ጭላሎ ተራራ በእሳት እንዲወድም ያደረገው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ‼️
የጭላሎ ተራራ ደን በእሳት እንዲወድም ያደረገው ግለሰብ #በፅኑ_እስራት ተቀጣ፡፡ ተከሳሹ የአርሲ ተራራ የጭላሎ ፓርክ ደን ለጊዜው ካልተያዙ ሁለት ግለሰቦች ጋር በመሆን ጥር 23 ቀን 2011 ዓ.ም 11 ሰዓት ላይ በእሳት እንዲያያዝ ማድረጋቸውን አቃቤ ህግ በክሱ ጠቅሷል።
ሁለቱ ተጠርጣሪዎች ለጊዜው ከአካባቢው ሲሰወሩ ተከሳሹ በአካባቢው ነዋሪዎች እጅ ከፍንጅ መያዙ ነው የተገለጸው።
ለሶስት ቀናት የዘለቀውን የእሳት ቃጠሎ የአካባቢው ነዋሪዎች ለማጥፋት ርብርብ ያደረጉ መሆኑ በክሱ የገለፀው አቃቤ ህግ እሳቱን ለማጥፋት የሰው ኃይልን ጨምሮ ከ210 ሺ ብር በላይ ወጪ እንዲወጣም ተከሳሹ ምክንያት ሆኗል ብሏል።
ተከሳሹና ግብረ አበሮቹ በጭላሎ ተራራ በለኮሱት እሳት ከ800 ሄክታር በላይ ደን መውደሙን በመግለፅ አቃቤ ህግ በጢዮ ወረዳ ፍርድ ቤት ክስ መመስረቱም ነው የተገለጸው።
በዚህም ተከሳሹ የወንጀል ድርጊቱ መፈፀሙን ቢያምንም ለአካባቢው እንግዳ መሆኑና ከብቶችን ጅብ በልቷል በሚል ሊያቃጥሉ የሄዱ ሁለት ሰዎችን ተከትሎ ከቤት መውጣቱን ለፍርድ ቤት ገልጿል።
የግራና ቀኙ ክርክር ያደመጠው የጢዮ ወረዳ ፍርድ ቤትም ተከሳሹ አቃቤ ህግ ያቀረበበትን ማስረጃ ማስተባበል ባለመቻሉ በ7 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።
እጃቸው ያልተያዙ ሁለት ተከሳሾችን ህዝብ አሳልፎ እንዲሰጥና ፖሊስም ለህግ እንዲያቀርብ ፍርድ ቤቱ ማዘዙም ታውቋል፡፡
ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia