባደረጉ ንግግር የኪነጥበብ ባለሞያዎች በሚሰሯቸው የኪነጥበብ ስራዎች የአገር መከላከያ ሰራዊትን በተመለከተ በጥንቃቄ ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

የሰራዊቱን ስም #በማጠልሸት የሚገኝም ምንም አይነት ቁምነገር እንደሌለም ጠቅላይ ሚንስትሩ አንስተዋል፡፡

#ሆሊውድ አገርን በውትድርና ማገልገል ትልቅ ሞያ እንደሆነ በማሳየት በኩል #ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ሲሆን አሜሪካ በተሸነፈችባቸው አውደ ውጊያወችም ጭምር ወታደሮቿ የፈፀሙትን ገድል በማሳየት የወታደሮቻቸውን ጀግንነትና አገልጋይነት ለማጉላት ይሰራሉ፡፡

በአንፃሩ በአገራችን በአብዛኞቹ ፊልሞቻችን፣ ቀልዶቻችንና ፅሁፎቻችን የሚሳለው የወታደሮች እና የጦር አመራሮች ገፀባህሪ ቀረፃ #ጥንቃቄ_የጎደለው እንደሆነ መታዘብ እንደሚቻል ጠቅላይ ሚንስትሩ ጠቅሰዋል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሩ ለሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች መከላከያ ሰራዊት ነገ ህዝብ የመረጠው ፓርቲን ተቀብሎ የሚያስቀጥለው ሰራዊት በመሆኑ ከጅምላ ፍረጃ እና ሂስ ሊታቀቡ እንደሚገባ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ምንጭ፦ ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia