ኤል ቻፖ ጉዝማን‼️
#ሜክሲካዊው የዕፅ ነጋዴ #ዮአኪን ''ኤል ቻፖ'' ጉዝማን በኒው ዮርክ ፌደራል ፍርድ ቤት በቀረቡበት 10 ክሶች በሙሉ ጥፋተኛ ተባለ።
የ61 ዓመቱ ''ኤል ቻፖ'' በሚል ቅጽል ስሙ የሚታወቀው ዮአኪን ጉዝማን ኮኬይን እና ሄሮይን በማስራጨት፣ በህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ባለቤትነት እና በህገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ክሶች ቀርበውበታል።
የፍርድ ቤቱን ውሳኔ የሚጠባበቀው ኤል ቻፖ የተቀረውን እድሜውን በእስር ሊያሳልፍ እንደሚችል ተገምቷል።
ኤል ቻፖ ከሜክሲኮ ወደ አሜሪካ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት ከፍተኛ ጥበቃ ከሚደረግላቸው ሁለት የሜክሲኮ እስር ቤቶች ማምለጥ ችሎ ነበር።
በድጋሚ ታህሣሥ 2008 በቁጥጥር ሥር የዋለው ኤል ቻፖ 2009 ላይ ለአሜሪካ ተላልፎ ተሰጥቷል። ኤል ቻፖ በብዛት ወደ አሜሪካ ለሚገቡ ዕፆች ተጠያቂ ሆኖዋል።
ሲቢኤስ ኒውስ እንደዘገበው ከሆነ ጥቁር ጃኬት እና ክራቫት አስሮ ከፍርድ ቤቱ የተገኘው ኤል ቻፖ የጥፋተኝነት ውሳኔ ሲተላለፍበት ምንም አይነት የስሜት መለዋወጥ አላሳየም።
ከፍርድ ቤቱ በፖሊስ ኃይል ታጅቦ ሲወጣ የፍርድ ሂደቱን ስትከታተል ለነበረችው የ29 ዓመቷ ባለቤቱ ኤማ ኮርኔል የቅንጡ ሰላምታ ሰጥቷታል።
የጉዝማን ጠበቆች ይግባኝ እንደሚጠይቁ ተናግረዋል።
.
.
#ኤል_ቻፖ ጉዝማን ማነው?
"ኤል ቻፖ'' ማለት ''አጭሩ'' እንደማለት ሲሆን በሰሜናዊ ሜክሲኮ ሲናሎአ የተሰኘ የዕፅ አዘዋዋሪ ቡድን መሪ ነበረ።
ኤል ቻፖ የሚመራው ቡድን ወደ አሜሪካ ለሚላከው ዕፅ ትልቁን ድርሻ ይዞ ነበር። እአአ 2009 ፎርብስ ኤል ቻፖ ጉዝማን የተጣራ 1ቢሊዮን ዶላር ያስመዘገበ ከበርቴ ነው በማለት የዓለማችን 701ኛው ሲል የሃብታሞች ዝርዝር ውስጥ አካቶታል።
የፍርድ ሂደቱ ተደብቆ የቆየውን የኤል ቻፖ ጉዝማን ህይወትን አደባባይ ያወጣ እንደሆነ በርካቶች ይስማማሉ። በፍርድ ሂደቱ ላይ የቀድሞ የቅርብ አጋሩ የነበሩ ሁሉ መስክረውበታል።
ከተሰጡበት ምስክርነቶች አንዳንዶቹ ሰዎችን በድንጋጤ ጭው ያደረጉ ነበሩ። ዕድሜያቸው ለጋ የሆኑና እስከ 13 ዓመት የሚደርሱ ሴቶችን ከመድፈሩ በፊት አደንዛዥ ዕፅ እንዲጠቀሙ ያደርግ ነበር ተብሏል።
ጉዝማን ለቀድሞው የሜክሲኮ ርዕሰ ብሔር ኤንሪክ ፔና ኒቶ በ2012 ስልጠን ከያዙ በኋላ እርሱ ላይ የሚደረገው ክትትል እንዲቆም በመጠየቅ አንድ መቶ ሚሊየን ዶላር ጉቦ መክፈሉም የተሰማው በዚያው ችሎት ላይ ነው። ርዕሰ ብሔሩ ግን ይህ ውንጀላ እውነትነት የለውም ሲሉ አስተባብለዋል።
ገድሎ ያቃጠላቸው የአደንዛዥ ዕፅ ከበርቴ ተፎካካሪዎች እንዳሉ ከዘመዶቹ መካከልም የገደላቸው እንዳሉ ተገምቷል።
ችሎቱ ኤል ቻፖ በ2015 በሜክሲኮ እጅግ ጥብቅ ከሆነው እስር ቤት እንዴት እንዳመለጠም በዝርዝር አድምጧል። ልጁ በእስር ቤቱ አቅራቢያ የሚገኝ ቤት እንደተከራየና ጂፒኤስ ያለው ሰዓት ወደ እስር ቤቱ በድብቅ ማስገባቱ ተመስክሯል።
በሚስቱ እና በቅምጦቹ ላይ ለመሰለል በስልኩ ላይ ሶፍትዌር ይጠቀም እንደነበርም ተመስክሮ፤ ኤፍ ቢ አይ የተለዋወጣቸውን የፅሑፍ እንዲያቀርብ ተደርጓል።
በአንድ የፅሁፍ መልዕክቱ ላይም ከነበረበት ቤት አሜሪካዊያንና ሜክሲኳዊያን ከከፈቱበት ድንገተኛ ዘመቻ እንዴት እንዳመለጠ የሚገልጽና ልብስ፣ ጫማ እና ጥቁር ሪዝ እንዲመጣለት የጠየቀበት መልዕክቱም ተነቧል።
ጉዝማን በአሜሪካ የፍትህ አደባባይ ለፍርድ ከቀረቡ የሜክሲኮ የአደንዛዥ ዕፅ ከበርቴዎች መካከል ትልቁ ነው።
ምንጭ፦ BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia